የአፍሪካ ሬድዮ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሆኑት ፓትሪክ ኩዋርኮ የተመራ የአፍሪካ ሬድዮ ግሩፕ የሚዲያ ቡድን እና የቃና ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቪድ ወርቁ እንዲሁም የ”ኢንክሉሲቭ ብሮድካስት”ማኔጅመንት አባላት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኘት ጉብኝት ያካሄዱ ሲሆን ከኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ መሳይ ሽፈራው ጋር አየር መንገዱ ከሚዲያዎቹ ጋር አብሮ ሊሰራ በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
👍3❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“የሁላችንም ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰርቪስ ኢንደስትሪው እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል።”
ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
👍2
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @KileleshwaFarms ናቸው ፤ እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፤መልሰን እናጋራዎታለን።#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአለም አቀፉ አየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) የ CEIV ሰርተፍኬት የተሰጠው የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 400 ሚሊየን ዶዝ የሚጠጋ የኮቪድ 19 ክትባት ከ 35 በላይ ለሚሆኑ የአለም ሀገራት ማጓጓዙን ሲገልፅ ኩራት ይሰማዋል። አስተማማኝ እና ጥራት ያለው የካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚን ይቀላቀሉ፣ በአቪዬሽን የሙያ ዘርፍ ብቁ እና ውጤታማ ይሁኑ።
corporate.ethiopianairlines.com/eaa/training-schools
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
corporate.ethiopianairlines.com/eaa/training-schools
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግማሽ ዓመቱ 4.1ሚሊዮን ደንበኞችን አጓጓዘ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም በገንዘብ ሚኒስቴርና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በሂልተን ሆቴል በዛሬው ዕለት በተገመገመበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ ኢሳያስ ወልደ ማሪያም እንደገለፁት አየር መንገዱ ከመሰል ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ድርጅቶች አንጻር በተለያዩ መመዘኛዎች ሲታይ የላቀ ዕድገት አሳይቷል፤ ትርፋማነቱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ቀጥሏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ በአሁኑ ጊዜ በርካታ የአየር መንገዶች በአስቸጋሪ ወቅት ላይ ቢሆኑም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ባሳየው ትርፋማነት፣ በወጪ ቅነሳ ረገድ ውጤት ማስመዝገቡና በተለይ በዕቃ ማጓጓዝ አገልግሎት ያሳየው አመርቂ አፈፃፀም የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ በአሁኑ ጊዜ በርካታ የአየር መንገዶች በአስቸጋሪ ወቅት ላይ ቢሆኑም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ባሳየው ትርፋማነት፣ በወጪ ቅነሳ ረገድ ውጤት ማስመዝገቡና በተለይ በዕቃ ማጓጓዝ አገልግሎት ያሳየው አመርቂ አፈፃፀም የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።
👍1
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በማረፋቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ እና ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መፅናናትን እንመኛለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777-8 Freighter የተሰኘውን አዲስ የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላን ምርት ለመግዛት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ጋር ተፈራረመ።
ስምምነቱ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከመጣው የካርጎ ጭነት አገልግሎት ፍላጎት ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ሲሆን እያስመዘገበ የሚገኘውንም ዕድገት ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ስምምነቱን አስመልክተው “በአፍሪካ አቪየሽን መስክ ቀዳሚ አየር መንገድ እንደመሆናችን መጠን ይህንን አዲስ ፣ ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ የጭነት አውሮፕላን ከቦይንግ ካምፓኒ ለመግዛት የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረማችን ደስታ ይሰማናል” ያሉ ሲሆን “ይህ አዲሱ ቦይንግ777-8F የጭነት አውሮፕላን እያደገ የመጣውን የአየር መንገዱን የካርጎ ጭነት አገልግሎት በማስፋፋት አሁን ያሉትን 66 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ለማሳደግ በእጅጉ ይረዳዋል” ብለዋል።
ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-and-boeing-sign-memorandum-of-understanding-for-new-777-8-freighter