Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.76K photos
141 videos
2 files
412 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ-ንዋይ ያፈሰሰበትን የሀገር ውስጥ ተርሚናል በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ። ጥልቅ ዕድሳትና ማስፋፋት የተደረገለት ተርሚናሉ በቀን ከ200 በላይ የሀገር ውስጥ በረራዎችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትህትና በተላበሰ ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ሊያገለግልዎ ሁሌም ዝግጁ ነው።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምቾትዎን በሚያስጠብቁና ከከባቢ ጋር ተስማሚ በሆኑት ዘመናዊ አውሮፕላኖቻችን ወደየት እንድናጓጉዝዎ ይሻሉ?
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ1445ኛውን የሐጅ ጉዞ በስኬት ለማካሄድ የሚያስችለውን ልዩ ዝግጅት ማጠናቀቁን ለመግለጽ ይወዳል።
ይህ ልዩ ዝግጅት ለተከታታይ ዓመታት የተደረገ ሲሆን በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ፡- ጂዳ፣ መዲና፣ ሪያድ እና ደማም ከተሞች በሳምንት በጠቅላላው 35 የመንገደኛ እና ስድስት ተጨማሪ የጭነት በረራ የሚያደርግ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ደማቅ ፈገግታ በተላበሰው ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን አይረሴ የበረራ ትዝታን ይሰንቁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቡና ላኪዎችን ለማበረታታት እና የሀገራችንን ቡና በዓለም ለማስተዋወቅ የሚጫወተውን ሚና በማጠናከር ወደ ኤዥያ እና መካከለኛው ምስራቅ በሚልኩት የቡና ምርት ላይ በኪሎ እስከ 1.50 ዶላር ድረስ ቅናሽ ማድረጉን በደስታ ይገልጻል።
ተጨማሪ መረጃ በድረ ገፃችን CargoSales@ethiopianairlines.com ያግኙ። #የኢትዮጵያአየርመንገድካርጎናሎጂስቲክስአገልግሎት
ወደ ውቧ የቦትስዋና ከተማ ሞን መንፈስዎን እንዲያድሱ ልዩ የሽርሽር ጥቅል አቅርበንልዎታል፤ 5 ልዩ ምሽቶችን እና 6ቀናትን በ1800 ዶላር ብቻ። እንዳያመልጥዎ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በሴራሊዮኗ ፍሪታዎን በነጻነት መዝናናት ይሻሉ? እንግዳውስ ማራኪ የ5ምሽቶች እና የ6 ቀናት ልዩ የጉዞ ጥቅል በ1272 ዶላር ብቻ አዘጋጅተን የእርስዎን መምጣት ብቻ እንጠባበቃለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን Monametsi Sokwe ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሳሰቢያ
ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የዕሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።
እሳቱ የተፈጠረው ከአውሮፕላን ማረፊያው አጥር ውጭ ባሉ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንደነበረና አሁን ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተረድተናል።
በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ምንም ዓይነት መስተጓጎል እንዳልነበረ ለመግለጽ እንወዳለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 720 ቢ አውሮፕላን ለሶስተኛ ጊዜ ሲረክብ፣ በዋሽንግተን ሬንተን. #የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ