#ከኢፕድ_ማህደር ‼️
48 ዓመታት ቀሚስ የለበሰው ወንድ ተከሰሰ
48 ዓመት ሙሉ እንደ ሴት ቀሚስ በመልበስ ሸዋዬ ደገፉ በመባል በሴት ስም ይጠራ የነበረ ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡
ሸዋዬ ደገፉ የወንድ ጾታውን በመደበቅ ቀሚስ ለብሶ በሴት ስም በመጠራት ካሳለፈው 48 ዓመታት ውስጥ በናዝሬት 10 አመት፣ በአሰላ ከተማ አራት አመት፣ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ 11 አመት በታላላቅ ሰዎች ቤት በሴት ሥራ ሙያ እየተቀጠረ መኖሩን ገልጿል፡፡
ሸዋዬ የወንድነት ጾታው እንዳይታወቅበት በአገጩ ግራና ቀኝ በመጠኑ የሚበቅለውን ጢም በየዕለቱ ይላጫል፡፡ ጠጉረ በራ በመሆኑም ዘወትር እንደ ሴት ሻሽ ይጠመጥማል፡፡ የጆሮ ጉትቻም እንደማይለየው ታውቋል፡፡
ሸዋዬ በትውልድ አገሩ በየረርና ከርዩ አውራጃ በኢጀሬ ከህጻንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሴት ቀሚስ ይለብስ እንደነበር ጠቅሶ ወደ ፊትም እስከ ዕለቱ ሞቱ ድረስ ቀሚስ መልበሱን እንደማይተው አስረድቷል፡፡
ተከሳሹ የሴቶቹን ሙያ አጠናቆ የሚያውቅ መሆኑን ገልጾ ከህጻንነቱ ጀምሮ ዘፈን የሚወድ፤ በዚህም ሙያ ብዙ ጊዜ እንደተጠቀመበት አረጋግጧል፡፡
ሸዋዬ ደገፉ በናዝሬት፣ በአሰላና በአዲስ አበባ እየተዘዋወረ ለ25 ዓመታት ተቀጥሮ በሚያገለግልበት ጊዜ የወንድነት ጾታው ያልታወቀበት መሆኑን አስረድቷል፡፡
ሸዋዬ ዘመዶቹን ለመጠየቅ ወደ ትውልድ አገሩ ወደ ኤጀሬ ሲጓዝ ለጥቂት ጊዜ በናዝሬት ከተማ በሴት ሥራ ሙያ ተቀጥሮ ገንዘብ ለማግኘት ባለው ዕቅድ መሰረት በከተማው ውስጥ ሲዘዋወር ፖሊሶች በጥርጣሬ ያዙት፡፡ ከዚያም ሲጠየቅ ወንድ መሆኑንና በዚሁ በሴት ሁኔታ 48 አመታት ሙሉ መኖሩን አስረድቷል፡፡
በዚህም ጾታ የመለወጥና ቀሚስ የመልበስ አድራጎቱ ተከሶ አዳማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ሆኖም በዚሁ ሁኔታ ለመኖር የፈለገበት ምክንያት በሚገባ እስኪጣራ ድረስ በዋስ መለቀቁ ታውቋል፡፡
የካቲት 6 ቀን 1963 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ

ጠጉሩን ሹሩባ ተሰርቶ የተያዘው ወንድ ልጅ ከእስሩ ነጻ ሆነ
አፍሮ ጠጉሩን ሹሩባ ተሰርቶ በመገኘቱ ለባህል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት ፈጽሟል ተብሎ ከተከሰሰ በኋላ በቅርቡ ታስሮ የነበረው አበበ ወልደፃድቅ ከክሱ ነጻ ሆኖ መዝገቡ የተዘጋ መሆኑን የአዲስ አበባ አውራጃ ፍርድ አቃብያን ህግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
አበበ ክስ ቀርቦበት ሊታሰር የቻለው በቅርቡ አፍሮውን ሹሩባ ከተሰራ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ አፍንጮ በር አካባቢ 50...https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02iQuLEVfPQVVhW1guLe227x24WgNghLDZpqnT5pxVMS72WrFWYFhCrgUrejqp3qSsl