Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ በምስል ያስቀሩትን ማራኪ እይታ ያጋሩን Don Datta ናቸው እናመሰግናለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአርብ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ ሁለት ከፍ ማድረጉን እያስታወቀ በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ እንደሚጨምር ይገልፃል። በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ባሉበት ቦታ ሆነው ድረ ገፃችንን እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችንን ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን።
www.ethiopianairlines.com
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዳግላስ DC- 6B አውሮፕላን እ.ኤ.አ በ 1966 ዓ.ም በለንደን ጋትዊክ አየር ማረፊያ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሽሬ ከተማ በቀን አንድ በረራ ማድረግ የሚጀምር መሆኑን እያበሰረ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ ሶስት ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል፡፡ በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ ብዛት እንደሚጨምር ይገልፃል።
በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ባሉበት ቦታ ሆነው ድረ ገፃችንን እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችንን ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን።
www.ethiopianairlines.com
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአቪየሽን ዘርፍ ብቁ የሚያደርግዎትን የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ይቀላቀሉ።
https://corporate.ethiopianairlines.com/eaa
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ ን ቀዳሚ ምርጫዎ ያድርጉ። መልካም የስራ ሳምንት ተመኘን።
በፈገግታ ታጅበው ከእኛ ጋር ይጓዙ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ በምስል ያስቀሩትን ማራኪ እይታ ያጋሩን @Atuhairecarol10
ናቸው እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስል በመልዕክት መቀበያ ሳጥን በኩል ይላኩልን መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የተከበራችሁ መንገደኞቻችን፣
የገና እና ሌሎች በዓላትን ምክንያት በማድረግ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአሜሪካና ከሌሎች ሃገሮች በርከት ያለ ሻንጣ ይዘው ወደ ሃገር ቤት እየመጡ በመሆኑ በአውሮፕላን የቦታ እጥረት ምክንያት የተወሰኑ ሻንጣዎች በእለቱ ሳይጫኑ ከመነሻቸው ይቀራሉ።
ወደ ኋላ ከሚቀሩት ሻንጣዎች መሃል አብዛኛዎቹ በሚቀጥለው በረራ ስለሚመጡ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ የሻንጣ ማስረከቢያ አካባቢ መጠነኛ ጫና መፈጠሩን አስተውለናል፡፡ በዚህ ምክንያት መንገደኞቻችን ለገጠማቸው መጉላላት ከልብ ይቅርታ እየጠየቅን፣ ችግሩን ለመፍታት አየር መንገዳችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
ወደ ኋላ የቀሩ ሻንጣዎችን በተቻለ ፍጥነት ለመንገደኞቻችን የምናስረክብ መሆኑን እየገለፅን ለምታሳዩት ትዕግስት ከልብ እናመሰግናለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ላይ መስተንግዶ ባልደረቦቻችን በዘመን #ትውስታ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር እንኳን በደህና መጡ!
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ በምስል ያስቀሩትን ማራኪ እይታ ያጋሩን @metishewyilma
ናቸው እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስል በመልዕክት መቀበያ ሳጥን በኩል ይላኩልን መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከእኛ ጋር ይብረሩ ፣ የምቹ መስተንግዷችን ተጠቃሚ ይሁኑ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በመጪው የካቲት ወር በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በሚካሄደው “The STAT Times International Award for Excellence in Air Cargo” ውድድር ላይ በምርጥ የአመቱ የአፍሪካ ካርጎ ኤርፖርት፣ የአመቱ ፈጣን እድገት ያስመዘገበ ዓለም ዓቀፍ ካርጎ አገልግሎት ፣ የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ እና ዘላቂና አስተማማኝ የካርጎ አገልግሎት አመራር ዘርፎች ይወዳደራል። ከታች ባለው ሊንክ እስከ ጥር 7 2015 ዓ.ም በአራቱ ዘርፎች ድምፅዎን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ይስጡ።
https://www.stattimes.com/air-cargo-africa-2023/nominations
በቻይና መንግስት ተጥለው የነበሩ የኮቪድ-19 ክልከላዎች መነሳታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው የካቲት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ቻይና ወደሚገኙ መዳረሻዎቹ የሚያደርገውን ሳምንታዊ የበረራ ምልልስ ከፍ በማድረግ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሱትን ምስል በመልዕክት ሳጥን መቀበያችን በኩል ይላኩልን መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ