Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
83.2K subscribers
2.37K photos
91 videos
2 files
300 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ከመነሻዎ እስከ መድረሻውም ደረጃውን የጠበቀ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ልንሰጥዎ ዝግጁ ነን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በደማቅ ፈገግታ ተቀብለን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ሳምንትዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይጀምሩ። መልካም ሳምንት ይሁንልዎ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምስል: TonyRoberts
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር እንኳን በደህና መጡ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ዕለታዊ ማድረጉን ሲገልጽ ደስታ ይሰማዋል። ኣራት አስርት ዓመታትን ባስቆጠረው የአገልግሎት ዘመናችን እጅግ የተዋጣለት የአየር ትራንስፖርት አቅርቦት ስናበረክት ቆይተናል። ሳምንታዊ በረራችንን በየዕለቱ ማድረጋችን ክቡራን መንገደኞቻችን የተመቸ የጉዞ አማራጭ እንዲኖራቸው ያስችላል። ይምጡ ከእኛ ጋር ዓለምን ይቃኙ!
#የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን የጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ህንጻ እና ድጋፍ ሰጪ መሰረተ ልማቶች በዛሬው ዕለት በደማቅ ስነ-ስረዓት አስመረቀ። በ3500 ካሬ ስፋት ላይ ያረፈው ይህ ዘመናዊ መሰረተ ልማት ወደ ከተማዋ የሚጓዙ መንገደኞችን ምቾት ከፍ የሚያደርግና የአካባቢውን የቱሪስት ፍሰት በከፍተኛ መልኩ የሚያግዝ ነው። ውድ ክቡራን መንገደኞቻችን ወደየትኛውም የዓለም ጫፍ ጉዞዎን ማድረግ ሲያሻዎ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ትኬት ቢሮ በአካል በመሄድ አልያም የሞባይል መተግበሪያችንን ወይም ድረገጻችንን በመጠቀም ትኬትዎን ገዝተው የማይረሳ ጉዞ ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በምናብ ወደኋላ ተጉዘን የቀደሙትን ስናስታውስ።
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ያልተቆጠበ አገልግሎት!
ከልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ጋር አይረሴ ጉዞዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በላቀ አገልግሎታችን እየተደሰቱ ከእኛ ጋር በምቾት ይብረሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ በረራ ማድረግ የጀመረበትን 25ኛ ዓመት በሉሳካ በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ የሚያደርጋቸው በረራዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ አስምረውበታል።
አየር መንገዳችን አሁን ላይ ወደ ሉሳካ 11 እንዲሁም ወደንዶላ በሳምንት 5 ጊዜ በመብረር ላይ ሲገኝ፤ በቅርቡም ወደ ንዶላ የሚደረገውን በረራ ወደ 7 ከፍ በማድረግ ወደ ዛምቢያ የሚደረጉትን አጠቃላይ ሳምንታዊ በረራዎች 18 የሚያደርስ ይሆናል።