አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#👉⚖️ በሀገራችን የወንጀል ሕግ ሥርዓት መሠረት ያለአግባብ ለተከሰሱ፣ ለተቀጡም ሆነ ፍርዳቸውን ለተቀበሉ ሰዎች ካሳ የሚከፈልበት ሥርዓት የለም፤ ነገር ግን ንፁሐን ለደረሰባቸው በደል መነሻ የሆኑት የግል አቤቱታ አቃራቢዎችና ሐሰተኛ ምስክሮች ሚጠየቁበት ሥርዓት አለ።
#በወንጀል ጉዳይ ክስ የቀረበበት ሰው ከቀረበበት ክስ ነፃ መሆንን በሁለት መንገድ መመልከት ይቻላል።
🚨1ኛ. ዓቃቤ ሕግ ክሱን ባለማስረዳቱ ነፃ መሆን
#👉⚖️ በመርህ ደረጃ በወንጀል ጉዳይ ከሳሽ የሚሆነው ዓቃቤ ሕግ ነው። ዓቃቤ ሕግ የሚያቀርበውን ክስ ተከሳሽ የፈጸመው ስለመሆኑ የማስረዳት ግዴታ አለበት። ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ግለሰቡ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ከጥርጣሬ በፀዳ ሁኔታ Beyound reasonabl doubt ማስረዳት ይጠበቅበታል።
#👉⚖️ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ ይህንን ግዴታውን ካልተወጣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር1️⃣4️⃣1️⃣መሠረት ግለሰቡን ተከላከል ማለት ሳያስፈልገው በነፃ ሊያሰናብተው ይችላል።
🚨2ኛ. ተከሳሽ ወንጀሉን አለመፈጸሙን በመከላከሉ ነፃ መሆን
#👉⚖️ በወንጀል የተከሰሰ ሰው ክስ የቀረበበትን ጉዳይ በበቂ ሁኔታ ከተከላከለ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር1️⃣4️⃣9️⃣መሠረት ከክሱ ነፃ ይሆናል።
🚨የወንጀል ኃላፊነት
#👉⚖️ በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 447 ላይ እንደተመለከተው ሰውን በሐሰት ወንጀል ወይም መክሰስ ከ5 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እሥራትና በመቀጮ ያስቀጣል። ነገር ግን በሐሰት የቀረበው ክስ ግለሰቡን ከዚህ በላይ የሆነ ቅጣትን አስከትሎ እንደሆነ በንፁህ ሰው ላክ በተወሰነው ቅጣት ልክ ይቀጣል። @lawsocieties
ምንጭ ይግባኝ ምክረ ሕግ
Facebook
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube
https://youtube.com/@Ale_Hig
★ ዳሽን ባንክ አዲስ የስራ ማስታወቂያ

Deadline: May 5, 2024

Dashen Bank invites qualified applicants for following job positions
.

Position 1: Attorney, Litigation
Position 2: Attorney, Sheriah & Legal Research and Advisory

Position 10: Principal Attorney, Legal Research & Advisory I

Position 12: Senior Attorney, Legal Research & Advisory

❇️ Qualification: Information Technology, Computer Science, Computer Information System, Software Engineering, Law preferable, Risk Management, Economics, Accounting, Finance, or Banking, Marketing Management, Management, Business Administration, Human Resource Management , or any other equivalent fields

🔻Salary: Based on Salary Scale and benefits.

🌀 How to Apply Online??
👇👇👇👇
https://dailyjobsethiopia.com/2024/04/26/dashen-bank-new-vacancy-21/
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
EFAA BYLAW FINAL PDF.pdf
480.3 KB
ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ
*******

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆ
ች ማህበር በቅርቡ ለሚያካሂደው ጉባኤ ዝግጅቶችን እያደረገ ያለ መሆኑ ይታወቃል::

በዚሁ ጉባኤ ላይ ከሚቀርቡ ሰነዶች አንዱና ዋነኛው የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ነው:: በመሆኑም መላው የማህበሩ አባላት ይህ ሰነድ የማህበሩን ህጋዊ አቋም ፤ የአመራር አደረጃጀት እና አስራር የሚወስን ወሳኝ ሰነድ መሆኑን በመገንዘብ በአግባብ በማንበብ እና ሀሳባቸውን በማደራጀት መስጠት እንደሚገባቸው ታምኖበታል::

በመሆኑም የማህበሩ አባላት መተዳደሪያ ደንቡ የተሻለ እና ማህበሩን የሚያጠናክር ሆኖ እንዲወጣ የበኩላቸውን እንዲወጡ ማህበሩ ጥሪውን ያቀርባል::

መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ይፋዊ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::

ፌስቡክ- https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=9R9pXO


የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሚያዝያ 18 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ፤
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አለሕግAleHig ️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በፌደራል ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች የታክስ አከፋፈል ጥናት አተገባበር ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ
        በፌደራል ጠበቆችና በጥብቅና ድርጅቶች የታክስ አከፋፈል የህግ እና የአተገባበር ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ በሶስቱ ባለድርሻ አካላት በተከናወነው ጥናት አተገባበር ላይ ሰፊ ውይይት ተደረገ::

       በውይይቱ የፍትህ ሚ/ር የመንግስት ህግና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ "በጠበቆች የታክስ አስተዳደር ላይ የተከናወነው ጥናት ተጨባጭ ችግሮችን የለየ በመሆኑ ጥናቱ ባመላከታቸው መጠቁሞች መሰረት ወደ መሬት እንዲወርድ እና ጉዳዩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ" አሳስበዋል::

      የፌደራል ጠበቆች ማህበር ተ/ፕሬዚደንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው "ጥናቱ የተደራጀ እና ከህግ ዘርፍ አልፎ ለሀገራችን የታክስ ስርዓት መዳበር እንድ አንድ ግብአት ሊወሰድ የሚችል መሆኑን እና በጥናቱ በተቀመጠው አግባብ ከረጅም ግዜ መፍትሄ አንፃር ክፍተቶችን ሊመልስ የሚችል ልዩ መመሪያ መዘጋጀት እንዳለበት ጠቅሰው"፤

"ባለፉት ሁለት አመታት በግብር ወቅት ከተፈጠሩ ችግሮች አንፃር የዚህ አመት የግብር ዘመን ሳይደርስ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ቀድመው እንዲቀመጡ የማህበሩ ፍላጎት መሆኑን አስገንዝበዋል"::

  
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አደገኛ ወንጀል ነው!

አለም አቀፉ የጉምሩክ ድርጅት /WCO/ ኮንትሮባንድን እንደሚከተለው ይተረጉመዋል፡፡ ኮንትሮባንድ ማለት ማንኛውም በህግ የተከለከለ አሰራር ሲሆን እነርሱም፡- ከማምረት /production/፣ ከማጓጓዝ /shipment/፣ ከመቀበል /receipt/፣ ባለቤት ከመሆን /possession/፣ ከማከፋፈል /distribution/፣ ከመግዛትና መሸጥ እንዲሁም ማንኛውም ለዚህ አሰራር ሁኔታዎችን ማመቻቸትን /facilitation/ ያካትታል፡፡

የኢትዮጵያ ጉምሩክ አዋጅ ኮንትሮባንድን <<ህጎችንና በህግ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን በመተላለፍ ወደ ጉምሩክ ክልል ዕቃዎችን ማስገባት፣ በህጋዊ መንገድ የወጡትን በህገ ወጥ መንገድ መልሶ ማስገባት፣ መያዝ፣ ማከማቸት፣ ማዘዋወር፣ ማስተላለፍ፣ እንዲገቡ ወይም እንዲወጡ ለማድረግ መሞከር፣ እንዲሁም እነዚህ ዕቃዎችን መግዛትን፣ መሸጥንና ለዚህ ድርጊት ተባባሪ መሆንን ያጠቃልላል፡፡; በማለት ተርጉሞታል።

1. የኮንትሮባንድ ወንጀል በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ብቻ ሳይሆን የህዝብን ጤንነት፣ የሀገርን ሰላምና ፀጥታ የሚያውኩ ዕቃዎችን በማስገባት አገራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል አደገኛ ወንጀል ነው፡፡
2. ከኢኮኖሚ አንፃር የኮንትሮባንድ ወንጀል ህጋዊ ነጋዴውንና አምራቹን አዳክሞ ከገበያ በማስወጣት ምርታመነትንና ህጋዊ ንግድን ያቀጭጫል፤ ህጋዊ የንግድ ውድድርን ያዳክማል፤ የመንግስትን የገቢ ምንጭ ያደርቃል፡፡
አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig