Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዴንማርክ ኮፐንሀገን ከተማ በሳምንት አምስት ግዜ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት በአንድ የመቀመጫ ውቅር ያለውን ቦይንግ 787-9 አውሮፕላን ተቀበለ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቪዬና በኩል ወደ ዴንማርክ ባደረገዉ የመጀመሪያዉ በረራ በኮፐንሀገን ኤርፖርት ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን Hassan Moussa ናቸው ፤ እናመሰግናለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በስተቀኝ፣ ካፒቴን ልዑል አባተ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል (Ethiopian MRO) ባልደረባ በነበሩበት ወቅት::
(“ካፒቴን ልዑል አባተ ሕይወቱ ፣ የአብራሪነትና የአውሮፕላን ጠለፋ ትዝታዎቹ” ገፅ- 48)
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ምልሰት
ለመላው አፍሪካውያን በሙሉ መልካም የአፍሪካ ቀን ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የአፍሪካቀን
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው “APEX” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “ ሽልማት አሸናፊ ሆነ። አየር መንገዳችን ሽልማቱን የተቀዳጀው በምርጥ የበረራ መስተንግዶ ዘርፍ ፣ በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ ዘርፍ፣ በምርጥ የበረራ ላይ ምግብ እና መጠጥ ዘርፍ፣ በምርጥ የበረራ ላይ ምቾት ዘርፍ እንዲሁም በምርጥ የበረራ ላይ የገመድ ዓልባ ኢንተርኔት “Wi-Fi”አገልግሎት ዘርፍ ነው። ልማቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ዛሬ አየርላንድ ደብሊን ከተማ በተካሔደ የሽልማት አሰጣጥ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ተቀብለዋል።