አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለኔ ጥብቅና አርት ነው። የምፅፋቸው ክርክሮች የህግ መሰረት፣ ትንተና እና ጥሩ አመክንዮ ያላቸው፣ ግልፅና ቀላል ሆነው ካገኘኋቸው ደስ ይለኛል። አንዳንዴ 'ታክል/ጠረባ መሳይ ጣል ሳደርግም እንደዚያው፣ በተለይ ቃል ክርክር ላይ። ባጭሩ ጥብቅና ያዝናናኛል።

የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ያስገርሙኛል እንጂ አያናድዱኝም። የትኛውንም ጉዳይ የግሌ አድርጌ/ፐርሰናሊ አልወስድም፣አልብሰለሰልም። ይልቅ የማተኩረው የቻልኩትን አድርጌያለሁ ወይስ አላደረግሁም የሚለው ላይ ነው። የቻልኩትን ካደረግሁ፣ ቀሪው የተከበረው ፍርድ ቤት ስራ ነው።

ግን ደግሞ የውሳኔዎች ጥራት ማሽቆልቆል ያሳስበኛል፣ ለኔ ሳይሆን፣ ደንበኞቼ በኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት ላይ ያላቸው ዕምነት ስለሚሸረሸር፣ ይህም ኢንቨስትመንት ሰለሚያሸሽ። ግን እሱንም ቢሆን፣ እኔ ላደርግ የምችለው ነገር ውስን ስለሆነ፣ እዚያ ላይ አተኩራለሁ። ቀሪው የመንግስት ኃላፊዎች ጉዳይ ነው፣ እነሱን ደግሞ ተክቼ ልሰራ አልችልም፣ ከማሳሰብ በቀር። ከሰሙ ዲየግ፣ ታልሰሙም ምን ይደረጋል፣ ያገሪቱ ያርባ ቀን ዕድል ነው።

ለምሳሌ የሰበር አጣሪ ችሎቶችን እንውሰድ። በቅርብ ጊዜ በተደጋጋሚ እንዳየሁት፣ ለምሳሌ እኔ የምቀርብበት 2ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት፣ ያለማጋነን በየቀኑ ከ35 እስከ 40 የሰበር አቤቱታዎችን ይሰማል፣ ፣ ብይንም በአንድ ወይም ሁለት ቀን ውስጥ ይሰጣል ላብዛኛው። ሲጀመር መዝገቦችን መርምሮ ብይን ለመስጠት በቂ ጊዜ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። በዚህ ጫና ውስጥ ሆኖ አንድ ዳኛ ውስብስብ የህግ ክርክሮች ያሉበትን መዝገብ በአግባቡ ለመመርመር የሚያስችል ጊዜ ያገኛል ወይ? በነርሱ ቦታ ሆኜ ባየው፣ ይህ በጣም ጫና ያለው፣ አታካች ስራ ነው። በቂ ረዳቶች አሏቸው ወይ? ተጨማሪ የሰበር አጣሪ ችሎቶች አያስፈልጉም ወይ? የሚለውን ጉዳይ የፍርድ ቤቱ ኃላፊዎች ቢያዩት ጥሩ ነው እላለሁ።

በተጨማሪም፣ በተለይ ለየት ያሉ እንደ ታክስ፣ አዕምሯዊ ንብረት፣ ሰብዓዊ መብት ያሉ ልዩ ዕውቀት የሚጠይቁ ውስብስብ ጉዳዮችን የሚያዩ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በየዘርፉ ተገቢው የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ እንዲኖራቸው (ለምሳሌ በነዚህ ዘርፎች የማስተርስ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ) ቢደረግ፣ በዘርፉ ለስነሕግ ዕድገትም ይጠቅማል፣ (ለምሳሌ የህጉን ምክንያት፣ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን እና እና የሌሎች አገሮች ጠቃሚ ልምድ ለማካተት)፣ ፍትሐዊ ውሳኔ ለመስጠትም ያገለግላል። ይህ ሲሆን የውጭ ባለሃብት በሃገሪቱ የፍትህ ስርዓት ላይ ያለው አመኔታም ይጨምራል።
ስለሆነም፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ በየዘርፉ የመደባቸው ዳኞች ያላቸው ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት ከተመደቡበት ዘርፍ ጋር አብሮ የሚሄድ ነወይ የሚለውን ቢገመግም ጥሩ ሊሆን ይችላል። በዘርፉ ልምድ ያላቸው ዳኞች ቢያንስ በሰብሳቢነት ቢሾሙ፣ ቀሪዎቹ ዳኞች ልምድ እየቀሰሙ እንዲሄዱ ለማድረግ ይረዳል እላለሁ። ይሔ አሳብ ጥሩ ከመሰላቸው አላፊዎቹ ቢያዩት፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አማካሪ ምክር ቤትም ውይይት ቢደረግበት ይጠቅም ይሆን?
እኔና ጥብቅና በሚል ወዳጄ Abebe Asamere ጥብቅና ያስጠላል ስለሚሉ ሰዎች የጻፈውን አነበብኩት ብለው የሰጡት አስተያየት ነው።
ከቁምላቸው ዳኘ ፌስቡክ ገጽ ተወሰደ #Kumlachew_Dagne
Thank you all*via #AleHig

Mikias Melak & Associates Law Office

🔴Attorney and Legal Consultant ጠበቃና የሕግ አማካሪ

Website & Social Media
Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

https://www.linkedin.com/in/mikias-melak-76499811a?utm_source=share&utm_campaign=share_via&utm_content=profile&utm_medium=android_app

📱Facebook:
https://www.facebook.com/share/1BXx3RSsLZ/

📱Telegram: ✉️ @MikiasMelak⭐️📱

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com

Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595

Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍385🔥1