አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለተቀነሱ ሠራተኞች የሚከፈል ክፍያ

የሥራ ውል ሲቋረጥ ደመወዝና ከደመወዝ ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን አሰሪው ለተቀነሱ ሰራተኞች እንዲከፍል ህግ ያስገድደዋል ፡

1. በመጀመሪያነት የሚከፈለው ክፍያ ደሞዝ ነው ፡ ሰራተኞቹ ለሰሩበት ወር ላተከፈለ ደሞዝ ካለ እሱን መክፈል ፡፡

2. በመቀጠል ደግሞ ለሚቀነሱት ሰራተኞች መከፈል ያለበት ክፍያ የስራ ስንብት ክፍያ ነው ፡፡ ብዙውን ጊዜ አሰሪዎች በቶሎ ለመፈፀም የሚከብዳቸው ክፍያ ፡ የስራ ስንብት ክፍያ ነው ፡፡ ቢሆንም ግን በአዋጅ 1156/20 አንቀጽ 39 () (ሐ) እና አንቀጽ 40 መሰረት ፤ አሰሪ በእራሱ አነሳሽነት ፡ በሰራተኛው በኩል ምንም ጥፋት ሳይኖር ሰራተኞችን የሚቀንስ ከሆነ ፡ ለተቀነሱ ሰራተኞች የስራ ስንብት ክፍያ በወቅቱ ይከፈላል ፡፡

የስራ ስንብት ክፍያ ስሌት

ስሌቱ በትክክለኛው መንገድ በአዋጅ 1156/20n አንቀጽ 40(1) እና (2) መሰረት ሲሰላ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ በድንጋጌዎቹ መሰረት ስሌቱን ለመስራት መጀመሪያ የሠራተኛው አማካይ የቀን ደመወዝ መታወቅ አለበት፡፡

የሥራ ሰዓቱ በሳምንት 48 ሰዓት የሆነ ሠራተኛ ወርሃዊ የሥራ ሰዓቱ 208 ሰዓት ነው፡፡ በወር የሚያገኘው ደመወዝ 208 ሰዓት ለሰራበት የሚከፈለው ክፍያ ነው፡፡ ወርሃዊ ደመወዙ ለ208 ሰዓት ሲካፈል የአንድ ሰዓት ደመወዙን ይሰጠናል፡፡ በወር 9,00o ብር እየተከፈለው ለሶስት አመት የሰራ ሰራተኛ : የአንድ ሰዓት ደመወዙ ብር 9000/208 ብር 43.26923 ነው፡፡ የአንድ ሰዓት ደመወዝ በስምንት የሥራ ሰዓት ሲባዛ 43.26923 x በ8 የሚሰጠን ውጤት ብር 346.15 አማካይ የቀን ደመወዝ ነው፡፡

የሠራተኛው የቀን ደመወዝ ብር 346.5 መሆኑን ከለየን ቀጣዩ ስራ የስንብት ክፍያውን በአንቀጽ 40(1)

እና (2) መሰረት ማስላት ይሆናል፡፡ በዚሁ መሰረት፤ ሀ. ለመጀመሪያው ዓመት አገልግሎት ብር 346.15 (የሠራተኛ አማካይ የቀን ደመወዝ) ሲባዛ በ30= ብር 10,384.5 ለ. የብር 10,384.5 አንድ ሶስተኛ ብር 3,461.5 ሲሆን ይህም በቀሪዎቹ የአገልግሎት ዓመታት ላይ ይባዛል፡፡ ብር 3,461.5 ሲባዛ በ2) እኩል ይሆናል ብር 6,923፡፡

ሐ. ከላይ በ ሀ እና ለ የተገኘው ው ውጤት ሲደመር ጠቅላላውን የስንብት ክፍያ መጠን ይሰጠናል፡፡

ስለሆነም ብር 10,3845 ሲደመር ብር 6,923 ብር 17,307.5

በተጨማሪም የስራ ውሉ የሚቋረጠው በሰራተኞች ቅነሳ ከሆነ ፡ የሰራተኛው የቀን ደሞዝ በ 60 ተባዝቶ የሰንብት ክፍያው ላይ ይደመራል ፡፡ የቀን ደሞዝ 346.15 x 60 20,769 ፡፡ 20,769 ሲደመር =

17,307.5 = 38,076.5

ስለሆነም ፡ የሰራተኛው የስንብት ክፍያ ድምር ብር 38,076.5 ይመጣል፡፡

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
አሠሪና ሠራተኛ - የአሠሪ ትርጓሜ ሰ/መ/ቁ 232984 ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም

አንድ ፕሮጀክት አንድ ድርጅት የተወሠነ ሥራን በተወሰነ ጊዜ ለማጠናቀቅ አቅዶ የሚፈጽመዉ /የሚያከናዉነዉ/ ሥራ ወይም ተግባር በመሆኑ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 2(2) መሰረት ራሱን የቻለ የድርጅቱ ቅርንጫፍ ወይም ድርጅት ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡
ለተወሰነ ሥራ ወይም ጊዜ የተዯረገ የሥራ ዉሌ ሥራዉ ወይም ጊዜዉ በመጠናቀቁ ምክንያት የሠራተኛዉ የስራ ዉል ቢቋረጥ የድርጅቱ ወይም የፕሮጀክቱ ለዘለቄታዉ መዘጋት አለመዘጋት ከሥራ ዉሉ መቋረጥ ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ስለማይኖር ለሠራተኛዉ የሚከፈል የስራ ስንብት ክፍያ አይኖርም፡፡
👉via ethiolawreviews
የሙስናና ብልሹ አሰራር ድርጊቶችን በጥቆማ መስጫ አድራሻዎች ያጋልጡ፣ ይጠቁሙ!!

*******************
የመሸሸግ ወንጀል
በንብረት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን አስምልክቶ በወንጀል ህጉ ከተደነገጉ በንብረት ላይ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መካከል የመሸሸግ ወንጀል አንዱ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የመሸሸግ ወንጀልን ምንነት እና የሚያስከትለውን ተጠያቂነት እንመለከታለን፡፡
የመሸሸግ ወንጀል ምንነት
በወንጀል ህጉ አንቀፅ 682 መሰረት መሸሸግ ማለት ዕቃው የተገኘው በአንድ ንብረት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ምክንያት መሆኑን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባ ይህንኑ ዕቃ በመግዛትም ሆነ በተውሶ፣ በስጦታ፣ በመያዣነት መቀበል ወይም በማናቸውም ይህን በመሳሰለ አኳኋን መውሰድ፣ መገልገል፣ ማስቀመጥ ወይም መደበቅ፣ አሳልፎ መሸጥ ወይም በመሸጥና በመለወጥ ስምምነት ውስጥ አገናኝ በመሆን መርዳት እንዲሁም የወንጀል ተግባር ባስገኘው ፍሬ የመጣ መሆኑን እያወቁ በዚሁ በወንጀል ድርጊት በተገኘ ዕቃ ምትክ በልዋጭ የተገኘውን ወይም በሽያጭ ዋጋ የተገዛውን ሌላ አይነት ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ መቀበል ነው፡፡
በዚህ መሰረት የመሸሸግ ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት
 ተሸሽጎ የተገኘው ዕቃ በአንድ ንብረት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ምክንያት የተገኘ ወይም የወንጀሉ ተግባር ባስገኘው ፍሬ የመጣ መሆን
 ሸሻጊው ዕቃው በወንጀል ምክንያት መገኘቱን ማወቅ ወይም መገመት ሲገባው በቸልተኝነት ወንጀሉን የፈፀመ መሆን
 በወንጀል ተግባር የተገኘን ዕቃ የገዛ፣ የተቀበለ፣ የወሰደ፣ የተገለገለ ወይም በመሰል ድርጊት ውስጥ የተገኘ መሆን አለበት፡፡
የመሸሸግ ወንጀል የህግ ተጠያቂነት
ከላይ በተገለፀው ሁኔታ የመሸሸግ ወንጀል አስቦ የፈፀመ ማንም ሰው በቀላል እስራት ወይም ከባድ በሆነ ጊዜ ከአምስት አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በመቀጮ ይቀጣል፡፡ ድርጊቱ በቸልተኝነት የተፈፀመ እንደሆነ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡
ከባድ መሸሸግ
የመሸሸግ ወንጀል የተፈፀመው
 በሰዎች ወይም በንብረት ላይ ወንጀል ለመፈፀም የተቋቋመ ቡድን አባልነት እንደሆነ
 ወንጀል ፈፃሚው የተሰጠውን የሥራ ወይም የንግድ ፍቃድ በወንጀል የተገኘን ንብረት ለመሸሸግ ተገልግሎበት እንደሆነ
 ወንጀል ፈፃሚው የሸሸገው ንብረት የውንብድና፣ የዘረፋ፣ የባህር ውንብድና፣ የቅሚያ፣ የማስፈራራት ፍሬ መሆኑን ወይም ዕቃው የተገኘው ከመከላከያ ሠራዊት ንብረት ወይም በጠቅላላው ከመንግስት ሀብት ውስጥ መሆኑን እያወቀ እንደሆነ
ወንጀሉ ከባድ የመሸሸግ ወንጀል የሚሆን ሲሆን ፈፃሚውም አስራ አምስት አመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና እስከ ብር ሀያ ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ እንደሚችል ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ በማወቅም ወይም በቸልተኝነት በእንድ የወንጀል ድርጊት አማካኝነት የተገኘን ንብረት መግዛት፣ መዋስ፣ በስጦታ ወይም በመያዣነት መቀበል ወዘተ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑን በመገንዘብ ዕቃዎችን ሲገዛም ሆነ በተለያዩ መንገዶች ሲቀበል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
#ከኢፕድ_ማህደር ‼️

48 ዓመታት ቀሚስ የለበሰው ወንድ ተከሰሰ

48 ዓመት ሙሉ እንደ ሴት ቀሚስ በመልበስ ሸዋዬ ደገፉ በመባል በሴት ስም ይጠራ የነበረ ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡

ሸዋዬ ደገፉ የወንድ ጾታውን በመደበቅ ቀሚስ ለብሶ በሴት ስም በመጠራት ካሳለፈው 48 ዓመታት ውስጥ በናዝሬት 10 አመት፣ በአሰላ ከተማ አራት አመት፣ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ 11 አመት በታላላቅ ሰዎች ቤት በሴት ሥራ ሙያ እየተቀጠረ መኖሩን ገልጿል፡፡

ሸዋዬ የወንድነት ጾታው እንዳይታወቅበት በአገጩ ግራና ቀኝ በመጠኑ የሚበቅለውን ጢም በየዕለቱ ይላጫል፡፡ ጠጉረ በራ በመሆኑም ዘወትር እንደ ሴት ሻሽ ይጠመጥማል፡፡ የጆሮ ጉትቻም እንደማይለየው ታውቋል፡፡

ሸዋዬ በትውልድ አገሩ በየረርና ከርዩ አውራጃ በኢጀሬ ከህጻንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሴት ቀሚስ ይለብስ እንደነበር ጠቅሶ ወደ ፊትም እስከ ዕለቱ ሞቱ ድረስ ቀሚስ መልበሱን እንደማይተው አስረድቷል፡፡

ተከሳሹ የሴቶቹን ሙያ አጠናቆ የሚያውቅ መሆኑን ገልጾ ከህጻንነቱ ጀምሮ ዘፈን የሚወድ፤ በዚህም ሙያ ብዙ ጊዜ እንደተጠቀመበት አረጋግጧል፡፡

ሸዋዬ ደገፉ በናዝሬት፣ በአሰላና በአዲስ አበባ እየተዘዋወረ ለ25 ዓመታት ተቀጥሮ በሚያገለግልበት ጊዜ የወንድነት ጾታው ያልታወቀበት መሆኑን አስረድቷል፡፡

ሸዋዬ ዘመዶቹን ለመጠየቅ ወደ ትውልድ አገሩ ወደ ኤጀሬ ሲጓዝ ለጥቂት ጊዜ በናዝሬት ከተማ በሴት ሥራ ሙያ ተቀጥሮ ገንዘብ ለማግኘት ባለው ዕቅድ መሰረት በከተማው ውስጥ ሲዘዋወር ፖሊሶች በጥርጣሬ ያዙት፡፡ ከዚያም ሲጠየቅ ወንድ መሆኑንና በዚሁ በሴት ሁኔታ 48 አመታት ሙሉ መኖሩን አስረድቷል፡፡

በዚህም ጾታ የመለወጥና ቀሚስ የመልበስ አድራጎቱ ተከሶ አዳማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ሆኖም በዚሁ ሁኔታ ለመኖር የፈለገበት ምክንያት በሚገባ እስኪጣራ ድረስ በዋስ መለቀቁ ታውቋል፡፡

የካቲት 6 ቀን 1963 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ
ለ 48 ዓመታት ቀሚስ የለበሰው ወንድ ተከሰሰለ
48 ዓመት ሙሉ እንደ ሴት ቀሚስ በመልበስ ሸዋዬ ደገፉ በመባል በሴት ስም ይጠራ የነበረ ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡

ሸዋዬ ደገፉ የወንድ ጾታውን በመደበቅ ቀሚስ ለብሶ በሴት ስም በመጠራት ካሳለፈው 48 ዓመታት ውስጥ በናዝሬት 10 አመት፣ በአሰላ ከተማ አራት አመት፣ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ 11 አመት በታላላቅ ሰዎች ቤት በሴት ሥራ ሙያ እየተቀጠረ መኖሩን ገልጿል፡፡

ሸዋዬ የወንድነት ጾታው እንዳይታወቅበት በአገጩ ግራና ቀኝ በመጠኑ የሚበቅለውን ጢም በየዕለቱ ይላጫል፡፡ ጠጉረ በራ በመሆኑም ዘወትር እንደ ሴት ሻሽ ይጠመጥማል፡፡ የጆሮ ጉትቻም እንደማይለየው ታውቋል፡፡

ሸዋዬ በትውልድ አገሩ በየረርና ከርዩ አውራጃ በኢጀሬ ከህጻንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሴት ቀሚስ ይለብስ እንደነበር ጠቅሶ ወደ ፊትም እስከ ዕለቱ ሞቱ ድረስ ቀሚስ መልበሱን እንደማይተው አስረድቷል፡፡

ተከሳሹ የሴቶቹን ሙያ አጠናቆ የሚያውቅ መሆኑን ገልጾ ከህጻንነቱ ጀምሮ ዘፈን የሚወድ፤ በዚህም ሙያ ብዙ ጊዜ እንደተጠቀመበት አረጋግጧል፡፡

ሸዋዬ ደገፉ በናዝሬት፣ በአሰላና በአዲስ አበባ እየተዘዋወረ ለ25 ዓመታት ተቀጥሮ በሚያገለግልበት ጊዜ የወንድነት ጾታው ያልታወቀበት መሆኑን አስረድቷል፡፡

ሸዋዬ ዘመዶቹን ለመጠየቅ ወደ ትውልድ አገሩ ወደ ኤጀሬ ሲጓዝ ለጥቂት ጊዜ በናዝሬት ከተማ በሴት ሥራ ሙያ ተቀጥሮ ገንዘብ ለማግኘት ባለው ዕቅድ መሰረት በከተማው ውስጥ ሲዘዋወር ፖሊሶች በጥርጣሬ ያዙት፡፡ ከዚያም ሲጠየቅ ወንድ መሆኑንና በዚሁ በሴት ሁኔታ 48 አመታት ሙሉ መኖሩን አስረድቷል፡፡

በዚህም ጾታ የመለወጥና ቀሚስ የመልበስ አድራጎቱ ተከሶ አዳማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡
የኤክሳይዝ_ታክሰ_ማሻሻያ_አዋጅ_ቁጥር_1287_2015.pdf
3.9 MB
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባዔው ያጸደቀው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1285/2015
ሠ/መ/ቁጥር 222680 ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ.ም
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ስር በጽሑፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ የተጻፈዉ ቀን በፈራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነዉ የሚለዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678/ሐ፣1719/2 እና 1723/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት በሕግ የታዘዘዉን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ ለተደረገ ዉል እንጂ ለማንኛዉም ዉል አይደለም፡፡

[በሌላ አነጋገር በድንጋጌው ላይ የተመለከተው የማስረጃ ደንብ ውልን ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ሳይደረግ ሆኖም ውሉ መኖሩ የታመነ /ያልተካደ/ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ላይ ተፈጻሚ አይሆንም።
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties