አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌደራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_የአገልግሎት_ቅድመ_ሁኔታዎች.pdf
134.8 KB
በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
(ፋይል ለመክፈት፣ አዲስ አቤቱታ አቅራቢ ማሟላት የሚገባቸው፣ በሬጅስትራር በኩል መልስና የመልስ መልስ ለመቀባበል መሟላት ያለባቸው፣ መልስ እና የመልስ መልስ አቀራረብ  እንዲሁም የውሳኔ ግልባጭ ለመውሰድ መሟለት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች )
We are #hiring!


LHR is looking for a #Project_Coordinator, who will be responsible for, among others, coordinating the legal aid services in police stations located in Addis Ababa and supervising the activities of other consortium members in Adama and Hawassa. Apply before January 26, 2024!
https://www.ethiojobs.net/display-job/518166/Project-Coordinator.html?fbclid=IwAR1-YChtO5mT7yzRHwf-_5aXabpSUJCpw4IO2YDlVKUeVrixrZFDiU63ugY

#Ethiopia #jobopportunities #HiringNow #projectcoordinator #LegalAidServices #jobopening
ማሳሰቢያ!

ከዚህ በፊት አጭበርባሪዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ የእቃ ጭነት አገልግሎት (ካርጎ) በኩል ለተለያዩ ግለሰቦች ዕቃ እንደተላከላቸው አስመስሎ በመደወል እና ሐሰተኛ የእቃ ጭነት መለያ ቁጥር Air Waybill (AWB) በመጠቀም የተላከውን ዕቃ ለመቀበል የሚከፈል በሚል ክፍያ በመጠየቅ እንዲሁም ስራ ፈላጊዎችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመቀጠር ለምዝገባ እና ለተለያዩ ወጪዎች በሚል ገንዘብ በማስከፈል የማታለል ተግባር ላይ መሰማራታቸውንና ማሕበረሰቡ ይህንን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰባችን ይታወቃል፡፡

በቅርቡም የካናዳ መንግስት የስራ እና የትምህርት እድል እንዳወጣ እና ተቋማችን ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሰው እንደወከለ እንዲሁም መመዝገብ ለሚፈልጉም ሁሉ ክፍያ የሚፈፅሙበት የባንክ አካውንትም አንዳሳወቀ በማስመሰል ደብዳቤ በማዘጋጀት ሰዎችን የማታለል ተግባር ላይ አጭበርባሪዎች መሰማራታቸውን ደርሰንበታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ለተላከላቸው ደንበኞቹ ዕቃቸው መድረሱን እና ወደ ድርጅቱ በመምጣት አስፈላጊ ሂደቶችን እንዲያስጀምሩ ከማሳወቅ ውጪ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ እንዲከፍሉ በስልክ የማይጠይቅ መሆኑን፣ ለስራ ቅጥር ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ የማይጠይቅ እና ከማንኛውም አይነት ኤጀንት ጋር አብሮ የማይሰራ መሆኑን እና ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ የትኛውም ሀገር ሰዎችን የመላክ ስራ ላይ እንዳልተሰማራ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

ስለሆነም ማሕበረሰቡ ይህንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለማሳሰብ እንወዳለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉Facebook Page 👈

👉Telegram Channel 👈


Website
http://alehig.wordpress.com/
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
👉የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት የሚመለከቱትን ትዕዛዞች ለመስጠት
 እያንዳንዱ ውርስ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር የማይበልጥ የኑዛዜ ስጦታ ለማድረግ፣
 አካለ መጠን ላላደረሱ ልጆቹ አስተዳዳሪን ወይም ሞግዚትን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን ለመስጠት ነው፡፡

በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ውስጥ ከብር አምስት መቶ በላይ ኑዛዜ ተደርጎ ከሆነ ከአምስት መቶ ብር በላይ ያለው ተቀናሽ ይሆናል፡፡ በቃል የተደረገ ኑዛዜ ከተደረገበት ከሶስት ወር በኋላ ተናዛዡ በህይወት የቆየ እንደሆነ ኑዛዜው ተፈፃሚ አይሆንም ወይም ፈራሽ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ተናዛዡ ያንያህል ጊዜ ሳይሞት ከቆየ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜን ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜን ለማድረግ እድል አለው ተብሎ ይገመታል፡፡

በሌላ በኩል ብዙ ኑዛዜዎች ካሉ አብሮ ተፈፃሚ ሊሆኑ በሚችሉበት መጠን ልዩ ልዩ ኑዛዜዎች አብረው ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን የሁለት ኑዛዜዎች ቃላት ሁለቱም ሊፈፀሙ ያልቻሉ ወይም የተቃረኑ እንደሆነ በኋላ የተደረገው ኑዛዜ ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡

በአጠቃላይ ንብረቱን በኑዛዜ ማስተላለፍ የሚፈልግ ሰው ሶስቱን የኑዛዜ አይነቶች ፎርማሊቲያቸውን በሟሟላት እንደየሁኔታው ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡ ኑዛዜ አድራጊው የኑዛዜ ቃላት ተፈፃሚነት እንዲያገኙ በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች በጥንቃቄ መከተል አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ኑዛዜው ውድቅ ስለሚሆን የተናዛዡ ፍላጎት ተፈፃሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡

 የኑዛዜ ማስረጃ ወይም ማረጋገጫ

በኑዛዜው የሰፈረውን ቃልና ኑዛዜው መኖሩን ማስረዳት ያለበት በዚህ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚለው ሰው ነው፡፡ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የተደረገ ኑዛዜ መኖር የሚረጋገጠው የኑዛዜውን ፅሁፍ ዋናውን በማቅረብ ወይም ለማዋውል ስልጣን በተሰጠው ሰው ዘንድ ወይም ፍርድ መዝገብ ቤት ሹም ተክክለኛ ሆኖ የተመሰከረ አንድ ግልባጭ በማቅረብ ነው፡፡ ኑዛዜዎቹን ለማስፈፀም በማናቸውም ሌላ መንገድ ለማስረዳት አይቻልም፡፡ ነገር ግን በጥፋት ወይም በቸልተኝነት ኑዛዜው እንዲጠፋ ካደረገ ሰው የጉዳት ኪሳራ ለማግኘት ከሆነ በማናቸውም አይነት መንገድ ኑዛዜዎችን ማስረዳት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ በአንድ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚል ሰው ሁለት ነገሮችን በመሰረታዊነት ማስረዳት ያለበት ሲሆን እነሱም በተናዛዡ የተደረገውን ኑዛዜ በማቅረብ የኑዛዜን መኖር እና የኑዛዜውን ይዘት በማስረዳት ማለትም እሱ የኑዛዜው ተጠቃሚ (beneficiary) መሆኑን ማስረዳት ናቸው፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልተጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/alehig
https://t.me/lawsocieties
#አለሕግ #ህግ  #AleLaw #አለጠበቃ #አለሕግአማካሪ #አለሕግ ነገረፈጅ #አለShare #lawsocieties
ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ህግ ባለሙያ ያማክሩ!
#አለሕግ #AleHig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Public #Access To #Legal #Information In Ethiopia
🎙Key Note Speaker: Mikias Melak
Public access to legal information in Ethiopia encompasses the availability and accessibility of legal resources like laws, cases, policies, and institutions for the general populace. It plays a crucial role in advancing the rule of law, human rights, democracy, and good governance in the country.

Despite Ethiopia's ratification of various international and regional human rights instruments affirming citizens' right to access justice and information, barriers exist. These hurdles include poverty, illiteracy, language disparities, geographical distance, corruption, discrimination, and lack of awareness.
አለሕግAleHig ️
Public #Access To #Legal #Information In Ethiopia 🎙Key Note Speaker: Mikias Melak Public access to legal information in Ethiopia encompasses the availability and accessibility of legal resources like laws, cases, policies, and institutions for the general…
To overcome these challenges, diverse initiatives by the government, civil society, and development partners aim to enhance public access to legal information. The Ethiopian Institutions of Ombudsman (EIO) leads the implementation of the 2008 Freedom of Expression and Access to Information Proclamation, monitoring progress and ongoing efforts. Additionally, Public Information Noble (PIN) Ethiopia collaborates with IEYA ongoing advocacy to ATI focuses on training, manuals, procedures, and awareness campaigns to address both demand and supply aspects of access to information.

The Alehig/አለሕግ platform is set to contribute significantly by providing searchable databases of Ethiopian laws, cases, and legal resources. It also includes audio files tailored for lawyers with visual impairments, ensuring inclusivity in legal information access.
Mikias Melak Birhanie
Attorney & consultant at law
https://t.me/lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ
የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ
አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው። ሠራተኞችና አሠሪዎች የየራሳቸውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችላቸው የኅብረት ስምምነት ድርድር በማድረግ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የወልም ሆነ የግል የሥራ ክርክሮች፣ የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በተጨማሪ አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ለመጠበቅ እንዲቻል የአሰሪና ሰራተኛ ህግ በኢትዮጵያ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡
በዚህ አጭር ጽሁፍም በግል በተቋቋሙ ድርጅቶችና መንግስታዊ በሆኑ የልማት ድርጅቶች ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ባለው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ተደንግጎ የሚገኘውን የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱን እንመለከታለን።
የሰራተኞች ቅነሳ መቼ ይደረጋል?
የሰራተኞች ቅነሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ ሊደረግ የሚችለው የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት በሚከተሉት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ ነው:-
አለሕግAleHig ️
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው።…
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ
የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ
አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው። ሠራተኞችና አሠሪዎች የየራሳቸውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችላቸው የኅብረት ስምምነት ድርድር በማድረግ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የወልም ሆነ የግል የሥራ ክርክሮች፣ የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በተጨማሪ አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ለመጠበቅ እንዲቻል የአሰሪና ሰራተኛ ህግ በኢትዮጵያ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡
በዚህ አጭር ጽሁፍም በግል በተቋቋሙ ድርጅቶችና መንግስታዊ በሆኑ የልማት ድርጅቶች ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ባለው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ተደንግጎ የሚገኘውን የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱን እንመለከታለን።
የሰራተኞች ቅነሳ መቼ ይደረጋል?
የሰራተኞች ቅነሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ ሊደረግ የሚችለው የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት በሚከተሉት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ ነው:-
• ሠራተኞች የተሰማሩባቸው ሥራዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት፤
• በአዋጁ አንቀጽ 18(5) እና (6) ላይ የተቀመጡት ከስራ ውል የሚመነጩ መብቶችና ግዴታዎች ለጊዜያዊ የሚታገዱበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ አሠሪው በሚያመርታቸው ምርቶች ወይም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ የሥራ ውል ማቋረጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
• የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የአሠራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ ናቸው፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ነው ሊያስብል የሚችለው ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ቁጥራቸው ከድርጅቱ ሠራተኞች ቢያንስ ከመቶ አሥር የሚያህለውን ወይም የሠራተኞች ቁጥር (የአንድ አመት አማካኝ የሰራተኞች ቁጥር) ከሀያ እስከ ሀምሳ በሆነበት ድርጅት ቢያንስ አምስት ሠራተኞችን የሚመለከት ከአሥር ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የሚቆይ የሥራ ውል መቋረጥ ሲከሰት እንደሆነ በአስሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 29 ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ሂደት
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ አሰሪ በራሱ ጊዜ የፈለገውን ሰራተኛ መቀነስ የማይችል ሲሆን ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ በመጀመሪያ አሠሪው ከሠራተኞች ማኅበር ወይም ተወካይ ጋር በመመካከር የሥራ ችሎታ ያላቸውና ከፍተኛ የምርት ውጤት የሚያሳዩ ሠራተኞች በሥራቸው ላይ እንዲቆዩ ያደርጋል ወይም ከማይቀነሱ ሰራተኞች መካከል ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን በድርጅቱ ውስጥ ተመሳሳይ የሥራ ችሎታ ያላቸውና ተመሳሳይ የምርት ውጤት የሚያመርቱ ሠራተኞች በሚኖሩ ጊዜ የሰራተኞች ቅነሳ የሚደረገው በሚከተለው ቅደም ተከተል መሠረት ይሆናል:-
1. በድርጅቱ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ያገለገሉ ሠራተኞች፤
2. አነስተኛ ቁጥር የሆነ ጥገኞች ያሏቸው ሠራተኞች፤
3. ከተራ ቁጥረ (4) እስከ (7) ከተዘረዘሩት የሠራተኛ ክፍሎች ውጭ የሆኑ ሠራተኞች ቅነሳው በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከታቸው ይሆናል፤
4. አካል ጉዳተኛ የሆኑ ሠራተኞች፤
5. በድርጅቱ ሳሉ በሥራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች፤
6. የሠራተኞች ተጠሪዎች፤
7. ነፍሰጡር ሠራተኞች ወይም ከወለዱ እስከ 4 ወር ድረስ የሆናቸው ሴት ሠራተኞች ናቸው፡፡
በልዩ ሁኔታ የኮንስትራክሽን ስራ ማለትም ሕንጻ፣ መንገድ፣ የባቡር ሐዲድ፣ የባሕር ወደብ፣ የውሃ ግድብ፣ ድልድይ፣ የመሣሪያ ተከላና ሌላም ተመሳሳይ ሥራ የመሥራት የመለወጥ፣ የማስፋፋት፣ የማደስና የመጠገን ሥራ ተከታታይነት እያለቀ ሲሄድ የሥራው መጠን በመቀነሱ ምክንያት ተቀጥረው በሚሰሩ ሠራተኞች ላይ ቅነሳ ሲደረግ አሠሪው በዚህ ከላይ የተመለከቱትን የሠራተኞች ቅነሳ ሥነ ሥርዓት መከተል አይጠበቅበትም፡፡ ነገር ግን ሰራተኞች የተቀጠሩበት ሥራ ከማለቁ በፊት ከሆነ የሰራተኛ ቅነሳ ሲደረግ በአዋጁ ላይ የተገለጸውን ሥነ-ሥርአት መከተል የግድ ይለዋል። በተጨማሪም ቅነሳ ለማካሄድ አሰሪው የሁለት ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሚቀነሱት ሰራተኞች የመስጠት ግዴታ አለበት (አንቀፅ 35/1/መ)፡፡ እንዲሁም ድርጅቱ የሚወስደው እርምጃ፣ ከሰራተኞች ጋር የህብረት ስምምነት ካለው ይህንኑ እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በዚህ ረገድ የሚያወጣውን መመሪያ ያከበረ መሆን አለበት፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ያለው ውጤት
አንድ ሰራተኛ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 29 መሰረት በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ሲቋረጥ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው። የስራ ስንብት ክፍያ መጠንን በተመለከተ ለመጀመሪያው የአንድ ዓመት አገልግሎት የሠራተኛው ማለትም የተቀነሰው ሰራተኛ የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡ከአንድ ዓመት በታች አግልግሎ ለተቀነሰ ሰራተኛ ግን እንደአገልግሎት ጊዜው እየተተመነ ተመጣጣኝ ክፍያ ያገኛል፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎ በሰራተኛ ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ የተቋረጠበት ሠራተኛ ከላይ በተጠቀሰው ክፍያ ላይ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት ዓመት ከላይ የተጠቀሰው ክፍያ አንድ ሦስተኛ እየታከለ የስራ ስንብት ክፍያው ይከፈለዋል፡፡ ነገር ግን ጠቅላላው ክፍያ ከሠራተኛው የ12 ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡
በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ተቋርጦ ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ ከላይ ከተጠቀሰው የስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የሠራተኛው የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዝ በ60 ተባዝቶ እንደሚከፈለው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ከዚህ ባለፈ አለመግባባት የሚፈጠር ከሆነ ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ሰላም ለመፍጠር፣ ምርታማነትን ለማሻሻል ብሎም የሰራተኞች ህጋዊ መብቶች ለማስክበር በስራና ክህሎ ሚኒስቴር በሚመደብ አስማሚ ችግሩ እንዲፈታ መመልከት ወይም ይህን መሰል ጉዳይ የወል ስራ ክርክር በመሆኑ ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ዳኝነት መጠየቅ ይቻላል፡፡
Federal Justice and Law Institute
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

https://alehig.wordpress.com/blog-2/
#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig