#ከትግራይ #ክልል የተመለሱ #የዩኒቨርሲቲ #ተማሪዎች፣
" ተማሪዎቹ በቀጣይ 2 ሳምንታት ውስጥ መፍትሄ ያገኛሉ " - ኢዶሳ ተርፋሳ (ዶ/ር)
ከ150 በላይ ከትግራይ ክልል የተመለሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በማቅናት ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ይሁን እንጂ "ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ" የተማሪዎቹ ተወካዮች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጸዋል።
በመቀጠልም በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ስር ወደተጠቃለለው የቀድሞው ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በማምራት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክተር የሆኑት ኢዶሳ ተርፋሳ (ዶ/ር) አራት የተማሪዎች እና የወላጆች ተወካዮችን አነጋግረዋል።
"ሚኒስቴሩ ከትግራይ ክልል የተመለሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጉዳይ ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ እየሰራበት እንደሚገኝ" ዳይሬክተሩ ለተወካዮቹ ገልጸዋል።
"ተማሪዎቹ በቀጣይ 2 ሳምንታት ውስጥ መፍትሄ እንደሚያገኙም " ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በትግራይ ክልል ከሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች በነሐሴ መጀመሪያ ተጠቃለው የወጡ ሲሆን ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ካቋረጡ ሁለት ወር አልፏቸዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች በቲክቫህ ዩኒቨርሲቱ በኩል ተከታተሉ።
በቲክቫህ ኢትዮጵያ