አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የተጠርጣሪ፣ የተከሳሽ እና የታራሚ ልዩነት

ተጠርጣሪ፣ ተከሳሽ እና ታራሚ የሚሉት ቃላቶች በወንጀል ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚነሱ ሲሆኑ ነገር ግን በአብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በእነዚህ ቃላቶች መካከል ያለውን ልዩነት ባለማወቅ እና ባለመረዳት አንዱን ቃል ለአንዱ በመተካት እና በመቀያየር ሲጠቀምበት ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም በዚህ ፅሁፍ የተጠርጣሪ፣ የተከሳሽ እና የታራሚን ምንነት፣ በመካከላቸው ያለውን አንድነት እና ልዩነት ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡

ተጠርጣሪ

ተጠርጣሪ ማለት የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረ እና በወንጀል ሥነ ሥርአት ህጉ መሰረት ለፖሊስ ወይም በህግ ክስ ለመቀበል ስልጣን ለተሰጠው አካል የወንጀል ክስ አቤቱታ ወይም ጥቆማ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ነው፡፡ በዚህም ፖሊስ ተጠርጣሪው የተባለውን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀም ወይም አለመፈፀሙ ማስረጃ የማሰባሰብ እና የምርመራ ሥራ ያከናውናል፡፡ በዚህ መልኩ የሚሰራው ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ የምርመራ መዝገቡ ለዐቃቤ ህግ የሚቀርብ ሲሆን ዐቃቤ ህግም የቀረበውን ማስረጃ በመመልከት ተጠርጣሪው ወንጀሉን ስለመፈፀሙ የሚያስረዳ በቂ ማስረጃ ያለ ከሆነ በፍርድ ቤት ክሰ ሊመሰርት፣ በተጨማሪነት መቅረብ ያለበት ማስረጃ ካለ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሊሰጥ ወይም ማስረጃው አጥጋቢ ካልሆነ የአያስከስስም ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ተጠርጣሪው የተጠረጠረበትን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀሙ የሚያመለክት አጥጋቢ ማስረጃ እስካልተገኘበት ድረስ በቁጥጥር ስር የማይውል ሲሆን የወንጀል ምርመራ በሚደረግበት ወቅትም ተጠርጣሪው እንደተጠረጠረበት የወንጀል አይነት፣ ክብደት፣ የአፈፃፀም ሁኔታ፣ እንደ ተጠርጣሪው ባህሪ እና ሌሎች ሁኔታዎች በፖሊስ ዋስትና፣ በፍርድ ቤት ዋስትና ወይም በማረፊያ ቤት ሆኖ የወንጀል ምርመራ ሂደቱ ሊከናወን ይቻላል፡፡

ተከሳሽ

ተከሳሽ ማለት በወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ በፖሊስ የወንጀል ምርመራ የተጠረጠረበትን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀሙ በቂ እና አሳማኝ ማስረጃ ተገኝቶ በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ያለ እና የፍርድ ውሳኔ ያልተሰጠበት ማንኛውም ሰው ነው፡፡

ተከሳሽ በፍርድ ቤት ዋስትና ወይም በማረፊያ ቤት ሆኖ የወንጀል ክስ ሂደቱን ሊከታተል ይችላል፡፡ ተከሳሽ በክስ መሰማት ሂደት ወቅት ለህዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመሰማት፣ ክሱ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዲነገረው እና በፅሁፍ የማግኘት፣ በተከሰሰበት ወንጀል እንደጥፋተኛ ያለመቋጠር፣ በራሱ ላይ በምስክርነት እንዲቀርብ ያለመገደድ፣ የቀረበበትን ማንኛውንም ማስረጃ የመመልከት እና የቀረበበትን ማንኛውንም ምስክሮች የመጠየቅ፣ ራሱን ለመከላክል የሚያስችለውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ፣ በመረጠው የህግ ጠበቃ የመወከል፣ በተሰጠው ፍርድ ላይ ይግባኝ የማለት እና በመንግስት ውጪ አስተርጎሚ የማግኘት መብት አለው፡፡

ታራሚ

በፌደራል ማረሚያ ቤት አዋጅ ቁጥር 1174/2012 አንቀጽ 2(8) መሰረት ታራሚ ማለት በፍርድ ቤት የተወሰነበትን ፍርድ በማረሚያ ቤት ውስጥ በመፈፀም ላይ የሚገኝ ሰው ነው፡፡ በህገ መንግስቱ እና በዚህ አዋጅ መሰረት ማንኛውም ታራሚ ሰብአዊ ክብሩ በሚጠብቁ ሁኔታዎች የመያዝ፣ ከትዳር ጎደኛው፣ ከቅርብ ዘመዶቹ፣ ከጎደኞቹ፣ ከሀይማኖት አባት፣ ከሐኪም እና ከህግ አማካሪዎቹ ጋር ለመገናኘት እና እንዲጎበኙት እድል የማግኘት መብት አለው፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
8. የንግድ ሕጉ አንቀፅ 57(4) ደላላው ኃላፊነት አለበት ይላል። ደላላው ለደንበኛው ወይም አገልግሎቱን ለጠየቀው ወገን ያሉበትን ግዴታዎች ተላልፎ የደንበኛውን ጥቅም በሚጎዳ አኳኀን ለሌላ 3ኛ ወገን ጥቅም የሠራ እንደሆነ ወይም ደንበኛው ሳያውቅ ከ3ኛ ወገን ክፍያ ከተቀበለ አበል የማግኘት መብቱ ቀሪ ይሆናል። በተግባር ግን ብዙዎች ደላላ ቢጎዳቸውም ከመበሳጨት በስተቀር በፍርድ ቤት ከሰው በኃላፊነት ካሳ ሲጠይቁ አይታይም።

ለማንኛውም ደላላ ስትጠቀሙ በተለይ አበሉን በተመለከተ በቁርጥ በቅድሚያ ተስማሙ። በመቶኛ ከሆነ አበላቸውን ለመጨመር ዋጋውን ከፍ ሊያደርጉት ስለሚችሉ በቁርጥ አድርጉት። አበሉን ተስማምታችሁም ቢሆን ከሰጡት አገልግሎት ጋር የክፍያው መጠን ከተጋነነ ይገባል ከምትሉት በላይ አልከፍልም በሉ። ጉዳዩ ፍ/ቤት ከደረሰ ሊቀነስላችሁ ይችላል። ቢቻል የንግድ ፍቃድ ባላቸው ደላሎች ተጠቀሙ። ደላላው የሚጠራውን ዋጋ ከማመናችሁ በፊትም በተለያየ ዘዴ የገበያውን ዋጋም ለማጣራት ሞክሩ።
EBC
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ሰ/መ/ቁ 235844 የማይንቀሳቀስ ንብረት በባልና ሚስት ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቢሆንም ከጋብቻ በፊት መፈራቱ ወይም መገዛቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካለ የአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት ነው።
Abrham yohanes
የሆቴሎች የአለባበስ ሥርዓት ረቂቅ ደንብ ይፋ ሆነ
*
(ኢ ፕ ድ)

በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች የሚደርስባቸውን አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጫናን ያስቀራል የተባለለት ረቂቅ ደንብ ይፋ ተደረገ፡፡

አዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የገፅታና የውበት አጠባበቅ እንዲሁም የጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥነ-ሥርዓት ያወጣውን የደንብ ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

በቢሮው የቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃፍታይ ገ/እግዚአብሔር በወቅቱ እንደገለጹት፤ በባለሙያዎች የሚደርስን ጥቃት የሚያስቀር የአለባበስ ሥርዓት ረቂቅ ደንብ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የደንብ ረቂቁ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችም የተካተቱበት ነው፡፡

በሂደቱም የቢሮው የቱሪዝም ባለሙያዎች፣ የኢትዮጵያ መስተንግዶ ማህበር፣ የአዲስ አበባ ሆቴሎችና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም እና የአዲስ አበባ ሆቴሎች ሥራ አስኪያጅ ማህበር እንደተሳተፉበት ገልጸዋል።

እንደ አቶ ሃፍታይ ገለጻ፤ ደንቡ በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴሎችና መሰል ተቋማት ወጥ የሆነ ሥርዓት እንዲኖራቸው....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=115367
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የዳኝነት_ሳይከፈል_በነፃ_ስለሚቀርብ_ክስ

ማንኛውም የፍትሐብሔር ክስ ሲከፈት በፍርድ ቤት ለሚሰጠው የዳኝነት አገልግሎት የዳኝነት እንዲከፈል ይጠበቃል፡፡ ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ለግዜው የዳኝነት መክፈል ባለመቻሉ ብቻ መብቶቹን እንዳያጣ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህጉ መፍትሄ አስቀምጧል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ስለሚቀርብ ክስ ምንነት እና ስለሚቀርብበት ሥነ ሥርዓት እንመለከታለን፡፡
የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ የሚቀርብ ክስ ምንነት
በ1958 ዓ.ም በወጣው የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 467 መሰረት የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ የሚቀርብ ክስ ማለት ገንዘብ የሌለው እና ገንዘብ ለማግኘት የማይችል ማንኛውም ደሀ ሰው የዳኝነት ሳይከፍል በነፃ ፋይል ክፍቶ ክስ የሚያቀርብበት ሂደት ነው፡፡
የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ የሚቀርብ ክስ ሥነ-ሥርዓት
በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 467 መሰረት ዳኝነት መክፈል የማይችል ደሀ ሰው የዳኝነት ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል ሳይከፍል የነፃ ፋይል ማስከፈት የሚችለው ከክሱ አቤቱታ ጋር የነፃ ዳኝነት ማመልከቻ በቃለ መሀላ አስግፎ ዋናውን ጉዳይ ለሚያየው ፍርድ ቤት ሲያቀርብ ነው (ቁ.468)፡፡ ፍርድ ቤቱም ማመልከቻውን ተመልክቶ ስለአመልካች የሀብት ሁኔታ እና ስለማመልከቻው ተገቢነት አስፈላጊ ማስረጃ ለማግኘት አመልካችን ወይም ወኪሉን አስቀርቦ ሊጠይቀው ይችላል፡፡
ፍርድ ቤቱ የቀረበው ማመልከቻ ሲመረምር የሚነቀፍበት ምክንያት ካላገኘ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 471 መሰረት አመልካች ድሀ ስለመሆኑ እንዲያስረዳ እና በአንፃሩም አመልካቹ ሀብት አለው የሚሉ ሰዎች እንዳሉ እንዲያስረዱ ቀጠሮ በመስጠት ከቀጠሮ አስር ቀን በፊት ለባለጋራው ማስታወቂ እንዲደርሰው ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ማስረጃው ተሰምቶ ከተመረመረ በኋላ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻውን ሊቀበል ወይም ውድቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ አመልካቹ ዳኝነት ሳይከፍል ያቀረበው ክስ ዳኝነት እንደተከፈለበት እንደማንኛውም ክስ ተቆጥሮ በመደበኛ ሥነ ሥርአት ይመራል፡፡
ይህም ውሳኔ በነፃ ዳኝነት የቀረበው ክስ ቀጥሎ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ የሚያገለግል እና ማስረጃነቱ የሚቀጥል ሲሆን ይህ ማስረጃ ግን ለሌሎች ክርክሮች እንደ ማስረጃ ሊሆን አይችልም፡፡ በይግባኝ ደረጃ የሚሄድ ክርክር አመልካች ይግባኝ ባይ ከሆነ በነፃ ይግባኝ መዝገብ እንደ አዲስ ይከፈትልኝ እስካላለ ድረስ በነፃ እንዲከራከር በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው የድህነት ማስረጃ አያገለግለውም፡፡ ነገር ግን በይግባኝ ክርክሩ መልስ ሰጪ ከሆነ የድህነት ማስረጃው ያገለግለዋል (ቁ.474)፡፡
በሌላ በኩል ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ እንዲታይ የሚቀርብ ማመልከቻ ተቀባይነት ላያገኝ ይችላል፡፡ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 470 መሰረት ማመልከቻው ተቀባይነትን ላያገኝ የሚችለው፡-
 አመልካቹ ድሀ አለመሆኑ ከተረጋገጠ፣
 በነፃ ለመክሰስ ያቀረበው ነገር የማያስከስስ የሆነ እንደሆነ፣
 ክስ ከማቅረቡ ከሁለት ወር በፊት የነበረውን ንብረት ለሌላ ሰው አስተላልፎ እንደሆነ ወይም በማጭበርበር መንገድ ንብረቱን አዛውሮ ከሆነ ወይም ዳኝነት ከመክፈል ለመዳን ዘዴ ፈጥሮ ከሆነ፣
 ክርክር በሚያቀርብበት ንብረት ወይም መብት ውስጥ ሌላ ሶስተኛ ሰው እንዲጠቀም ወይም ማናቸውንም መብት እንዲያገኝ ተዋውሎ ወይም ተስማምቶ እንደሆነ ነው፡፡
የዳኝነት ሳይከፍል ልከራከር የሚለው ማመልከቻ ውድቅ ከተደረገ በዚሁ ጉዳይ ድጋሚ መቅረብ የማይችል ሲሆን ክስ ማቅረብ የሚችለው የዳኝነት ክፍያ እንዲሁም የነፃ ዳኝነት እንዲፈቀድለት ባቀረበ ጊዜ ባለጋራው ለመቃወም ያወጣውን ወጪና ኪሳራ ከፍሎ እንደሆነ ከፍሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 477 መረዳት ይቻላል፡፡
በነፃ ለመከራከር የተፈቀደለት ሰው በነፃ የመከራከር መብቱን ሊያጣ የሚችልባቸው ሁኔታዎች
በፍሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 475 መሰረት የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ መከራከር ማስረጃ ዋጋ ሊያጣ የሚችል ሲሆን ይኸውም
 ክርክሩ እንዲሰማ በተቀጠረው ቀነ ቀጠሮ የዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ልከራከር ባይ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ ወይም የማወክ፣ የማስቸገርና የተንኮለኛነት ጠባይ ያሳየ እንደሆነ፣
 ክርክሩ በሚቀጥልበት ጊዜ ሀብት ያለው መሆኑ የተገለፀበት እንደሆነና በነጻ ዳኝነት መጠቀም ወይም በዚህ መቀጠል የማይገባው መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳ እንደሆነ፤
 ለክርክሩ መነሻ በሆነው ሀብት ላይ ሌላ ሶስተኛ ወገን ጥቅም እንዲያገኝ ስምምነት አድርጎ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡
ሀብት ያለው መሆኑ ተገልፆበት ወይም ለክርክሩ መነሻ በሆነው ሀብት ላይ ሌላ ሶስተኛ ወገን ጥቅም እንዲያገኝ ስምምነት አድርጎ በመገኘቱ በነፃ መከራከር መብቱ የተሰረዘበት ሰው ተገቢውን የዳኝነትና ማናቸውንም ለፍርድ ቤት የሚከፈለውን ገንዘብ እንዲከፍል ይታዘዛል፡፡
በነፃ እንዲከራከር የተፈቀደለት ድሀ በክርክሩ የመርታት ወይም ሀብት የማግኘት ውጤት
በነፃ እንዲከራከር የተፈቀደለት ሰው የዳኝነት ሳይከፍል የሚከራከርበትን ጉዳይ ራሱ በፍርድ አፈፃፀም የረታ እንደሆነ ፍርድ አስፈፃሚው በፍሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 476 መሰረት ለመንግስት የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብና ማናቸውንም ወጪ ከረታው ሀብት ላይ ተቀናሽ በማድረግ ገቢ ካደረገ በኋላ ቀሪው ሀብት ረቺው እንደ ፍርዱ እንዲረከብ ማድረግ እንዳለበት ተደንግጎአል፡፡ ሌሎች በነፃ ለመዳኘት የሚቀርቡ ማመልከቻዎችና ይህንን ለመመርመር የሚያስፈልጉ ማናቸውም ወጭዎች ሁሉ ለዳኝነት ከሚከፈል ገንዘብ ጋር የሚታሰቡ እንደሆኑ ከፍሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 479 መረዳት ይቻላል፡፡
በተጨማሪም የዳኝነት ሳይከፍል የሚከራከር ወገን ማስረጃው በተሰጠው በአስር አመት ግዜ ውስጥ ወይም ክርክሩ በሚቀጥልበት ጊዜ ሀብት ካገኘ ይህንኑ አስታውቆ ዳኝነቱን መክፈል እንዳለበት በፍሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 478 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ገንዘብ አግኝቶ እያለ ይህንን የማያስታወቅ ወይም የመክፈል ግዴታውን ባይወጣ በአታላይነት ወንጀል እንደሚጠየቅ በድንጋጌው ተመልክቷል፡፡
ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ የሚቀርብ ክስ የዳኝነት ለመክፈል አቅም ያጡ ሰዎች ገንዘብ በማጣት መብቶቻቸውን እንዳያጡ ለማድረግ በህጉ የተቀመጠ መፍትሄ ሲሆን በዚሁ መልኩ የተከራከረ ሰው ሀብት ሲያገኝ በአግባቡ አስታውቆ የዳኝነት መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ስለሆነም ገንዘብ ሲያገኙ መክፍል እንደተጠበቀ ሆኖ የዳኝነት ለመክፈል አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ገንዘብ ማጣታቸው ዳኝነት እንዳያገኙ እንደማይከለክላቸው አውቀው ተገቢውን ማስረጃ በማቅረብ በህጉ በተቀመጠው መልኩ መስተናገድ ይችላሉ፡፡
መረጃው፡- ከፍትሕ ሚኒስቴር የተገኘ ነው!
Federal Justice and Law Institute