አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዋቢ የምዝገባ ሂደት

ጠበቃ ኖት? አሁኑኑ ይመዝገቡ፤ ዋቢን መጠቀም ይጀምሩ!

ዋቢ ላይ መመዝገብ ቀላል ነው! የዋቢ ድህረ ገፅ ላይ በመሄድ እነዚህን ቅደም ተከተሎች ይከተሉ:

በመጀመሪያ ወደ ዋቢ የምዝገባ ገጽ ይሂዱ: https://wabilaws.com/am/users/sign_up

1. ባለ ሶስት መስመር ማውጫውን ይጫኑ
2. ይግቡ የሚለውን ይጫኑ
3. እንደ ጠበቃ ይመዝገቡ
4. መረጃዎትን ያስገቡ - ይመዝገቡ
5. በኢሜይል የተላከውን የአካውንት ማረጋገጫ ሊንክ ይጫኑ

ዋቢን ይጎብኙ!
Wabilaws.com

የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ይከታተሉ!

Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=61562959684020
Instagram:
https://www.instagram.com/wabi_laws?igsh=aWR0M3ZqMWZnemcx&utm_source=qr
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/wabilaws/
Telegram:
https://t.me/WABI_laws

ማሳሰቢያ:
ይሄ ድህረ-ገፅ የአዋጅ 1249/2021 መሠረት በማድረግ የተቋቋመ ሲሆን በአዋጁ የተከለከለውን በአገናኝ የሚደረግ የጥብቅና አገልግሎት በማይፃር መልኩ ይሰራል። ዋቢ ከጠበቃውም ሆነ ከደንበኛው እንደ አገናኝ ምንም አይነት ክፍያ አይቀበልም ።
👍112
Forwarded from ስለፍትሕ (Licensed Lawyer Mikias Melak 🔊 ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ)
ከንግድ አሰራር ጋር በተያዘ  የሚደረጉ ለውጦች 


መመርያ  143/2011  አንቀጽ 4  መሰረት 
ለውጦችን  ማሳወቅ 
4 ታክስ ከፋዩ የሚያሳውቃቸው ለውጦች


1/ ማንኛውውም  ታክስ ከፋይ ከዚህ በታች የተመለከቱትን  ለውጥ ሲያደርግ ለውጡ በተደረገ  በ30 (በሰላሳ) ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴሩ በጽሁፍ  ማሳወቅ አለበት፡ 
ሀ) በንግድ ድርጅት ስያሚ የተደረገ ለውጥ
ለ) በድርጅት ስም የተመዘገበ
  (1) ቋሚ የንግድ ስራ ፣የቢሮ እና የመኖርያ ቤት አድራሻ ለውጥ ፣
(2) በማምረቻ ቦታ  ወይም ታክስ ከፋዩ በሚጠቀምበት መጋዘን ላይ ተደረገ የአድራሻ ለውጥ
(3)በፖስታ ወይም በመደበኛ እና በተንቀሳቃሽ ስልክ ፣ፋክስ ወይም ኢ-ሜይል አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ
ሐ) በዋንኛ የስራ እንቅስቃሴው ወይም  በቅርንጫፍ ወይም በንግድ ሥራው ዘርፍ ወይም መስክ ላይ የተደረገ ለውጥ
መ) በድርጅቱ መተዳደርያ ደንብ ወይም የመመስረቻ ጽሑፍ የሽርክና ስምምነት  ላይ የተደረገ ለውጥ
ሠ) በአክስዮን ባለድርሻ  አባላት ላይ የተደረገ ለውጥ ፣
ረ) በድርጅቱ  ወይም በታክስ አንደራሴው የባንክ ሂሳብ ወይም የባንክ ቅርጫፍ አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ
ሰ) በታክስ እንደራሴው እና ከሚንስቴሩ ጋር ግንኙነት በሚደረግበት የኤሌክትሮኒክስ አድራሻ ላይ  የተደረገ ለውጥ
ሸ በተመዘገበና በተከፈለ ካፒታል ላይ የተደረገ ለውጥ
ቀ) የንግድ ስራው በከፊል  ወይም በሙሉ በማቋረጥ  በሽያጭ ወይም በስጦታ በማስተላለፍ ወይም በመለወጥ ወይም በዋስትና በማስያዝ በድርጅቱ ላይ የተደረገ ለውጦች 
በ )የንግድ ስራ ወኪል በታክስ አንደራሴው የተደረገ ለውጥ ፣
ተ) የአክስዮን ትረፍ ድርሻ ለካፒታል ማሳደጊያ ሲውል ፣
ቸ የገቢ ምንጭ መቋረጥን ወይም መሻሻልን በተመለከተ
(1)  የቤት ወይም የህንጻ ወይም ወይም የመጋዘን ኪራይ ውል ሲቋረጥ ወይም ሲሻሻል ፣
(2)   በተሸከርካሪ ወይም በኮንስትራክሽን መሳርያዎች ወይም ሌሎች  የካፒታል ወይም የንግድ ስራ እቃዎች የተደረገ የኪራይ ውል መቋረጥ ወይም መሻልሻ ፣

(3)  በራስ ገቢውን የሚስታወቅ ተቀጣሪ ስራውን ሲለቅ ወይም ሲቀየር ወይም የደሞዝ ለውጥ ሲኖር
(4)  የንግድ ስራ አንቅስቃሴው በጊዚያውነት ወይም በቋሚነት ሲቋረጥ ወይም ሲሻሻል ፣
ኃ) ታክስ ከፋዩ ሰራተኛ ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ወይም የሰራተኞች የደሞዝ ለውጥ ሲያደርግ ፣
2/ ታክስ ከፋዩ በዚህ አንቀጽ  ንዑስ አንቀጽ (1) ከተዘረዘሩት ለውጦች የተለየ ለውጥ ማሳወቅ ያለበት ሆኖ ሲገኝ  ሚኒስቴሩ የለውጡን አይነት በሰርኩላር ያሳውቃል ፡፡
ለተጨማሪ ሙሉ መመሪያውን ይመልከቱ” ከንግድ አሰራር ጋር በተያዘ  የሚደረጉ ለውጦች  ” መመርያ  143/2011  ያንብቡ
 
Ministry of Revenues, Addis Ababa. @AboutJustices
https://t.me/AboutJustices
👍12
ከጠበቃ እና የሕግ አማካሪ የሕግ ምክር እና አማራጭ የሕግ እውቀት መረጃ፣ በቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑ👇 https://t.me/AleHig
ለተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ እና  ማብራሪያዎች ያገኛሉ +251920666595
alehig.com
ወይም
https://linktr.ee/alehig
👍42
ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሬጅስትራሮችን ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቶ ምዝገባ ያካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረው ተመዝጋቢዎች ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና ስለሚሰጥ ማንነታችሁን የሚገለጽ መታወቂያ በመያዝ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድተወስዱ እያሳወቅን በፈተናው ወቅት የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን መጠቀም የማይቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

TikTok
https://www.tiktok.com/@alehigofficial

Instagram https://www.instagram.com/alehigofficial

Twitter /X
https://x.com/AlehigOfficial?t=yFRauAZ7v70Je2MEPIGGsQ&s=09

official website
https://www.alehig.com

#LegalAwareness #AleHig #LegalUpdates #AccessToJustice
👍104🔥1
የሞት ቅጣት በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲወገድ ጥሪ ቀረበ።

የአውሮፓ ህብረት እና የአውሮጳ ምክር ቤት በጋራ በሰጡት መግለጫ ሁለቱ ተቋማት በሁሉም ጉዳዮች ላይ የሞት ቅጣትን እንደሚቃወሙ አረጋግጠዋል።

ድርጊቱን ኢሰብአዊ እና የሰብአዊ ክብር ጥሰት ሲሉ አውግዘው የሞት ቅጣት በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲወገድ ጠይቀዋል።

አሁንም የሞት ቅጣት እየፈጸሙ ያሉ ጥቂት የማይባሉ ሃገራት ቅጣቱን በማስቀረት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦረል እና የአውሮፓ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ አላይን ቤርሴት የሞት ቅጣት የመቀነስ አለም አቀፋዊ አዝማሚያ ቢታይበትም አሁንም በተለያዩ ሀገራት ቅጣቱ መቀጠሉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

በ2023 የሞት ቅጣት የፈጸሙ ሀገራት ቁጥር ዝቅ ማለቱን ጠቅሰው "ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት ሀገራት የሞት ቅጣትን በህግ ወይም በተግባር ሰርዘዋል" ብለዋል።

ይሁን እንጂ መግለጫው አምስት አገሮች ማለትም ቻይና፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሶማሊያ እና ዩናይትድ ስቴትስ በሞት በመቅጣት ከቀዳሚዎቹ  ሃገራት መካከል እንደቀጠሉ አመልክቷል።

ከተላለፉ እና ተፈጻሚ ከሆኑ የሞት ቅጣቶች ውስጥ 74 በመቶ የተፈጸሙት በኢራን ነው።

የአውሮፓ ህብረት እና የአውሮፓ ምክር ቤት በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አዲስ እና አወዛጋቢ የሞት ቅጣት መፈጸሚያ የሆነውን የናይትሮጅን ሃይፖክሲያ አጠቃቀምን በተመለከተ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መግለጫው አሁንም የሞት ቅጣት የሚቀጣባት ብቸኛዋ አውሮፓዊት ሀገር ቤላሩስ መሆኗን አመልክቷል።

የሞት ቅጣት ወንጀልን እንደሚከላከል የሚያምኑ በርካታ ሃገራት ቢኖሩም የአውሮፓ ህብረት እና የአውሮፓ ምክር ቤት አደረኩት ባሉት ጥናት የሞት ቅጣት በወንጀል ቅነሳ ላይ የሚያመጣው ለውጥ አነስተኛ ወይም ምንም ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የሞት ቅጣት ፍርድን በህጋቸው ከሚያስተናግዱ ሀገራት አንዷ ናት። ሞት ቅጣት ፍርድ ተገቢ ነው ብለው ያምናሉ?


@tikvahethmagazine
👍19🤔42🤬2
#ሪልስቴት

ያልተገነባ ቤት / ግንባታ ከማከናወናቸው በፊት ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ ሊገደዱ ነው ፤ በተጨማሪ ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ሊከለከሉ ነው።

ይህንም የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ቀርቧል።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?

ቤት ለመገንባት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ያላገኙ የሪል ስቴት አልሚዎች ደንበኞችን #እንዳይመዘግቡ እና #ቅድመ_ክፍያ እንዳይሰበስቡ ይከለክላል።

በአሁኑ ጊዜ ባለው አሠራር መሠረት የንግድ ፈቃድ በማውጣት ብቻ ወደ ሪል ስቴት ገበያው ሲቀላቀሉ የነበሩት አልሚዎች፤ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ " የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ " የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብት ሪል ስቴት አልሚዎች ይህንን ፈቃድ ለማግኘት ቢያንስ 50 ቤቶችን ገንብተው የሚያስከረክቡ መሆን አለባቸው።

የአገር ውስጥ እና የውጭ አልሚዎች ግንባታውን ለማከናወን የሚያስፈልገውን " የፋይናንስ አቅርቦት ምንጭ " የማቅረብ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦባቸዋል። ይሁንና ረቂቁ፤ " የቅድሚያ ቤት ሽያጭ ተጠቃሚነት " መብትን ከቅድመ ሁኔታ ጋር ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ሰጥቷል።

ይህ አሠራር የሪል ስቴት አልሚዎች የቤት ግንባታውን ሳያከናውኑ ወይም በሂደት ላይ እያለ ለግንባታው የሚውልን ፋይናንስ የሚያሰባስቡበት እና ገንዘቡብ ለግንባታው የሚያውሉበት መንገድ ነው።

የቤት ግንባታው ሳይከናወን በፊት ከገዢዎች ጋር ውል ማሰር እና ክፍያ መፈጸም ኢትዮጵያ ውስጥ በሪል ስቴት ልማት ላይ በተሰማሩ አልሚዎች በኩል የተለመደ አሰራር ነው።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ በዚህ ዓይነት መልኩ ለግንባታ የሚውለውን ሀብት ማሰባሰብ የሚፈልጉ አልሚዎች " አግባብ ካለዉ አካል ፈቃድ ማቅረብ " ይጠበቅባቸዋል። ይህም ግዴታ ነው።

የቅድመ ሽያጭ ዘዴን መጠቀም የሚፈልጉት ሪል ስቴት አልሚዎች፤ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡት ገንዘብ የሚቀመጥበት የባንክ ሂሳብ እና የገንዘብ አወጣጥ ላይም አስገዳጅ አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተጥሎባቸዋል።

አልሚዎቹ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ " የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ " እንዳለባቸው ረቂቅ ሕጉ ላይ ሰፍሯል።

አዲሱ ሕግ፤ ገንዘቡ የሚቀመጥበት ዝግ የባንክ አካውንት የሚከፈተው " አግባብ ባለው አካል ፈቃድ መሠረት " እንደሆነም ያስረዳል።

በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ ከረቂቅ አዋጁ መፅደቅ በኋላ በሚወጣ ደንብ ይወሠናል።

ከዚህም ባሻገር በቅድሚያ የተሸጠው ቤት ተገንብቶ ለተጠቃሚዎች እስከሚተላለፍ ድረስ የቤት የመሥሪያ ቦታው የይዞታ ማስረጃ " በሚመለከተው አካል እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥ " እንደሚታገድ ረቂቁ ይገልጻል።

ቤት ቀድመው በሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ እነዚህ አስገዳጅ አሠራሮች የተቀመጡት " ደንበኞች የሚደርስባቸውን እንግልት እና ኪሳራ ለመቀነስ በማሰብ " እንደሆነ የአዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል።

ረቂቅ አዋጁ በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ሌሎችንም ግዴታዎች ጥሏል።

በረቂቁ መሠረት፤ የሪል ስቴት አልሚዎች ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ተከልክለዋል።

" ያለደንበኛው ፍላጎት እና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም " ይህንን ለማድረግ በቅድሚያ ደንበኛው መስማማት እንዳለበት ያመለክታል።

ሪል ስቴት አልሚዎች ቤት ገዢዎችን መመመዝገብ እና ቅድመ ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉበት ጊዜም ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦበታል።

አልሚዎች ምዝገባ ማድረግ እና ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉት " የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከተረከቡ " በኋላ ነው።

" በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም " የሚለውም ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ከተቀመጡት ግዴታዎች መካከል ነው።

ለሪል ስቴት ልማት አሠራር የሚዘረጋው አዲሱ አዋጅ፤ ከግዴታዎች ባሻገር አልሚዎች ከመንግሥት " መሬት በስፋት " ማግኘት የሚችሉበትን ሂደትም ያስቀመጠ ነው።

ከመንግሥት መሬት " በስፋት " የሚቀርብላቸው አልሚዎች ረቂቁ ላይ ከተጠቀሱ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ ቢያንስ አንዱን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል በብዛት ቤቶችን መገንባት እና ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ " 40 በመቶውን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የማኅበረሰብ ክፍል ተደራሽ " ማድረግ የሚለው አንዱ ነው።

ይህንን ቅድመ ሁኔታ የሚከተሉ አልሚዎች የሚገነቡበት ቤት ብዛት " እንደ ከተሞች ደረጃ በአንድ ጊዜ ከ500 እስከ 5 ሺህ " ሊሆን እንደሚችል በረቂቁ ላይ ተጠቅሷል።

መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ መሬት " በስፋት " የሚያቀርበው " በአዲስ አበባ ከ5 ሺ በላይ ቤት ለሚገነባ እና ለሚያስተላልፍ " አልሚ እንደሆነ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

በሌሎች ከተሞች መሬት " በስፋት " የሚቀርበው እደሚኖራቸው " ተጨባጭ የቤት ፍላጎት " ሲሆን፣ " ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባሉ ከተሞች " ደግሞ ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች እንደሚቀርብላቸው ረቂቁ ያስረዳል።

ከመንግሥት መሬት " በስፋት " ማግኘት የሚፈልጉ አልሚዎች የተቀመጠባቸው ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተገናኙ ናቸው።

በአገር ውስጥ " በጥራት እና በብዛት የማይገኙ " ግብአቶችን በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ (ፍራንኮ ቫሉታ) የሚያስገቡ እንዲሁም የሚያገኙትን ትርፍ እስከ አስር ዓመት ከአገር ሳያወጡ አገር ውስጥ መልሰው የሚጠቀሙ አልሚዎች የዚህ አሠራር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

" የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይት እና ግመታ " የተሰኘው ይህ ረቂቅ አዋጅ የቀረበለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተጨማሪ ዕይታ ወደ ከተማ፣ መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቶታል።

መረጃው ከቢቢሲ አማርኛ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
👍137
#NewsUpdate: የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ/ም የዳኝነት የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በ6 ኪሎ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተካሂዷል።

ፍርድ ቤቶች ከነሀሴ 1/ 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መከረም 30/ 2017 ዓ/ም ለሁለት ወራት በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩ ሲሆን ዛሬ ጥቅምት 1 በይፋ መከፈታቸው ተበስሯል።
#tikvahethmagazine
Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

TikTok
https://www.tiktok.com/@alehigofficial

Instagram https://www.instagram.com/alehigofficial

Twitter /X
https://x.com/AlehigOfficial?t=yFRauAZ7v70Je2MEPIGGsQ&s=09

official website
https://www.alehig.com

#LegalAwareness #AleHig #LegalUpdates #AccessToJustice
👍112🔥1
Forwarded from ሕግ ቤት
International Organization for Migration(IOM) would like to invite qualified and competent applicants to apply for the following vacant post

Position: 1. Project Associate

Position: 2. National Officer

https://g.co/kgs/C1SvG96
👍31
#Passport
የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ ሊል ነው.....
👏11👍31
በሕግ ፊት እውቅና ያላቸው የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች


ሀ.
በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈጸም ጋብቻ


ለ.
በሃይማኖት ሥርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ

ሐ.
በባህል ሥርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ ናቸው። #የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ከአንቀጽ 2 እስከ 4
ሁሉም ዓይነትየጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች በሕግ ፊትእኩል እውቅና እና ውጤት አላቸው።



ተጋብተው 6 ወር ያልሞላቸው ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት አይቀፈድላቸውም።

#የተሻሻለው የቤተስሰብ ሕግ አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 2

ማንኛውም ተጋቢዎች ፍቺ በሚጠይቁበት ወቅት በአቤቱታቸውም ሆነ በቃል የፍቺያቸውን ምክንያት እንዲገልጹ አይገደዱም።

#የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 3

በተጋቢዎች መካከል ያለ ጋብቻ ሊፈርስ የሚችለው
ሀ. ከተጋቢዎቹ አንዱ ሲሞት ወይም በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥ ወይም
ለ. ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት በሕግ መሠረት ጋብቻው እንዲፈርስ ሲወሰን ወይም
ሐ. የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ በመንደር የሚደረጉ የመፋታት ስምምነቶች ተቀባይነት የላቸውም።
#የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75


በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ጋብቻ ያለ መሆኑን ለማስረዳት የጋብቻ ምስክር ወረቀት በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል።

የጋብቻ ምስክር ወረቀቱ በሌለ ጊዜ ጋብቻ ለመፈጸሙ የትዳር ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ ማስረዳት ይቻላል።
#የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 94 እና 95
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
👍142
የአባቷን ገዳይ ለመያዝ የፖሊስ አባል የሆነችው እንስት ከ25 አመታት በኋላ ገዳዩን በቁጥጥር ስር አዋለች!!


የአባቷን ገዳይ በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስን የተቀላቀለችው ብራዚላዊት እንስት ከ25 አመታት በኋላ ገዳዩን በቁጥጥር ስር አውላለች፡፡

ጥር 16፣ 1999 ከዛሬ 25 አመት በፊት ቦአ ቪስታ በተባለ የብራዚል ከተማ ውስጥ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ጊቫልዶ ጆሴ ቪሴንቴ የተባለው ሰው በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ያልፋል፡፡ሬይሙንዶ አልቬስ የተባለው ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ ሟቹ የነበረበትን 150 ሪልስ የብራዚል ገንዘብ መልስልኝ በሚል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ግጭት ያድጋል፡፡ቀጥሎም ገዳዩ መጠጥ ቤቱን ትቶ ከወጣ ከጥቂት ቆይታዎች በኋላ ሽጉጥ ታጥቆ በመምጣት የአምስት ልጆች አባት የሆነውን ጊቫልዶ ቬሴንቶ ጭንቅላቱ ላይ ተኩሶ ገድሏል፡፡

በወቅቱ በአፋጣኝ ከአካባቢው የተሰወረው ገዳይ በስሙ የፖሊስ ማደኛ ቢወጣበትም ፖሊስ የተለያዩ ክትትል እና ማጣርያዎችን ቢያደርግም ሊይዘው አልቻለም፡፡ በጊዜው የ9 አመት እና የቤተሰቡ የመጀመርያ ልጅ የሆነችው ታዳጊ ለአመታት በፍትህ ማጣት ሲብሰለሰሉ የኖሩ ቤተሰቦቿ ሁኔታ በአዕምሯ ውስጥ ተቀርጾ አደገች፡፡

ጂስሊየን ሲልቫ ዴዲውስ የተባለችው ብራዚላዊት የአባቷን ሞት ተከትሎ አምስት ልጆችን ለማሳደግ ሀላፊነት የወደቀባትን እናቷን ለማገዝ የተለያዩ ስራዎችን ሰርታለች፡፡ ሆኖም ጎን ለጎን ትምህርቷን መከታተል እና የምንግዜም ህልሟ የሆነውን የአባቷን ገዳይ ለፍትህ የማቅረብ ጉዳይ ዘንግታ አታውቅም፡፡ በ8 አመቷ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከተመረቀች በኋላ ህግ በማጥናት ለ7 አመታት ጠበቃ ሆና አገልግላለች፡፡

በ2022 የጥብቅና ስራዋን በመተው የአባቷን ገዳይ ለመያዝ ፖሊስን ተቀላቀለች፡፡ በፖሊስ አባልነት የግድያ ወንጀል ምርመራዎችን በማጣራትም የአባቷ ገዳይ ላይ መድረስ ችላለች፡፡ጎሜዝ የተባለው የአባቷ ገዳይ በ2013 በሌላ የነፍስ ማጥፋት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ 12 አመታትን ታስሮ እንደወጣ ካወቀች በኋላ የሚገኝበትን ቦታ አፈላልጋ በማወቅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገዋለች፡፡
 
ጂስሊየን ሲልቫ ዴዲውስ የአባቷ ገዳይ ወደ ሚገኝበት የእርሻ ስፍራ ከሄደች በኋላ የዛሬ 25 አመት በፈጸመው ወንጀል በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን እርሷም የሟቹ የጓደኛው አባት መሆኗን ነግራው ወደ እስር ቤት ይዛው ሄዳለች፡፡ እንስቷ የገዳዩን መያዝ በቁጥጥር ሰር ያዋለቸውም እርሷ እንደሆነች ለቤተሰቦቿ ስትነግራቸው የተሰማቸው ስሜት ሁሌም ከአዕምሮዋ እንደማይጠፋ ተናግራለች፡፡(ምንጭ፣ አልአይን)
Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

TikTok
https://www.tiktok.com/@alehigofficial

Instagram https://www.instagram.com/alehigofficial

Twitter /X
https://x.com/AlehigOfficial?t=yFRauAZ7v70Je2MEPIGGsQ&s=09

official website
https://www.alehig.com

#LegalAwareness #AleHig #LegalUpdates #AccessToJustice
👍253