ህጋችን !
ስለችሎታ እና ክልከላ ሕጉ ምን ይላል?
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሁላችንም ሰው በመሆናችን መብት እና ግዴታዎችን የሚፈጥሩ ተግባራትን መከወን እንችላለን።መብት እና ግዴታን የሚፈጥሩ ተግባራት የሚባሉት ውል መዋዋል ፣ወኪል መሆን፣መክሰስ፣መከሰስ፣ንብረት ማፍራት በንብረት መብት መጠቀም፣ ጋብቻ መፈፀም ኑዛዜ ማድረግ እና የመሳሰሉት ናቸው።
እነኚህን መብቶችን ለመጠቀም ነፃ እና ምክንያታዊ ውሳኔ መወሰን የማንችልበት ሁኔታ ላይ እንዳለን ሕግ ግምት ሲወስድ ከእነኚህ ሕጋዊ ውጤት ካላቸው ተግባራት ልንከለከል እንችላለን። እስኪ የፍትሐብሔር ሕጋችን ስለ ክልከላ ምን እንደሚል እንመልከት።
1. ስለችሎታ
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 192 ‘ሁላችንም በሕግ ተወስኖ ካልተገለፀ በቀር ማንኛውንም አይነት የማህበራዊ ኑሯችንን ተግባር ለመፈፀም ችሎታ አለን’ ይላል። ይህን ችሎታ የሚያሳጡት በዕድሜ ለአካለ መጠን አለመድረስ (ከ18 ዓመት በታች መሆን) የአዕምሮ ህመም፣ድርጊቱን ለመፈፀም ወሳኝ የሆነ የአካል ክፍል ጉዳት እና በፍርድ ቤት የሚጣል ከመብት የመሻር ቅጣት ናቸው፡፡
የተወሰኑ ነገሮችን ብቻ የማድረግ ችሎታ የሚያሳጣው ደግሞ የኢትዮጵያ ዜጋ አለመሆን ሲሆን፤ ለዜጎች ብቻ በተከለከሉ ተግባራት ለምሳሌ መምረጥ ወይም መመረጥ፣በተወሰኑ የሥራና የንግድ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ በመገናኛ ብዙሀን፣ በብሮድካስት አገልግሎት እና በመሳሰሉት የተወሰኑ መስኮች ለመሰማራት የኢትዮጵያ ዜጋ ያልሆነ ሰው በሀገራችን ሕጎች ስለተከለከለ ለነዚያ ተግባራት ኢትዮጵያዊ ዜጋ ባለመሆኑ ችሎታ ይጎለዋል፡፡
#ኪዳኔ #መካሻ
By #kidane #Mekasha
#አለሕግ #Alehig
Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ! 0920666595
#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍8