አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
===============================
አዲስ አበባ 25/11/2015ዓ.ም(ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን አስመልክቶ ለንግዱ ማህበረሰብ፣ ለምሁራን፣ ለሚዲያ ባለሙያዎችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጠበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ኢትዮጵያ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ለመግባት የተቃረበችበት ወቅት በመሆኑ ሁሉም የንግድ ማህበረሰብና ምሁራን እንዲመክሩበትና አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ታልሞ መሆኑን የሚኒስቴር መስራ ቤቱ የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ምንነት፣ ለተግባራዊነቱ ከማን ምን ይጠበቃል የሚሉትና ቀጣናዊ የንግድ ትስስር ምንነት የስልጠናው ይዘቶች ናቸው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን:-
Email: fdremotri@gmail.com
fdremotri@motri.gov.et

For trade license : www.etrade.gov.et
website: www.motri.gov.et
ሰ.መ.ቁ 226490 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም

የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት የተሰጠው ሰው የመብት ጥያቄ ሲያቀርብ ሌላኛው ወራሽ የመውረስ መብት እንደሌለው ክርክር ለማቅረብ በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃውን ማሰረዝ አስፈላጊ አይደለም። ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ የተሰጠው ሰው የውርስ ድርሻውን ለማግኘት ባቀረበው ክስ ላይ የሟች ልጅ አይደለም ብሎ ለመቃወም በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃው እንዲሰረዝ አቤቱታ አቅርቦ ማሰረዝ አይጠበቅበትም። ወራሽነትን በማረጋግጥ የሚሰጥ የወራሽነት ማስረጃ በአመልካች ብቻ የቀረበውን የአንድ ወገን ማስረጃ በመቀበል የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory judgment) ለመክሰስ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን አሳይቶ የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ ለማቅረብ በማስረጃነት የሚቀርብ፤ በማንኛውም ተዓማኒነት እና ክብደት ባለው ማስረጃ ሊስተባበል የሚችል ማስረጃ በመሆኑ ማስረጃው በተሰጠበት መዝገብ ላይ መብት ወይንም ጥቅሜን ይነካል በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበት አይደለም።
Join 🛑👇
#ethiolawtips
contract farming directive .pdf
1.2 MB
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

በውልና በኢንቨስትመንት እርሻ የለማ ምርት የግብይት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 929 /2015

በውልና በኢንቨስትመንት እርሻ የለማ የሰብል ምርት የግብይት አፈጻጸም

መመሪያ ቁጥር ቁጥር 929 /2015

ሙስና በኢንቨስትመንት እርሻ የለማ የሰብል ምርት የግብይት አሰራር ስርዓት በመዘርጋት የአምራቹን እና የአስመራቹን መብቶች እና ጥቅሞችን ማስከበር በማስፈለጉ በል እና ኢንቨስትመንት እርሻ የተመረቱ ምሮቶች ግብይት ስርዓት ወስጥ የታዩ ህግ ወጥ ድርጊቶችን እና የቀርብ የተዛባ የምርት መረጃዎችን / በመከላከል ፍትሃዊና በዉድድር ላይ የተመሰረት ግብይት ስርዓትን በማሳለጥ የጠጪ ምርቶች ለ በ በማቅረብ የገቢ ግኝትን ጎቤ ማሳደግ በማስፈለጉ

የጥራጥሬ ምርቶች ግብይት ደንብ ቁጥር 377/20e እንቀጽ 21 እና የሰሊጥ እና ነጭ ቦሎቄ ግብይት ደንብ ቁጥር 17520 አንቀጽ 27 መሰረት የንግድ እና ጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይህንን በመሪያ አውጥቷል፡፡

1. አጭር ርዕስ

ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች

ይህ መመሪያ በውልና በኢንቨስትመንት እርሻ የለማ የሰብል ምርት ግብይት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር ቁጥር 929 /2015 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
..ዜና መግለጫ.............................................................

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2016 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡
*****
የፌዴራል
ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ እና በሕግ በተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የሚቀርቡ ጉዳዮችን በማስተናገድ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠበቁ ሰላም እና ስርዓት እንዲከበር የማድረግ ተግባራትን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በዚህ መሰረት በ2015 በጀት ዓመት በነበረዉ የመዛግብት አፈጻጻም አንጻር ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች በአጠቃላይ 213,116 መዛግብት ቀርበዋል። ከእነዚህም ዉስጥ ለ184,467 (86.56%) መዛግብት እልባት መስጠት የተቻለ ሲሆን 28,675 (13.44%) መዛግብት ደግሞ ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2014 በጀት ዓመት ለፌ/ፍ/ቤቶች የቀረቡት 209,317 መዛግብት ሲሆኑ ዕልባት ያገኙት ደግሞ 176,767 ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት መዛግብት በ2014 በጀት ዓመት ከቀረቡት በ3,799 (1.8%) ከፍ ያሉ ሲሆን በተመሳሳይ ዕልባት ያገኙትም በ7,670 (4.3%) መዛግብት ከፍ ያሉ ናቸው፡፡

የፍርድ ቤቶቹ አፈጻጸም በተናጠል ሲታይ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት 26,185 መዛግብት ቀርበው ለ19,201 ዕልባት የተሰጠ ሲሆን 6,984 መዛግብት ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ በተመሳሳይ በ2015 በጀት ዓመት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የመዛግብት ብዛት 33,721 ሲሆን 26,301 መዛግብት ዕልባት አግኝተዋል፡፡ ወደ 2016 የተሻገሩት መዛግብት ብዛትም 7,420 ሆኗል፡፡ እንዲሁም ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት 153,210 መዛግብት ሲሆኑ 138,965 ዕልባት በማግኘታቸው 14,245 ወደ 2016 በጀት ዓመት ተላልፈዋል፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጁ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 38 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የስራ ጊዜ የተደነገገ ሲሆን በዚህም ፍርድ ቤቶቹ ከነሐሴ1 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ እና በዚህ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤቶች አስቸካይ ጉዳዮች ሊያስተናገዱ እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ በዚሁ መሰረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ የሚሆኑ ሲሆን ፍርድ ቤቶቹ በዚህ በከፊል ዝግ በሚሆኑበት ጊዜ አሰቸኳይ የሆኑ ጉዳዮችን በተረኛ ችሎት ላይ በሚመደቡ ዳኞች የሚያስተናግዱ ይሆናል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ቀናት ውስጥ ዳኞች በፈቃደኝነት የበሰሉ የምርመራ መዝገቦችን በመመርመር የተለያዩ የዳኝነት ተግባራትን በተለይም ፍርድ እና ውሳኔዎችን በመሥራት የሚያሳልፉ ይሆናል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚከፈቱበት ወቅት በክረምት የዳኞች እረፍት ጊዜያት እልባት የተሰጠባቸዉ መዛግብቶች ከጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለባለጉዳዮች በግልጽ ችሎት የሚገለጹ ይሆናል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በ2015 በነበረው አፈጻጻም ላይ ለተገኘው ውጤት ዳኞች፣ የጉባኤ ተሻሚዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ለነበራቸው ትጋት ምስጋና እያቀረቡ በቀጣይ በ2016 ለሚሰጠው የዳኝነት አግልግሎት በቂ ዝግጅት በማድረግ ፍርድ ቤቶቹ የተጣለባቸውን ሕገ መንግስታዊ እና ሕጋዊ ኃላፊነቶች በላቀ ውጤታማነት ለማከናወን በጋራ እንስራ ለማለት ይወዳሉ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
Ale_Hig is a law society's channel who provides alternative legal Education (ALE), such as free legal consulting, different laws, proclamations, directives, regulations, lawsuits, contract forms, articles, cassation decisions and other legal documents. We have a YouTube channel 👇👇👇 https://www.youtube.com/@Lawsocieties where you can find all kinds of laws and experts. We also offers a telegram 👇👇👇 https://t.me/lawsocieties and an email address lawsocieties@gmail.com for contacting us. we believes that basic legal information knowledge is key and important for everyone. Subscribe and follow us to learn more about the law. All in one, for all.
It's great to see a platform like Ale_Hig providing free legal services and information. Having access to legal resources is crucial for individuals. Make sure to check out their YouTube https://www.youtube.com/@Lawsocieties channel and follow them https://t.me/lawsocieties for updates in the law!
የዓይነት ጥቅሞች

ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብርን በተመለከተ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 410/2009 መሰረት በዓይነት ለተቀጣሪው የሚሰጥ ጥቅማጥቅም ዋጋ የሚሰላበትና የሚወሰነው እንደሚከተለው ነው፡-

የዓይነት ጥቅሞችን በተመለከተ ቀጣሪ ለተቀጣሪ የሚሰጣቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጥቅሞች የዓይነት ጥቅሞች ናቸው፡-

 ከዕዳ ነጻ የመደረግ፤
 የቤተሰብ አገልግሎት ሠራተኞች፤
 የመኖሪያ ቤት፤
 የቅናሽ ወለድ ብድር፤
 የምግብ ወይም የመጠጥ አገልግሎት፤
 የግል ወጪዎች፤
 የንብረት ወይም አገልግሎቶች፤
 የሰራተኞች የአክሲዮን ዕቅድ፤
 የተሽከርካሪ እና
 ሌላ ዓይነት ጥቅም፡፡

 አንድ ተቀጣሪ ጥቅም ያገኘ እንደሆነ፣ ይህን ጥቅም ለማግኘት ያወጣው ወጪ የቅጥር ገቢን ለማግኘት ያደርገው የነበረ ወጪ እስከሆነ ድረስ እንደ ዓይነት ጥቅም አይቆጠርም፡፡

 ማንኛውም ጥቅም የዓይነት ጥቅም መሆኑን እና የዓይነት ጥቅምን ዋጋ ለመወሰን ጥቅሙን በማስተላለፍ ረገድ የተጣለ ገደብ መኖሩ እና ጥቅሙ በሌላ ሁኔታ ወደገንዘብ መለወጥ አለመቻሉ ከግምት ውስጥ አይገባም፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
Ethiopia-Digital-ID-proc.1284-2023.pdf
1.6 MB
Ethiopian Digital Identification Proclamation 1284/2015

አዋጅ ቁጥር 1284/2015 የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ
ኤግዚቢት ምንድን ነው?
ኤግዚቢት ምንድን ነው?
በተለያዩ አጋጣሚዎች ኤግዚሂቢት ተያዘ፣ ኤግዚቢት ተመለሰ፣ ቀረበ ወዘተ ሲባል ሰምተዋል ብለን እናስባለን። ለመሆኑ ኤግዚቢት ምንድን ነው?

በክርክር ሂደት የአንድን አከራካሪ ፍሬ-ነገር መኖር ወይም አለመኖር ማረጋገጥ የሚቻለዉ ማስረጃ በማቅረብ ነዉ፡፡ ማስረጃ በምስክሮች፣ በሰነድ ወይም በተለይ በወንጀል ክርክር በኤግዚቢት መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ በዚህ ፅሁፍ የኤግዚቢትን ምንነት እና ኤግዚቢትን በሚመለከት የሚሰጡ ውሳኔዎችን በአጭሩ እንደመለከታለን፡፡

የኤግዚቢት ምንነት

ኤግዚቢት በወንጀል ምርመራ ወይም ክስ ሂደት አንድን ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ ማስረጃ ተደርጎ የሚቀርብ ተጨባጭነት ያለው ንብረት ወይም ቁስ (real item) ነው፡፡ አንድ ቁስ ኤግዚቢት ሊሆን የሚችለው ተፈፀመ ከተባለው የወንጀል ድርጊት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ አሣማኝ ግንኙነት ያለው ሲሆን ነው፡፡ ኤግዚቢት ወንጀሉ የተፈፀመበት፣ ለመፈፀሚያነት የዋለ እና ሌላ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያለውን ቁስ ሁሉ ያካትታል፡፡

ኤግዚቢትን በተመለከተ የሚሰጡ ውሳኔዎች
ዐቃቤ ህግ ኤግዚቢቱ የማስረጃነት ጠቀሜታ ያለው ሆኖ ካገኘው ክስ ሲመሰርት የኤግዚቢቱን ምንነት እና ያለበትን ሁኔታ በማስረጃ ዝርዝር በመጠቀስ ሊጠቀምበት ወይም ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ኤግዚቢት በዚህ መልኩ በማስረጃነት የሚቀርበው ፍርድ ቤት ተመልክቶት በክሱ የተካተተው የወንጀል ፍሬ ነገር መፈፀሙን ግንዛቤ እንዲወስድ ለማስቻል ሲሆን ፍርድ ቤቱ በዋናው ጉዳዩ ላይ ውሳኔ ሲሰጥ አብሮ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል፡፡ በአንፃሩ ዐቃቤ ህግ የቀረበውን ኤግዚቢት የማስረጃነት ጠቀሜታ ካላገኘበት ወይም ሌላ በቂ ማስረጃ ካለው እንደ ኢግዚቢቱ አይነት ንብረቱ ለባለቤቱ እንዲመለስ፣ በህግ መሰረት ለመንግስት ገቢ መሆን ያለበት ከሆነ ገቢ እንዲሆን ወይም አደገኛ በመሆኑ መወገድ ያለበት ከሆነ እንዲወገድ ሊወስን ይችላል፡፡

ፍርድ ቤት ኤግዚቢት በማስረጃነት ተጠቅሶ ከቀረበለት ኤግዚቢቱ ለወንጀል ተግባር ሊያገለግል የሚችል ወይም ያገለገለ ወይም የወንጀል ተግባር ፍሬ ከሆነ እና የህዝብ ሰላም፣ ጤና እና መልካም ጠባይን የሚጎዳ ሲሆን እንዲወረስ የመወሰን ስልጣን አለው፡፡ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 100(1) መሰረት ወንጀል ለመፈፀም ማነሳሻ፣ ለተፈፀመ ወንጀል ዋጋ የተሰጠ ወይም ሊሰጥ የታቀደ ጥቅም ሁሉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ በወንጀል ህግ አንቀፅ 98(2) ላይ እንደተመለከተው ተከሳሹ ጥፋተኛ ከተባለ ወንጀለኛው በወንጀል ተግባሩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ያገኘውን ንብረት ሁሉ እንዲወረስ ሊወሰን ይችላል፡፡ በአንፃሩ ንብረቱ የግለሰብ ንብረት ከሆነ እና ንብረቱ አደገኛነት የሌለው ወይም በህግ ያልተከለከለ የንፁ ሶስተኛ ወገኖች ንብረት ከሆነ ለባለቤቱ እንደሚመለስ ከወንጀል ህጉ አንቀፅ 140(2) መረዳት ይቻላል፡፡ ሆኖም ባለንብረቱ እስከ 5 አመት ካልተገኘ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ንብረቱ በባህሪው ጎጂ ከሆነ ማለትም እንደ አደገኛ እፅ፣ የተበላሹ መድሀኒቶች እና የመሳሰሉት ከሆነ እንዲወገድ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

በሌላ መልኩ የሚነሳው እግዚቢት እና የወንጀል ፍሬ መካከል ያለው ግንኘነት ነው፡፡ እላይ በተገለፀው አግባብ አንድ ማስረጃ ኤግዚቢትም የወንጀል ፍሬም ሊሆን ይችላል፡፡ አግዚቢት የወንጀል ፍሬ በሚሆንበት ጊዜም በህግ የሚወረስ ሲሆን ይህንኑ እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ህጋዊ ለማስመሰል መሞከር በተጨማሪ ወንጀል ያስጠይቃል፡፡ በዚህም በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኘነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀፅ 35 መሰረት ንብረቱ ወይም ገንዘቡ ከወንጀል የተገኘ ሲሆን ህጋዊ ለማስመሰል ከተሞከረ ለወንጀሉ መፈፀሚያ የዋለ ንብረት፣ በንብረቱ ተለውጦ የተገኘው ፍሬ፣ ንብረቱ ተቀላቅሎት የተገኘው ወንጀለኛው ንብረት እንደሚወረስ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የሙስና ወንጀልን በተመለከተ በተሻሻለው ልዩ የፀረ ሙስና ሥነ ሥርአትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀፅ 29 መሰረት በሙስና ወንጀሉ ወንጀለኛው ያገኘው ንብረት እና በዚሁ ንብረት ያፈራው ንብረት እንዲሁም በመንግስት፣ በህዝባዊ ድርጅት እና የመንግስት የልማት ድርጀት ጥቅም ላይ ላደረሰው ጉዳት ማካካሻ የሚሆን የወንጀለኛው ንብረት ሊወረስ ይችላል፡፡

በጥቅሉ ኤግዚቢት ከአንድ ከተፈፀመ ወንጀል ጋር ግንኙነት ያለው እና ወንጀሉ ስለመፈፀሙ የሚያሳይ ተጨባጭነት ያለው ንብረት ወይም ቁስ ሲሆን ይህንኑ ንብረት በተመለከተ የሚሰጡ ውሳኔዎችም እንደየ ጉዳዩ አይነት ንብረቱ በመንግስት እንዲወረስ፣ ለባለቤቱ እንዲመለስ ወይም እንዲወገድ ሊወሰን ይችላል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
አለመቻሉ ከግምት ውስጥ አይገባም፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
በፍትሀብሄር ክርክር የሚቀርብ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ

ሰዎች በእለት ተእለት በሚኖራቸው መስተጋብር የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በራሳቸው መፍታት ሳይችሉ ሲቀሩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረባቸው በየእለቱ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ፍርድ ቤት ሲቀርብም ከክስ አቀራረብ ጀምሮ የክርክር ሂደቱ የሚመራበት ሥነ ሥርአት አለው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ በሚያቀርብበት ወቅት ሊቀርብ የሚችልን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምንነት እንዲሁም የሚቀርብበት ጊዜና ሁኔታ እንመለከታለን።

የመጀመሪያ ደርጃ መቃወሚያ ምንነት

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ወደ ዋናው ክርክር መግባት ሳያስፈልግ የቀረበው ክስ ውድቅ የሚሆንበትን ምክንያት በመግለፅ ክሱ ውድቅ እንዲሆን በማንኛውም ተከራካሪ ወገን የሚቀርብ መቃወሚያ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(1) መረዳት ይቻላል።

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምክንያቶች

አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ እንዲያቀርብ በታዘዘ ጊዜ በቀረበበትን ክስ ላይ ከሚያቀርባቸው ክርክሮች መካከል አንዱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነው። የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(2) የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር አመልክቷል፡፡ ይኸውም፡-

• ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ነገሩን ወይም የቀረበውን ክስ ለመስማት ስልጣን የሌላው ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት ቀርቦ በክርክር ላይ ያለ ከሆነ
• አንደኛው ተከራካሪ ወገን በነገሩ የማያገባው መሆኑን በመግለፅ በጉዳዩ ገብቶ መከራከር አይገባውም የሚባል ከሆነ
• ክሱ በይርጋ የታገደ ከሆነ
• ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ ከሆነ
ይህን በመግለፅ መቃወሚያ ሊቀርብ ይችላል።

ለቀረበበት ክስ መልስ የሚሰጥ ማንኛውም ወገን ከላይ ከተጠቀሱት መቃወሚያዎች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን በተቻለ መጠን በቶሎ ተጠቃለው መቅረብ አለባቸው። አንድ ተከራካሪ መቅረብ ከሚገባው መቃወሚያ ውስጥ አንዱን የተወ እንደሆነ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ካልሆነ በስተቀር መቃወሚያውን ለማቅረብ እንዳልፈለገ እንደሚቆጠር በድንጋጌው ንኡስ ቁጥር 3 ላይ በግልፅ ተመልክቶ ይገኛል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔና ውጤቱ

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ያቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ በቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ማስረጃ እንዲቀርብለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(1) መሰረት ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተገቢና በቂ በሆነ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ በመሆኑ ወይም ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ በመሆኑ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ በመሆኑ እንደሆነ የቀረበውን ክስ በመዝጋት ባለጉዳዮችን ያሰናብታል። የቀረበው መቃወሚያ ከእነዚህ ውጭ ሆኖ መቃወሚያው ተገቢ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ መዝገቡን በመዝጋት ተገቢ መስሎ የታየውን ትእዛዝ ይሰጣል።

ሌላው የቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት አግኝቶ መዝገቡ የተዘጋ እንደሆነ ከሳሽ ክሱን አሻሽሎ በዚያው ጉዳይ መጀመሪያ ክስ ላቀረበበት ፍርድ ቤትም ይሁን ለሌላ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሱን እንደገና የማቅረብ መብቱ የተረጋገጠ ሲሆን ፍርድ ቤቱም መዝገቡን በሚዘጋበት ወቅት ከሳሽ እንደገና ክስ የማቅረብ መብት እንዳለው በትእዛዙ ላይ መግለፅ እንደሚችል በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(3) ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ መዝገቡን የዘጋው ‘ፍርድ ቤቱ ነገሩን የማየት ስልጣን የለውም’ በሚል መቃወሚያ መሰረት ሲሆን ከሳሽ ከከፈለው የዳኝነት ገንዘብ ላይ የሚቀነሰው ተቀንሶ የተረፈው ገንዘብ እንደሚመለስለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(4) ላይ በግልፅ ተደንግጓል።

በአጠቃላይ የፍትሐብሔር ክስ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ወደ ዋናው ክርክር ከመግባቱ በፊት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244 ሥረ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ባሉ ጊዜ ይህንኑ በመጥቀስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ይህም ወዲያውኑ መቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
በድሬዳዋ ሊሰርቅ የሰው ቤት ገብቶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ውስኪ ሲጠጣ የተገኘው ሌባ በ3 አመት እስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታወቀ!

ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ ነዋሪነቱ በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን ሀምሌ 9 ቀን 2015ዓ.ም ከቀኑ 8ሰአት ገደማ በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ጎሮ 32 መንገድ ከሚገኘው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በር ሰብሮ በመግባት ነበር አስገራሚ የሆነውን ተግባር የፈፀመው።

ተከሳሹ የግል ተበዳዮችን በር ሰብሮ ከገባ በኋላ ጤረጵዛ ላይ ታብሌት ስልክ ተቀምጦ ይመለከታል እሱን ይዞ ለመውጣት ያስብና ቀና ሲል ውስኪ ብፌ ውስጥ ያያል ልቡ ሸፈተ ቆይ በዚህ ውስኪ ለምን ትንሽ ዘና አልልም ይልና ብርጭቆ አቅርቦ ሶፋ ላይ ፈልሰስ ብሎ ተቀምጦ ልክ እንደራሱ ቤት እየተዝናና እያለ ነበር ከተወሰነ ሰአት በኋላ የግል ተበዳዮች መምጣታቸውን ይሰማና ጠረጴዛ ላይ የነበረውንና የዋጋ ግምቱ 12ሺ ብር የሚያወጣ ታብሌት ስልክ ብድግ አድርጎ በድንጋጤ ሽንት ቤት ይደበቃል፣ የግል ተበዳዮችም ወደ ቤታቸው ሲገቡ ውስኪውን እና ብርጭቆ ጤረጴዛ ላይ ይመለከታሉ ታዲያ በዚህ ሰአት ማነው እዚህ ቤት የገባው ብለው በድንጋጤ ቤታቸውን ሲፈትሹ ተከሳሹን ግለሰብ ከነሰረቀው ንብረት ሽንትቤት ውስጥ እጅከፍንጅ በመያዝ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይደውላሉ።

በዚህም መሰረት ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ ወደ ጣቢያ ይወሰዳል ለፈፀመው ከባድ የስርቆት ወንጀልም በአቃቤ ህግ ክስ ይመሰረትበታል።

በፖሊስ ተጣርቶ በአቃቤ ህግ የተመሰረተበትን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሀምሌ 21 ቀን 2015ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ እንዳሻው ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው በሶስት አመት ከሶስት ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

ዘገባው የድሬዳዋ ፖሊስ ነው።
#ethio_mereja
#State_of_Emergency

ነገ በአማራ ክልል እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የሕዝብ ተወካዮች በሚሰጡት ድምፅ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኛል።

ምክር ቤቱ፤ ከቀናት በፊት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ለነገ ሰኞ 8 ሰዓት ለምክር ቤት አባላት አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በዚሁ መሰረት አባላት ተሰብስበው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሕጉ ምን ይላል ?

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘ ወዲያውኑ እንደሚሻር የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ ሁለት (ሀ) ይደነግጋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባልሆነበት ወቅት የታወጀ እንደሆነ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ እንዳለበት፣ የምክር ቤቱን ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘም ወዲያውኑ እንደሚሻር የሕገ መንግሥቱ ቀጣይ አንቀጽ ይደነግጋል።

6ኛው ዙር ምርጫ በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረ ግጭትና አለመረጋጋት ሳቢያ በተሟላ ሁኔታ ባለመከናወኑ፣ በሥራ ላይ የሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ካሉት 547 ወንበሮች መካከል የተወሰኑት የተጓደሉ ናቸው።

በአጠቃላይ አሁን በሥራ ላይ በሚገኘው ምክር ቤት መቀመጫ የያዙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ብዛት 427 መሆኑን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ መረዳት ይቻላል።

በመሆኑም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ም/ ቤቱ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ማፅደቅ ይኖርበታል በሚለው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊፀና የሚችለው ከአጠቃላይ የምክር ቤቱ አባላት ማለትም በስድስተኛው ዙር ተመርጠው በምክር ቤቱ መቀመጫ ከያዙት 427 ተወካዮች መካከል 285 የሚሆኑት የድጋፍ ድምፅ ከሰጡ ነው።

ከተጠቀሱት 427 ተመራጮች ውስጥ 142 የምክር ቤት አባላት የተቃውሞ ድምፅ ከሰጡ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀሪ ሊሆን ይችላል። 

በም/ቤቱ ወንበር ካገኙ አጠቃላይ 427 አባላት ወስጥ 410 የሚሆኑት በገዢው ፓርቲ ብልፅግና አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 125 ያህሉ በአማራ ብልፅግና ፓርቲ አቅራቢነት የተወዳደሩና የክልሉን ሕዝብ የሚወክሉ ናቸው።

ከብልፅግና ፓርቲ ውጪ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ አምስት የሕዝብ ተወካዮች ሲኖሩ፣ በኢዜማ አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ ሌሎች አራት የሕዝብ ተወካዮች እንደሚገኙም ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም ለምክር ቤቱ በቀረቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ላይ ለተሰጠው ድምፅ ሥሌት የተደረገው በዕለቱ የነበረውን የምክር ቤቱ ምልዓተ ጉባዔ መሠረት አድርጎ በመሆኑ፣ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምክር ቤት በሚቀርብበት ወቅት የሚኖረው የድምፅ አሰጣጥ ሥሌት በዕለቱ የሚኖረውን ምልዓተ ጉባዔ ታሳቢ የሚያደርግ ይሆናል።

በመሆኑም የሁለት ሦስተኛ ድምፅ ሥሌቱ ከላይ የምክር ቤቱን ጠቅላላ አባላት መሠረት በማድረግ ከተገለጸው ውጤት ያነሰ የድጋፍ እና ተቃውሞ ድምፅ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ ነው።

(የሕግ ጉዳይ ማብራሪያ ከሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
ስለ ይዞታ እና የቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት
በ፡ ሙሉቀን ሰዒድ

በዚህ አጭር ጽሑፍ የይዞታ ትርጉም ምን እንደሆነ፣ ይዞታን መሠረት ያደረገ የሁከት ይወገድልኝ ክስ በምን አግባብ ሊቀርብ እንደሚችልና ይህ ክስ ከባለቤትነት ክርክር ጋር ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ፣ ሁከት ይወገድልኝ የሚል ክስ ሲቀርብ ፍርድ ቤቶች የሚይዙት ጭብጥ በተመለከተ ዳሰሳ ተደርጎበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት ትርጓሜው ምን እንደሆነና ቀዳሚ የመግዛት መብት ካለው መሀከል ባልና ሚስትን፣ ወራሾችን በተመለከተ በህጉ ሊስተናገዱ የሚችሉበት አግባብ ለማየት ተሞክሯል፡፡

በመጨረሻም የቅድሚያ ግዥ መብት ያለው ሰው በሚገዛበት ጊዜ ስላለው የሽያጭ ስነ- ስርዓት፣ ግድግዳና ጣራቸው በአንድ በኩል የተያያዙ ቤቶችን በተመለከተ በቅድሚያ ግዥ መብት ሊስተናገዱ የሚችሉበት የህግ አግባብና የዘመዶች በቅድሚያ የመግዛት መብትን እስመልክቶ በጽሁፍ በወፍ በረር ቅኝት ተደርጎበታል፡፡

መልካም ንባብ!

https://www.abyssinialaw.com/blog/possessory-action-and-priority-acquisition
ክስ ይዛወርልኝ

• በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ የግዛት ስልጣን በሌለው ሌላ ፍርድ ቤት ወይም በዛው ፍርድ ቤት በሌላ ችሎት ተዛውሮ እንዲታይ በመጠየቅ በተከራካሪዎች የሚቀርብ አቤቱታ

በአንድ ወረዳ ፍ/ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ ወደ ሌላ ወረዳ ፍ/ቤት ተዛውሮ እንዲታይ አንደኛው ወገን ሲያመለክት ተገቢ ምክንያቶች መኖራቸው ተረጋግጦ በክስ ይዛወርልኝ አቤቱታው እንደየሁኔታው አግባብነት ያለው ውሳኔ ሊሰጥ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 31 ተመልክቷል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ለማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል፡፡ በስር ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ ፋይል ባልተከፈተበት ወይም ቀድሞ የተዘጋ መዝገብ ባልተንቀሳቀሰበት ሁኔታ የሚቀርብ የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 93171 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 31

የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ /Change of Venue/ የሚስተናገድበትን አግባብ ህጉ የዘረጋው ስርዓት ያለ ሲሆን በ1958ቱ የፍትሐብሔር ስነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 31 ስር የተመለከተው አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ህግ በኋላ በፌደራልም ሆነ በክልሎች የወጡት የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጆች ተመሣሣይ ይዘት ያለውን ድንጋጌ ስራ ላይ አውለው ይገኛል፡፡ አንድ ክስ ወደ ሌላ ስፍራ ሊዛወር የሚችልበትን አግባብ ከሚደነግጉት የስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ጥያቄው ከተከራካሪ ወገኖች የሚቀርብ መሆኑና ህጋዊ ምክንያቶች ተብለው በህጉ ከተመለከቱት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ መሟላት ያለበት መሆኑን ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 66945 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.
31
ኢትዮ-ሕግ🇪🇹⚖️🇪🇹Ethio-Law
   ለቴሌግራም መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
#EthioLawtips

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig