Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.7K subscribers
3.83K photos
144 videos
2 files
414 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በአፍሪካ ታላቁና የአህጉሪቱ የአቪየሽን መሪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑን ዛሬ ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም ዳግም ወደ አየር መለሰ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የአየር መንገዱ የማኔጅመንት አባላት፣ የቦይንግ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣አምባሳደሮች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ጋዜጠኞችና ደንበኞች በዚህ የመጀመሪያ በረራ ላይ ታድመዋል።
አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ አገልግሎት መመለስ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ “የበረራ ደህንነት የአየር መንገዳችን ተቀዳሚና ወሳኝ ጉዳይ ነው፤ እያንዳንዷ የምንሰራት ስራና የምንወስናት ውሳኔ በበረራ ደህንነት አብይ ጉዳይ የተቃኘ ነው። በዚህ መርህ ላይ በመመስረት ነው ዛሬ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላናችንን ወደ አገልግሎት የመለስነው።" ብለዋል።
የፌዴራል አቪዬሽን አድሚኒስትሬሽን /FAA/፣ የአውሮፓ ህብረት የአቪየሽን ደህንነት ኤጀንሲ /EASA/፣ ትራንስፖርት ካናዳ፣ የቻይና ሲቪል አቪየሽን አስተዳደር /CAAC/፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን /ECAA/ እንዲሁም ሌሎች የአቪየሽን ተቆጣጣሪ አካላት ለአውሮፕላኑ ምስክርነትና ማረጋገጫ የሰጡ ሲሆን፣ 36 የሚሆኑ የአለም አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደ አገልግሎት መልሰዋል። የማክስ አውሮፕላን ሞዴል ዳግም ወደበረራ ከተመለሰበት አንድ ዓመት ወዲህ በአጠቃላይ 349 ሺህ በረራዎችን ያደረገ ሲሆን፣ በዚህም ወደ 9መቶ ሺህ የሚደርስ የበረራ ሰአት አስመዝግቧል።
👍21
ትውስታ ከካፒቴን አዳሙ መድሀኔ ጋር። #ትውስታ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ አገልግሎት የተመለሰበት የመጀመሪያ በረራ በእሁድን በኢቢኤስ @EBStv #የኢትዮጵያአየርመንገድ https://www.youtube.com/watch?v=aC8MfFsTRZg
ሳምንትዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይጀምሩ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
📸 joaquinspotter
ከእኛ ጋር ያለዎትን ቆይታ ልዩ እና ምቹ ለማድረግ ሁሌም እንተጋለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፍቅረኞች ቀን (Valentiene’s Day) በሚውልበት በዚህ ወር የሙቀት መቆጣጠሪያ በተገጠመላቸው ዘመናዊ እቃ ጫኝ አውርፕላኖቹ የአበባ ምርቶችን ወደተለያዩ የአለም ሐገራት እያጓጓዘ ይገኛል። ባሳለፍነው አመት በተመሳሳይ ወር አየር መንገዳችን ወደ 95 ሚሊየን የሚጠጋ አበባ አጓጉዟል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 707 አውሮፕላን በ1968 እ.ኤ.አ. ከቀደምት ፎቶ ማህደራችን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አባል የሆነበት “ስታር አሊያንስ” የአየር መንገዶች ሕብረት በ 2022 የአየር ትራንስፖርት ሽልማት ላይ ለ 4ኛ ጊዜ የ “ምርጥ የአየር መንገዶች ሕብረት” ሽልማትን ተቀዳጅቷል። ስታር አሊያንስ 26 አየር መንገዶችን በአባልነት የያዘ ሲሆን አየር መንገዳችን ይህንን የአየር መንገዶች ሕብረት ከተቀላቀለ አስር አመታትን አስቆጥሯል ። ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ ። https://www.airtransportawards.aero/
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 86 በረራዎችን በማድረግ ከ110 ሚሊየን በላይ የአበባ ምርት ወደተለያዩ ሀገራት አጓጉዟል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚን ይቀላቀሉ ፣ በአቪዬሽን የሙያ ዘርፍ ብቁ ተወዳዳሪ ይሁኑ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለመረጃ እባክዎን ድረገጻችንን ይጎብኙ፤ http://www.ethiopianairlines.com/eaa
👍1
ቀጣይ በረራዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በማቀድ ሳምንቱን ይጀምሩ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምስል; tocalero
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቅጽዎን (Boarding Pass) ባሻዎት ጊዜ እና ቦታ በምቾት ማግኘት የሚችሉበትን ሁነኛ አማራጭ ሲያቀርብልዎ በታላቅ ደስታ ነው:: በእጅ ስልክዎ ወይም በድረ ገፃችን ቼክ ኢን ሲያደርጉ ጊዜዎን ቆጥበው ቀልጣፋ አገልግሎት ያገኛሉ። አገልግሎቱን እጅግ በቀላሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድን መተግበሪያ ከGoogle Play ወይም Apple Store ላይ በማውረድ ተጠቃሚ ይሁኑ:: ለበለጠ መረጃ በአቅራቢያዎ የሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮ ያነጋግሩ ወይም በስልክ ቁጥራችን +251116179900 ይደውሉ::
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://youtu.be/gBQYLYywzGg
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @ capt.tewodros ናቸው ፤ እናመሰግናለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
2👍2