#Tigray
ዛሬ በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ምንድን ነው የተከሰተው ?
እንስት ዘውዱ ሃፍቱ ከሁለት ዓመት በፊት በግፍ ከተገደሉት ሴቶች አንድዋ ናት።
የሟችዋ ጉዳይ በፓሊስ ተጣርቶ መዝገቡ ወደ ፍርድ ደርሶ ለሁለት ዓመት ያህል ውሳኔ ሳያገኝ በይዋል ይደር ረጅም ጊዜ መውሰዱ የተበዳይዋ ቤተሰብና የፍትህ ፈላጊዎች ሁሉ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።
ይህ በእንዲህ አንዳለ የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰዓት በፊት የመጨረሻው ውሳኔ ለመስጠት ችሎት ይቀመጣል።
ፍርድ ቤቱ በግድያ ወንጀሉ በተጠረጠሩት ላይ የመጨረሻ ያለውን የጥፋተኝነት የቅጣት ውሳኔ ይሰጣል።
ይህንን ተከትሎ ችሎቱ በሚከናወንበት አዳራሽ የነበሩት ብዛት ያላቸው የተጠርጣሪ ወገኖች ጠረጴዛ በመደብደብና የተለያዩ ድምፆች በማሰማት ረብሻ ይጀምራሉ።
ከረብሻ በዘለለ ዳኞቹን " እናንተም እንደመስሳቹሃለን ፤ ቀናችሁን ጠብቁ " የሚሉ የስድብ ናዳና ዛቻ ያወርዳሉ።
በችሎት አዳራሹ በቂ የሆነ ስርዓት አስከባሪ ባለመኖሩና ዳኞቹ ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ እና አስፈሪ በመሆኑ ምክንያት ውሳኔውን ሳይቋጩ ለግንቦት 18/2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ስጥተዋል።
የችሎት መድፈር ተግባሩ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ሰፊ መነጋገሪ ሆኖዋል።
ጠበቃ ሚኪኤለ ፍስሃ የተባሉ የሟች ጠበቃ " በፍርሃት ስራዬን አላቋርጥም፤ የተበዳይን እንባ ለማበስ ነገም ዛሬም እሰራለሁ " ሲሉ በማህበራዊ ሚድያ የትሰስር ገጻቸው ላይ ሀሳባቸውን አስፍረዋል።
በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የህግ ልዕልና እንዲከበር አገልግሎት በሚሰጠው ፍርድ ቤትና ዳኞች ላይ የተፈፀመ ድፍረት በምሬትና በቁጣ ሲያወግዙት ተስተውለዋል።
የመቐለ ማእከላይ ፍ/ቤት በያዝነው ሳምንት ብቻ የእንስት ዘውዱን ጨምሮ 4 በግፍ የተበደሉ ሴቶችን ጉዳይ መመልከቱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከቦታው መረጃውን አድርሷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia