አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር አሰጣጥ

ታክስ ከፋዮችን ለመለየት እንዲቻል ሚኒስቴሩ ለታክስ ሕጎች ዓላማ ሲባል ለተመዘገበ ሰው “የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር” በሚል የሚታወቅ ቁጥር ይሰጣል:: ታክስ ከፋዩም የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን የታክስ ሕጎች በሚያዙት መሠረት መጠቀም አለበት፡፡

የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ስለመሰጠት

ሚኒስቴሩ፤ ለታክስ ሕጎች ዓላማ ሲባል ለታክስ ከፋይ አንድ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የሚሰጥ ሲሆን አንድ ታክስ ከፋይ ከአንድ የታክስ መለያ ቁጥር በላይ ሊኖረው አይችልም፡፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የሚሰጠው ምዝገባው በሚከናወንበት ጊዜ ይሆናል፡፡ በታክስ ከፋይነት የተመዘገበ ሰው የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳያወጣ እና የንግድ ሥራ ላይ ሳይሠማራ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፊኬት በመያዙ ብቻ የታክስ ግዴታ እንዲወጣ ሊጠየቅ አይችልም፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የጸና የንግድ ሥራ ፈቃድም ሆነ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፊኬት ባይኖረውም ማንኛውም ገቢ ያገኘ ሰው ታክስ የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡

ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ወይም የከተማ አስተዳደር በንግድ ሥራ ወይም ቤት በማከራየት ሥራ ላይ ተሠማርቶ ገቢ የሚያገኝ ሰው በእያንዳንዱ ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ተቀጽላ ያለው የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሊሰጠው ይችላል፡፡

የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት በተለያዩ ምክንያት ከጠፋና ታክስ ከፋዩ በባለሥልጣኑ በተዘጋጀ ቃለ መሀላ ፎርም ሞልቶ ያቀረበ እንደሆነ ነባሩን የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የያዘ የምስክር ወረቀት ታትሞ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡
የታክሰ ከፋዩ የታክስ መለያ ቁጥር በተለያዩ ምክንያቶች ከተበላሸና በጽሑፍ ካመለከተ የተበላሸውን መልሶ ነባሩን የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የያዘ የምስክር ወረቀት ታትሞ ይሰጠዋል፡
https://t.me/lawsocieties
AFD TOR Readvertizement .pdf
489.7 KB
Readvertisement of the Call for Consultancy‼️
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Entrust🔷ETC)
ለህግ ባለሙያው የፍቅር ደብዳቤ የተሰጠ መልስ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ውድ የህግ ባለሙያው፡
የፃፍክልኝን የፍቅር ደብዳቤ ከሽብር አዋጁ ባልተናነሰ ደምፍላት
ውስጥ ሆኜ አነበብኩት፡፡
በእውነቱ በወስላታነትና በስግብግብነት
ተነሳስተህ ደብዳቤውን በመፃፍህ ልቤን እንዳከብድብህና የፍቅር
ጥያቄህንም በብይን እንድዘጋው አስገድዶኛል፡፡
ደግሞም ባለፈው
ቅዳሜ ይህንን ውሳኔዬን አሳውቄሃለሁ፡፡ አሁን ድጋሜ ዳኝነት
የጠየቅክበት ምክንያት አልገባኝም፡፡ የቅን ልቦና አፍቃሪ (lover in
good faith) አይደለህም፡፡
በኔ ውሳኔ ተነስተህ ሴቶችን በሙሉ
አጠቃለህ መዝለፍህ hasty generalization ሆነብህ፡፡
ድሮም
ንግግር ከማያውቅ ወንድ የሚጠበቅ ነው፡፡ ቢሆንም ንግግርን
አለማወቅ ይቅርታ አያሰጥም (ignorance of speech is no
pardon)፡፡ ሲጀመር አለባበስህ ተማሪ እንደገነጣጠለው የጀስቲስ
ማቴሪያል የተዝረከረከ ነው፡፡ እንደ 'ፍርድ' ዓ/ነገር የረዘመ ቁመና
ቢኖርህም ልብህ ግን እንደ 'ትዕዛዝ' ያጠረ ነው፡፡ እንደ ግራቨን
ፅሁፍ የቀጨጩ ልም አይኖችህን ሳያቸው ያቅለሸልሹኛል፡፡
ካንተም ብሶ እንደ ዙፋን ችሎት ታካብዳለህ!? አመለካከትህ
ጭብጥ እንደሌለው መዝገብ የተምታታ ነው፡፡ ወሬህ
አይጨበጥም፡፡ እንደ ዳብል ራንቯ ዶክትሪን (double renvoi
doctrine) አንዴ እዚያ አንዴ እዚህ ትረግጣለህ፡፡ ልብህና
አንደበትህ እንደ አማርኛውና እንግሊዝኛው የህግ ቅጅ (version)
የተለያዩ ናቸው፡፡ ሀሣብህ እንደ ቀሽም ዐቃቤ-ህግ ጥያቄ እርባና
ቢስ ነው፡፡ "በቸልተኝነት የሚፈፀም አስገድዶ መድፈር ልፈፅምብሽ
ነበር" ያልከውን ፅሁፍህን ሳነበው ክርክሩን እንዳሸነፈ ጠበቃ
ብቻየን እንባዬ እስኪወርድ ሳቅሁ፡፡ ሞክረኸኝ በሆነ! ታስቦ
በሚፈፀም ከባድ የአካል ጉዳት ጥርስህን አርግፌህ አንድ ጥርስህ
በኤግዚቢትነት ተተክሎ ታዬው ነበር፡፡ ደግሞ የገረምከኝ "ላንቺ
ያለኝን ፍቅር ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ (beyond
reasonable doubt) ላስረዳሽ ሞክሬአለሁ ማለትህ ነው፡፡
ፅድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ አሉ! 'ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ'
የሚል ከንቱ ቅዠትህ ቀርቶ 'በበቂ ሁኔታ' (sufficient
evidence) ብታቀርብልኝ እንኳ አልገፋህም ነበር፡፡ ዳሩ ምን ዋጋ
አለው:: ፍቅርህን የማስረዳት ሸክሙ (burden of proof) ያንተ
ቢሆንም የምታቀርበው መከራከሪያ ሁሉ ባዶ የድምፅ ብክለት
(noise pollution) ሆነብኝ፡፡ በእርግጥ በፍቅርሽ ተማረክሁ
ያለኝን (prisoner of war (POW)) እንዲጎሳቆል የምወድ
አረመኔ አይደለሁም፡፡ ብታበሳጨኝም ታሳዝነኛለህ፡፡ ነገር ግን እንደ
ህገመንግስቱ አንቀፅ 39 ባዶ ተስፋ ልሰጥህም አልፈልግም፡፡
አንተና እኔ እንደ አገራችን ህግ (the law) እና አሰራር (the
practice) ፍፁም የተለያየን ሰዎች ነን፡፡ የምፈልገውን ልትሰጠኝ
አትችልም፡፡ ፍቅር ደግሞ ሰጥቶ መቀበል (quid pro quo
relationship) እንጅ የበጎ አድራጎት ስራ (pro bono service)
አይደለም፡፡ አንደ አስጠቂ ምስክር አልከኝ? ህ! አንተማ እንደ
መሀይም መርማሪ ፖሊስ ያንተን ሀሳብ መልሼ እንዳስተጋባልህ
ነበር የፈለከው፡፡ አያያዝህ እንደ crime control model
ያስጨንቃል፡፡ እያደረስክብኝ ያለው ስነ-ልቦናዊ ጫና (undue
influence) ምስኪኑን ሚራንዳ የሆንኩ ያህል እንዲሰማኝ
አድርጎኛል፡፡ ወዳጄ! እንኳን ፍቅር ውልም በነፃነት ሲሆን ነው
የሚፀናው፡፡ ግግም ብሎ ማፍቀር aquisitive prescription
የሚሰጥህ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል፡፡ ሽህ አመት ብታፈቅረኝም
እኔ ያንተ ልሆን አልችልም፡፡ በጊዜ ዘወር ብትል ይሻልሃል፡፡
ካለበለዚያ በነጭ ድሀ ላይ እንዳስፈረደ የፍርድ ባለገንዘብ
(judgment creditor) አይን አይን ስታይ መኖርህ ነው፡፡ ወደድኩ
ብለህ ስትንቀዋለል ባለቤት አልባ (res nullies) ሆነህ
እንዳትቀር ተጠንቀቅ፡፡ አካሄድህ ሁሉ ለዩኒቨርስቲ ሴት
አይመጥንም፡፡ ልብህን ወደ ሀይስኩል ችኮች ሪማንድ (remand)
ብታደርገው የተሻለ ነው፡፡ ለኔ የምትቀባጥረውን ፍቅር ግን void
abinitio ብየዋለሁ፡፡ ወዳጄ! አንድ ነገር ልንገርህ! እንደ
intrinsic element በቂጥ በቂጤ አትከተለኝ፡፡ በቃ አታናግረኝ፡፡
ከኔ ጋር ለመነጋገር locus standi እንደሌለህ ልታውቅ
ይገባሃል፡፡ አድብቶ መንከስ (wait and bite) አልወድም፡፡
ቀድሜ ማስጠንቀቂያ (notice) ልስጥህ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ባጠገቤ
ብትደርስ እንደ አገራችን ፌደራሊዝም (centrifugal
federalism) እንደምበታትንህ እወቅ፡፡ ላንተ እበቃሃለሁ፡፡
የሶስተኛ ወገን ጣልቃገብነት (third party intervention)
አያስፈልገኝም፡፡ ዋ!!! ይሄ ውሳኔ የመጨረሻ ነው፡፡ ይግባኝ
የለውም፡፡ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ!
የማይነበብ ፊርማ አለበት፡፡
(ደሱ ፍቅርኤል)
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ስሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 228002 በሰጠ ውሳኔ መሰረት መንግስት/ቀበሌ ቤትን ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት አያጎናጽፍም አንድን ቤት ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍ በመሆኑ እንዲሁም ቤቱ የመንግስት መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌሉበትሁኔታ በተቋሙ የመረጃ ስርአት ቅጽ 008 በቀበሌ ቤትነት መመዝገቡ ብቻ ቤቱ በመንግስትየተወረሰ የቀበሌ /የመንግስት ቤት ነው ሊያስብለው አይችልም።
በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለረጅም ግዜ በመንግስት እጅ የነበረ ቤትን በሚመለከት በስህተት አላግባብ ያለህጋዊ ምክንያት ተሰጥቷል የተባለው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመከነና በመንግሰት ባለቤትነት የሚታወቅ ስለመሆኑ በተገለጸበት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት መንግስት የወረሰው መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌለበት ቤቱን የመንግስት ንብረት አያሰኘውም።
To all students and recent grads!!

UNDP Internship Program 2023 (Paid Internships)

Internships at UNDP are a great opportunity for students and recent graduates to acquire direct exposure to UNDP's work.
Locations: UNDP Country Offices, at Regional Hubs or at Headquarters in New York.

Details:

Host Organization: UN Development Program
Program Locations: UNDP Country Offices
Internship Type: Full-time/Part-time (Paid)
Eligible Countries: All
Deadline: Varies

Fore more info: https://bit.ly/3PLgmtA

hashtag#work
hashtag#allafrican
hashtag#opportunity hashtag#students hashtag#internship hashtag#phd hashtag#internships hashtag#unitednations hashtag#undp hashtag#talent hashtag#youth hashtag#internationalaffairs hashtag#jobs hashtag#paidinternship hashtag#development                                                                           Join our community👇
           For More 
https://t.me/allafrican
https://t.me/allafrican
https://t.me/allafrican
በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ  የአፃፃፍ ፎርሙ👆👆👆👆👆👆
በፍ/ሕ/ቁ 880 መሠረት ሦስት አይነት የኑዛዜ ፎርሞች አለ እንዚህም:
👉1-በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ 2-በተናዛዥ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ
3-በቃል የሚደረግ ኑዛዜ
የመጀመሪያው የኑዛዜ አይነት በግልፅ የሚደረገው ሲሆን  ይህም ኑዛዜው ተናዛዡ እየተናገረ ማናቸውም ሌላ ሰው ወይም ተናዛዡ ራሱ የሚፅፈው ነው ።
👉በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ በተናዛዡና በአራት ምሰክሮች ፊት ካልተነነበበና ይህም ሥርዓት መፈፀሙን የተፃፈበትን ቀን የሚያመላክት መሆን አለበት ይህን ፎርማሊቲ ተከትሎ ካልተፃፈ ፈራሽ የሚደረግ ኑዛዜ ይሆናል።
👉እንዲሁም በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ ላይ ተናዛዡና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ወዲያውኑ ፊርማቸውን ወይም ያውራ ጣት ምልክታቸውን ካላደረጉበት በቀር ፈራሽ ነው።
👉በግልፅ ለሚደረግ ኑዛዜ ከምስክሮች መካከል አንዱ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሆኖ ኑዛዜውም የተደረገው ይህ ዳኛ ወይም ይህ ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሥራቸውን በሚያካሂዱበት ክፍል ውስጥ የሆነ እንደ ሆነ ለኑዛዜው ዋጋ ለማግኘት ሁለት ምስክሮች ብቻ በቂ ናቸው።
👉በግልፅ የሚደረገው ኑዛዜ ምስክሮች አካለመጠን ያደረሱና በፍርድ ወይም በሕግ ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው።
👉ምስክሮቹ ኑዛዜው የተፃፈበትን ቋንቋ ለማወቅና የተፃፈውን ለመስማት ወይዬይ ለማንበብ ራሳቸው ችሎታ ያላቸው መሆን አለባቸው።እነዚህ ትዕዛዞች የማይፈፀሙ ከሆነ ኑዛዜው ፈራሽ ነው።ከፍ/ሕ/ቁ880-883!
ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ሔኖክ ታየ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
የከተማ መሬት ሕግ በአዲስ አበባ - ክፍል አንድ - የሕግ መጽሐፍ

የመጽሐፉ ጸሐፊ ጠበቃና የሕግ አማካሪ ዳዊት መንግሥቴ ምንተስኖት ሲሆን መጽሐፉ የሚያተኩረው ስለ መሬት ሕግ ጠቅላላ ጽንሰ ሃሳባዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ስለ እስከዛሬው የአገራችን የመሬት ስሪት ሁኔታ፣ ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ስላላቸው የመዲናችን ዋና ዋና ጉዳዮች ለምሳሌ የመዲናችንን የቆዳ ስፋት፣ የወሰን አከላለል እና ሕጋዊ አቋም የሚያብራሩ እንዲሁም ከመዲናችን ምስረታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን የመሬት ስሪት ሁኔታ የሚያስረዱ ነጥቦችን አሁን ለንባብ በበቃው የመጀመሪያው ክፍል ይዟል፡፡

ስለሆነም ይህንኑ የምርምር መጽሐፉን እንድታነቡለት ጸሐፊው ይጋብዛል።

https://www.abyssinialaw.com/blog/a-book-entitled-urban-land-law-in-addis-ababa-has-been-published
★ አንበሳ ኢንሹራንስ አዲስ የስራ ማስታወቂያ

Deadline: September 28, 2023

Lion Insurance Company invites interested and qualified candidates for the following positions.

Position 1: Legal Officer III

Position 2: Senior Legal Officer

Place of work: Addis Ababa

How to Apply Online??


https://dailyjobsethiopia.com/2023/09/19/lion-insurance-new-vacancy/
አስቸኳይ ማሳሰቢያ
ለትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ እና የአቻ ግመታ አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ!
የኢፊዲሪ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል እና ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ፡፡ ከነዚህም ተግባራት መካከል የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ እና የአቻ ግመታ አገልግሎትን ጊዜና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ አማካኝነት https://neta.gov.et መተግበሪያን በመጠቀም ከመስከረም 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎቱን ማግኝት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በፍትሀብሄር ክርክር የሚቀርብ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ

ሰዎች በእለት ተእለት በሚኖራቸው መስተጋብር የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በራሳቸው መፍታት ሳይችሉ ሲቀሩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረባቸው በየእለቱ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ፍርድ ቤት ሲቀርብም ከክስ አቀራረብ ጀምሮ የክርክር ሂደቱ የሚመራበት ሥነ ሥርአት አለው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ በሚያቀርብበት ወቅት ሊቀርብ የሚችልን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምንነት እንዲሁም የሚቀርብበት ጊዜና ሁኔታ እንመለከታለን።

የመጀመሪያ ደርጃ መቃወሚያ ምንነት

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ወደ ዋናው ክርክር መግባት ሳያስፈልግ የቀረበው ክስ ውድቅ የሚሆንበትን ምክንያት በመግለፅ ክሱ ውድቅ እንዲሆን በማንኛውም ተከራካሪ ወገን የሚቀርብ መቃወሚያ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(1) መረዳት ይቻላል።

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምክንያቶች

አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ እንዲያቀርብ በታዘዘ ጊዜ በቀረበበትን ክስ ላይ ከሚያቀርባቸው ክርክሮች መካከል አንዱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነው። የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(2) የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር አመልክቷል፡፡ ይኸውም፡-

• ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ነገሩን ወይም የቀረበውን ክስ ለመስማት ስልጣን የሌላው ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት ቀርቦ በክርክር ላይ ያለ ከሆነ
• አንደኛው ተከራካሪ ወገን በነገሩ የማያገባው መሆኑን በመግለፅ በጉዳዩ ገብቶ መከራከር አይገባውም የሚባል ከሆነ
• ክሱ በይርጋ የታገደ ከሆነ
• ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ ከሆነ
ይህን በመግለፅ መቃወሚያ ሊቀርብ ይችላል።

ለቀረበበት ክስ መልስ የሚሰጥ ማንኛውም ወገን ከላይ ከተጠቀሱት መቃወሚያዎች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን በተቻለ መጠን በቶሎ ተጠቃለው መቅረብ አለባቸው። አንድ ተከራካሪ መቅረብ ከሚገባው መቃወሚያ ውስጥ አንዱን የተወ እንደሆነ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ካልሆነ በስተቀር መቃወሚያውን ለማቅረብ እንዳልፈለገ እንደሚቆጠር በድንጋጌው ንኡስ ቁጥር 3 ላይ በግልፅ ተመልክቶ ይገኛል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔና ውጤቱ

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ያቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ በቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ማስረጃ እንዲቀርብለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(1) መሰረት ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተገቢና በቂ በሆነ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ በመሆኑ ወይም ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ በመሆኑ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ በመሆኑ እንደሆነ የቀረበውን ክስ በመዝጋት ባለጉዳዮችን ያሰናብታል። የቀረበው መቃወሚያ ከእነዚህ ውጭ ሆኖ መቃወሚያው ተገቢ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ መዝገቡን በመዝጋት ተገቢ መስሎ የታየውን ትእዛዝ ይሰጣል።

ሌላው የቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት አግኝቶ መዝገቡ የተዘጋ እንደሆነ ከሳሽ ክሱን አሻሽሎ በዚያው ጉዳይ መጀመሪያ ክስ ላቀረበበት ፍርድ ቤትም ይሁን ለሌላ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሱን እንደገና የማቅረብ መብቱ የተረጋገጠ ሲሆን ፍርድ ቤቱም መዝገቡን በሚዘጋበት ወቅት ከሳሽ እንደገና ክስ የማቅረብ መብት እንዳለው በትእዛዙ ላይ መግለፅ እንደሚችል በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(3) ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ መዝገቡን የዘጋው ‘ፍርድ ቤቱ ነገሩን የማየት ስልጣን የለውም’ በሚል መቃወሚያ መሰረት ሲሆን ከሳሽ ከከፈለው የዳኝነት ገንዘብ ላይ የሚቀነሰው ተቀንሶ የተረፈው ገንዘብ እንደሚመለስለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(4) ላይ በግልፅ ተደንግጓል።

በአጠቃላይ የፍትሐብሔር ክስ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ወደ ዋናው ክርክር ከመግባቱ በፊት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244 ሥረ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ባሉ ጊዜ ይህንኑ በመጥቀስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ይህም ወዲያውኑ መቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
Job Vacancy Notice

Position: Legal Assistant

Location: Bole bulbula, Addis ababa

Compensation: 5,000 birr per month

Job Type: Full-time

Tamiru yacob attorney at law is seeking a dedicated and motivated individual to join our legal team as a Legal Assistant. This is an excellent opportunity for individuals who are looking to start their career in the legal field with no prior experience required. We are committed to providing training and mentorship to help you grow in your role.

Responsibilities:

- Assist attorneys in legal research and document preparation.
- Organize and maintain legal files, documents, and records.
- Draft and proofread legal documents, including contracts, pleadings, and correspondence.

**Background
              : LLB from recognisable university
             :fluency in the English and amharic languages  
             : basic computer and typing skills
             : No previous working experience  required
Interested and qualified applicants can apply through tamiruyac@gmail.com
P.S. we do not accept any applications besides through emails so apply accordingly
 
Deadline:-  september 27, 2023
Position 1: Legal Officer III
Educational back ground: LLB in Law
Relevant Work Experience: Four (4) Years
Additional skill: Excellent written and verbal communication, Basic computer skill ,Knowledge of all applicable laws, rules and regulations, High attention to detail, Strong negotiation  skills, Ability to prepare complex  legal  documents
Required Number: 2
Place of work: Addis Ababa


Position 2: Senior Legal Officer
Educational back ground: LLB in Law
Relevant Work Experience: Six (6) Years
Additional skill: Excellent written and verbal communication, Basic computer skill ,Knowledge of all applicable laws, rules and regulations, High attention to detail, Strong negotiation  skills, Ability to prepare complex  legal  documents
Place of work: Addis Ababa
Deadline: September 28, 2023


How to Apply:
Interested applicants, who full fill the aforementioned requirements can submit non-returnable application latter, CV & copies of testimonials accompanied by original documents in person within 10 (TEN) consecutive days from the date of this announcement in the Reporter news paper to:-
Lion insurance Company (S.C) Head office, located at Haile G/slassie Avenue, Lion Insurance Building HR& Facility Management Department 4th floor; Tell: – 0116187000/0116352285 –
Addis Ababa-Ethiopia.

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
The Addis Ababa University School of Law is Celebrating its 60th Anniversary. Congratulations for reaching this Milestone ! I will never forget how excited i was when i joined the School as Lecturer of Law in 2010, partly it was because of the impeccable track record of the School.