አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
proclamation no. 1249.pdf
1.2 MB
የፌዴራል ጥብቅና አስተዳደር አዋጅ
አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍2
ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
ሰ/መ/ቁ. 226596
የኢንሹራንስ ዉልን መነሻ ያደረገ ክርክር ሲሆን ከሳሻ በምርጫዉ የኢንሹራንስ ኩባኒያዉ በሚገኝበት ዋና መስሪያ አካባቢ ስልጣን ላለዉ ፍ/ቤት ክስ ማቅረብ የሚችል በመሆኑ ምንም እንኳ ለክሱ መነሻ የሆነዉ አደጋ የተከሰተዉ ከአዲስ አበባ ውጭ በሌላ ክልል ዉስጥ ቢሆንም፣ የተክሳሽ ድርጅት ዋና መስሪያ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሚያስችሉበት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኝ ከመሆኑ አንፃር ሲታይ ከሳሽ በእራሱ ምርጫ ክሱን ለፌዴራል ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል። ፌዴራል ፍርድ ቤቶችም ክሱን ሰምቶ ለመወሰን የአካባቢ የዳኝነት ስልጣን አለው።
👍31
26 ክሶችን ያልተረታው ዳኛ በ27ኛው  ራሱ ተከሰሰ 😳
         
በኬንያ ምንም አይነት የህግ ትምህርተ ሳይወስድ  በሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃ  ጠበቃ ሆኖ ሲሰራ የነበረ አንድ ግለሰብ በፖሊስ መያዙ ተዘግቧል።

ግለሰቡ ለ26 ክሶች ጠበቃ ሆኖ ቀርቦ ሁሉንም በአሸናፊነት ፋይል አዘግቷል።ነገር ግን የህግ ትምህርት  በዲፕሎማም ሆነ በዲግሪ ደረጃ አለመማሩን  የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑን ዘግበዋል። አሁን ላይ 27ኛው  ክስ  የራሱ ሆኖ ቀርቦለታል😳

Via: DW

Ephrem H. From woldia university school of law

ለሌሎች  ሼር ያድርጉት፣ ያጋሩት ይማሩበታል ያተርፉበታል
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
👍14😁71
ችግርን_በሰነድ
አንድ የህግ ባለሙያ በባቡር እየተጓዘ ሳለ
አንድ በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ መጥታ ፊት ለፊቱ ከሚገኘው ወንበር ላይ ተቀመጠች።
በዚህም የህግ ባለሙያው ደስ አለው። ቀና ብሎ ሲመለከታት አይን ለአይን ተያዩ ከዛም ፈገግ አለች።
አሁን ደግሞ በይበልጥ ደስ አለው። ትንሽ ቆይታ አጠገቡ ሄዳ ተቀመጠች። በዚህን ጊዜ እጅግ በጣም ደስ አለው።
ትንሽ ቆየችና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ "ያለህን ገንዘብ; የATM ካርድህን ከነፓስ ዎርዱ እና የሞባይል ቀፎህን አሁኑኑ ካልሰጠኸኝ ስትጎነትለኝ እንደ ነበረና ፆታዊ ትንኮሳ እንደደረሰብኝ እዚህ ባቡር ውስጥ ላሉት ሁሉ በመንገር እጮኃለሁ።" አለችው።
የህግ ባለሙያው በቸልተኝነት ቀና ብሎ ተመለከታትና ከቦርሳው ውስጥ ወረቀትና እስክሪብቶ አውጥቶ እንዲህ ብሎ ፃፈላት "ይቅርታ መናገርና መስማት የተሳነኝ ነኝ። እባክሽን ማለት የፈለግሽውን ሁሉ እዚህ ወረቀት ላይ ፃፊልኝ።"
ልጅቷም ቀደም ብላ ስትነግረው የነበረውን ሁሉ ጽፋ ሰጠችው።
የህግ ባለሙያው ወረቀቱን ተቀብሏት በጥሩ ሁኔታ አጥፎ ኪሱ ከከተተው በኋላ ከተቀመጠበት ተነስቶ ጎርነን ባለ ድምጽ ምን ቢላት ጥሩ ነው "አሁን እንደፈለግሽ መጮህ ትቺያለሽ።"

የታሪኩ ምግባር: ሰነድን በአግባቡ መያዝ ምን ግዜም አስፈላጊ ነው።
ለሌሎች  ሼር ያድርጉት፣ ያጋሩት ይማሩበታል ያተርፉበታል

("ዮኒ እንደተረጎመው"]
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/
👍41👏43
ማስታወቂያ
።።።።።።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በዕጩ ዓቃቤ ሕግነት አወዳድሮ ለመቅጠር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እሁድ ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም እትም ማውጣት ይታወቃል።
በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከጥቅምት 5 ቀን ጀምሮ ባሉ 15 የስራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share

#Telegram #channel:

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

#Telegram #Group:
https://t.me/AleHig
https://t.me/AleHig
https://t.me/
👍3👏1
#United Insurance Company S.C#

▪️1- Underwriting Officer II
▪️2 - Senior Attorney
▪️3  - Documentation/Filing Clerk
▪️4 - Junior Attorney
▪️5 - Attorney II
▪️6 -  Head-Legal Service
▪️Find More Details here
          💧💧💧💧💧
https://elelanajobs.com/job/united-insurance-s-c-oct-16-23/

▪️Deadline: October 20/2023
ስልጣን ባለው አካል ፊት መረጋገጥና መመዝገብ ስላለባቸው ውሎች

ሰዎች በማኅበራዊ ህይወት ውስጥ ሲኖሩ በግብይ መልክ ያላቸውን ይሰጣሉ የሌላቸውን ይቀበላሉ፡፡ በዚህም የተለያዩ ህጋዊ ልውውጦችን ያካሂዳሉ፡፡ በመሆኑም ሂደቱ አስተማማኝ እንዲሆን፣ በሀብትና ንብረቶቻቸው ላይ ያሏቸው መብቶች ዋስትና እንዲያገኙ የልውውጡን ሥርዓት የሚገዛ ሕግ ያስፈልጋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ውል አንዱ ነው፡፡ ውሎች በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1731 መሠረት በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ውሎች ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ሕግ ናቸው፡፡ ይህም ለሕግና ለሞራል እስካልተቃረነ ድረስ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ጸንቶ የሚቆይ መሆኑን ያሳየናል፡፡ ከነዚህ ውሎች መካከል ሕግ ባለ ጊዜ እና ተዋዋይ ወገኖች ሲፍቀዱ በጽሁፍ እና ሥልጣን ባለው አካል ፊት መደረግ ያለባቸውና መመዝገብ ያለባቸው ውሎች ብዙ ናቸው፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የውሎች ምዝገባ ሥርዓት አሥፈላጊነትና ጠቀሜታ፣ መረጋገጥና መመዝገብ ስለሚገባቸው ሰነዶች፣ ውሎችን የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጣቸው የመንግስት አካላት እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱ ውሎችን አረጋግጦ ስለ መመዝገብ የሚሉትን እንመለከታለን፡፡

የውሎች ምዝገባ ሥርዓት አሥፈላጊነትና ጠቀሜታ
የውሎች ምዝገባ አስፈላገነት ከማየታችን በፊት ስለ ውል (ሰነድ) ትርጉም ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ "ሰነድ መመዝገብ" ማለት አንድን ሰነድ ለዚሁ በተዘጋጀ መዝገብ መለያ ቁጥር በመስጠት መመዝገብና ማስቀመጥ ወይም በሕግ መሠረት በሰነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ተቋም ዘንድ እንዲቀመጥ የተባለ ሰነድን ተቀብሎ መመዝገብና ማስቀመጥ ነው በማለት የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ (2) ንዑስ አንቀጽ (3) ደንግጎት እናገኘዋለን፡፡

ውሎች በጽሁፍ የሚደረጉት አንድም አንዳንድ በባህሪያቸው ለየት ያሉ የውል ዓይነቶች የግድ በጽሁፍ መደረግ አለባቸው የሚሉ አዛዥ ደንቦች በሚኖሩበት ጊዜ አለያም ተዋዋዮቹ ራሳቸው ውላቸውን በጽሁፍ ለማድረግ በሚስማሙበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንድ ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው ሁሉም ዓይነት የጽሁፍ ሰነዶች የሚጋሩት የውል ባህርይ በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2005 የተመለከተውና የጽሁፍ ሰነዶች በላያቸው ላይ ስለ ሰፈረው ፍሬ ነገር በተዋዋዮቹ መሀከል ሙሉ እምነት የሚጣልባቸው በቂ ማስረጃዎች ናቸው ይላል፡፡ የዚህ ደንብ ዝርዝር የአፈጻጸም ሥርዓቶችና ልዩ ሁኔታዎች በዚሁ ሕግ ከቁጥር 2006 እስከ 2019 በተመለከቱት ደንቦች ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ሌላው ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፊት (በባለሥልጣን ፊት) የተደረገ (authentic deed) በግል ከተደረጉ ጽሁፎች (non-authentic deeds or private acts) በይዘት፤ በቅርጽ፤ ይልቁንም ተአማኒነቱና ህጋዊነቱ የበለጠ አስተማማኝ ነው፡፡ መንግስት በአንድ በኩል በእርሱና በዜጎቹ መካከል ያለውን ግንኙነት በሌላ በኩል ደግሞ ዜጎች የግለሰቦችን እርስ በእርሳቸው የሚያደርጓቸው ግንኙነቶች የህግ አግባብ የተከተለና ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲመሩ፣ ለእነዚህ ግኑኝነቶች ህጋዊ ጥበቃና ዋስትና መስጠት ካለው ሀላፊነት አንፃር የሚመነጭ በተለይም ለፍትህ ሥርዓቱ አስተዳደር እና ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል፡፡

የውሎች ምዝገባ ሥርዓት ወንጀል ከመከላከልና የማጭበርበር ተግበራትን በመከላከል ረገድም አይነተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ የውሎች ምዝገባ የሚካሄዱት የንግድም ሆነ ሌሎች ተግባራትን (transactions) ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲካሄድ የተዋዋይ ወገኖች ማንነት በማረጋገጥ ተዋዋዮች በሚዋዋሉት ተግባር የተሟላ ግንዘቤ እንዲኖራቸውና ውጤቱን አውቀውና ፈቅደው እንዲገቡ በማስቻል፣ ሲፈርሙ እርግጠኛ ሁነው እንዲፈርሙ በማድረግ አመኔታ ያለው የንግድና ሌላም ህጋዊ ተግባራት እንዲካሄዱ ያግዛል፡፡ ስለዚህ የውሎች ሥልጣን ባለው አካል በመመዝገብ ሂደት ማጭበርበር (forgery)፣ የማይመለከተው በማሳሳት (misrepresentation)፣ ማስገደድን ለማስወገድ እና ግድፈቶችን (omission) ለመከላከል ውጤታማ እገዛ አለው፡፡ ስለዚህ የውሎች ምዝገባ ሥርዓት በሚከተሉት ሁኔታዎች የንብረት ማጭበርበርን የመመዝገብ ሥልጣን ባለው አካል ፊት በመገኘትና በመፈፀም ዜጋው ያልሆኑ ተግባራትን እንዳይፈጽም ይከላከላል፡፡ በዚህም እጅግ ወሳኝ የሆኑ ቀጣይ ዋስትናዎችንም በንብረት ማስተላለፉ ሂደት ያካሄዳል፡፡

1. በአካል መቅረብን (personal appearance) ህጎችና አሰራሮች ተዋዋይ ወገኖች ንብረትን ሲያስተላልፉ በአዋዋዩ ፊት ቀርበው ፈቃዳቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
አረጋጋጩ ፊት ያልቀረበና ያልተፈረመ ፊርማ ተቀባይነት የለውም፡፡ በስሚስሚ (Hearsay) ማረጋገጥ የለበትም፡፡ ቀደም ሲል አንደኛው ወገን ፈርሟል በሚልም የሚደረግ ማዋዋል አይኖርም፡፡ በዚህም የአረጋጋጩ ሁሉም ተግባራት ወይም አገልግሎት ሰነዶችን የሚፈርሙ ሁሉም ወገኖች በአካል በመቅረባቸው ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

2. ማንነትን መለየት (identification) ፈራሚው በአረጋጋጩ ፊት በአካል ከቀረበ በኋላ አረጋጋጩ የፈራሚው ግለሰብን ማንነት በጥንቃቄ ያጣራል፡፡ የፈራሚው ማንነት ማረጋገጥ ፈራሚው አስመሳይ አለመሆኑንና ታማኝ ባልሆነ ሰነድ እንዳያጭበረብር ዋስትና ነው፡፡

3. መሰረታዊ ግንዛቤ መፍጠርና የኃይል አለመኖር ማረጋገጥ (basic awareness and absence of duress):: የፈራሚዎችን ማንነት በማረጋገጥ ሂደት አረጋጋጩ ፈራሚዎች ስለ ጉዳዩ ተጠንቅቀውና ዕውቅና ኖሯቸው ያለምንም ማስገደድ ወይም ፍርሃት እየፈረሙ ለመሆናቸው ይታዘባል፣ የረጋግጣል፣ ጥርጣሬ እያለውና ተዋዋዮች አውቀውና በነፃ ፍቃዳቸው የገቡበት ተግባር መሆኑን በጥንቃቄ ያረጋግጣሉ፡፡

4. ሰነዶችን መመዘገብ (paper trail) አረጋጋጮች በህግ ወስደው ከመልካም ልምድ (best practice) መሰረት እያንዳንዱ የሚያረጋግጡት ሰነድ መመዝገብ ወይም ሪከረድ ማድረግ ይጠበቀባቸዋል፡፡ ይህም ሰነድ የህግ መዝገብ ስለሚሆን የማጭበርበር ተግባር ወይም የማጭበርበር ወንጀል በሚኖር ጊዜ ለዓቃቢ ህግ አይነተኛ ማስረጃ ይሆናል፡፡

5. የተሟላ ሰነዶች መቅረብ (complete documents) አረጋጋጮች ሰነዶች የተሟሉ መሆናቸውና በባዶ ሰነዶች (blanck cheque) እንዳያረጋግጡ ሁሉንም ሰነዶችና ገጾችን መመርመር ማጣራት ይኖርባቸዋል፡፡

የንግድ እንቅስቃሴ ከተጀመረበት ዘመን ጀምሮ የማጭበርበር ወንጀልም አብሮ የነበረ ነውና ይህን ለመቀነስ ወይም ለመከላከል፡-
• የተፃፉ ውሎችን በመመስረት እንዲረጋገጡ ማድረግ፣
• ወሳኝ የሆኑ ውሎችና ተግባራት በተዋዋይ ወገኖች ወይም ፈራሚዎች በዕውቀትና በነፃ ፈቃድ እየተፈፀሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የውሎች ምዝገባ ሥርዓት ጊዜ የፈቀደው ሂደት መሆኑን መገንዘብ፣
• ቋሚና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን (Real-estate) መመዝገብ ግልጽ የሆነ ህዝብ ሪከርድ (መዝገብ) ስለሆነ መንግስትና ተዋዋይ ወገኖች የሚተማመኑበት ሰነድ ነው፡፡
👍81