Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.75K photos
141 videos
2 files
411 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ1445ኛውን የሐጅ ጉዞ በስኬት ለማካሄድ የሚያስችለውን ልዩ ዝግጅት ማጠናቀቁን ለመግለጽ ይወዳል።
ይህ ልዩ ዝግጅት ለተከታታይ ዓመታት የተደረገ ሲሆን በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ፡- ጂዳ፣ መዲና፣ ሪያድ እና ደማም ከተሞች በሳምንት በጠቅላላው 35 የመንገደኛ እና ስድስት ተጨማሪ የጭነት በረራ የሚያደርግ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ደማቅ ፈገግታ በተላበሰው ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን አይረሴ የበረራ ትዝታን ይሰንቁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቡና ላኪዎችን ለማበረታታት እና የሀገራችንን ቡና በዓለም ለማስተዋወቅ የሚጫወተውን ሚና በማጠናከር ወደ ኤዥያ እና መካከለኛው ምስራቅ በሚልኩት የቡና ምርት ላይ በኪሎ እስከ 1.50 ዶላር ድረስ ቅናሽ ማድረጉን በደስታ ይገልጻል።
ተጨማሪ መረጃ በድረ ገፃችን CargoSales@ethiopianairlines.com ያግኙ። #የኢትዮጵያአየርመንገድካርጎናሎጂስቲክስአገልግሎት
ወደ ውቧ የቦትስዋና ከተማ ሞን መንፈስዎን እንዲያድሱ ልዩ የሽርሽር ጥቅል አቅርበንልዎታል፤ 5 ልዩ ምሽቶችን እና 6ቀናትን በ1800 ዶላር ብቻ። እንዳያመልጥዎ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በሴራሊዮኗ ፍሪታዎን በነጻነት መዝናናት ይሻሉ? እንግዳውስ ማራኪ የ5ምሽቶች እና የ6 ቀናት ልዩ የጉዞ ጥቅል በ1272 ዶላር ብቻ አዘጋጅተን የእርስዎን መምጣት ብቻ እንጠባበቃለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን Monametsi Sokwe ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሳሰቢያ
ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የዕሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።
እሳቱ የተፈጠረው ከአውሮፕላን ማረፊያው አጥር ውጭ ባሉ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንደነበረና አሁን ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተረድተናል።
በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ምንም ዓይነት መስተጓጎል እንዳልነበረ ለመግለጽ እንወዳለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 720 ቢ አውሮፕላን ለሶስተኛ ጊዜ ሲረክብ፣ በዋሽንግተን ሬንተን. #የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ! ምቹ እና አስደሳች የበረራ ጊዜ ያሳልፉ! ትኬትዎን በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን ፣ በድረ ገፃችን አሊያም በትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችን ይግዙ።
https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
https://www.ethiopianairlines.com/et
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጲያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ለዲግሪ ፕሮግራም ያመለከታችሁ እና በኦፕን ሃውስ ፕሮግራም ለተሳተፋችሁ አመልካቾች
የመግቢያ ፈተና ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል።
• የፈተና ዓይነት፡ የትምህርት ክፍሉን የተመለከተ
• የፈተና ጊዜ፡ ከጠዋቱ 03፡00 ሰዓት ይጀምራል
• የፈተና ቦታ፡ በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ (ከዚህ መልዕክት ጋር የተለጠፈውን ምስል ልብ ይበሉ)
ለፈተና በምትቀርቡበት ጊዜ መታወቂያ (የትምህርት ቤት፣ የቀበሌ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ወይንም ፓስፖርት) ማምጣት ይኖርባችኋል።

ማሳሰቢያ፡
1. እባክዎን በኢ-ሜልዎን የላክንልዎት መልዕክት ይመልከቱ።
2. ለፈተና መግቢያ የምዝገባ ፎርም: https://forms.gle/VmRtMuwWmN7oW7XB8
3. እባክዎትን ከፈተና ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ቀድመው ይድረሱ።
4. የራስዎን የስሌት መሳሪያ (ካልኩሌተር) ያምጡ።

የኢትዮጲያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ
ምቾትዎን ጠብቀን ልናስተናግድዎ ሁሌም ዝግጁ ነን። መልካም ቀን ይሁንልዎ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር እንኳን በደህና መጡ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎት በአውሮፓዊቷ ቤልጂየም የሌዥ ከተማ ቀዳሚ ከሆኑ የጭነት አየር መንገዶች ተርታ መሰለፉን አስመስክሯል።
አየር መንገዱ እ.ኤ.አ. በ2023 ዓ.ም. ከ160 ሺህ ቶን በላይ ጭነት ከሌዥ ከተማ ወደ አፍሪካ፣ ኤዥያ፣ አውሮፓ መካከለኛው ምስራቅ እና ወደ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ሀገራት በማመላለስ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴው ውስጥ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያአየርመንገድጭነትእናሎጂስቲክስአገልግሎት
ይህ በውጭ ሀገራት አየር መንገዳችን በ1950ዎቹ ከነበሩት ቢሮዎች አንዱ ነው። እባክዎ የት ሀገር የሚገኘው ቢሯችን እንደነበረ ይገምቱ።
ትክክለኛውን መልስ በአስተያየት መስጫ ሳጥኑ ውስጥ እናኖራለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ