Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.55K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሲንጋፖር “ማሪና ቤይ ሳንድስ”በተዘጋጀው የ 2023 የኢስያ ቡና እና ሻይ ኤግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ በአለም ተመራጭ እና ልዩ የሆነውን የኢትዮጵያን ቡና አስተዋወቀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የአቪዬሽን የስልጠና ዘርፎች በትርፍ ሰዓታቸው የሚያስተምሩ ብቁ መምህራንን በጊዜያዊነት ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ፋላጎቱ እና ብቃቱ ያላችሁ ባለሙያዎች በዩኒቨርስቲው ድረገጽ እስከ መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ ይጋብዛል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ
(https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies).
መልካም የእረፍት ቀናት ይሁንልዎ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስደናቂ እና ውብ መልከዓምድር ፤ የብዝሀሕይወት እና የዓለም ቅርሶች መገኛ ኢትዮጵያ!
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ! ኢትዮጵያን ይጎብኙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ምድረቀደምት #ውብኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ለንደን ከተማ ከሚያደርገው 7 ሳምንታዊ በረራ በተጨማሪ ከሕዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ 3 ሳምንታዊ በረራዎችን ወደ ጋትዊክ ኤርፖርት በመጀመር ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን የበረራ አድማስ ማስፋቱን ሲገልፅ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አዲሱን ሳምንት ስንቀበል ወዳሰቡበት የጉዞ መዳረሻዎ ልናደርስዎ ዝግጁ ሆነን ነው፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ጅቡቲ ተጨማሪ ሶስት ሳምንታዊ የምሽት በረራዎችን በማከል ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ አስራ ሰባት ከፍ እንደሚያደርግ ለመግለፅ ይወዳል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በላቲቪያ ሪጋ የዓለም የጎዳና ሩጫ ላይ በመሳተፍ ድል ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ትናንት ምሽት ከፍራንክፈርት ሲነሳ ደማቅ አሸኛኘት አድርጎለታል።
አስደሳች የበረራ ግዜ በኢትዮጵያ አየር መንገድ!
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ በምስል ያስቀሩትን ማራኪ ዕይታ ያጋሩን፤ Yalemsew Birehanu ናቸው እናመሰግናለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በምናብ ወደኋላ ተጉዘን የቀደሙትን ስናስታውስ።

#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኬንያ ሞምባሳ የ50% የደርሶ መልስ ትኬት ልዩ ቅናሽ አድርጎ ይጠብቅዎታል። ትኬትዎን እስከ ጥቅምት 4 ፣2016 ዓ.ም ይግዙ ፤ በረራዎን እስከ ሕዳር 20፣ 2016 ዓ.ም ያድርጉ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዚሁ አጋጣሚ በረራ ያላችሁ ውድ ደንበኞቻችን ዛሬ ከሰዓት እና ነገ ጠዋት የመንገድ መጨናነቅ ሊኖር ስለሚችል የበረራ መስተጓጎል እንዳያጋጥማችሁ ከተለመደው ሰዓት ቀድማችሁ ወደ ኤርፖርት እንድታመሩ በትህትና እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደሚያስደስትዎ መዳረሻ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 18, 2016 ዓ .ም ጀምሮ ወደ ጋና አክራ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ያሳድጋል። በዚህም መሰረት በቀን ሁለት ጊዜ በመብረር ሳምንታዊ ምልልሱን ወደ 14 የሚያሳድግ ይሆናል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከ 130 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች! ምርጫዎን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያድርጉ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር እንኳን በደህና መጡ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የእንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰብ አባል ክብርት ሶፊ ሄሌን ራይስ ጆንስ ፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደርና በአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልእክተኛ ዳረን ዌልች እና የልዑካን ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸው ወቅት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የአየር መንገዱ አመራር አባላት ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጉብኝታቸው ማጠቃለያም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እንግሊዝ በረራ ማድረግ የጀመረበት 50ኛ ዓመት በኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርስቲ ተከብሯል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ