Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.8K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በአውሮፓ 24ኛ መዳረሻችን በሆነችው የፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው ስንደርስ በዋርሶው ቾፒን ኤርፖርት (Warsaw Chopin Airport) ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎልናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
47👍24👏1
ፈገግታ በተሞላ እንክብካቤ ፍፁም ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ መስተንግዷችን እየተዝናኑ ዓለምን ከእኛ ጋር ይጎብኙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
65👍18🥰11👏3
ያገባደድነው የሰኔ ወር በርካታ ስኬቶች ያስመዘገብንበት ሆኗል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ወር አራት አዲስ በረራዎችን የጀመረ ሲሆን እየበረረ በሚገኝባቸው መዳረሻዎቹ ላይ ስድስት ተጨማሪ የበረራ ምልልሶችንም አክሏል። ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ የሰኔ ወር አየር መንገዳችን የ APEX እና Skytrax ሽልማቶችን በመቀዳጀት አህጉራዊ መሪነቱን ብሎም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ስኬታማጉዞ
👍5413👏11
በህንድ አራተኛ መዳረሻ ከተማችን ወደሆነችው ቸናይ በረራ ማድረግ የጀመርንበትን ሁለተኛ ዓመት በደመቀ ሁኔታ አክብረናል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህንድን ዋና ከተማ ኒው ዴልሂን ጨምሮ፣ ሙምባይ እና ባንግሎር ከተሞችን ከአፍሪካ እና ከመላው ዓለም ጋር ያገናኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ቸናይ
44👍12👏7🎉3
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፖላንድ ዋርሶ የመጀመሪያ በረራ በግሩም የእራት ድግስ በዋርሶ ደምቆ አምሽቷል። በምሽቱ ለበረራው መሳካት የራሳቸውን አሻራ ላኖሩ አካላት ዕውቅና እና ምስጋና ተበርክቷል።
አሁን ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ጋር ደማቋን ዋርሶን ለመጎብኘት ሁሉም ተመቻችቶልዎታል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍5920👏11😍9