አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት፤ የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ እንዲተላለፍ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ውሳኔው የተላለፈው በዛሬው እለት በተካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ ነው፡፡

ይህ የተገለጸው ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 23/2017 ከተካሄደው 44ኛ መደበኛ ስብሰባ በኋላ ነው፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዚህ ስብሰባ ላይ በአራት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ወደ ፓርላማ ሲመራ፤ ሁለት ደንቦች በሥራላይ እንዲውሉ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ወደ ፓርላማ እንዲመሩ ከተደረጉት መካከል ሆኗል፡፡

ምክት ቤቱ ሕጉ የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ ለውጭ ዜጎች ህጋዊ አሠራር መዘርጋቱ “የውጭ ካፒታል በሀገሪቱ ሥራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታት፣ የቤት ልማት እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማነቃቃት፣ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና አቅርቦት ሚዛን ለማስጠበቅ እና ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል” ብሏል፡፡

በተመሳሳይ ዛሬው ስብሰባ ምክር ቤቱ የተወያየው በአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን መቋቋሚያ ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ ትኩረቱን በመሠረተ ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብት እና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ልማት ላይ በማድረግ ለግል አልሚዎችና ለመንግሥት አካላት የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመው ኮርፖሬሽኑ፤ ኢትዮጵያ በአባልነት መቀላቀሏ ለግሉ ዘርፍ ተጨማሪ የፋይናንስ ሀብት በማቅረብና የግል ዘርፉን የማይተካ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት ሚና በማሳደግ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠንና ድህነትን ለመቀነስ ጠቀሜታ ያለው እንደሆነም ገልጿል፡፡

በምክር ቤቱ ውይይት ተደርጎበታል የተባለው ሌላው ጉዳይ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት የዕቃዎች ቀረጥ ምጣኔ ቅነሳን ለማስፈፀም በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ስምምነቱ በአባል ሀገራት መካከል ንግድ እንዲስፋፋ፣ የገበያ ትስስሩ እንዲጠናከር፣ የእሴት ሠንሰለቱ እንዲጎለብት እና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማበረታታት የሚያስችል እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡ በአባል ሀገሮች መካከል የሚደረጉ ግብይቶች በታሪፍ ምክንያት ሳይደናቀፉ የእቃዎች ፍሰት የተሳለጠ እንዲሆን ከአባል አገራት በሚመጡ እቃዎች ላይ የጉምሩክ ታሪፍ ምጣኔ ለይቶ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን ውይይት ተደርጎበት፤ ምክር ቤቱ ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተፈፃሚ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ፤ ቀጥሎ የተወያየው በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለሚሰጡ አገልግሎቶች እና በኢ.ፌዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ለሚሰጡ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን በቀረቡ ሁለት ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው፡፡ ተቋማቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያወጡትን ወጪ በመሸፈን፣ ገቢያቸውን አሳድገው ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ የሚያስችል የደንበኞችን አቅም ባገናዘበ መልኩ የአገልግሎት ክፍያ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ፤ በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
#AleHig
Mikias Melak & Associates Law Office

🔴Attorney and Legal Consultant ጠበቃና የሕግ አማካሪ

Website & Social Media
Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

https://www.linkedin.com/in/mikias-melak-76499811a?utm_source=share&utm_campaign=share_via&utm_content=profile&utm_medium=android_app

📱Facebook:
https://www.facebook.com/share/1BXx3RSsLZ/

📱Telegram: ✉️ @MikiasMelak⭐️📱

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com

Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595

Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍6😁1