በምድረቀደምቷ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ከዋክብት ተገኝተዋል! ከስፖርት፣ ከመዝናኛው፣ ከፋሽን ወዘተ ኢንዱስትሪ የተሰባሰቡት ከዋክብቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስካይላይት ሆቴል ማራኪ የራት እና የዕውቅና ምሽት ነበራቸው። ከዋክብቱ በሀገራችን ያደረጉት ቆይታ በአፍሪካውያን ዘንድ የባህል ልውውጥ እንዲጎለብት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንዱ ማሳያ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአህጉሪቱ የዘረጋው ሰፊ የጉዞ መረብ አፍሪካውያን በባህል፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ግንኙነት ያላቸውን ሀብት እንዲጋሩ እያስቻለ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አፍሪካ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አፍሪካ
በአፍሪካ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ፖላንድ ሪፐብሊክ ርዕሰ መዲና ዋርሶ አዲስ በረራ ጀመረ። አዲሱ በረራ በሳምንት አራት ቀናት የሚደረግ ሲሆን በአፍሪካ እና በፖላንድ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሻግር ይሆናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቻይና ሻንግሀይ በተካሄደ ፕሮግራም የዕቃ ጭነት በረራ በሚያደርግባቸው የቻይና ከተሞች ለሚገኙ ኤርፖርቶችና የተለየዩ የስራ አጋሮቹ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ሁለንተናዊ ዕድገት እና ስኬት ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ ምስጋና እና የዕውቅና ሽልማት አበረከተ።በዕውቅና አሰጣጥ ስነስርዓቱ ላይ በቤልጂየም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ በረራ መዳረሻ የሆነው ሊዬዥ ኤርፖርት ልዩ ዕውቅና ተበርክቶለታል።
በአውሮፓ 24ኛ መዳረሻችን በሆነችው የፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው ስንደርስ በዋርሶው ቾፒን ኤርፖርት (Warsaw Chopin Airport) ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎልናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ፈገግታ በተሞላ እንክብካቤ ፍፁም ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ መስተንግዷችን እየተዝናኑ ዓለምን ከእኛ ጋር ይጎብኙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ያገባደድነው የሰኔ ወር በርካታ ስኬቶች ያስመዘገብንበት ሆኗል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ወር አራት አዲስ በረራዎችን የጀመረ ሲሆን እየበረረ በሚገኝባቸው መዳረሻዎቹ ላይ ስድስት ተጨማሪ የበረራ ምልልሶችንም አክሏል። ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ የሰኔ ወር አየር መንገዳችን የ APEX እና Skytrax ሽልማቶችን በመቀዳጀት አህጉራዊ መሪነቱን ብሎም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ስኬታማጉዞ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ወር አራት አዲስ በረራዎችን የጀመረ ሲሆን እየበረረ በሚገኝባቸው መዳረሻዎቹ ላይ ስድስት ተጨማሪ የበረራ ምልልሶችንም አክሏል። ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ የሰኔ ወር አየር መንገዳችን የ APEX እና Skytrax ሽልማቶችን በመቀዳጀት አህጉራዊ መሪነቱን ብሎም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ስኬታማጉዞ