Forwarded from ሕግ ቤት
በዚህ ጉዳይ የተለያዩ የቶክ ሾው ዝግጅቶች ላይ በሰፊው አውርተንበታል፡፡በእርግጥ ይህ ጉዳይ ሩሲያ ውስጥ የተከሰተ ነው፡፡ሰውዬ በግድያ ወንጀል ለ8 አመት ተፈርዶበት ከ7 አመት በሇላ ወጣ፡፡ከዛም ሰውዬውን መንገድ ላይ አገኘውና ባንተ ም/ት ብዙ አመት እስርቤት ቆየሁ በሚል ገደለው፡፡በድጋሜ ሰውዬው ለፍርድ ቀረበ፡፡የሩሲያ ፍ/ቤትም በጉዳይ ላይ ውሳኔ መስጠት አቅቶት ለ6 ጊዜ ቀጠሮ አመላለሰው፡፡የህግ ሙህራኖች ሁላ ሳይቀር በተለያዩ ሚዲያዎች ተወያዩበት፡፡ነገር ግን አለ...በመጨረሻም የሩሲያ ፍ/ቤት ውሳኔ የሚሰጥበት ወንጅል ወይምበ ጥፋት እስከሆነ ድረስ ሰውዬው በድጋሜ ይፈረድበታል በማለት ዳግም ፈረደበትና ወደ እስር ቤት አወረደው፡፡በርካታ የአሜሪካና እንግሊዝ ዳኞች ከdouble jeopardy ጋር አያይዘው ብዙ ቢሉም ለውጥ አልመጣም፡፡ከዛም በዚህ ም/ት የተለያዩ ህጎች ተሻሽለዋል፡፡የኛም "የወንጀለኛ መቅጫ ህግ" ይል የነበረው በአሁኑ ሰአት "የወንጀል ህግ" ብቻ እንዲል ተደርጎ ተሻሻለ፡፡የስሙ መለወጥ አሁን ለተነሳው ጉዳይ ትልቅ ለውጥ አመጣ፡፡የኛ ህገ መንግስትም አንዴ ፍርድ/የመጨረሻ ውሳኔ ባገኘ ጉዳይ ላይ ድጋሜ መከሰስ እንደሌለ ይደነግጋል ነገር ግን ወንጀልን ለመከላከል በሚል አተረጓጎም እንዲህና መሠል ድርጊቶች በድጋሜ እንደሚታዩ በተግባር አረጋግጧል፡፡እንደውም ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በወንጀል ህግ ቁጥር 16በውጭ አገር ስለተሰጡ ፍርዶች በውጤት ደረጃ ሲያስቀምጥ በተመሳሳይ መልኩ በአንድ ወነጀል ከ ድጋሜ ከመቀጣት ጋር ይጋጫል፡፡በእርግጥ በዚህ አንቀፅ ንኡስ ከንቀፅ -1- ላይ የወንጀሎቹን አይነትና ይዘት ይገድባቸው እንጅ እንደገና ከመከሰስ ወይም ከመቀጣት እንደማያድን በግልፅ አስቀምጧል፡፡
.
.
የሆኖ ሆኖ በተመሳሳይ ድርጊት የመጨረሻ ውሳኔ ባገኘ ጉዳይ ላይ በድጋሜ መከሰስን ወይም ለፍርድ መቅረብን አስመልክቶ እስካሁን በተግባር ላይ ያለው ይቻላል ሲሆን ብዙ የህግ ሙህራኖች ግን ይቃወሙታል፡፡
#አህመድ.M.
ከአርባ ምንጭ

Forwarded from Arey Bin
#ሰላም ለእናንተ ይሁን
እንዲህ ባንዲ መንደር ለመሆን የተገደድነው ለአንድ ትልቅ አላማ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡የመሰባሰባችን ትርጉም ታዲያ ከእያንዳንዳችን የሚጠበቀውን ገንቢ ሃሳብ በመለዋወጥ ለተመሰረተው ህብረት የሚረባ ስራ ለመስራት ነው፡፡በኔ እይታ የመዳከም አይነት ስሜት እንዳይጠናወተን እሰጋለሁ፡፡ባይሆንስ አይነት አስተሳሰብ እየበዛ ቸልተኝነታችን እያደገ እየቻልን አለመቻላችነን እንድናምንና አርፈን እንድንቀመጥ ልንገደድ እንችላለን ብዬም እጠራጠራለሁ፡፡ም/ም እስካሁን የምን እንስራ ምን ይጠበቃል ከእያንዳንዳችን ከዛም እንደ አደረጃጀት ደግሞ ምን እናድርግ አይነት ውይይት እየጠበኩ ነበር፡፡በነገራችን ላይ የቢሮክራሲ ጉዳየ ሆድ አይሞላም ከጉንጭ ማልፋት ያለፈ ትርፍ የለውም ለኛ ደግሞ ይሄ አይበጀንም በላጩ በመተባበርና በመደጋገፍ በመከባበር ወደ ተመሰረትንበት አላማ መራመድ ነው፡፡.
.
.
ይህ ግሩፕ የብዙ ሃሳቦች መፍለቂያ መሆን አለበት፡፡የብዙ የመፍትሄና የአማራጮች ማግኛ ሚዲያ መሆን አለበት፡፡እንዴት ከማለት በፊት ወዴት ይቀድማል ከዛም ቀጣይ ከማንጋ የሚል ነው፡፡ጉዟችን አንድ ነው አለማቀፋዊ ይዘትና አስተሳሰብ ያለው ብቁና ሚዛናዊ እይታ ያለው የህግ ባለሙያ ማፍራት ነው፡፡እንዴት ካልን ወደዚህ ከፍታ መውጫ መሰላሉ ከሁላችንም የሚጠበቅ ነው....ለምሳሌ...ተመሳሳይ መዋቅራዊ የህግ ት/ት ዝርጋታን መፍጠር፣ምቹ የመማር ማስተማር ኡደትን ማስቀጠል ወይም መፍጠር፣የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት የአንድነት ውይይቶችን ማካሄድ አይነት ሊሆን ይችላል፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ ቁርጠኝነትና አንድነት በመስተጋብር መርህ ታስረው መያዝ አለባቸው፡፡
የሆኖ ሆኖ እንወያይ ፡፡
.
.
#አህመድ.M.ከአርባ ምንጭ

ሰላም በያላችሁበት......
ሃበን....ከመቀሌ. ዩ.
ልክ ነህ ግን፡፡ በዚህ አሁን ባለን አቋም ምንም አይነት ስራ መስራት አንችልም ብዬ አምናለሁ፡፡ከላይ ካስቀመጥካቸው ነጥቦች ውስጥ በዋናነት ባለፈው በነበርን ውይይት የልምድ ልውውጦቾን በመውሰድ የሌሉንን እንዲኖሩን ለማድረግ እንችል ይሆናል፡፡በሌሎቹ ነጥቦች ዙሪያ ግን መቅደም ያለበዥ ጉዳይ አለ ፡፡የህብረቱ የስራ እ/ሴና ይዘት በግልፅ ሊታወቅ ይገባል ለዚህም የረቂቅ ዝግጅትና መመሪያውን በመተርጎም ህጋዊ ሰውነት ሊያገኝ የሚችልበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ፡፡ከመግቢያና አላማ እስከ ተፈፃሚነት ወሰን ለሚመለከተው አካል በቅድሚያ ሊደርሰውና ሊያውቀው ይገባል ፡፡የተዋቀረው ስራ አስፈፃሚም የራሱ የሃላፊነት መጠንና ይዘት ሊገለፅለት ይገባል ፡፡አለበለዚያ እየገባን ምን እንስራ አይነት ልመና እንጀምራለን እንደፈለግን ያሻንን ሃሳብ እየመረጥን ቢሆንስ እያልን ለመቀጠል እንገደዳለን፡፡መመሪያና ደንብም ያስፈለገው ይህ አይነት ክፍተት እንዳይፈጠር ከተፈጠረም ለመሙላት ነው፡፡ምን እንስራ ለማለት ቅድሚያ የመዋቅራዊ አሰራሩ ከመመሪያና ደንቡጋ ተዋህዷል ወይ የሚለው መረጋገጥ አለበት፡፡ከዛም በወሰደው ሃላፊነት ልክ እንዲሰራ ይገደዳል ለተጠያቂነትም ለጠያቂነትም ምቾትን ይፈጥራል፡፡
.
.
በተደጋጋሚ እንደገለፅኩት የadvisor ኮሚቴዎችም የሰራቸው ሁኔታ በግልፅ ሊታወቅ ይገባል፡፡የተሻሉ ሃሳቦችን ለማምጣት ሊታይ የሚችል ስራ ለመስራት የሚያስችል ስልት ሲዘረጋ ብቻ ነው የሚሰራው፡፡ከዛ ውጪ በሃሳብ ልውውጥ ብቻ ይቀራል፡፡
.
.
በሌላ መልኩ የexit exam ጉዳይን በተመለከተ አሳሳቢ ቢሆንም መሰረታዊ መዋቅራችን ተስተካክሎ "እኛ"ብለን ለመናገር የሚያስችል አቅም ከሌለን ተፅእኖ መፍጠር አንችልም፡፡የመናገር እድሉን ስላገኘነው ብቻ ተናግረን ለማለፍ ካልሆነ በስተቀር እንጅ፡፡
ይሄ እንዳለ ሆኖ በቅድሚያ፡-
1ኛ፡የህብረቱ መመሪያና ደንብ ተተርጉሞ ግልፅ ሊሆን ቢችል፡- ጥቅሙ...የተዋቀረው ስራ አስፈፃሚ የሃላፊነት ወሰኑን አውቆ ባለበትና በቻለው መጠን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ስለሚያደርገው
2ኛ፡የተዋቀረው ስራ አስፈፃሚ የህብረቱን ህጋዊ ሰውነት ዳር ማድረስ ቢችል ማለትም አንድ ወጥ የሆነ አቋም እንዲኖረውና ለተቋቋመበት አላማ ለስራው እ/ሴ ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር......ከተጠሪቱ እስከ አጋራ አካላቶቹ ከግንኙነት ወሰኑ እስከ ጠቅላላ የስራ እ/ሴዎቹና ተያያዥ ጉዳዮች መቋጫ ስለሚያስገኝ
3ኛ፡የአጭር ጊዜ የስራ እቅድ ማዘጋጀት.....ይህም ማንኛችንም እንደፈለግን እንዳንሄድና በተመረጡና በተመጠኑ እቅዶች እንድንቀሳቀስ ስለሚያስገድደን ወዳውም ለምንሰራው ስራ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ግልፀኝነትን የሚያመጣና የሚታይ ስራ ለመስራት ስለሚያግዝ በሌላ መልኩ ደግሞ ሁሌም የጠባቂነት መንፈስ ይዞን በቸልተኝነት እንዳንተኛ ሲያደርገንና ስራዎቻችነን የበለጠ ቀና እና ውጤታማ ስለሚያደርገን፡፡አለበለዚያ አድስ ሃሳብ ሲመጣልን ለምን ይሄን አንሰራም እያልን የቅንጅት ስራ ሳይሆን የፍላጎት ብቻ ይሆናል፡፡
4ኛ፡ የህብረቱን የበጀት አቅም ግንባታ ለማሳደግ የሚረዳ የፋይናንስ ስትራቴጂ መንደፍ.....መቼም ቢሆን ይህን የሚያክል አገራዊ ህብረት ፈጥረን በይሁንታና በልመና በየቢሮው እየዞርን ለዝግጅት ስንፈልግ ልንሰቃይ አይገባም፡፡አንድም በጀት ከሌለው ንቀትን ያመጣል ሁለትም በተሳታፊዎች ዘንድ የሞራል ውድቀትን ያስከትላል በሌላ መልኩ ህብረቱ ህልውናውን ያጣል፡፡በመሆኑም ከአጋራ አካላት ጀምሮ እስከ መደበኛ አባላት ድረስ የሚያስተዳድርና የሚመራ ብሎም የበጀት አቅምን ሊያሳድግ የሚያስችል ረቂቅ ቢዘጋጅ፡፡ይህ መሆን ካልቻለ ግን መዳረሻችን ግልፅ ነው ተስፋ ካልቆረጥን በየቢሮው በመዞን ደጅ መጥናት ካልሆነ ደግሞ ህብረቱ ይፈርሳል፡፡የምናስባቸው ትልልቅ ሃሳቦች የሚራመዱት በፋይናንስ ነው የ፡ስራ አስፈፃሚው እንደ ልቡ ሮጦ ጉዳዮችን የሚያስፈፅመው በዚሁ ፋይናንስ ነው ተገናኝቶ ለማውራትም ብቻ አጠቃላይ እ/ሴያችን ካለን እውቀት ባለፈ እንደውም ከዛም በላይ የፋይናንስ አቅም ሲኖረን ነውና ቢታሰብበት፡፡
5ኛ፡የመወያያ አጀንዳዎችን በመምረጥና በማዘጋጀት መወያየት ቢቻል....ገንቢና አዳድስ ሃሳቦችን ለመሰብሰብ ስለሚያግዝ ወዳውም አንድነታችንን ስለሚያጠናክር......
መልካም ጊዜ