Follow the Alehig/አለሕግ Legal Service channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va8we4WG3R3hJxkEqN1t
WhatsApp.com
አለሕግ/Alehig Legal Service | WhatsApp Channel
አለሕግ/Alehig Legal Service WhatsApp Channel. Stay Connected with AleHig!
https://linktr.ee/alehig
AleHig is active across multiple social media platforms, ensuring easy access to legal information, updates, and services for everyone.
Whether you’re looking…
https://linktr.ee/alehig
AleHig is active across multiple social media platforms, ensuring easy access to legal information, updates, and services for everyone.
Whether you’re looking…
👍2
የጋብቻ አፈፃፀም በተሻሻለው የፌዴራል ቤተሰብ ህግ
መግቢያ
ጋብቻ በሀገራችን ለዘመናት አክብሮት ተሰጥቶት የኖረ የማህበራዊ መስተጋብራችን አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ጋብቻ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን የሚያስከትል እንደመሆኑ ከምስረታው ጀምሮ በህግ የሚገዛ እና ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ፅሁፍም የጋብቻን ምንነት፣ በህጉ እውቅና ያላቸውን የአፈፃፀም ሥርአቶች እና ጋብቻ ለመመስረት ሊሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በአጭሩ የምንመለከት ይሆናል፡፡
የጋብቻ ምንነት
ጋብቻ በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ ቀጥተኛ ትርጓሜ ባይሰጠውም ከህጉ ጠቅላላ መንፈስ መረዳት የሚቻለው አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ህጋዊ እና ማህበራዊ ተቀባይነት ባለው ሥርአት የሚፈጥሩትን ጥምረት የሚወክል ነው፡፡
ጋብቻ ያለው የህግ ጥበቃ
ጋብቻ ህጋዊ እና ማህበራዊ ውጤቶችን የሚያስከትል እንደመሆኑ ሀገራችን ተቀብላ ባፀደቀቻቸው አለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ሰነዶች፣ በእነዚህ የሰብአዊ መብት ሰነዶች መሰረት በተቃኘው የኢፌድሪ ህገ መንግስት እንዲሁም በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ የቤተሰብ መመስረቻ መንገድ መሆኑ ታውቆ የህግ ጥበቃ ይደረግለታል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት በአንቀፅ 34(3) ቤተሰብ የህብረተስብ የተፈጥሮ መሰረታዊ መነሻ እንደሆነ እና የህብረተሰብ ብሎም የመንግስትን ጥበቃ የማግኘት መብት እንዳለው ደንግጓል፡፡ ጋብቻም የዚህ ቤተሰባዊ ግንኙነት ዋነኛ መመስረቻ ሥርአት እንደመሆኑ ጥበቃ የሚደረግለት ነው፡፡ በተጨማሪም በ1992 ዓ.ም የወጣው የተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ 213/1992 የቤተሰብ ህግ ከምስረታው ጀምሮ በሚኖረው ቆይታ እንዲሁም በሚፈርስበት ሂደት የሚደረግለትን ጥበቃ በዝርዝር የደነገገ ህግ ነው፡፡
የጋብቻ አፈፃፀም ሥርአቶች
በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 1 መሰረት ሶስት አይነት የጋብቻ አፈፃፀም ሥርአቶች አሉ፡፡ ይኸውም፡-
• በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ
በተሻሻለው በቤተሰብ ህግ አንቀፅ 2 መሰረት አንድ ወንድ እና ሴት ጋብቻ ለመፈፀም ተስማምተው በክብር መዝገብ ሹም ፊት በመቅረብ ፈቃዳቸውን ሲገልፁ እና የክብር መዝገብ ሹሙም ይህንኑ ፈቃዳቸወን ሲቀበል ጋብቻ የሚፈፀምበት ሥርአት ነው፡፡
• በሀይማኖት ሥርዐት መሠረት የሚፈፀም ጋብቻ
በተሻሻለው በቤተሰብ ህግ አንቀፅ 3 መሰረት አንድ ወንድ እና አንድ ሴት በሀይማኖታቸው ወይም ከሁለቱ በአንዳቸው ሀይማኖት መሠረት የሚፀና ጋብቻ ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ሥርዐት ሲፈፅሙ ጋብቻ የሚፈፀምበት ሥርአት ነው፡፡ ይህ አማኞች በሚከተሉት እምነት ማለትም በእስልምና፣ በክርስትና እንዲሁም በሌሎች እምነቶች መሰረት የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡
• በባህል ሥርዐት መሰረት የሚፈፀም ጋብቻ
በተሻሻለው በቤተሰብ ህግ አንቀፅ 4 መሰረት አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በሚኖሩበት አካባቢ ባህል ወይም በሁለቱ ተጋቢዎች ወይም ከሁለቱ ተጋቢዎች በአንዳቸው ባህል መሰረት የሚፀና ጋብቻ ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ሥርዐት ሲፈፅሙ ጋብቻ የሚፈፀምበት ሥርአት ነው፡፡
ጋብቻ ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
ጋብቻው በየትኛውም አይነት አፈፃፀም ሥርአት የሚፈፀም ቢሆንም ከመፈፀሙ በፊት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላትታቸው መረጋገጥ አለበት፡፡
• ፈቃድ
ጋብቻ በተጋቢዎች ነፃ እና ሙሉ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ማለት ተጋቢዎች ወይም ከተጋቢዎቹ አንዱ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ጋብቻ እንዲፈፅሙ ሊገደዱ አይችሉም ማለት ነው፡፡ ይህ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 34(2) እና በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 6 የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ተጋቢዎች እራሳቸው ፈቃዳቸውን መግለፅ ያለባቸው ሲሆን በማስገደድ፣ በማሳሳት እና በመሳሰሉት መንገዶች ጋብቻው ቢፈፀም እንኳል ሊፀና አይችልም (የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 13 እና 14)፡፡
• እድሜ
በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 7 መሰረት ወንዱም ሆነ ሴቷ 18 አመት ካልሞላቸው ጋብቻ አይፈፀምም፡፡ ሆኖም ከባድ ምክንያት ባጋጠመ ጊዜ ተጋቢዎቹ ወይም ከተጋቢዎቹ የአንዳቸው መላጆች ወይም አሳዳሪ ጥያቄ ሲቀርብ ፍትህ ሚኒስቴሩ ከመደበኛ የጋብቻ እድሜ ከ2 አመት ያልበለጠ ጊዜ ቀንሶ እንዲጋቡ በልዩ ሁኔታ ሊፈቅድ ይችላል፡፡
• የሥጋ እና የጋብቻ ዝምድና
በተሸሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 8 መሰረት በቀጥታ የሥጋ ዘመዳሞች ማለትም በወላጆችና በተወላጆች፣ ወደ ጎን በሚቀጠሩ የሥጋ ዘመዶች ማለትም በወንድምና እህት እንዲሁም የአክስትና የአጎት ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካካል ጋብቻ ሊፈፀም አይችልም፡፡ በተመሳሳይ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 9 መሰረት በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች፣ ወደ ጎን በሚቆጠር የጋብቻ ዘመዳሞች ማለትም አንደኛው ተጋቢ ከሌላኛው ተጋቢ እህትና ወንድም ጋር ጋብቻ መፈፀም የተከለከለ ነው፡፡
• የቀደም የፀና ጋብቻ መኖር
አስቀድሞ ጋብቻ የፈፀመ ሰው የቀደመ ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ሌላ ጋብቻ እንዲፈፅም አይፈቀድለትም (የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 11)፡፡
• የፍርድ ክልከላ መኖር
የህግ ውጤት ያላቸውን ተግባራት እንዳያከናውን በፍርድ ቤት ክልከላ የተደረገበት ሰው ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቦ ካልፈቀደለት በስተቀር ጋብቻ መፈፀም አይችልም (የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 15)፡፡
የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ጥሶ ጋብቻ ሊፈፅም ያሰበ ቢኖር በሚመለከተው ወገን ተቃውሞ የሚቀርብ ሲሆን ይኸውም ተቃውሞው
• በእድሜ ምክንያት ሲሆን ወላጆች፣ ዐቃቤ ህግ ወይም ሌላ ማንኛውም ሰው
• በሥጋ ወይም በጋብቻ ዝምድና ምክንያት ከሆነ የተጋቢዎቹ ወላጆች፣ 18 አመት የሞላቸው ወንድምና እህቶች ወይም ዐቃቤ ህግ
• በጋብቻ ላይ ጋብቻ ከሆነ ጋብቻ ከሚፈፅመው ሰው ጋር የቀደመ የፀና ጋብቻ ያለው ሰው ወይም ዐቃቤ ህግ
• በፍርድ ክልከላ የተደረገበት ከሆነ ደግሞ አሳዳሪው ወይም ዐቃቤ ህግ
በተሸሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 18 መሰረት ጋብቻው እንዳይፈፀም መቃወም ይችላሉ፡፡
ማጠቃለያ
ጋብቻ የማህበረሰብ መሰረት የሆነው ቤተሰብ የሚመሰረትበት ሥርአት ሲሆን ከአመሰራረቱ ጀምሮ የህግ ጥበቃ የሚደረግለት እና አፈፃፀሙም በህግ የሚመራ ነው፡፡ ስለሆነም ጋብቻ ህጉን ተከትሎ እንዲመሰረትና ጥሰቶችም ሲገኙ እነዲታረሙ በማድረግ ጤነኛ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፡፡
በንቃተ ህግ ተምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍14❤1
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
🥰5👍2
#Ethio Cement PLC#🚩For Fresh & Exp
▪️4 - Lawyer
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://kebenajobs.com/job/ethio-cement-plc-feb-14-24/
▪️Deadline: February 15/24
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
▪️4 - Lawyer
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://kebenajobs.com/job/ethio-cement-plc-feb-14-24/
▪️Deadline: February 15/24
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍3
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ
የማከማቸት ሕግ (the law of accumulation)
ታዋቂው የስኬትና የመልካም ስብእና አስተማሪ ብራያን ትሬሲ ስለ አንድ የማይለወጥ ሕግ ይነግረናል፡፡ ይህንን ሕግ፣ የማከማቸት ሕግ (the law of accumulation) በማለት ይጠራዋል፡፡ ሕጉ እንደዚህ ይላል፡-
“ማንኛውም የምናደርገው ነገር ሁሉ ወይ ወደ ክሬዲት ወይም ደግሞ ወደ ዴቢት በመግባት ይቆጠራል“።
ከዚህ ውጪ ምንም ስሌት የለም፡፡ ከራስ በራስ ጋር ባለን ግንኙነት እሳቤም ሆነ አንዳንድ ልማዶች አንጻር ስንመለከተው የምናደርገው ነገር ሁሉ ወይ እንድናከማች ወይም እንድናባክን ያደርገናል፡፡
ዛሬ በግዢ፣ በሽያጭ፣ በመስጠት፣ በመቀበልና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ከገንዘብ ጋር የነበራችሁ ንክኪ አስቡት ይህ ሂደት ወይ ክሬዲት ተጨምሮላችኋል ወይም ዴቢት ሆኖ ተቀናሽ አድርጋችኋል፡፡
ከሰዎች ጋር ባለንም ግንኙነት ስሌቱ ይኸው ነው፡፡ የምደርጋቸው ነገሮች፣ ከማድረግ የምንከለከላቸው ነገሮች፣ የምንናገራቸው ነገሮች . . . በሙሉ ወይ ጨምረውልናል ወይም ቀንሰውብናል፡፡
ሁኔታዎችን በዚህ መልኩ ማየት ስንጀምር ለምናደርጋቸውም ሆነ ለማናደርጋቸው ነገሮች በሙሉ ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ እንድንንቀሳቀስ ያግዘናል፡፡
ካደረግን ወይም ካላደረግን፣ ከተናገርን ወይም ዝም ካልን በኋላ ስለወጤቱ ከማሰብና ከመጨነቅ ቀድ ሞውኑ ይህ ነገር የሚታሰብልኝ ወደ ክሬዲት ነው ወይስ ወደ ዴቢት ብለን እናሰብ፡፡
via #Dreyob በዶ/ር እዮብ
#Ethiopialegalinfo
@Ethiopialegalinfo
https://t.me/Ethiopialegalinfo

👍11❤2
Forwarded from ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕
ማንኛውም #የመንግሥት ሠራተኛ ለጋብቻ በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ሰባትም(7) የሥራ ቀናት ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
የመንግሥት ሠራተኛ አዋጅ 1064/2010 አንቀፅ 45
ማንኛውም #የግል ድርጅት ሠራተኛ ሕጋዊ ጋብቻ ሲፈጽም ከክፍያ ጋር ለ ሶስት(3)የሥራ ቀናት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 አንቀፅ 81 (1)(U)(ለ)
@NegereFej
https://t.me/NegereFej
#NegereFej #ነገረፈጅ

ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2)
Ignorance of the law is no excuse.
civil code article 2035(2)
ነገረ ፈጅ ከፈለጉ አለን @NegereFeji_Bot ወይም negerefej@gmail.com ይላኩልን።
Ignorance of the law is no excuse.
civil code article 2035(2)
ነገረ ፈጅ ከፈለጉ አለን @NegereFeji_Bot ወይም negerefej@gmail.com ይላኩልን።
👍9❤6
የግራፊክስ ችሎታ ያለው creative/ innovative የሆነ
የአለሕግን #ሎጎ የሚሰራ እንፈልጋለን።
Name:
Slogan:
የሎጎውን አይነት እና መሰል ጉዳይ👇
ማንኛው የአለሕግ ቤተሰብ መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ ይችላል።
የአለሕግን #ሎጎ የሚሰራ እንፈልጋለን።
Name:
Alehig/አለሕግ
Slogan:
Alternative legal enlightenment(ALE)
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
የሎጎውን አይነት እና መሰል ጉዳይ👇
ማንኛው የአለሕግ ቤተሰብ መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ ይችላል።
👍16👎4
በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሠራተኛ እና አሠሪዎች ማኅበራትን በተመለከተ በስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ለተደረገ ጥናት መረጃ የሰጡ ባለሙያዎች በኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ላይ የመብት ጥሰት እንደሚፈፀም አስረድተዋል።ከሥራው ጋር ያልተመጣጠነ አነስተኛ ደመወዝ ክፍያ፣ ያለምንም ክፍያ ትርፍ ሰዓት ማሠራት እና ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ የደኅንነት እና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ሳይሟሉ እንዲሠሩ መገደደ ከመብት ጥሰቶቹ መካከል ተጠቀሱ ናቸው።
ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀኖች፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማ እና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት እንዳላቸው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 43 ስር ተደንግጓል።
#healthinovation
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀኖች፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማ እና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት እንዳላቸው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 43 ስር ተደንግጓል።
#healthinovation
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍5❤1👏1
“400 የኢቢሲ ሠራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳላቸው” ያጋለጠው ግለስብ ከሥራ “ተባረረ”
ዓርብ የካቲት 8 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኢቢሲ) ለዘጠኝ ዓመታት ያገለገለው ወገን አበበ የተባለ ግልሰብ በኢቢሲ የተለያየ የሥራ ዘርፍ ላይ ያሉ “400 የሚሆኑ ሠራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ” እንዳላቸው አጋልጠሃል በሚል ከስራ መባረሩን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በወገን አበበ ላይ “ሃሰተኛ መረጃ በማሰራጨት” ወንጀል ክስ የመሰረተበት ሲሆን፤ ወገን አበበ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው ሠዎችን ሥም ዝርዝር በማቅረብ ተከራክሮ ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 7 ቀን 2016 በዋለ ችሎት ወገን አበበ በነጻ እንዲለቀቅ ወስኗል።
“በተቋሙ ውስጥም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ የሚያነሳና ቅሬታ የሚያቀርብ ካለ ከስራhttps://addismaleda.com/archives/36171
———

👍15😢7❤4😁1
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ
986_ስለ_ውጭ_ድርጅቶች_ምዝገባና_አስተዳደር_የወጣ_መመሪያ_ቁጥር_986_2016_.pdf
1.4 MB
ስለ ውጭ ድርጅቶች ምዝገባና አስተዳደር የወጣ መመሪያ
ቁጥር 986/2016
A DIRECTIVE ON THE REGISTRATION AND
ADMINISTRATION OF FOREIGN ORGANIZATIONS
NO . 986 /2024
https://t.me/Ethiopialegalinfo
#Ethiopialegalinfo
ቁጥር 986/2016
A DIRECTIVE ON THE REGISTRATION AND
ADMINISTRATION OF FOREIGN ORGANIZATIONS
NO . 986 /2024
https://t.me/Ethiopialegalinfo
#Ethiopialegalinfo
👍4❤2
በ24 አመት ውስጥ 17 ጊዜ የወሊድ ፈቃድ የወሰደችው ጣሊያናዊት ተከሰስች
ትራስ በሆዷ ይዛ አረማመዷንም የነፍሰጡር በማስመሰል ለአመታት ቀጣሪዎቿን ስታጭበረብር የቆየችው የ50 አመቷ ጎልማሳ አንድም ልጅ አልወለደችም።
https://bit.ly/3SGyU1q
ትራስ በሆዷ ይዛ አረማመዷንም የነፍሰጡር በማስመሰል ለአመታት ቀጣሪዎቿን ስታጭበረብር የቆየችው የ50 አመቷ ጎልማሳ አንድም ልጅ አልወለደችም።
https://bit.ly/3SGyU1q
አል ዐይን ኒውስ
በ24 አመት ውስጥ 17 ጊዜ የወሊድ ፈቃድ የወሰደችው ጣሊያናዊት ተከሰስች
ግለሰቧ በወሊድ ሰበብ ለአመታት ከስራ ከመቅረቷ ባሻገር ከ120 ሺህ ዶላር በላይ የወሊድ ድጎማ ወስዳለች ተብሏል
😁16👍6
DIRECTIVE_ON_THE_REGISTRATION_AND_ADMINISTRATION_OF_FOREIGN_ORGANIZATIONS.pdf
1.2 MB
ስለውጭ ድርጅቶች ምዝገባና አስተዳደር የወጣ መመሪያ ቁጥር 986/2016
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
A DIRECTIVE ON THE REGISTRATION AND ADMINISTRATION OF FOREIGN ORGANIZATIONS
NO . 986 /2024
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👍3
በህንፃ ለሚደርስ ጉዳት የሚኖር ኃላፊነት፡- ህንፃው በመፍረስ ወይም በመደርመስ በሌላ ሰው መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዳት ቢያደርስ ያደርሳል ተብሎ ያልታሰበም ሆነ አልሆነ የህንፃው ባለቤት ወይም ባለይዞታ ጥፋት ያለበት መሆኑን ማስረዳት ሳያፈስልግ ተጠያቂ ይሆናል (ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2077)፡፡ ከሕንፃዎች ጋር በተያያዘ ኃላፊነትን የሚያስከትለው በመፍረስ ብቻ ለሚደርስ ጉዳት ሳይሆን ከሕንፃው ላይ በሚወድቁ ዕቃዎችም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ኃላፊነት የሚወስደው የግድ የሕንፃው ባለቤት ሳይሆን በሕንፃው የሚኖረው ሰው ይሆናል (ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2080)፡፡ ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
+251920666595
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
+251920666595
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
❤9👍2
Women have the fundamental right to move freely and safely from one place to another, including in their use of public transportation services.
ሴቶች የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶችን መጠቀምን ጨምሮ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በነፃነት እንዲሁም ደህንነታቸው ተጠብቆ የመንቀሳቀስ መሰረታዊ መብት አላቸው።
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
ሴቶች የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶችን መጠቀምን ጨምሮ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በነፃነት እንዲሁም ደህንነታቸው ተጠብቆ የመንቀሳቀስ መሰረታዊ መብት አላቸው።
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👍9❤1
ለ:- ሁሉም መገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሙሉ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ:- የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጠን ስለመጠየቅ
ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ተቋማችን የፌዴራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ባለ ድርሻ ካላት ጋር በመሆን ʺበኢትዮጵያ እና ሶማሌ ላንድ መካከል የባሕር ዳርቻ በሊዝ ለመጠቀም የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት አለም አቀፍ ሕጋዊ ተቀባይነት እና አንደምታˮ በሚል ርዕስ የውይይት መነሻ ጥናት ጽሑፍ የሚቀርብበትና ውይይት የሚደረግበት መድረክ የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ቸርቸር ጎዳና የሚገኘው ግራንድ ኤሊያና ሆቴል የሚያካሄድ ይሆናል፡፡
በመሆኑም የተለያዩ የፍትሕ ዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢንስቲትዩታችን ባልደረቦች፣ ዳኞች፣ አቃቤ-ህጎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የሕግ ባለሙያዎች የሚገኙበትን መርሃ ግብር ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ቸርቸር ጎዳና በሚገኘው ግራንድ ኤሊያና ሆቴል በመገኘትና ሪፖርተሮችን ወደ ስፍራው በመላክ እንዲዘግቡልንና እና በሚዲያችሁ እንድታሰራጩልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

👍13❤3