Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
አስደሳች ዜና በግል ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለሚፈልጉ በሙሉ!

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ህልምዎን የሚያሳኩበትን ሁነኛ ዕድል ይዞ ብቅ ብሏል! ዩኒቨርሲቲው ለአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የ10% ቅናሽ በማድረግ ስልጠናውን ለመስጠት መዘጋጀቱን ሲያስተዋወቅ በደስታ ነው! የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ በግል ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪ ለመሆን ለሚፈልጉ እና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈሮች የሚያሟሉ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ይፈልጋል።

የትምህርት ደረጃ፡ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የወሰዱ፣ እንዲሁም በሂሳብ፣እንግሊዘኛ እና ፊዚክስ ዉጤት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገቡ
ዕድሜ: 18 እና ከዚያ በላይ
እንግሊዘኛ፡ ደረጃ 4
ቁመት: 1ሜ 62 ሴ.ሜ እና ከዚያ በላይ
የጤና ሁኔታ፡ ደረጃ 1 የጤና ሰርተፊኬት
የስልጠና ርዝማኔ፡ 1 አመት ከ 3 ወር
ይፍጠኑ! ይህ የማስታወቂያ ቅናሽ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው።
የምዝገባ ሂደቱን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ ከታች በተቀመጡት አድራሻዎቻችን ያነጋግሩን።
📧 ኢሜል አድራሻ : etauinfo@ethiopianairlines.com
eaainfo@ethiopianairlines.com
📞 ስልክ ቁጥር: +251-115174600/8598
🌐 በድህረ ገጻችን https://ethiopianaviationuniversity.azurewebsites.net/admission/applyonline ያመልክቱ::

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲን በመቀላቀል ህልምዎን እዉን ያድርጉ!
108👍86😍12🥰10🎉5
ለተከታታይ 5 ዓመታት በአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል የመንገደኞች አገልግሎት ዘርፍ የስካይትራክስ ሽልማት አሸናፊ ከሆነው አየር መንገዳችን ጋር በምቾት ይጓዙ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
85👍34👏8🥰7
ለኢስዋቲኒ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ሩሴል ምሚሶ ድላሚኒ እና የልዑክ ቡድን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መስሪያ ቤት የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል በማድረጋችን ኩራት ተሰምቶናል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩና የልዑክ ቡድኑ በአፍሪካ ግዙፍ ስለሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጠቃላይ የስራ አፍጻጸም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ በአቶ መስፍን ጣሰው እና በከፍተኛ አመራሮች ገለጻ ከተደረገላቸው በኋላ የአየር መንገዳችንን ዘመናዊ የስራ ክፍሎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በምልከታቸውም አየር መንገዳችን ለልህቅትና ፈጠራ እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነትም አድንቀዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍8919🥰9😍3🎉1
ምቾትዎን በሚያስጠብቁና ከከባቢ ጋር ተስማሚ በሆኑት ዘመናዊ አውሮፕላኖቻችን ወደየት እንድናጓጉዝዎ ይሻሉ? #የኢትዮጵያአየርመንገድ
😍6240👍22👏16🎉1
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ጉዞዎን በቅንጦት ያድርጉ::

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
103👍39🥰19👏6
በረራዎን አይረሴ ለማድረግ ከእኛ ዘንድ ሁሉም ተሰናድቷል። መልካም ሳምንት ይሁንልዎ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
72👍42🥰26👏10
ሳምንቱን በስኬት ከፍታ ላይ ሆነው ያሳልፉ! ከዘመናዊ አውሮፕላኖቻችን ውስጥ በየትኞቹ በርረዋል?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
86👍30🥰7👏3
በቀደሙት ግዜያት ስንከተለው የነበረው “አፍሪካውያንን እርስ በርስ ማስተሳሰር” የተሰኘው መርሀችን ዛሬም በድምቀት ቀጥሎ ለ37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በአፍሪካዋ መዲና አዲስ አበባ የተገኙ 20 የአፍሪካ አገራት መሪዎችን በግዙፉ እና ዘመናዊው የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በክብር ተቀብለን አስተናግደናል። የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በአፍሪካ ከሚገኙ ትላልቅ ሆቴሎች አንዱ ሲሆን በውስጡም 1024 ክፍሎች አሉት። የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል እንደ አህጉራችን አፍሪካ ሁሉ በህብረ ቀለማት አሸብርቆ እንግዶቹን በክብር አስተናግዶ ሸኝቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #ፓንአፍሪካዊ
👍8934🥰9
ያሳለፍነው የፍቅረኞች ቀን በመላው አለም ደምቆ እንዲከበር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ60 በላይ የበረራ አገልግሎቶች 250 ሚሊዮን (4500 ቶን) የሚጠጉ የአበባ ዘለላዎችን ከአዲስ አበባ፣ ናይሮቢ እና ቦጎታ ወደ መላው የዓለም ክፍል አጓጉዟል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍8524👏12🎉7😍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው 37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የመጡትን ከ50 በላይ የሀገራት መሪዎችንና ልዑካን አውሮፕላኖች ከተለያዩ “ቪአይፒ” እና “ቪቪአይፒ” እንግዶች አውሮፕላኖች ጭምር በአዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ከመደበኛ በረራዎቹ ጎን ለጎን በተቀላጠፈ እና ሙያዊ ብቃትን ባጣመረ መልኩ በስኬት አስተናግዷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍12135👏22🎉4🥰3