በአሜሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአለም ሁለተኛ ከአፍሪካ ደግሞ በቀዳሚነት ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ደማቅ አቀባበል አደረገ ። በአቀባበል ስርዐቱ ላይ አምባሳደር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፣አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ፣ እና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንትና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
❤61👍26🥰10
በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሁለተኛ ደረጃን ይዞ ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
❤36👍24🥰7👏7
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚያደርገውን የኤርባስ A350-1000 ትዕዛዝ ከኤርባስ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ጋር ተፈራረመ። አየር መንገዳችን ከዚህ በፊት 22 ኤርባስ A350-900 በማዘዝ 16ቱን ተረክቦ በማብረር ላይ ሲሆን ከተቀሩት የኤርባስ A350-900 አውሮፕላን ትዕዛዞች አራቱ ወደ ኤርባስ A350-1000 እንዲቀየሩ ስምምነት ተደርጓል። ይህ ስምምነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000ን አገልግሎት ላይ የሚያውል የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ ያደርገዋል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://bit.ly/3BiEJei
👍85👏15❤11🤩11