Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.76K photos
141 videos
2 files
412 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሴራሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታውን አዲስ በረራ ዛሬ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም በደማቅ ስነ-ስርዓት አስጀምሯል።
በሳምንት ሦሥት ቀናት የሚደረገው በረራ በዘመናዊው የቦዪንግ B787 አውሮፕላን የሚከናወን ይሆናል። ይህንን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ትኬትዎን ከሞባይል መተግበሪያችን፣ ከድረገጻችን አልያም በአቅራቢያዎ ካሉ የሽያጭ ቢሮዎቻችን እና የጉዞ ወኪልዎ በመግዛት በምቾት ማራኪዋን ከተማ ለመጎብኘት ይዘጋጁ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ክብር ጉዞኣችንን በሞቀ መስተንግዶ እና እንክብካቤ ለሚያጅቡ የበረራ መስተንግዶ ባለሙያዎቻችን። መልካም ዓለም-አቀፍ የበረራ መስተንግዶ ባለሞያዎች ቀን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስደሳች እና የማይረሳ ጉዞ ከእኛ ጋር ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምቾትዎን ጠብቀን ልናስተናግድዎ ሁሌም ዝግጁ ነን። ከእኛ ጋር ቀጣይ መዳረሻዎ የት ነው?
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሳሰቢያ
የአዲስ አበባ ፖሊስ በከተማዋ እየተከናወነ ባለው የመንገድ ኮሪደር ልማት እና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ወደ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስዱ አንዳንድ መንገዶች በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል።
በመሆኑም ክቡራን መንገደኞቻችን ለበረራ በምትመጡበት ወቅት ይህን ታሳቢ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል መዘግየት ራሳችሁን እንድትጠብቁ እናሳስባለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አላያንስ አባል
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዓለምን በአንድ ቋንቋ የሚያግባባው እግር ኳስ ከነገሰበት የአውሮፓ ክለቦች ሻምፒዮና መንደር ተገኝተናል። ትልቁን ዋንጫ ለ15ኛ ጊዜ በማሸነፍ ድልን የተጎናጸፈው የሪያል ማድሪድ ክለብ ደጋፊዎች ምርጫ በመሆን ደጋፊዎቹን ከማድሪድ ወደ እግር ኳሱ ድግስ እንግሊዝ ምድር በማጓጓዝ የዚህ ታሪክ አካል በመሆናችን ደስ ይለናል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ እና በዓለም እየሰጠ ከሚገኘው መደበኛ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በተጨማሪ የቻርተር በረራዎችን በመስጠት ተመራጭ አየር መንገድ መሆኑን በማስመስከር ላይ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #UCLFinal #championsleague #CHAMP15NS
በዚህ ልብ በሚገዛ ፈገግታ ታጅበዉ ወደየት መጓዝ ይሻሉ?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና በረራ በማድረግ ከአፍሪካ የመጀመርያው ከአለም አየር መንገዶች ደግሞ አራተኛው ነበረ ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ቻይና የተጓዘው መቼ እንደነበር ያውቃሉ?
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲን ተቀላቅለው ህልምዎን ያሳኩ!
ለበለጠ መረጃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲን የፌስቡክ ገፅ ይመልከቱ።
https://www.facebook.com/EthiopianAviation
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያአየርመንገድአቪዬሽንዩኒቨርሲቲ
የአክብሮት ሰላምታችን ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል በያላችሁበት ይድረስ። መልካም ቀን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊውን የሰራተኞች ቀን በደማቅ ሁኔታ አከበረ። በስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ተካልኝ ተርፋሳ፣ የባለድርሻ አካላት ተወካዮች፣ ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን የላቀ የስራ አፈፃፀም ያስመዘገቡ የስራ ክፍሎች እና ሰራተኞች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ