Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.6K subscribers
3.58K photos
134 videos
2 files
400 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ከአውሮፕላኖቻችን የበረራ ብቃትና አስተማማኝነት ጀርባ ያሉ ድንቅ የጥገና ባለሙያዎቻችን እጆች። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ በካሜራዎ ያስቀሩትን ምስል በመልዕክት መቀበያ ሳጥናችን በኩል ይላኩልን ፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
ምስል :- ቅድስት አማረ

#የመስኮትምልከታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሴት ሠራተኞች በ 1977 ዓ.ም. በልዩ የአቪዮኒክስ ሥልጠና ላይ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
እ.አ.አ በ1935 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ተገጣጥማ በረራ ያደረገችው ፀሐይ አውሮፕላን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ በደመቀ ሁኔታ አቀባበል አድረገንላታል።
ፀሐይ እንኳን ደሕና መጣሽ!!!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ልባዊ በሆነ አስደሳች መስተንግዶአችን ልንቀበልዎ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ብሔራዊ እንዲሁም አፍሪካዊ ኩራታችን በሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር እንኳን በደህና መጡ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አዲሱ ጎዴ ኡጋስ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በደማቅ ስነ-ስረዓት ተመረቀ፡፡
በ3500 ካሬ ስፋት ላይ ያረፈው ይህ አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ አራት ዲ ሃቪላንድ Q400 ወይም B737 አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ የውሃ ማጠራቀሚያ፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና ሌሎችም መሰረተ ልማቶችን አካቷል፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደ አቀዱት መዳረሻዎ በሞቀና ተሸላሚ ባደረገን ልዩ መስተንግዶ ልናደርስዎ ዝግጁ ነን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከአዲስ አበባ ወደ ብራዛቪል በሚደርጉት ጉዞ በካሜራቸው ቀርፀው ያስቀሩትን ይህ ውብ ዕይታ @Elirri አጋርተውናል፡፡ እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን ለዓለም እናጋራለን፡፡

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የመስኮትምልከታ
ለአንድ ግብይት ድርብ ሽልማት!!

ዉብ የቆዳ ዉጤቶችን ከኬርኤዥ ኢትዮጵያ ሲገዙ በእያንዳንዱ የ100 USD ግብይት እስከ 50% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽና ተጨማሪ 300 ማይሎችን ያግኙ! ግብይቶችን ሲፈፅሙ የሼባማይልስ አባልነት ቁጥርዎን ማስመዝገብዎን ያረጋግጡ::
ይህ ልዩ አጋጣሚ እስከ ሚያዝያ 22 2016 ዓ.ም ይቆያል፡፡
አሁኑኑ ይሸምቱ https://www.kerezhius.com/#xd_co_f=YzNiMGQyOTYtMzE2OS00MjU4LTlhYjQtZjMzYzMwNWNmNjgx~

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሼባማይልስ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ ሉዋንዳ በሳምንት አምስት ቀናት ሲያደርግ የነበረውን በረራ ከመጋቢት 22 ፣2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዕለታዊ በረራ እንደሚያሳድግ ሲገልፅ ደስታ ይሰማዋል። አየር መንገዳችን ላለፉት 38 ዓመታት ወደ ሉዋንዳ በረራ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ወደ ከተማዋ የምናደርገው በረራ ዕለታዊ መሆን እያደገ የመጣውን የአንጎላ ምጣኔ ሐብታዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንዲጎለብት ከማገዙም በላይ አየር መንገዳችን ከሚበርባቸው ከ135 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ጋር በየዕለቱ ለማስተሳሰር የጎላ አስተዋፅዖ ይኖረዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ