አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
=========== የዉል ህግ ======
============== የዉል ምንነት
==
ዉል ማለት አንድ ሰዉ፣ተፈጥሮአዊ ሆነ በህግ ሰዉነት የተሰጠዉ፣ አንድን ተግባር ለመፈጸም ወይም ከመፈጸም ለመቆጠብ የሚገባዉን ግዴታ የሚያስርበት የስምምነት አይነት ነዉ፡፡ ይህ ዉል እቃዎችን ለመግዛት፣ ለመሸጥ ወይም አገልግሎት ለመስጠት፣ መብት ለመስጠት ወይም መብት ለማስቀረት፣ ስጦታ ለመስጠት፣ የስራ ቅጥር ለመፈጸም እንዲሁም የተለያዩ ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ ተመስርቶ ሊፈጸም ይችላል፡፡
አንድ ዉል ምን አይነት ሁኔታዎችን ማሟላት አለበት?
የዉል ህግ የሚገዛዉ በሀገራችን የፍትሐብሔር ህግ ስር ነዉ፤ የተለያዩ ልዩ ሁኔታዎች እሚያስቀምጡ ህጎች ካሉ የእነሱ ተፈጻሚነት እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡ ይህም የሆነዉ ከጠቅላላ ህግ ልዩ ህግ ቅድሚያ ስለሚሰጠዉ ነዉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአገራችን ዉል ህግ በአራተኛዉ መጽሃፍ ስር ከአንቀጽ 1675 ጀምሮ ባለዉ ይገዛል፡፡ አንቀጽ 1675 ዉልን ሲተረጉም “ዉል ማለት ንብረታቸዉን የሚመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸዉ ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መካከል የሚደረግ ስምምነት ነዉ፡” በማለት ያስቀምጠዋል፡፡ ከዚህ ትርጉም መረዳት እንደምንችለዉ ዉል አንዱ ንብረት መፍጠሪያ መንገድ ነዉ፡፡ ይህም መብት የሚፈጠረዉ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ በሆኑ ሰዎች ሆኖ ግዴታዎች ላይ በመመርኮዝ ነዉ፡፡ ግዴታ ተቋቋመ ፣ተለወጠ ወይም ቀረ የሚባለዉ እነዚህ ሰዎች በሚገቡት ዉል ላይ በሚያስቀምጡት መዘርዝር ነዉ፡፡ በመሆኑም አንድ ዉል እነዚህን መብቶች መፍጠሩን በግልጽ ማሳየት አለበት፡፡
አንድ ዉልም ዉል ለመባል፡-
1. ዉሉ ችሎታ ባላቸዉ ሰዎች የተፈጸመ መሆን አለበት፡፡
አንድ ሰዉ ችሎታ አለዉ የሚባለዉ በህጉ የተቀመጠዉን የእድሜ ገደብ ሲሞላ ወይም ምንም አይነት የአእምሮ እክል ከሌለበት፣ ወይም በህግ የተከለከለ ካልሆነ ነዉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎችም ተሟልተዉ ቢሆን ዉሉን የሚገባዉ ሰዉ ሙሉ ፈቃዱን የሰጠ መሆን አለበት፡፡ ማንም ሰዉ ቢሆን በማስፈራራት፣ በመደለል፣ በማታለል ሆነ በማስገደድ የዉል ግዴታ ዉስጥ ማስገባት አይቻልም፡፡
2. በዉሉ ላይ እንዲፈጸም የተቀመጠዉ ጉዳይ በአግባቡ ትርጉም የተሰጠዉ ወይም እርግጠኝነት ያለዉ፣ ሊፈጸም የሚቻልና ህጋዊ የሆነ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ አለም ዉጪ የሆነ ወይም ለመፈጸም በማንኛዉም መልኩ ቢሆን አዳጋች የሆነ እንዲሁም ህገ-ወጥ ተግባር ለመፈጸም ዉል መግባት አይቻልም፡፡
3. በህጉ በአንድ በተለየ ፎርም እንዲፈጸም የተቀመጠ ዉል ከሆነና ይህንም ፎርም ያልተከተለ ከሆነ የሚጸና ዉል አይሆንም፡፡ ህጎች ብዙ ግዜ አንድን ዉል በጽሁፍ መሆን አለበት ካሉ በኋላ መልሰዉ የተለየ ሁኔታ የሚያስቀምጡበት ሁኔታ አለ፡፡ ለምሳሌ አንድ ዉል በጽሁፍ የሰፈረ መሆን አለበት ካለ በኋላ መልሶ ደግሞ ዉሉ መፈጸሙን በምስክር ማስረዳት ይቻላል ሲል ሊያስቀምጥ ይችላል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ህጉ የተለየ ፎርም አስቀምጦ ከሆነ በዛዉ መልኩ መፈጸሙ ወደፊት ሊነሱ የሚችሉ ክርክሮች ሊያስቀርና የህግም ድጋፍ  ያገኛል።
ውብአለም መስፍን
የቦሌ/ክ/ከ/የህ/ስ/ም/መ ዳይሬክቶሬት ዐ/ህግ

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አለ_ህግ🔵Ale_Hig:
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ 
Addis Ababa City Administration Residence ID Proclamation.pdf
941.9 KB
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 145/2015
=====+++++++
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ለማቋቋም በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ.ም አንቀጽ 55 እና አንቀጽ 15 (2) (ሠ) ላይ በተጠቀሰዉ መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አለ_ህግ🔵Ale_Hig:
#አለ_ህግ
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
የነጋዴ ግዴታዎች ምንድን ናቸው?
          ================
አዲስ አበባ 21/01/2015ዓ.ም (ንቀትሚ)

1. የንግድ ዕቃዎቹንና የአገልግሎቶቹን ታክስ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ሌሎች ሕጋዊና ክፍያዎችን ያካተተ የዋጋ ዝርዝር በንግድ ቤቱ በግልፅ በሚታይ ቦታ የማመልከት ወይም በንግድ ዕቃዎቹ ላይ መለጠፍ (አንቀፅ 15)፤

2. በሚሸጣቸው የንግድ ዕቃዎች ላይ መግለጫ የመለጠፍ ወይም በተለየ ወረቀት ላይ ጽፎ ለሸማቹ መስጠት (አንቀፅ 16)፤

3. መግለጫው የዕቃውን ስም፣ የተሠራበትን ሀገር፣ ክብደቱን፣ ብዛቱን፣ ጥራቱን፣ ይዘቱን፣ አጠቃቀሙን፣ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ …ወዘተ ያካትታል፤ (አንቀፅ 16/2 ሀ-ኀ)

ለነጋዴ የተከለከሉ ድርጊቶች (አንቀጽ 22)
1. የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ስላላቸው ጥራት ወይም መጠን ወይም ብዛት ወይም ተቀባይነት ወይም ምንጭ ወይም ባህርይ ወይም ውሁድ ወይም ጥቅም የተሳሳተ መረጃ መስጠት(22/1)፤
2. የንግድ ዕቃዎች ስለአዲስነታቸው ወይም ስለሞዴላቸው ወይም አገልግሎታቸው የቀነሰ ወይም የተለወጡ ወይም እንደገና የተሠሩ ወይም በአምራቹ እንዲሰበሰቡ የተባሉ ወይም ያገለገሉ ስለመሆናቸው በትክክል አለመግለጽ(22/2)፤
3. የሌላውን ነጋዴ የንግድ ዕቃዎች በአሳሳች ሁኔታ መግለፅ(22/3)፤
4. የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶችን በማስታወቂያ እንደተነገረላቸው አለመሸጥ ወይም ማስታወቂያው የመጠን ውሱንነት መኖሩን ካልገለፀ በስተቀር ሸማቾች በሚፈልጉት መጠን ልክ አለመሸጥ (22/4)፤
5. ስለዋጋ ቅናሽ ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃ ማስተላለፍ(22/5)
6. የሸማቹን መብት የሚጠብቅ ባልሆነ ምክንያት የንግድ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን አልሸጥም ማለት(22/12)፤
7. የንግድ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን በንግድ መደብሩ ውስጥ ከተለጠፈው ዋጋ አስበልጦ መሸጥ(22/14)፤
8. ከሽያጭ ጋር በተያያዘ የተገባ የዋስትና ግዴታን አለመወጣት(22/7)፤
9. የንግድ ዕቃ የሚያስፈልገው ጥገና ወይም የሚተኩ ክፍሎች      እንደማያስፈልጉት አድርጎ ማቅረብ(22/8)
10. የንግድ ዕቃዎች የተሠሩበትን ሀገር አሳስቶ መግለጽ(22/15)፤
11. በሸማቾች መካከል ተገቢ ያልሆነ አድልዎ መፈጸም(22/16)፤
12. ማንኛውንም አገልግሎት የመስጠት ሥራን በንግድ ሥራው ከሚታወቀው ደረጃ በታች ወይም ባልተሟላ ሁኔታ መስጠት922/9)፤
13. በግብይት ወቅት ማንኛውንም የማጭበርበር ወይም የማደናገር ተግባር መፈፀም(22/11)፤
14. ደረጃ የሚያስፈልጋቸውን የንግድ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ያለደረጃ ማህተም ለሽያጭ ማቅረብ (22/13)፤
15. አንድን የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት ለመሸጥ ሸማቹ ያልፈለገውን ሌላ የንግድ ዕቃ አብሮ እንዲገዛ ማስገደድ(22/17)፤
16. ሕገ ወጥ በሆነ ማንኛውም የመለኪያ መሣሪያ መጠቀም(22/18)፤
17. ለሰው ጤናና ደህንነት አደገኛ የሆነ፣ ምንጩ ያልታወቀ፣ የጥራት ደረጃው የወረደ፣ ወይም የተመረዘ፣ አገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈ ወይም ከባዕድ ነገሮች ጋር የተደባለቁ የንግድ ዕቃዎችን ለሽያጭ ማቅረብ ወይም መሸጥ(22/10)፤
18. አንድ ሸማች አንድን የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛቱ ወይም የገንዘብ መዋጮ በማድረጉ እና በሸማቹ አሻሻጭነት ከእሱ ቀጥሎ ሌሎች ሸማቾች የንግድ ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን የሚገዙ ወይም የገንዘብ መዋጮ የሚያደርጉ ከሆነ ወይም በሽያጭ ስልቱ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ በሸማቾቹ ቁጥር ልክ ተጨማሪ የገንዘብ ወይም የዓይነት ጥቅም እንደሚያገኝ የሚገልጽ ፒራሚዳዊ የሽያጭ ስልት ተግባራዊ ማድረግ(22/6)፤
• ከላይ ከተጠቀሱት መብቶች ውስጥ ያልተከበረ ካለ ግብይቱን በፈጸሙበት አካባቢ ለመገኝ ንግድ ቢሮ ወይም ለፖሊስ በማቅረብ በሕግ ምላሽ እንዲሰጥዎ ያድርጉ፡፡
• በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ በተፈጸመ ግብይት በሸማቹ ላይ ለደረሰ ጉዳት የካሳ ትያቄ በፍትህ ሚኒስቴር የንግድ ውድድና የሸማቾች ጥበቃ ዳኝነት ችሎት ማቅረብ ይቻላል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን:-
Email: fdremotri@gmail.com
fdremotri@motri.gov.et
FB: Ethiopian ministry of trade and regional itegration
ለጥብቅና ፍቃድ
ፈተና የሚሰጥበት ቀን መቀየሩን ለማሳወቅ የቀረበ ማስታወቂያ

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ ለማግኘት ይቻል ዘንድ ፈተናው መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ በማስታወቂያ መነገሩ ይታወቃል፡፡

ነገር ግን መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም የኢሬቻ በአል የሚከበርበት ቀን በመሆኑና ለፈተናው አሰጣጥ አመቺነት ሲባል ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ወደ ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲቀየር ተወስኗል፡፡

በዚህም መሰረት ተፈታኞች ይህንን አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እያሳሰብን ፈተናው የሚሰጥበትን ቦታና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን በቀጣይ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አለ_ህግ🔵Ale_Hig:
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ 
አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ዛሬ ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።

አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል።

ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ።

አስፈላጊ #መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/

አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
በስምምነት የተደረገ የውርስ ኃብት ድርሻ ክፍፍል በሕግ ፊት ስለሚኖረው ውጤት፡፡ 

ወራሾች ራሳቸው ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከፍርድ ቤት ውጪ የውርስ ኃብት ክፍፍል ያደረጉ ከሆነ ይህ ስምምነት ፍርድ ቤት ቀርቦ ባይጸድቅም የሚጸና ነው፡፡ ማንኛውም ወገን ስምምነቱ በፍርድ ቤት ቀርቦ አልጸደቀም ስለዚህ ሊጸና አይገባም የሚል መከራከሪያ ቢያቀርብ የሕግ መሰረት የለውም፡፡ ( የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1079(1) እና 1080(1)
via #ethiolawtips
Legal vacancy:
በሥነምግባር ግድፈት የተከሰሱ 24 ጠበቆች ተቀጡ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 22/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፍትህ ሚኒስቴር የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሥነምግባር ኮሚቴ በሥነምግባር ግድፈት ክስ የቀረበባቸው 24 ጠበቆችን መርምሮ ጥፋተኛ በማለት ቅጣት ጥሎባቸዋል።

ከ24ቱ ተከሳሾች መካከል 18ቱ የጥብቅና ፍቃዳቸውን በወቅቱ ባለማደስ የተከሰሱ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ግን በባለጉዳይ በቀረበባቸው የሥነምግባር ግድፈት ክስ ነው ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት የተጣለባቸው፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ አስተዳደርና የነጻ ህግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ደምሴ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በሥነምግባር ግድፈት ክስ የቀረበባቸው 46 ጠበቆች ነበሩ።

ክስ ከቀረበባቸው ጠበቆች መካከል 24ቱ የቀረበባቸው ክስ ተመርምሮ ጥፋተኛ በመባላቸው ቅጣት እንደተጣለባቸው ገልጸው፥ ቀሪዎቹ ነጻ ተብለዋል።

ጥፋተኛ ከተባሉት 24 ጠበቆች ውስጥ ደግሞ 18ቱ በወቅቱ የጥብቅና ፍቃዳቸውን ባለማደስ በሥነምግባር ግድፈት የተከሰሱት በገንዘብ እንዲቀጡ ተወስኗል።

በተመሳሳይ በባለጉዳይ የሥነምግባር ግድፈት ክስ የቀረበባቸው አራት ጠበቆች በገንዘብ እንዲቀጡ የተወሰነ ሲሆን፥ አንድ ጠበቃ ደግሞ ለ3 ወራት ከጥብቅና ሙያው እንዲታገድ ተወስኗል። እንዲሆም ሌላኛው አንድ ጠበቃ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ኃላፊው ገልፀዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያ ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
Lion Insurance New Job Vacancies Oct 2023👈👈

Lion Insurance Company invites interested and qualified candidates for the following positions.

Position 1: Legal Officer III
Educational background: LLB in Law
Relevant Work Experience: Four (4) Years, at list 2 years in insurance company
Additional skill: Excellent written and verbal communication, Basic computer skill ,Knowledge of all applicable laws, rules and regulations, High attention to detail, Strong negotiation  skills, Ability to prepare complex  legal  documents

Required Number: 2
Place of work: Addis Ababa

Position 2: Senior Legal Officer
Educational background: LLB in Law
Relevant Work Experience: Six (6) Years, at list 2 years in insurance company
Additional skill: Excellent written and verbal communication, Basic computer skill ,Knowledge of all applicable laws, rules and regulations, High attention to detail, Strong negotiation  skills, Ability to prepare complex  legal  documents

Place of work: Addis Ababa
Deadline: October 10, 2023


How to Apply:👈👈👈👈
Interested applicants, who full fill the aforementioned requirements can submit non-returnable application latter, CV & copies of testimonials accompanied by original documents in person within 10 (TEN) consecutive days from the date of this announcement in the Reporter news paper to:-
Lion insurance Company (S.C) Head office, located at Haile G/slassie Avenue, Lion Insurance Building HR& Facility Management Department 4th floor;Tell: – 0116187000/0116352285 –
Addis Ababa-Ethiopia.
https://t.me/lawsocieties
#share 👈👈👈👈👈👈👈
🌿🌿Baga ayyaana Irreechaa   nagayaan isin ga'e jechaa
Qnash Ayyaana gaarii akka isiniif ta'uuf hawwiisaa isa guddaadha.

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ሰ/መ/ቁጥር 241073 ሀምሌ 27 ቀን 2015 ዓ/ም #ውርስ_ህግ #ኑዛዜ
አመልካች፡- አቶ ዳዊት አበራ አቶ ዳዊት አበራ- ሞግዚት ፀሐይነሽ ተሾመ 
ተጠሪ፡- ወ/ሮ አለምነሽ ከፈለኝ-
በሁኔታ ላይ የተመሰረተ (conditional legaty) ወይም በገደብ የተደረገ ኑዛዜ

በ#ወራሽ የገቢ ማጣት እና በጤና ሁኔታ ችግር የተነሳ ኑዛዜ ሊሻሻል ወይም ቀሪ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ
#ፍ/ሕ/ቁጥር 879/1 እና #ፍ/ሕ/ቁጥር 872

በዚህ መዝገብ አመልካች የሟች ልጅ ሲሆኑ ተጠሪ ሟች ኋላ ላይ (ከአመልካች እናት በኋላ) ያገቧት ሚስት ናት። ሟች ለልጆቻቸው ንብረታቸውን እንዲወርሱ ኑዛዜ የተዉ ቢሆንም በኑዛዜው ተጠሪ በህይወት እስካሉ የመጠቀም መብት የተሰጣቸው በመሆኑ ኑዛዜው ተፈጻሚነት የሚያገኘው ተጠሪ ከሞቱ በኋላ ነው።
የአመልካች ጥያቄ ሟች ለተጠሪ በውርስ ሐብት በህይወት እስካሉ እንዲጠቀሙ ኑዛዜ ማድረጋቸው አመልካች ያለብኝን የአይምሮ ጤና እና የኑሮ ችግር ለመወጣት እንዳልችል የሚያደርገኝ ስለሆነ (በተጨማሪም ኑዛዜው በዝምታ የነቀለኝ ስለሆነ የሚል መከራከሪያም አቅርበዋል።) ኑዛዜው ሊፈርስ ይገባል የሚል ነው።

የ#ሰበር ችሎቱ የተያዘውን ጉዳይ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ እና የሐተታው ክፍል ከዚህ በታች ይነበባል

አመልካች ባለባቸው ጤና ችግር ምክንያት ስራዎችን በመስራት ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት የራሳቸውን ገቢ ማግኘት እና ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን መሸፈን የማይችሉ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ሟች ለክርክሩ መሰረት በሆነው ኑዛዜ ለተጠሪ በህይወት እስካሉ በውርስ ሀብቱ የመጠቀም መብት ባያስተላልፉ ኖሮ አመልካች የውርስ ድርሻውን በማግኘት ለኑሮ እና ለጤና አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን ለመሸፈን ያስችላቸዋል፡፡ የሟችን ፍላጎት ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ የአመልካች የከፋ ችግር እየታወቀ በኑዛዜ የተቀመጠው ገደብ መቀጠል አለበት የሚባል ከሆነ የአመልካችን በህይወት የመኖር መብት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ለሞራል ተቃራኒ ይሆናል፡፡ ተጠሪ በሰጡት መልስ የአመልካች ብቻ ሳይሆን የተጠሪም የጤና ችግር ከግምት ሊገባ ይገባል በሚል የሚከራከሩ ቢሆንም ተጠሪ ለክርክር መሰረት ከሆነው ንብረት ላይ 50% የሚስትነት ድርሻ ያላቸው ከመሆኑ አንጻር በኑዛዜው ላይ የተቀመጠው ገደብ አመልካችን በተመለከተ ብቻ ተፈጻሚነቱ ቢቀር በተጠሪ ላይ የሚደርስባቸው ጉዳት ከፍተኛ ወይም ለሞራል ተቃራኒ ነው ሊባል አይችልም፡፡

ሟች ለተጠሪ በህይወት እስካሉ የውርስ ድርሻቸውን የመጠቀም መብት በኑዛዜ አስተላልፈዋል፡፡ በኑዛዜው መሰረት የሟች ወራሾች ድርሻቸውን ማግኘት የሚችሉት ተጠሪ ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ ብቻ ነው፡፡ ይህም ሟች ለወራሾቻቸው ያረጉት ኑዛዜ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ (conditional legaty) ወይም በገደብ የተደረገ ኑዛዜ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኑዛዜ የተጠቀሰው ሁኔታ ወይም በወራሾች ላይ በኑዛዜ የተደረገው ገደብ እንዳልተደረገ ሊቆጠር የሚችለው ግዴታው የማይቻል ወይም ለህግ ወይም ለመልካም ጠባይ ወይም ለሞራል ተቃራኒ ሆኖ ሲገኝ መሆኑን በፍ/ሕ/ቁጥር 879/1 ስር ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በፍ/ሕ/ቁጥር 872 ስር ሟቹ በፊት ካደረገው ጋብቻ የተገኙ ተወላጆች ያሉት ከሆነ ለኋላኛው ባል ወይም ሚስት ጥቅም የተደረገ የኑዛዜ ቃል በዳኞች ሊቀነስ ወይም ሊሻር እንደሚችል ተመልከልቷል፡፡

እነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች ሟች ከቀድሞ ትዳር የተፈሩ ልጆች እያሉ ለኋላኛው ሚስት ወይም ባል የተደረገ ኑዛዜ ከቀድሞ ትዳር የተወለዱትን ልጆች ጥቅም የሚጎዳ ከሆነ በተወላጆቹ ጠያቂነት ዳኞች ኑዛዜውን ለማሻሻል ወይም ሙሉ ለሙሉ ቀሪ ሊያደርጉ እንደሚችሉ፤ በተለይም ኑዛዜው በግዴታ ላይ የተመሰረተ ከሆነ እና ግዴታው ለህግ፣ ለሞራል ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ ከሆነ በኑዛዜው የተመለከተው ገደብ ወይም ግዴታ በኑዛዜው እንዳልተጻፈ ይቆጠራል፡፡ በእርግጥ እነዚህ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ሲደረጉ በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም ኑዛዜ የተናዛዙን ፍላጎት መግለጫ እና ሟች ንብረቱን ለሚፈልገው ሰው የማስተላለፍበት አንዱ መንገድ በመሆኑ ኑዛዜው ሲቀነስ ወይም ሲሻሻል ወይም በኑዛዜ የተቀመጠው ገደብ እና ግዴታ ቀሪ ሲደረግ የተናዛዙን ፍላጎት እንዳይቃረን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በሌላ በኩል ኑዛዜው ላይ የተገለጸው ግዴታ ለመፈጸም የማይቻል ወይም ለህግ ወይም ለሞራል ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ መሆኑ በጥንቃቄ በዳኞች ተመርምሮ ግዴታው ሊፈጸም የማይችል ወይም ለህግ ወይም ለሞራል ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ ሆኖ ከተገኘ በኑዛዜ ላይ የተመለከተው ገደብ ወይም ግዴታ ቀሪ ሊሆን ይገባል፡፡
ሰራተኛን ያለማስጠንቂያ ስለ ማሰናበት ያልታተመ የሰበረ ውሳኔ