አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ስለ ህግ ጉዳዮች መረጃ ከፈለጉ 👈
ስለ ህግ ማብራሪያ ከፈለጉ 👈
አዳዲስ ህጎችን፣ መመሪያ፣ ደንብ እና ልዩ ልዩ የህግ ውሳኔዎችን የሚያገኙት ከአለ ህግ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ይሁኑ።👈
ለሌሎች ሼር ያድርጉት፣ ያጋሩት ይማሩበታል ያተርፉበታል
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
26 ክሶችን ያልተረታው ዳኛ በ27ኛው  ራሱ ተከሰሰ 😳
         
በኬንያ ምንም አይነት የህግ ትምህርተ ሳይወስድ  በሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃ  ጠበቃ ሆኖ ሲሰራ የነበረ አንድ ግለሰብ በፖሊስ መያዙ ተዘግቧል።

ግለሰቡ ለ26 ክሶች ጠበቃ ሆኖ ቀርቦ ሁሉንም በአሸናፊነት ፋይል አዘግቷል።ነገር ግን የህግ ትምህርት  በዲፕሎማም ሆነ በዲግሪ ደረጃ አለመማሩን  የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑን ዘግበዋል። አሁን ላይ 27ኛው  ክስ  የራሱ ሆኖ ቀርቦለታል😳

Via: DW

Ephrem H. From woldia university school of law

ለሌሎች  ሼር ያድርጉት፣ ያጋሩት ይማሩበታል ያተርፉበታል
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
ችግርን_በሰነድ
አንድ የህግ ባለሙያ በባቡር እየተጓዘ ሳለ
አንድ በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ መጥታ ፊት ለፊቱ ከሚገኘው ወንበር ላይ ተቀመጠች።
በዚህም የህግ ባለሙያው ደስ አለው። ቀና ብሎ ሲመለከታት አይን ለአይን ተያዩ ከዛም ፈገግ አለች።
አሁን ደግሞ በይበልጥ ደስ አለው። ትንሽ ቆይታ አጠገቡ ሄዳ ተቀመጠች። በዚህን ጊዜ እጅግ በጣም ደስ አለው።
ትንሽ ቆየችና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ "ያለህን ገንዘብ; የATM ካርድህን ከነፓስ ዎርዱ እና የሞባይል ቀፎህን አሁኑኑ ካልሰጠኸኝ ስትጎነትለኝ እንደ ነበረና ፆታዊ ትንኮሳ እንደደረሰብኝ እዚህ ባቡር ውስጥ ላሉት ሁሉ በመንገር እጮኃለሁ።" አለችው።
የህግ ባለሙያው በቸልተኝነት ቀና ብሎ ተመለከታትና ከቦርሳው ውስጥ ወረቀትና እስክሪብቶ አውጥቶ እንዲህ ብሎ ፃፈላት "ይቅርታ መናገርና መስማት የተሳነኝ ነኝ። እባክሽን ማለት የፈለግሽውን ሁሉ እዚህ ወረቀት ላይ ፃፊልኝ።"
ልጅቷም ቀደም ብላ ስትነግረው የነበረውን ሁሉ ጽፋ ሰጠችው።
የህግ ባለሙያው ወረቀቱን ተቀብሏት በጥሩ ሁኔታ አጥፎ ኪሱ ከከተተው በኋላ ከተቀመጠበት ተነስቶ ጎርነን ባለ ድምጽ ምን ቢላት ጥሩ ነው "አሁን እንደፈለግሽ መጮህ ትቺያለሽ።"

የታሪኩ ምግባር: ሰነድን በአግባቡ መያዝ ምን ግዜም አስፈላጊ ነው።
ለሌሎች  ሼር ያድርጉት፣ ያጋሩት ይማሩበታል ያተርፉበታል

("ዮኒ እንደተረጎመው"]
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/
ማስታወቂያ
።።።።።።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በዕጩ ዓቃቤ ሕግነት አወዳድሮ ለመቅጠር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እሁድ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም እትም ማውጣት ይታወቃል።
በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከጥቅምት 5 ቀን ጀምሮ ባሉ 15 የስራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/
ስለዚህ በተዋወይ ወገኖች የሚደረጉ ውሎች፣ ስምምነቶችና ማረጋገጫዎች ለአጭበርባሪዎች የተጋለጡና ተገልጋዩን ለከፍተኛ ችግር ሊዳርጉ የሚችሉ ስለሆነ ማንኛውም ግለሰብ የሚፈልገውን ሰነድ በህግ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠና የተመዘገበ ሰነድ ከሆነ ዋስትና ያለው መሆኑን አረጋጋጩም የሚቀርቡለትን ሰነዶች አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ትክክለኛነታቸውን ማመሳከሪያዎችን በመጠቀም፣ በማረጋገጥና በመመዝገብ እምነት የሚጣልበት ሰነድ እንዲሆንና አጭበርባሪዎችን መከላከል የስፈልጋል፡፡
በአጠቃላይ የውሎች ምዝገባ ስርዓት አስፈላጊነቱና ጠቀሜታው በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው፡-
 መንግስትና ዜጎች/ግለሰቦች/የሚያደርጓቸው ግንኙነቶች ህጋዊ ጥበቃና ዋስትና ለመስጠት፣
 ለፍትህ ሥርዓቱ እገዛ ማድረግ፣
 በተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤቶች ሊፈጠር የሚችል የሙግት መጨናነቅን መቀነስ፣
 ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማቀላጠፍ፣
 የእያንዳንዱ ዜጋ የዕለት ተዕለት ኑሮ በሕግ እንዲመራ ማድረግ ናቸው።

መመዝገብ ስለሚገባቸው ሰነዶች

መመዝገብ የሚገባቸው ሰነዶች በዋናነት የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 9 ላይ የተጠቀሱት ሲሆኑ በአስገዳጅ ሁኔታ መመዝገብ እንዳለበቸው በንዑስ ቁጥር (1) ላይ የተዘረዘሩት ሰነዶች እና በዚህ አዋጅ መሰረት ካልተረጋገጡና ካልተመዘገቡ በስተቀር ህጋዊ ውጤት አይኖራቸውም በማለት
የተደነገጉት፡-

ሀ. አግባብ ባለው ህግ መሰረት መረጋገጥና መመዝገብ ያለባቸው ሰነዶች፣
ለምሳሌ፡- የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የሚመለከቱ ውሎች በጽሁፍ በሚገባ አኳኋን ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ፊት መሆን አለባቸው፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1723፡፡ ስለኑዛዜ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 891 እና ስለ ንግድ ቤት ኪራይ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀጽ 10(1) መሰረት የተመለከቱ ሰነዶችና ውሎች እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ለ. የውክልና ሥልጣን መስጫ ወይም መሻሪያ ሰነዶች፣
ሐ. የንግድና ሌሎች ማኅበራት መመስረቻ ጽሁፎች፣ መተዳደሪያ ደንቦች እና ማሻሻያዎቻቸው፣
መ. ባለጉዳዮች እንዲረጋገጡላቸውና እንዲመዘገቡላቸው የሚያቀርቧቸው ሌሎች ሰነዶች ናቸው፡፡

የሽያጭ ውል፣ የመያዣ ውል፣ የስጦታ ውል፣ የብድር ውል፣ የሥራ ቅጥር ውል፣ የእንደራሴነት ውል፣ የውርስ መብት ድርሻ መልቀቅ ውል፣ ከጋብቻ በፊት ንብረት የማስመዝገብ ውል፣ ቃለ መሀላና ማረጋገጫ (Declaration) የመሳሰሉት የተለያዩ የስምምነት ውሎች ሁሉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ይመዘገባሉ፡፡

ውሎችን የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው የመንግስት አካላት

ውል ለመመዝገብ ሥልጣን በኢትዮጵያ በአዋጅ ቁጥር 922/2008 መሰረት በሌላ ህግ ውሎችን የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቋማት እንደተጠበቀ ሆኖ ውሎችን የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት የሚከተሉት ናቸው፡-
1. የፌደራሉ ሰነድ የማረጋገጥና የመመዝገብ ሥራ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ (በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች)፣
2. በክልል መስተዳድሮች ሰነድ የማረጋገጥና የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት (የክልል ፍትህ ቢሮዎች) ፣
3. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኢምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ የውጭ ሀገር ኢምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች የተረጋገጡ ሰነዶች፤ በተቀባዩ ሀገር ሕግ እንዲረጋገጡ የሚፈለጉና እና ወደ ውጭ የሚላኩ ሰነዶችን ያረጋግጣል፣
4. በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ኢምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ ሰነዶችን ያረጋግጣሉ፣
5. የመከላከያ ሰራዊት የክፍል ሹሞች በግዳጅ ላይ የሚገኙ የሰራዊቱ አባላት የሚያቀርቡላቸውን ሰነዶች ያረጋግጣሉ፣
6. የፌደራል ማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ከታራሚዎች ወይም ከቀጠሮ እስረኞች የሚያቀርቡላቸውን ሰነዶች ያረጋግጣሉ፣
7. የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የክፍል ሹሞች በግዳጅ ላይ ከሚገኙ የፌደራል የፖሊስ አባላት የሚያቀርቡላቸውን ሰነዶች ያረጋግጣሉ፡፡

የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱ ውሎችን አረጋግጦ ስለ መመዝገብ ጠቅላላ ሁኔታ
ውል በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ተዋዋይ ወገኖች መካከል የሚደረግ በህግ ተቀባይነት ያለው ስምምነት ነው፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች ሕጉ ተዋዋይ ወገኖች የተለየ ሂደት እንዲከተሉ ያስገድዳል፡፡ ከእነዚህ ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ የውሉ ፎርም በጽሁፍ እንዲሆንና ውሉ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት ማስመዝገብን ያካትታል፡፡

በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1725 በግልጽ እንደተደነገገው የተለየ ፎርም /በፅሁፍ መሆን ያባቸው/ ሲል የሚያስቀምጣቸው የውል ዓይነቶች አሉ እነዚህም፡-
1. የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚመለከቱ ውሎች፣
2. ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎች፣
3. ለብዙ ዘመን የሚቆዩ ውሎች ማለትም የዋስትና፣ የኢንሹራንስ እና ሌሎች በህግ በፅሁፍ መሆን አለባቸው የተባሉ ሌሎች ውሎች ናቸው፡፡

እነዚህን በተመለከተ ለሚደረጉ ውሎች ህጋዊነት በህጉ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ግድ ይላል፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን አስመልክቶ የተቀመጠን ቅድመ ሁኔታ በተመለከተ በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1723(1) ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ተዋዋይ ወገኖች ይህን ሳይፈጽሙ ቢገኙ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2877 በተጠቀሰው መሰረት ውሉ ፈራሽ ይሆናል፡፡ ለውሉ ህጋዊነት ማግኘት የውሉ ማረጋገጥና መመዝገብ ሌላው አስገዳጅና አስፈላጊው መከናወን ያለበት ተግባር ነው፡፡

በአጠቃላይ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በማስመልከት የሚፈጸሙ ውሎች ከሌሎች ውሎች ለየት ባለ ሁኔታ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርበው እንዲረጋገጡ ማድረግ በአብዛኞቹ የሕግ ሥርዓቶች የሚፈጸም አካሄድ ነው፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ሕግ ሥልጣን ባለው አካል ፊት እንዲመዘገቡ ያላቸውና እንዲሁም ተዋዋይ ወገኖች በራሳቸው ፈቃድ እንዲመዘገቡላቸው የሚፈልጓቸውን ውሎች ከሌሎች አስረጅ ሰነዶች ጋር በማድረግ ውሎችን ለመመዝገብ ሥልጣን ወደ ተሰጠው አካል ቀርበው የሚያደርጉት ውል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

©~በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/
ማስታወቂያ ከኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር
በእጩ ዐቃቤ ሕግ ደረጃ ሶስት መደብ ተመዝጋቢዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መስከረም 18/2016 ማውጣቱ ይታወቃል።

መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እስከ ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም ድረስ ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስታወቂያ ላይ ባለው ፎርም ወይም በተቋሙ ድህረ ገጽ www.eag.gov.et ገብታችሁ አገልግሎታችን በሚለው ሥር በተቀመጠው ለእጩ ዐቃቤ ሕግ ደረጃ ቅጥር ተወዳዳሪዎች መመዝገቢያ ውስጥ ባለው ዝርዝር ማስታወቂያ መሰረት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በፎርሙ ላይ የምትጭኑትን ማስረጃዎች ለፈተና በምትጠሩበት ጊዜ አንድ ቀን ቀድማችሁ ዋናውንና የማይመለስ ኮፒውን ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።
https://docs.google.com/forms/d/1zdPhTTswHTdW8jltJNlyxZUgki56HAe0Oz7llsyQtCk/edit?ts=6527f279

©የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር

አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/
ማስታወቂያ
።።።።።።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በዕጩ ዓቃቤ ሕግነት አወዳድሮ ለመቅጠር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እሁድ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም እትም  ማውጣት ይታወቃል።
በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከጥቅምት 5 ቀን ጀምሮ ባሉ 15 የስራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/
እነዚህ አራት መሠረታዊ የቼክ መገለጫዋች በቼኩ ላይ ከሌሉ ቼኩ ሕጋዊ አይደለምና ጥንቃቄ አድርጉ
..............................................
1ኛ/ቼኩን ተቀብሎ ክፍያ እንዲፈፅም የታዘዘው የባንክ ቤት ስም በግልፅ በቼክ ላይ ሊኖር ይገባል።ይህም ባንክ በህግ የባንክ ቤትን ስራ ለማከናወን ስልጣን የተሰጠው ተቋም ብቻ መሆን ይኖርበታል።በኢትዮጽያ ከሚገኙ ባንኮች ተመሳስሎ የሚፃፋ የባንክ ቤት ስሞች ስለሚኖሩ ቼኩ ላይ የተፃፈው ባንክ በኢትዮጵያ እውቅና ያለውና  ሕጋዊ ፈቃድ አውጥቶ በስራ ላይ የሚገኝ  ባንክ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።በህጋዊ መልኩ ታትመው ከወጡት ጋር ተመሳስለው የሚሰሩ ቼክ መሳይ ሃሰተኛ ሰነዶች እየበዙ በመምጣታቸው ይህን በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል።በንግድ ሕጉ በግልፅ እንደተደነገገው ሕጋዊ እውቅና ካለው ባንክ ቼኩ ወጪ እስካልተደረገ ለክፍያ ወደ ባንክ ቢቀርብም ገንዘብ ክፍያ ተፈፃሚ አይሆንም።

2ኛ.ለቼክ አውጪው ሊከፈለው የሚገባውን የገንዘብ መጠን በግልፅ ሊፃፍበት ይገባል።  ይህም ሲባል ገንዘቡን ወጪ ለማድረግ ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን ቅድመሁኔታዋች ያላመላከተ መሆን ይጠበቅበታል።አንዳንዶች ቼኩን ሲሰጡ ቼኩ ላይ የሚገልፁት ሌሎች ፅሁፎች ቼኩ ተቀባይነት እንዳይኖረው ያደርጋሉ።ለአብነት ያህል ይህ እስኪደረግ ድረስ ክፍያ ተፈፃሚ እንዳይሆን የሚሉ ክልከላዋች እና ሌሎች መሠል ፅሁፎች የቼኩን ሕጋዊነት የሚያሳጡ ስለሚሆኑ በቼኩ ላይ ከባንክ ወጪ የሚደረገው የገንዘብ መጠን ብቻ የተጠቀሰበት ብቻ እንጂ ሊሆን የሚገባው ከዚህ በተጨማሪ እንደቅድመሁኔታ ገንዘቡን ወጪ ለማድረግ የሚቀመጡ መስፈርቶች ቼኩ ዋጋ እንዲያጣ የሚያደርጉ ስለሆኑ በቼኩ ላይ የሚገለፁ ፅሁፎችን በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል።

3=ቼኩ የወጣበት ቦታ እና ጊዜ በቼኩ ላይ የተፃፈበት መሆን አለበት ።ቼኩ የወጣበትን ቦታናጊዜ የማይገልፅ ከሆነ ህጋዊ ቼክ አይደለም።
4/ በቼኩ ላይ የተገለፀው ገንዘብ ከመቼ ጀምሮ ወጪ መደረግ እንደሚችል ቀኑን ወሩን እና አመተምህረቱን የተገለፀበት እንዲሁም ገንዘቡ የሚከፈልበትን  የባንክ ቤት ስም ወይም ቦታ የሚገልፅ መሆን አለበት።ይህን ያላሟላ ቼክ ህጋዊ ያልሆነ ሀሰተኛ ቼክ ሲሆን 
ሀሰተኛ ቼክ ማለት ቼክን ለማተም ስልጣን ባለዉ ባንክ ቤት ታትሞ ያልተሰጠ ወይም ታትሞ ከተሰጠዉ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ቼክ መሳይ ሰነድ ነው። 

የወንጀል ተጠያቂነት
----------------------------
ማንም ሰዉ ይህንን ሀሰተኛ ቼክ የሰራ ፣ የተገለገለ ወይም ህጋዊ አስመስሎ ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፈ እንደሆነ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ
አንቀፅ 375 ና በተከታዮቹ አንቀፃች እንዲሁም በተደራቢነት በወ.ህ.ቁ 692 መሰረት
በማታለል ወንጀል ተጠያቂ ይሆናል።
Via Lawyer Henok
አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/