አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
እነዚህ ፍርድ ቤቶች አንድ ሕግ ወይም አስተዳደራዊ ዉሳኔ ሕገ መንግስቱን የሚጥስ ወይም የሚቃረን እንዲሁም የሕጋዊነት ጉድለት አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ ሕጉን ከሕግነት ተራ በማስወጣት ተፈጻሚ እንዳይሆን ለማድረግ የአስተዳደር ዉሳኔዉም ተግባራዊ እንዳይሆን ለመወሰን የሚከተሉበት

አካሄድም እንደዚሁ የተለያየ ነዉ፡፡ አሜሪካ የዳኝነታዊ ክለሳ የምታደርግበት ሞዴል ያልተማከለ ዳኝነታዊ ክለሳ ሥርዓትን (The decentralized model of judicial review) ሲሆን በዚህ ሞዴል መሰረት የክለሳ ጥያቄዉ ከበታች ፍርድ ቤት ጀምሮ በየደረጃዉ ይግባኝ ሥርዓት በሚመስል አካሄድ ታይቶ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የመጨረሻ አስገዳጅ ዉሳኔ ተሰጥቶበት እንዲቋጭ ታደርጋለች፡፡ እንደጀርመን ያሉት ደግሞ የክለሳ ጥያቄዉ በቀጥታ ለሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የሚያደርግ ሥርዓት(The centralized model of judicial review) የሚከተሉ ሲሆን በዚሁ ፍርድ ቤት ክለሳ ተደርጎ የመጨረሻና አስገዳጅ ዉሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋሉ፡፡በደቡብ አፍሪካ ደግሞ የአንድ ሕግ ሕገ መንግስታዊነትና እና የአንድን የአስተዳደር/የአስፈጻሚ አካል ተግባር/ዉሳኔ ሕገ መንግስታዊነትና ሕጋዊነት በተመለከተ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የሕገ መንግስታዊነት ትርጉም (Preliminary Constututional Interpretation) ሕገ መንግስቱን ተርጉሞ እንዲወስን ሥልጣን ትሰጥና የሕገ መንግስታዊነት ጥያቄ የተነሳበት ሕግ እና የሕገ መንግስታዊነትና የሕጋዊነት ጥያቄ የተነሳበት የአስፈጻሚ/የአስተዳደር አካል ተግባር/ዉሳኔ ተፈጻሚነት እንዳይኖራቸዉ የመጨረሻዉን ዉሳኔ የመሰጠት ሥልጣን የሚኖረዉ ሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ነዉ የሚል ሥርዓት በሕገ መንግስቷ እንደዘረጋች በዘርፉ የተጻፉ ድርሳናት ያሳያሉ፡፡
የእኛን አገር ስርዓት የተመለከትን እንደሆነ በሦስቱ የመንግሥት አካላት መካከል ማለትም በሕግ አውጭው፣ ሕግ አስፈጻሚው እና በሕግ ተርጓሚው መካከል በፌዴራልና በክልል ሕግጋተ መንግስታት በተመለከተዉ አግባብ የሥልጣን ክፍፍል ያለ ቢሆንም በመካከላቸው የእርስ በእርስ ክትትልና ሚዛኑን ተጠብቆ (check and balance) እየተሰራ መሆኑ የሚረጋገጥበት ሥርዓት ከሌለ ተቋማቱ በሕግ የተጣለባቸውን የዜጎችን ሠብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር አይችሉም፡፡ በአንጻሩ የእርስ በእርስ ክትትልና ሚዛኑን ጠብቆ የመስራት መርህ አተገባበር አለአግባብ ጣልቃ መግባትን ካስከተለ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝንና የተጣለባቸውን ግዴታ እንዳይወጡ ሊያደርጋቸው ስለሚችል ቁጥጥሩ በሕግ በተዘረጋው ሥርዓት አግባብ መፈጸም አለበት፡፡
አስተዳደራዊ አካላት የሚሠጧቸው ውሳኔዎች በፍ/ሕ/ቁጥር 401/1 እንደተመለከተው ከተሠጣቸው ሥልጣን በማለፍ ከወሰኑ (ultra virus) ወይም በተሠጣቸው ሥልጣን ስር ሆኖ ነገር ግን በሕጉ የተመለከቱትን አስገዳጅ ሁኔታዎችና ፎርም ሳይከተሉ የሚፈጽሙት ተግባር ወይም ውሳኔ ፈራሽ ነው፡፡ በአስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ የዳኝነት ክለሳ መኖር ካለበት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ የመንግሥት አካላት የሥልጣን ክፍፍል መርሕ ነው፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 79/1 መሠረት የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡ ይህም ከሕገ-መንግሥታዊ ክርክሮች (constitutional disputes) ውጭ ማንኛውም በፍርድ ቤት ታይተው ሊወሰኑ የሚችሉ ጉዳዮች (justiciable matters) ላይ ፍርድ ቤቶች ዳኝነታዊ ክለሳ የማድረግ (judicial review) ተፈጥሮአዊ የሆነ ዳኝነታዊ ሥልጣን (inherent judicial power) እንዳላቸው ያሳያል፡፡ በፍርድ ቤት ታይተው ሊወሰኑ የሚችሉ ጉዳዮች የሚለውም የጉዳዮቹ ባሕሪ በፍርድ ቤት ሥልጣን ሥር ሊወድቁ የማይችሉ፣ አከራክሮ ሊፈጸም የሚችል ውሳኔ ሊሰጥባቸው የማይችሉ ጉዳዮችን የሚመለከት ሲሆን በሌላ በኩል ጉዳዮቹ በፍርድ ሊታይ የሚችሉ እንኳን ቢሆን ሌሎች የመንግሥት አካላት በሕገ- መንግሥት ባለው የሥልጣን ክፍፍል መርሕ መሠረት ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን (constitutionally mandated powers) መሠረት አድርገው የሚወስኗቸው ጉዳዮችንም ይጨምራል፡፡ በሌላ በኩል የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 78/4 እና 37 ላይ የተደነገገዉ አንድ ላይ ሲነበብ በሕግ የተደነገገን የዳኝነት ሥርዓትን የሚከተል የዳኝነት ነክ አካላት በሕግ የመዳኘት ሥልጣን ሊሰጣቸው እንደሚችል ያስገነዝባል፡፡ የእነዚህ አካላት የዳኝነት ሥልጣን በተፈጥሮ የሚገኝ ሳይሆን በግልጽ ሕግ ለመዳኘት ሥልጣን ሲሰጣቸውና የሚሰሩበት የተደነገገ የዳኝነት ሥርዓት ሲኖራቸውና ይህን ተከትለው ሲሰሩ የሚኖራቸው ሥልጣን ነው፡፡ ይህም በዘመናዊው የመንግሥት ሥርዓት መንግሥት ብዙ ጉዳዮች ላይ ሠፊ ሥልጣን ያለው አስፈጻሚዉ አካል በመሆኑ በመሆኑ ለመንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል የዳኝነት ነክ ሥልጣን አስፈላጊ በመሆኑ፣ የተወሰኑ ጉዳዮች

ደግሞ ፍሬ ነገሮችን ለመመልከት ልዩ ዕውቀት (specialization) የሚጠይቁ በመሆኑ እና ፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን የሥራ ጫና ለማቃለል ሥራ ላይ ይውላሉ፡፡

ነገር ግን ጠንካራና አስተማማኝ የዜጎች ሰብዓዊ መብት የሚከበርበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሕግ የበላይነትን ማስፈን ወሳኝ ነው፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት መግቢያ ላይ እንደተመለከተው የሕግ የበላይነትን የተረጋገጠበት አሰራር መዘርጋት የሕገ-መንግሥቱ ዋነኛ ዓላማ ሲሆን አንዱ መስፈርት ደግሞ የዜጎችን በፍርድ ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች በነፃና ገለልተኛ ፍርድ ቤት እንዲታይ መደረጉ ነው፡፡የሕግ የበላይነት መርሕ ሰፊ ሀሳቦችን የያዘ ቢሆንም በሕግ ሥልጣኑ የተገደበ መንግሥት እንዲኖርና የዜጎች መብት የተከበረበት ሥርዓትን ለመፍጠር የሚረዳ ነው፡፡ በፌዴራሉ ሕገ-መንገሥት መግቢያ ላይ የተመለከተዉ የሕግ የበላይነት ዓላማ ከግብ የሚደርሰዉ የመንግስት አካላት ለሚወስዱት እርምጃ ተጠያቂ መሆንና ኃላፊነት መውሰድ ሲችሉ ነዉ፡፡ይህም ከሚረጋገጥባቸዉ መንገዶች አንዱ በሰጡት አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ መብቱ የተነካበት ሰዉ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲችልና ፍርድ ቤቶችም ተገቢዉን መንገድ ተከትለዉ ጥያቄ የቀረበበት ዉሳኔ ሕጋዊነትን የተከተል መሆን አለመሆኑን በዳኝነት ማየት ሲችሉ ነዉ፡፡ እንዲሁም የአስተዳደር አካላት የሠጡት ውሳኔ በሕጉ የተዘረጋውን ሥርዓት የተከተለና ዜጎች ተገቢው የመሰማት መብት (due process of law) ያገኙ ስለመሆኑ ቁጥጥር ለማድረግ በአስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ የዳኝነት ክለሳ ያስፈልጋል፡፡
በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 79(1) መሠረት የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 ላይ ሰዎች ፍትሕ የማግኘት መብት ያላቸው በመሆኑ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች በፍርድ ሊዳኙ የሚችሉ እስከሆኑ ድረስ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ ጉዳዮችን እንዲመለክት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 78 መሰረት ሥልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት ቀርቦ መታየቱ ነጻ የዳኝነት አካል ያስፈለገበት ዓላማ ሊሳካ የሚችልበትና ሰዎች ያላቸውን መብት በሕግ ማስከበር የሚችሉበት ዋነኛ መሣሪያ አስተዳደራዊ ዉሳኔ በዳኝነታዊ ክለሳ ማየት መቻል ነው፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃም አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ የዳኝነት ክለሳ አስፈላጊ መሆኑን ያሰገነዝባል፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 13(1) ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና ማስከበር ኃላፊነት ከተሰጣቸው አካላት ዋነኛው
የዳኝነት አካሉ በመሆኑ የአስተዳደር አካላት ከዜጎች ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይኖር ለመከላከል ሆነ ጥሰት ሲኖር ዜጎች ጥሰቱን የሚያሳርሙበት ዕድል ስለሚያስፈልግ አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ የዳኝነት ክለሳ የግድ የሚል ስለመሆኑ ያስገነዝባል፡፡ ስለሆነም ከፍርድ ቤት ውጭ በሕግ የዳኝነት ነክ ሥልጣን በተሰጣቸዉ አካላት የሚሰጡ ዉሳኔዎችንም ሆነ በሕግ በተሰጣቸዉ ኃላፊነት የሚሰጧቸዉ አስተዳደራዊ ዉሳኔዎች በዳኝነታዊ ክለሳ ሂደት በማለፍ በፍርድ ቤት መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የይግባኝ(Appeal) አቀራረብ ሥርዓት ምንነት የተመለከትን እንደሆነ ይግባኝ የሚባልበት ሥነ ሥርዓት በዋናነት በበታች መደበኛ ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ በየተዋረዱ ባሉት የበላይ መደበኛ ፍርድ ቤቶች በሕግ በተዘረጋዉ ሥርዓት መሰረት እንደገና የሚመረመርበትን የሚመለከት ነዉ፡፡ (የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 12/2 321 እና አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 54 ይመለከቷል፡፡) በተጨማሪም አስተዳደራዊ ዉሳኔ ወይም የዳኝነት-ነክ ሥልጣን የተሰጠዉ አካል(Quasi-judicial organ) የሰጠዉ ዉሳኔ በየደረጃዉ በተቋቋመና በከፍተኛዉ የዳኝነት-ነክ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ወይም በሕግ በግልጽ ከተደነገገም እነዚሁ አካል የሰጡት ዉሳኔ በከፍተኛዉ መደበኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ የሚታይበትን ሥነ ሥርዓት የሚመለከት ነዉ፡፡(ለአብነት በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 69/2፣98/4፣ 115/2፣ 153/8፤ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 29(1 እና 4) እና በአዋጅ ቁጥር 714/2003 እና ይህንን አዋጅ በተካዉ አዲስ አዋጅ ላይ በተመሳሳይ በአንቀጽ 56(1 እና 4) እና በሌሎችም ላይ ተደነገገዉ ይመለከቷል፡፡የይግባኝ ሥርዓትን ከዳኝነታዊ ክለሳ የሚለዩትም ምክንያቶች በይግባኝ ጊዜ በልዩ ሁኔታ በሕግ እስካልተገደበ ድረስ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በበታች ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረዉን ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን፣በዉስን ሁኔታዎች አዲስ ማስረጃ መቀበልንና

የበታች ፍርድ ቤቶች ወይም የዳኝነት-ነክ አካል የሰጡት ዉሳኔ የሕግ ወይም የፍሬ ነገር ድምዳሜ ስህተት አለበት ብሎ ሲያምን ዉሳኔዉን ሽሮ አዲስ ዉሳኔ መስጠትን ጭምር የሚያካትት ሲሆን በዳኝነታዊ ክለሳ ደግሞ ሕግ አዉጪዉ ያወጣዉ ሕግ፣ሕግ አስፈጻሚዉ የፈጸመዉ ተግባር(የወሰነዉ ዉሳኔ) እንዲሁም የዳኝነት-ነክ ሥልጣን የተሰጠዉ አካል የወሰነዉ የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ ብቻ ተመስርቶ ሕገ መንግስታዊ ወይም ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን በመከለስ ሕገ መንግስታዊ ወይም ሕጋዊ አይደለም የሚል ከሆነ ተፈጻሚ እንዳይሆን መወሰን ወይም ዉሳኔዉን ሽሮ እንደገና ታይቶ እንዲወሰን መመለስ አሊያም የክለሳ ጥያቄዉን ዉድቅ በማድረግ ዉሳኔዉን ማጽናት እንጂ የራሱን አዲስ ዉሳኔ አይሰጥም፡፡

ከላይ በዝርዝር ከተመለከትነዉ ከተለያዩ አገራት ልምድ፣ በአገራችን በተለያዩ ሕግጋት እና በዳኝነት ሥራ ከዳበረዉ ተመኩሮ (judicial jurisprudence) ከተንጸባረዉ የምንገነዘበዉም አንድን ዉሳኔ በሰበር የማየት፣ በይግባኝ የማየት እና በዳኝነት አይቶ የመከለስ ሥርዓት በጽንሰ ሀሳብ ደረጃም ሆነ በአተገባበራቸዉ የተለያየ የክርክር አመራርንና መነሻ ምክንያትን የሚጠይቁ እንደሆኑ ነዉ፡፡በአገራችን በፌዴራል ደረጃ በልዩ ሁኔታ በሕግ በግልጽ በተቃራኒዉ አስካልተደነገገ ድረስ አንድ በፍርድ ቤት፣ በአስተዳደር አካል ወይም ዳኝነት ነክ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል የተሰጠ ዉሳኔ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ሊመረመር የሚችለዉ እንደነገሩ ሁኔታ በሕግ በተዘረጋዉ በይግባኝ እና በዳኝነታዊ ክለሳ ሥነ ሥርዓት ታይቶ የመጨረሻ ዉሳኔ ካገኘ በኋላ ብቻ ነዉ፡፡ምክንያቱም የሰበር ሰሚ ችሎት ሥልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ብቻ መርምሮ ስህተቱን የሚያርም ዉሳኔ መስጠት በመሆኑ ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አካል የተሰጠ ዉሳኔ በተለይም በዳኝነታዊ ክለሳ ሊታይ የሚችል ዉሳኔ በዳኝነታዊ ክለሳ ሳይታይ በቀጥታ ለሰበር ሰሚ ችሎት የሚቀርብ ከሆነ በመደበኛ ፍርድ ቤት በክለሳ ሥርዓት ሊመረመሩ የሚችሉና ፍሬ ነገሮችን ከማስረጃ አንጻር ጭምር መመርመርንና ማረጋገጥን የሚጠይቁ የክርክር ነጥቦች ወይም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልሆኑ ስህተቶች የሚታረሙበትን ሂደት የሚገድብ ይሆናል፡፡

እንዲሁም አንድ አስተዳደራዊ ዉሳኔ የመጨረሻ ነዉ ተብሎ እንደነገሩ ሁኔታ በይግባኝ ፣በዳኝነታዊ ክለሳ ቀጥሎም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ከሆነ በሰበር ሥርዓት ታይቶ የማይታረም ከሆነ የሕገ መንግስት የበላይነት መርህ ፣የዲሞክራሲያዊ መንግስት መገለጫ የሆነዉ የተጠያቂነት መርህ እና የዲሞክራሲያዊ መንግስት የሥልጣን ክፍፍል መሠረታዊ መርህ የሆነዉ የመንግስት አካላት እርስ በእርሳቸዉ የሚኖራቸዉ የሥልጣን ክትትልና ሚዛን የመጠበቅ (Check and Balance) መርህ እንዲሸራረፍ ያደርጋል፡፡በመሆኑም በሕግ በልዩ ሁኔታ በቀጥታ ለሰበር ቀርቦ እንዲታይ እስካልተደነገገ ድረስ በሰበር ከመታየቱ በፊት እንደነገሩ ሁኔታ በይግባኝ ወይም በዳኝነታዊ ክለሳ ሥነ ሥርዓት ሊታይ ይገባል፡፡
በሰ/መ/ቁጥር 214219 ላይ የተሰጠ ማብራሪያ
via Habesha legal advocate
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
ተገዶ_የመያዝ_Habeas_corpus_ስረ_ነገር_ስልጣን.pdf
320.7 KB
Habeas courps/ተገዶ መያዝን/የመዳኘት ስልጣኑ የፌደራል መጀመሪያ ደርጃ ፍ/ቤት ስለመሆኑ ያልታተመ የሠበር ውሳኔ።
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
ስለ ፍርድ አፈጻጸም.pdf
415.3 KB
ስለ ፍርድ አፈጻጸም

በዚህ አጭር ጽሑፍ የተብራሩ ሥነ-ሥርዓታዊ ጉዳዮች፡-

👉 ፍርድ እንዲፈጸም ስለሚቀርብ ማመልከቻ

👉 የፍርድ ባለዕዳውን ስለመመርመር

👉 ለፍርድ አፈጻጸም ንብረትን ስለማስከበር

👉 በተከበረ ወይም በተያዘ ንብረት ላይ ሦስተኛ ወገኖች የሚያቀርቡት መቃወሚያ

👉 ለፍርድ አፈጻጸም ንብረትን የመሸጥ ሥነ-ሥርዓት
https://t.me/lawsocieties
ግልጽነት የጎደለው የአሹራ ክፍያ ነገር•••
          ****
የአዲስ አበባ ግንባታና ቁጥጥር ባለስልጣን በመመሪያ ቁጥር ግፈቁባ/9561/3014፣ በ2014 ዓ.ም. ባወጣው የግንባታ ዋጋ ክለሳ መሰረት:-

ለሁሉም የህንጻ ዐይነቶች የግንባታ ተመን፣

1. G+0 ቤት ብር 10,000/ካሬ ሜትር፣
2. ከG+1 በላይ ለንግድ፣ ለመኖሪያ እንዲሁም ለቅይጥ ህንጻዎች ብር 12,200/ካሬ ሜትር፣
3. ለሆስፒታል አገልግሎት የሚሆን ህንጻ ብር 20,000/ካሬ ሜትር ፣

በሚል የዋጋ ትመና አውጥቶ ሰዎች የንብረት ስም ዝውውር በሚፈጽሙ ጊዜ ለመንግስት የሚከፈለው የ2% የቴምብርና የ4% የአሹራ ክፍያ በእዚህ ዋጋ ላይ ሲሰላ ቆይቷል።

ይሁንና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አዲስ የከለሰው መመሪያ ለህዝብ ግልጽ ባልተደረገበት ሁኔታ በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች ዜጎች የቤት ባለቤትነት ለማዘዋወር ጥያቄ ሲያቀርቡ  የቤቶች የግንባታ ዋጋ፣

1. G+0 ህንጻ ብር  20,000/ካሬ ሜትር፣
2. ከG+1 እስከ G+ 5 ህንጻ ብር 25,000/ካሬ ሜትር፣
3. ከG+6 እስከ G+ 10 ህንጻ ብር 30,000/ካሬ ሜትር፣
4. ከG+11 እስከ G+15 ህንጻ ብር 35,000/ካሬ ሜትር፣
5. ከG+15 ህንጻ በላይ ብር 40,000/ካሬ ሜትር፣

መሆኑን የሚገልጽ ነገር ተለጥፏል።

በየክፍለ ከተሞቹ ዜጎች ይሄንኑ አዲስ ወጣ የተባለ የዋጋ ትመና መሠረት ባደረገ መልኩ የአሹራ ክፍያ እየፈጸሙ ይገኛሉ።

መመሪያውን በተመለከተ...

1ኛ/የቤቱ ዓይነት ቅንጡ ህንጻም ይሁን እንደነገሩ የተገነባ ህንጻ ተመሳሳይ የግንባታ ዋጋ በካሬ ሜትር ማስቀመጡ፣

2ኛ/ኮንዶሚንየም የሚሸጡ ሰዎችን በተመለከተ መመሪያው ምንም ስለማይል ምድር ቤት ኮንዶሚንየም የሚሻሻጡ ሰዎች ዝቅተኛ አሹራ (20,000 በካሬ)፣ 6ኛ ፎቅ ላይ ያለ ቤት የሚሻሻጡ ሰዎች ከፍተኛ አሹራ (30,000 በካሬ) እንዲከፍሉ  ይገደዳሉ። ከእዚህ በተቃራኒ የቤት ሽያጭም ሆነ ኪራይ ዋጋ የሚወደደው ታች ባሉ ወለሎች ላይ መሆኑ እና መመርያው ይሄንን ከቁብ ያላስገባ መሆኑ፣

3ኛ/በቅርቡ ኢኮኖሚዬ hyperinflationary አይደለም (የሶስት አመት አጠቃላይ የግሽበት መጠኔ ከ100% አይበልጥም ) በማለት መግለጫ ያወጣ መንግስት፣ ዋነኛ የዋጋ ንረት መለኪያ የሆነው የግንባታ ወጪ በአመት ከ100% በላይ መናሩን ማመኑ፣ እንዲሁም

4ኛ/ መመሪያዎች ሲወጡ መመሪያው ለሚተገበርበት ህዝብ ግልጽ መሆን ሲኖርበት ያለመሆኑ እንዲሁም በመሬት ላይ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑ

ግርምትን አጭሮብኛል።
------------------

Tilahun Girma Ango

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
በህግ ስራ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ላይ የተደረገው ጥናት አተገባበር ዙሪያ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ውይይት ተደረገ
********

የኢትዮጵያ የፌደራል ጠበ
ቆች ፣ የህግ አማካሪዎችና፣  የጥብቅና ድርጅቶችን የታክስ አስተዳደር ስርአት የህግ እና የአተገባበር ችግሮች ላይ ለበርካታ አመታት ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችል ጥናት ለተከታታይ ወራት በኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ፣ በፍትህ ሚ/ር እና በገንዘብ ሚኒስቴር አማካኝነት ሲከናወን ቆይቶ መጠናቀቁ ይታወሳል::  ከጥናቱ መጠናቀቅ በኃላም በአዲስ አበባ ከተማ በጥናቱ ግኝቶችና መደምደሚያዎች ላይ ተከታታይ ውይይቶች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መከናወኑም የሚታወስ ነው::

የጠበቆች ማህበር ቀጣዩ የግብር ዘመን ላይ የባለፉት አመታት ችግሮችን ለመፍታት የአጭርና የረጅም ግዜ እቅዶችን በመንደፍ ያላሰለሰ ጥረቱን እንደሚቀጥልና ከፖሊሲ ውሳኔ ሰጪዎች እና ከቁልፍ ባለድርሻዎች ጋር ተከታታይ ውይይቶች እንደሚደረጉ ማሳወቁ ይታወሳል::

በዚህም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ እና የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር በጥናቱ ግኝቶች እና ቀጣይ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ዝርዝር ውይይቶች ተደርገዋል::

በመድረኩም  የኢትዮጵያ የፌደራል ጠበቆች ማህበር ተ/ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው የጥናቱን ዳራ ፤ መነሻ ምክንያቶች ፤ አጠቃላይ ሂደቱንና ፤ የጥናቱን ቁልፍ መደምደሚያዎች እንዲሁም በቀጣይ በአጭርና በረጅም ግዜ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የጥናቱ ግብረሀይል አባላትም የጉዳዩን አንገብጋቢነት የሚገልፁ ሀሳቦችን አንፀባርቀዋል::
አለሕግAleHig ️
በህግ ስራ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ላይ የተደረገው ጥናት አተገባበር ዙሪያ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ውይይት ተደረገ ******** የኢትዮጵያ የፌደራል ጠበቆች ፣ የህግ አማካሪዎችና፣  የጥብቅና ድርጅቶችን የታክስ አስተዳደር ስርአት የህግ እና የአተገባበር ችግሮች ላይ ለበርካታ አመታት ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችል ጥናት ለተከታታይ ወራት በኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ፣ በፍትህ…
የገንዘብ ሚ/ር  ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በመድረኩ እንደገለፁት ጉዳዩ በዚህ ደረጃ ተደራጅቶ መጠናቱ የተለየ እንደሚያደርገው ፤ የህግ ሙያ ለማደግ ፍትሃዊ ያልሆኑ አሰራሮች ሊታረሙ እንደሚገባ ገልፀው ፤ በቀረበው መሰረት የአጭርና የረጅም ግዜ መፍትሄዎቹ ላይ በተቻለ ፍጥነት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እንዲሰራ ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል::

ማህበሩ ይህን ለበርካታ አመታት ሲንከባለል የቆየና ላለፉት 11 ወራት ብዙ የተደከመበትን ስራ ከዳር ለማድረስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር  በመሆን ተገቢውን የመሪነት ሚናውን እየተወጣ የሚቀጥል ሲሆን ፤ የሚደርስባቸውን ውጤቶች በተለመዱት የማህበሩ የመገናኛ ዘዴዎች የሚያሳውቅ ይሆናል:: መላው የፌደራል ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች እንደወትሮው ሁሉ የግብር ግዴታችሁን ለመወጣት ከግብር መክፈያ ወቅት ቀድሞ ተገቢውን ዝግጅት እያደረጋችሁእንድትቆዩ ማህበሩ ያሳስባል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሰኔ 07 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ ፣
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
Law of Traders & Business
👇👇👇👇👇👇👇👆👆👆
The Text book on Law of Traders & Business Organizations is out of print today. USAID Feteh sponsored the work. Participate colleagues Misganaw K, Gizachew S. & Dagnachew W.This is exemplary collaborative work representing four universities.

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
የስብሰባ ጥሪ ፣
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባዘጋጀዉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የለዉጥ ፍኖተ-ካርታ ላይ ከጠበቆች ጋር ዉይይት ለማድረግ ማቀዱን ገልፆ 100 ጠበቆች በእለቱ እንዲገኙለት ጠይቆናል፡፡

በመሆኑም ዉይይቱ የሚካሄደዉ ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስብሰባ አዳራሽ መሆኑን አውቃችሁ በዉይይት መድረኩ ላይ እንድትገኙ ጠበቆች የተጋበዛችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር

ሰኔ 10 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ
ያለ ደረሰኝ (ቫት) ግብይት ማከናወን ወንጀል ሰ/መ/ቁ 211028
ያለ ደረሰኝ (ቫት) ግብይት ማከናወን ወንጀል ጋር በተያያዘ የድርጅት ሥራ አስኪያጅ የድርጅቱን አስተዳደር በሚመለከት በውክልና ለሌላ ሰው ያስተላለፈ መሆኑ እና ተወካዩም በተቀበለው ውክልና መሠረት ሥራውን የሚያከናውን መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ተጠያቂ የሚሆነው ውክልናውን ተቀብሎ ስራውን በውክልና የሚያስተዳድረው ሰው እንጂ ስራ አስኪያጁ ወይም የድርጅቱ ባለቤት ሊሆን አይገባም።

አዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 እንደተሻሻለው በአንቀጽ 56/1/፤ አንቀጽ 22/1/ እና አንቀጽ 50/ለ/1 መሠረት የአንድ የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው እሱ የሚመራው ድርጅት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ማከናወኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ፤ የድርጅቱ ሃላፊነት ከተረጋገጠ የሥራ አስኪያጁ ሃላፊነት የሕግ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ እንገነዘባለን።
4 ለ 1 አብለጫ ድምጽ የተሰጠ
የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁ 983/08 አንቀጽ 131(1)(ለ)፤ 131(1)(ለ)፤ 128

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
የፌድራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_ሰበር_ሰሚ_ችሎት_በሰበር_መዝገብ_ቁጥር_219862_ግንቦት_26_ቀን_2014.pdf
828.9 KB
የፌድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 219862 ግንቦት 26 ቀን 2014 የተሰጠ ውሳኔ

ከባድ vs ቀላል የአካል ጉዳት የሰ/መ/ቁ. 219862/ያልታተመ/ 
አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ በፈፀመው የድብደባ ድርጊት የአጥንት ስብራት መድረሱ ቢረጋገጥና ቆይቶ ስብራቱ መዳኑ ቢረጋገጥ ጉዳት ያደረሰው ሰው ጥፋተኛ ሊባል የሚገባው በከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ሳይሆን በቀላል የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ነው። በከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ጥፋተኛ ለማለት ታሳቢ ሊደረግ የሚገባው ወንጀሉ ሲፈፀም የደረሰውን የጉዳት መጠን ሳይሆን በድብደባው ምክንያት የደረሰውን የመጨረሻ የጉዳት ውጤት ነው።
ሰ/መ/ቁ.156521፣ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 555፣ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 556
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
219862 - Stamped.pdf
828.9 KB
አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ በፈፀመው የድብደባ ድርጊት የአጥንት ስብራት መድረሱ ቢረጋገጥና ቆይቶ ስብራቱ መዳኑ ቢረጋገጥ ጉዳት ያደረሰው ሰው ጥፋተኛ ሊባል የሚገባው በከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ሳይሆን በቀላል የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ነው። በከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ጥፋተኛ ለማለት ታሳቢ ሊደረግ የሚገባው ወንጀሉ ሲፈፀም የደረሰውን የጉዳት መጠን ሳይሆን በድብደባው ምክንያት የደረሰውን የመጨረሻ የጉዳት ውጤት ነው። ሰ/መ/ቁ.156521፣የወንጀል ሕግ አንቀጽ 555፣የወንጀል ሕግ አንቀጽ 556
#Click Ethiopian Laws
👆👆👆👆👆👆
145_2015የአዲስ_አበባ_ከተማ_ነዋሪነት_ምዝገባ_መመሪያ.pdf
942.5 KB
# መመሪያ ቁጥር 144/2015 የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ።