በአፍሪካ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ፖላንድ ሪፐብሊክ ርዕሰ መዲና ዋርሶ አዲስ በረራ ጀመረ። አዲሱ በረራ በሳምንት አራት ቀናት የሚደረግ ሲሆን በአፍሪካ እና በፖላንድ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሻግር ይሆናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቻይና ሻንግሀይ በተካሄደ ፕሮግራም የዕቃ ጭነት በረራ በሚያደርግባቸው የቻይና ከተሞች ለሚገኙ ኤርፖርቶችና የተለየዩ የስራ አጋሮቹ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ሁለንተናዊ ዕድገት እና ስኬት ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ ምስጋና እና የዕውቅና ሽልማት አበረከተ።በዕውቅና አሰጣጥ ስነስርዓቱ ላይ በቤልጂየም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ በረራ መዳረሻ የሆነው ሊዬዥ ኤርፖርት ልዩ ዕውቅና ተበርክቶለታል።
በአውሮፓ 24ኛ መዳረሻችን በሆነችው የፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው ስንደርስ በዋርሶው ቾፒን ኤርፖርት (Warsaw Chopin Airport) ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎልናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ፈገግታ በተሞላ እንክብካቤ ፍፁም ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ መስተንግዷችን እየተዝናኑ ዓለምን ከእኛ ጋር ይጎብኙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ያገባደድነው የሰኔ ወር በርካታ ስኬቶች ያስመዘገብንበት ሆኗል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ወር አራት አዲስ በረራዎችን የጀመረ ሲሆን እየበረረ በሚገኝባቸው መዳረሻዎቹ ላይ ስድስት ተጨማሪ የበረራ ምልልሶችንም አክሏል። ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ የሰኔ ወር አየር መንገዳችን የ APEX እና Skytrax ሽልማቶችን በመቀዳጀት አህጉራዊ መሪነቱን ብሎም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ስኬታማጉዞ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ወር አራት አዲስ በረራዎችን የጀመረ ሲሆን እየበረረ በሚገኝባቸው መዳረሻዎቹ ላይ ስድስት ተጨማሪ የበረራ ምልልሶችንም አክሏል። ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ የሰኔ ወር አየር መንገዳችን የ APEX እና Skytrax ሽልማቶችን በመቀዳጀት አህጉራዊ መሪነቱን ብሎም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ስኬታማጉዞ
በህንድ አራተኛ መዳረሻ ከተማችን ወደሆነችው ቸናይ በረራ ማድረግ የጀመርንበትን ሁለተኛ ዓመት በደመቀ ሁኔታ አክብረናል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህንድን ዋና ከተማ ኒው ዴልሂን ጨምሮ፣ ሙምባይ እና ባንግሎር ከተሞችን ከአፍሪካ እና ከመላው ዓለም ጋር ያገናኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ቸናይ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ቸናይ