አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ሰ/መ/ቁ 35962 (ያልታተመ)
ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት ያልተደረገ የቤት ሽያጭ ውል መሰረት በማድረግ ገዢ ቤቱን የሚመለከቱ ማንኛውም ሰነዶች እንዲያስረክበው በሻጭ ላይ ክስ አቅርቦ ጉዳዩን የሚያየው ፍርድ ቤት የቤት ሺያጭ ውሉ በፍ/ሕ/ቁ. 1723 መሰረት በዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ፊት ባለመደረጉ የህግ ውጤት የለውም የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረሰ ሻጭ ሰነዶችን ለማስረከብ እንደማይገደድ ከመወሰን አልፎ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ ውሳኔ ሊሰጥ አይገባም። ምክንያቱም የቤት ሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ ባለመኖሩ ፍ/ቤቱ በዝርዝር ባልቀረበ ወይም በግልጽ ባልተጠየቀ ጉዳይ ላይ ውሣኔ መስጠቱ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 282/2/ የሚቃረን ነው።
habeshaadvocatellp
#ethiolawtips
ፈቃድ ሳይኖረው ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ 3.8 ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በህገ-ወጥ መንገድ ከአገር ይዞ ሲወጣ የተያዘው ቻይናዊ ክስ ተመሰረተበት

በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ፈቃድ ሳይኖረው ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ 3.8 ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ እና ኮፐር፣ ዚንክና ሲልቨር የያዘ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ማዕድን በህገ-ወጥ መንገድ ይዞ ሲወጣ የተያዘው ቻይናዊ ተከሳሽ ላይ የኮንትሮባንድ ወንጀል ክስ ተመሰረተበት፡፡
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ #አለ_Share #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ሚስተር ፓን ችዋን የተባለው ቻይናዊ ተከሳሽ ገደብ የተደረገበት መሆኑን እያወቀ/ማወቅ ሲገባው የብቃት ማረጋገጫ እና ፈቃድ ሳይኖረው የዋጋ ግምቱ 18 ሚሊዮን 5 ሺ 939 ብር የሚያወጣ ቀረጥና ታክስ 12 ሚሊዮን 824 ሺ 53 ብር የሚከፈልበት 3.8 ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ እና 2 ሺ 196 ብር ቀረጥና ታክስ የሚከፈልበት በውስጡ ኮፐር፣ ዚንክና ሲልቨር የያዘ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ማዕድን የሻንጣ የብረት ዘንግ ውስጥ አድርጎ ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና አገር ይዞ ሲወጣ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የወጪ መንገደኞች የደህንነት ኤክስሬይ መፈተሻ ቦታ ላይ ስለተያዘ በፈፀመው ገደብ የተደረገበት ዕቃን በህገ-ወጥ መንገድ ይዞ መውጣት የኮንትሮባንድ ወንጀል የማዕድን ግብይት አዋጅ ቁጥር 1144/2011 አንቀጽ 12/1/፣ 5፣ እና 36/1/ እንዲሁም የጉሙሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 (በጉሙሩክ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀጽ 2/44/ እንደተሻሻለው) አንቀጽ 168/1/ ስር የተደነገገውን ተላልፎ የኮንትሮባንድ ወንጀል መፈፀም ክስ ቀርቦበታል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎትም ተከሳሹ የተከሰሰበትን ክስ ለመስማት ለየካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ #አለ_Share #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎትን እስከ ሀምሌ 1/2015ዓ.ም ድረስ ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን ለማድረግ እየተሠራ ነው
==================================
አዲስ አበባ 8/6/2015(ንቀትሚ) በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ለ781, 843 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎትን በኦን ላይን ለመስጠት ታቅዶ ለ 898, 284 ተሰጥቷል፡፡
የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመቅረፍ እና የንግድ ስራ አመቺነትን ለማሻሻል አወንታዊ ተፅእኖ ስላለው ተግባራዊ የተደረገው የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በቀጣዮቹ 6 ወራት ሙሉ በሙሉ ይተገበራል፡፡
የንግድ አሠራርን ማዘመን በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራበት ሲሆን በቀጣይም አሰራሮችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ማከናወን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡
በዘርፉ ያለውን አሠራር ከማዘመን አንፃር የንግድ ምዝገባና ፍቃድ እና ኢንስፔክሽን መመሪያ መመሪያ ቁጥር 935/2015 ተዘጋጅቶ ስራ ላይ እንድውል ተደርጓል፡፡
#ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) እና የአክሲዮን ማህበር ተመሳሳይነትና ልዩነት

በኢትዮጵያ ንግድ ህግ  ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል ኃላፊነቱ የተወሰነ  የግል ማህበር ( PLC ) እና የአክሲዮን ማህበር ይገኙበታል ።

ሁለቱም  ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም  ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።                       

#ተመሳሳይነታቸዉ

• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑን (የንግድ ህግ 256 እና 501 )
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣

#ልዩነታቸዉ

አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 495(4) ላይ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን ( share company ) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን  ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ አንቀጽ 248(3)  ላይ ይገኛል።

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር  አንድ በመቶ ማነስ አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር (496)

• አክሲዮን   ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ  አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር  በታች መሆን አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር 247)

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ  ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር  ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4  (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል (የንግድ ህግ ቁጥር (495(1) 

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ  ክፍት የሚደርግ አይደለም  አንቀጽ 495(2) ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ (የንግድ ህግ ቁጥር248)

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ  ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን  የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።

• አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም  ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( plc) ዉስጥ ቦርድ የለም።
        
#የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ
የኮ/መ/ቁ 282704/ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንግድ ችሎት ውሳኔ /

ቼክ በንግድ ህጋችን እንደ ንግድ ወረቀት ይቆጠራሉ ተብለው በን/ህ/ቁ 732/2/ ስር ከተዘረዘሩት የንግድ ወረቀቶች አንዱ ነው፡፡ ቼክ ከንግድ ወረቀቶች ውስጥ አንዱ ቢሆንም ከሌሎች የንግድ ወረቀቶች የሚለይባቸው ልዩ ባህሪያት ያሉት፣ ገንዘብን ተክቶ በስፋት አገልግሎት እየሠጠ ያለ፣ በንግድ ህጉ እንዲሁም በሌሎች ህጐቻችን ልዩ ጥበቃ የተሠጠው የንግድ ወረቀት ሲሆን ከነዚህ ልዩ ባህሪያት አንዱ ቼክ እንዲቀረበ የሚከፈልበት የንግድ ወረቀት መሆኑ ነው፡፡ ይህም በን/ህ/ቁ 854 ስር ተመልክቷል፡፡ የቼኩ አምጪ / Drawee / ቼኩን ለክፍያ ለከፋዩ ባንክ /Payee/ አቅርቦ ቼኩ ሳይከፈልበት ከተመለሰ የቼኩ አውጪ /Drawer/ ስለ ቼኩ አከፋፈል ዋስ በመሆኑ እና ገንዘቡን የመክፈል ሀላፊነት ያለበት በመሆኑ በቼኩ ላይ የተፃፈውን ገንዘብ የቼኩ አውጪ እንዲከፍለው መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህም በን/ህ/ቁ 840 ፣ 868 ፣ 881 /1/ ስር ተመልክቷል፡፡ የቼኩ አውጪም በን/ህ/ቁ 840 መሠረት ገንዘቡን የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡
የቼኩ አውጪ ከዚህ ኃላፊነት ሊድን የሚችለው ማለትም በቼኩ ላይ የተፃፈውን ገንዘብ ለቼኩ አምጪ የመክፈል ኃላፊነት የማይኖርበት፣ ቼክን መሠረት አድርጐ ለቀረበ ክስ በቼኩ አምጪ ላይ ሊቀርቡ ይችላሉ ተብለው በህጉ ተለይተው እና ተወስነው በን/ህ/ቁ 717 ስር የተቀመጡትን መከላከያ ምክንያቶች ያቀረበ፣ ይህን መከላከያ ምክንያቱንም ያስረዳ ሲሆን ነው፡፡ ይህ መከላከያም በን/ሕ/ቁጥር 717/1//3/፣ 849፣ 850 ስር የተቀመጠውን አይነት ከቼኩ አምጪ ጋር ያለውን የግል ግንኙነት መሠረት ያደረገ /Personal Relation Ship Defence/ ወይም በን/ሕ/ቁጥር 717/1/2/ ስር የተመለከቱት አይነት ከቼኩ አወጣጥ፣ ፎርም፣ የተፃፋ ቃላትና ፊርማ መሠረት ያደረጉ ቼኩን የሚመለከቱ መከላከያዎች /Real Defence/ ያቀረበ እና ይህንም መከለከያውን ያስረዳ ሲሆን ነው፡፡
#Daniel fikadu ዳንኤል ፍቃዱ /ጠበቃና የህግ አማካሪ/           
በፍርድ የማይዳኝ ጉዳይ /Justiciability/---በሰበር ችሎት

ፍቺ--ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በሕግ ለሌላ አካል የተሰጠ

ሰ/መ/ቁ. 51790 ቅጽ 12፣  የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁ. 587/2000 አንቀጽ 19/1/ ለ፣ የፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁ. 515/1999፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሠራተኞች አስተዳደር ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ. 155/2000 አንቀጽ 37

ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ. ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ ድንጋጌ በግልጽ የሚያሳየው ጉዳይ ነው፡፡ ከዚሁ የሕገ መንግስት ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ፍርድ ቤቶች አንድን ጉዳይ (አቤቱታ) ተቀብለው ውሳኔ መስጠት የሚችሉት ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በሕግ ለሌላ አካል ያልተሰጠ ጉዳይ በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ መሆኑን ነው፡፡ በሕግ ተለይተው በአስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲቋጩ በተባሉ ጉዳዮች ላይ መደበኛ ፍርድ ቤት የመዳኘት የስረ ነገር ስልጣን ስለሌለው በሕጉ መሰረት ለአንድ አስተዳደር አካል ቀርቦ አስተዳደራዊ ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ ወይም ለአስተዳደር መቅረብ የሚገባውን ጉዳይ ፍርድ ቤት ሊያስተናግደውም ሆነ አከራክሮ ውሳኔ ሊሰጥበት አይችልም፡፡ ለአንዳንድ የመንግስት አካላት በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የመወሰን ስልጣን የሚሰጡት ሕጎች መጠበቅና መከበር ያለባቸው ሲሆን የዳኝነት አካል ስልጣንም በሕግ የተወሰነ ስለሆነ ሕግ የመተርጎም ስራው በሕጉ በተመለከተው አድማስ የሚመራ ይሆናል፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 4 ድንጋጌ የሚያሳየውም ፍርድ ቤቶች በሌላ ሕግ በግልጽ በታገዱ ጉዳዮች ላይ አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የሌላቸው መሆኑን ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 54697 ቅጽ 12፣  ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 4

አንድ ጉዳይ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል ነው የሚባለው የክርክሩ መሠረታዊ ባህሪ በፍርድ ለመጨረስ አመች የሆነ ሲሆንና ተከራካሪዎቹ የሚከራከሩበት ጉዳይ ንድፈ ሃሳባዊ ወይም ምናባዊ የፈጠራ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ሣይሆን በነባራዊ ዕውነታና ተጨባጭ በሆነ ችግር ወይም ክስተት መሠረት ያደረገ የመብት ወይም የሃላፊነት ጥያቄ ሲሆን እንደሆነ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 42150 ቅጽ 12፣  ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ ዓለም አቀፍ የሲቨልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነት አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 1፣ የአፍሪካ የሰዎችና የህዝቦች መብት ቻርተር አንቀጽ 7
(የአንድ ዳኛ የተለየ ሓሳብ)

ግንባታ በጊዜው አለመጠናቀቁን ወይም የገንዘብ አቅም ማነስን አሊያም በሌላ ምክንያት አስተዳደሩ በሚወስዳቸው የኪራይ (lease) ይዞታ ማቋረጥ እርምጃዎች ላይ ባለይዞታው ቅሬታ ሲያድርበት ጉዳዩን ለማየት በሕግ በግልጽ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ሌላ አካል እስከሌለ ድረስ ጉዳዩ በፍርድ ሊወስን የሚገባው ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 80202 ቅጽ 15 

የንብረት ባለሀብትነት መብት ከአንዱ ወገን ወደ ሌላው እንዴት መተላለፍ እንዳለበት በህጉ የተመለከተውን ደንብና ሥርዓት ሳይከተል ስለሆነ የንብረቱ ባለሀብት ስለመሆኑ የህግ ግምት መውሰጃ የሆነው የባለቤትነት ምስክር ወረቀት ቀሪ ነው፤ ሊሰረዝ ይገባል በማለት የሚቀርብ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195፣ 1196 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/ እና 231/1/ሀ/ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት በፍ/ቤት ሊረጋገጥ የሚችል የዳኝነት ጥያቄ እንጂ ጉዳዩ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል ጉዳይ አይደለም ለማለት የሚያበቃ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 75414 ቅጽ 14፣  ፍ/ህ/ቁ 1195፣ 1196፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 33(2)፣ 231(1) ሀ

የቀበሌ ቤት የተከራይነት መብት ተከራይ ሲሞት ለወራሾቹ ወይም ለቤተሰቦቹ የሚተላለፍ መሆን ያለመሆኑ በፍ/ብ/ሕጉ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት የኪራይ ውል የተመለከቱትን ድንጋጌዎች፣ የቀበሌ ቤትን የኪራይ መብትና ግዴታ ለመግዛት በሚመለከተው አካል በወጡት ደንብና መመሪያዎች አንጻር ታይቶ በፍርድ ቤት ዳኝነት የሚሰጥበት እንጂ የቤቱ አስተዳዳሪ የሆነ ቀበሌ ለፈለገው ሰው የሚያከራየው ነው ተብሎ በፍርድ እንዳያልቅ የሚደረግ ጉዳይ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 97948 ቅጽ 17
#habeshaadvocatesllp
#ethiolawtips
https://t.me/lawsocieties
#የኑዛዜ_አይነቶችና_የኑዛዜ_ማረጋገጫ 
በኢትዮጵያ የውርስ ህግ ሰው ህይወቱ ካለፈ በኋላ በህይወት ዘመኑ ያፈራቸው ንብረቶቹን ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲከፋፈል የሚያደርግበት ሁለት አይነት መንገዶች አሉ፡፡ እነሱም ያለኑዛዜ የሚደረግ ውርስ እና በኑዛዜ የሚደረግ ውርስ ናቸው፡፡ በሁለቱም ዘዴዎች የሚደረግ የንብረት ማስተላለፍ ሂደት በፍትሐ ብሔር ህግ የሚገዛ ሲሆን ለውርሱ ተፈፃሚነት ህጉ ያስቀመጣቸው መስፈርቶች መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የኑዛዜ አይነቶች እና የኑዛዜ ማረጋገጫ በዝርዝር ይዳሰሳሉ፡፡
    
የኑዛዜ አይነቶች

በኢትዮጵያ ህግ 3 የኑዛዜ ዓይነቶች አሉ፡፡ ሁሉም የኑዛዜ አይነቶች መከትል ያለባቸው ፎርማሊቲዎች ወይም ቅድመ ሁኔታዎች በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐ ብሔር ህጋችን ውስጥ በዝርዝር የተቀመጡ ሲሆን መስፈርቶቹ ያልተሟሉ እንደሆነ ኑዛዜው በህግ ፊት ውድቅ (ፈራሽ) ይሆናል፡፡ ህጉ የመስፈርቶቹን መሟላት በተመለከተ ጥብቅ (strict) ነው፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት የኑዛዜ ቃል በሚፈፀምበት ወቅት ተናዛዡ በህይወት ስለማይኖር ትክክለኛ ሀሳቡን ማወቅ የሚቻለው ትቶት ከሄደው የኑዛዜ ሰነድ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ሰነድ ደግሞ ለአፈፃፀም እንዲያመች መስፈርቶቹን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ መከተል አለበት፡፡ በፍ/ህ/አ 880 ስር እንደተደነገገው 3ቱ የኑዛዜ አይነቶች

1. በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ (public will)
2. በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ (holographic will)
3. በቃል የሚደረግ ኑዛዜ (oral will) ናቸው

• በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ( የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 881-883)

በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ሌላ ሰው የሚፅፈው ወይም ተናዛዡ ራሱ የሚፅፈው የኑዛዜ አይነት ነው፡፡ ይህ ኑዛዜ በተናዛዡ ወይም በሌላ ሰው ከተፃፈ በኃላ ተናዛዡ እና ምስክሮች ባሉበት መነበብ አለበት፡፡ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ተቀባይነት እንዲኖረው ተናዛዡና ምስክሮች ባሉበት መነበቡ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ይልቁንም ይህ መስፈርት (formality) መሟላቱ በኑዛዜው ላይ መስፈር አለበት፡፡ ይኸውም በኑዛዜው ላይ  "ይህ ኑዛዜ ተናዛዡ እና ምስከሮች ባሉበት ተነቧል" ተብሎ መገለጽ አለበት፡፡ በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ ላይ የምስክሮች ብዛት 4(አራት) መሆን ሲኖርበት አራቱም ምስክሮች ኑዛዜው ተነቦላቸው በኑዛዜው ላይ ፊርማቸውን ወዲያውኑ ማስፈር አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በኑዛዜው ላይ ኑዛዜው የተደረገበት ቀን ማለትም ቀን፣ ወር፣ ዓመተ ምህረት መፃፍ አለበት፡፡

የምስክሮችን ብዛት በተመለከተ በግልፅ ለሚደረግ ኑዛዜ ከምስክሮቹ መካከል አንዱ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሆኖ ኑዛዜውም የተደረገው ይህ ዳኛ ወይም ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሥራቸውን በሚያካሄዱበት ክፍል ውስጥ የሆነ እንደሆነ ለኑዛዜው ዋጋ ማግኘት ሁለት ምስክሮች ብቻ በቂ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ የሚከተሉትን ፎርማሊቲዎች መከተል አለበት፡፡

 በተናዛዡ በራሱ ወይም እሱ እየተናገረ በሌላ ሰው ሊፃፍ ይችላል
 ተናዘዡና አራት ምስክሮች ባሉበት መነበብ አለበት
 በኑዛዜው ላይ ተናዛዡና ምስክሮቹ ባሉበት መነበቡ በግልፅ መፃፍ አለበት
 ኑዛዜው የተደረገበት ቀን፣ ወር እና ዓ.ም መፃፍ አለበት
 አራት ምስክሮች መኖር አለባቸው፣
 ተናዛዡና ምስክሮች ኑዛዜው እንደ ተነበበላቸው ወዲያውኑ ፊርማቸውን ወይም የጣት አሻራቸውን ማሳረፍ አለባቸው
 በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ምስክሮች አካለመጠንን የደረሱ (18 ዓመት የሞላቸው) ወይም በህግ ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው
 ምስክሮች ኑዛዜው የተፃፈበትን ቋንቋ ለማወቅና የተፃፈውን ለመስማት ወይም ለማንበብ ራሳቸው ችሎታ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

እነዚህ ከላይ የተመለከቱት መስፈርቶች ካልተሟሉ ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል፡፡ ፍርድ ቤቶችም የኑዛዜ ቃልን ለማስፈፀም መሟላት ያለባቸው መስፈርቶችን በጥብቅ የሚቆጣጠሩ ሲሆን መስፈርቶቹ ካልተሟሉ ኑዛዜውን ውድቅ ያደርጉታል፡፡

• በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ (የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 883-891)

በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደርግ ኑዛዜ ሙሉ በሙሉ በተናዛዡ የሚፃፍ የኑዛዜ አይነት ነው፡፡ ይህን የኑዛዜ አይነት የሚያደርገው የተማረ ወይም ኑዛዜው የሚፃፍበትን ቋንቋ መፃፍና ማንበብ በሚችል ሰው ሲሆን የምስክሮችን መኖር የሚፈልግ አይደለም፡፡ በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ በተናዛዡ የእጅ ፅሁፍ ወይም በማሽን (በኮምፒዩተር) ሊፃፍ ይችላል፡፡ ተናዛዡ ኑዛዜውን በኮምፒዩተር የሚፅፈው ከሆነ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ እራሱ ስለመፃፉ በእጅ ፅሁፉ ማመልከት አለበት፡፡ ይህም ኑዛዜውን ያደረገው ተናዛዡ እንደሆነ ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡ ኑዛዜው በማሽንም ሆነ በእጅ ቢፃፍ ተናዛዡ በእንዳንዱ ገፅ ላይ ቀን ፅፎ ፊርማውን ማስፈር ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም በኑዛዜ ሰነድ ላይ ተናዛዡ ይህ ሰነድ "ኑዛዜ" ነው በማለት በግልፅ መግለፅ አለበት፡፡ እነዚህ መስፈርቶች ካልተሟሉ ኑዛዜው ፈራሽ ነው፡፡ በተጨማሪ በተናዛዡ ፅህፈት የሚደረግ ኑዛዜ ኑዛዜው በተደረገ በሰባት(7) ዓመት ውስጥ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ወይም ፍርድ መዝገብ ቤት መቀመጥ አለበት፡፡

በአጠቃላይ በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ በህግ ፊት ተቀባይነት እንዲያገኝ እና ተፈፃሚነት እንዲኖረው የሚከተሉት መስፈርቶች በሙሉ መሟላት አለባቸው፡፡

 ሙሉ ለሙሉ በተናዛዡ መፃፍ አለበት
 በኑዛዜው ላይ በግልፅ "ይህ ሰነድ የኑዛዜ ሰነድ ነው "ተብሎ መገለፅ አለበት
 በተናዛዡ በአያንዳንዱ ገፅ ላይ ቀን እና ፊርማ መስፈር አለበት
 ኑዛዜው በተደረገ በሰባት አመት ውስጥ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ዘንድ መቀመጥ አለበት፣( የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 903)
 ተናዛዡ ግልፅ በሆነ ፊርማው ካላፀደቃቸው በስተቀር የተናዛዡን ፈቃድ ለመለወጥ የሚችል ፍቀት፣ ስርዝ ወይም ድልዝ ያለባቸው ኑዛዜዎች ፈራሽ ናቸው፡፡

ከእነዚህ ከላይ ከተገለፁት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ ወይም ከአንድ በላይ ካልተሟላ ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል ወይም ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ነገር ግን ኑዛዜ ፈራሽ ሆነ ማለት ወራሾች ንብረት አያገኙም ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ውርሱ በቁጥር 842 እና ተከታዮቹ መሰረተ ሳይናዘዝ የሞተ ሰው ውርስ በሚተላለፍበት ሂደት የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

  
የቃል ኑዛዜ (የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 892-894)

የቃል ኑዛዜ ማለት አንድ ሰው የሞቱ መቃረብ ተሰምቶት የመጨረሻ የፍቃድ ቃሎቹን ለሁለት ምስክሮች የሚሰጥበት የኑዛዜ አይነት ነው፡፡ ከፍ/ህ/ ቁጥር 892 እንደምንረዳው የቃል ኑዛዜ በመደበኛ ሁኔታ (under normal circumstances) የሚደረግ አይደለም፡፡ ተናዛዡ ይህን የኑዛዜ አይነት የሚያደርገው በቅርብ ጊዜ እሞታለው ብሎ ሲያስብ ለምሳሌ አደጋ ደርሶበት ፅኑ ህመም ውስጥ ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲህ ባለጊዜ ሌሎቹን የኑዛዜ አይነቶች ማለትም በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜን ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜን ለማድረግ ሁኔታዎች አይፈቅዱለትም ማለት ነው፡፡ በመሆኑም በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ላይ ተናዛዡ የሚናዘዘው በተገደበ ሁኔታ (restricted testamentary disposition) ይሆናል፡፡ በዚህ የኑዛዜ አይነት ተናዛዡ ሙሉ ፍላጎቱን ለማንፀባረቅ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ህጉ ገደቦችን አስቀምጧል፡፡

በፍ/ሕ/ቁጥር 893 መሰረት አንድ ሰው የቃል ኑዛዜ ማድረግ የሚችለው በተለይ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡
👉የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት የሚመለከቱትን ትዕዛዞች ለመስጠት
 እያንዳንዱ ውርስ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር የማይበልጥ የኑዛዜ ስጦታ ለማድረግ፣
 አካለ መጠን ላላደረሱ ልጆቹ አስተዳዳሪን ወይም ሞግዚትን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን ለመስጠት ነው፡፡

በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ውስጥ ከብር አምስት መቶ በላይ ኑዛዜ ተደርጎ ከሆነ ከአምስት መቶ ብር በላይ ያለው ተቀናሽ ይሆናል፡፡ በቃል የተደረገ ኑዛዜ ከተደረገበት ከሶስት ወር በኋላ ተናዛዡ በህይወት የቆየ እንደሆነ ኑዛዜው ተፈፃሚ አይሆንም ወይም ፈራሽ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ተናዛዡ ያንያህል ጊዜ ሳይሞት ከቆየ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜን ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜን ለማድረግ እድል አለው ተብሎ ይገመታል፡፡

በሌላ በኩል ብዙ ኑዛዜዎች ካሉ አብሮ ተፈፃሚ ሊሆኑ በሚችሉበት መጠን ልዩ ልዩ ኑዛዜዎች አብረው ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን የሁለት ኑዛዜዎች ቃላት ሁለቱም ሊፈፀሙ ያልቻሉ ወይም የተቃረኑ እንደሆነ በኋላ የተደረገው ኑዛዜ ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡

በአጠቃላይ ንብረቱን በኑዛዜ ማስተላለፍ የሚፈልግ ሰው ሶስቱን የኑዛዜ አይነቶች ፎርማሊቲያቸውን በሟሟላት እንደየሁኔታው ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡ ኑዛዜ አድራጊው የኑዛዜ ቃላት ተፈፃሚነት እንዲያገኙ በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች በጥንቃቄ መከተል አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ኑዛዜው ውድቅ ስለሚሆን የተናዛዡ ፍላጎት ተፈፃሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡

 የኑዛዜ ማስረጃ ወይም ማረጋገጫ

በኑዛዜው የሰፈረውን ቃልና ኑዛዜው መኖሩን ማስረዳት ያለበት በዚህ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚለው ሰው ነው፡፡ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የተደረገ ኑዛዜ መኖር የሚረጋገጠው የኑዛዜውን ፅሁፍ ዋናውን በማቅረብ ወይም ለማዋውል ስልጣን በተሰጠው ሰው ዘንድ ወይም ፍርድ መዝገብ ቤት ሹም ተክክለኛ ሆኖ የተመሰከረ አንድ ግልባጭ በማቅረብ ነው፡፡ ኑዛዜዎቹን ለማስፈፀም በማናቸውም ሌላ መንገድ ለማስረዳት አይቻልም፡፡ ነገር ግን በጥፋት ወይም በቸልተኝነት ኑዛዜው እንዲጠፋ ካደረገ ሰው የጉዳት ኪሳራ ለማግኘት ከሆነ በማናቸውም አይነት መንገድ ኑዛዜዎችን ማስረዳት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ በአንድ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚል ሰው ሁለት ነገሮችን በመሰረታዊነት ማስረዳት ያለበት ሲሆን እነሱም በተናዛዡ የተደረገውን ኑዛዜ በማቅረብ የኑዛዜን መኖር እና የኑዛዜውን ይዘት በማስረዳት ማለትም እሱ የኑዛዜው ተጠቃሚ (beneficiary) መሆኑን ማስረዳት ናቸው፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልተጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/alehig
https://t.me/lawsocieties
#አለሕግ #ህግ  #AleLaw #አለጠበቃ #አለሕግአማካሪ #አለሕግ ነገረፈጅ #አለShare #lawsocieties
ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ህግ ባለሙያ ያማክሩ!
#አለሕግ #AleHig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
በጌጣጌጥ ላይ የሚከፈል የኤክሳይስ ታክስ

በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 67/2013 መሰረት፡-
‹‹
1. የከበሩ ማዕድናትን (አልማዝ፣ ወርቅ፣ ብር እና ወይም ኦፖል ወ.ዘ.ተ) በከፊል የያዙ ጌጣጌጦች የኤክሳይስ ታክስ ይከፈልባቸዋል፡፡

2. በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው ቢኖርም በጌጣጌጥነት ያልተሰራ ጥሬ የከበረ ማዕድን (አልማዝ፣ ወርቅ፣ ብር፣ ኦፖል ከእነዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆኑት) የኤክሳይዝ ታክስ አይከፈልበትም፡፡

3. በጌጣጌጥ ላይ የኤክሳይስ ታክስ የመክፈል ግዴታ ጌጣጌጡ እንደ ተመረተ ይቋቋማል፡፡

4. ለጌጣጌጥ አምራቾች ጥሬው የከበረ ማዕድን እንደ ጥሬ እቃ ይቆጠራል፡፡

5. የከበሩ ማእድናትን (አልማዝ፣ ወርቅ፣ ብር፣ ኦፖል ከእነዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ) የሚያመርቱ የማእድን ኩባንያዎች ለኤክሳይዝ ታክስ የመመዝገብ ግዴታ የለባቸውም፡፡

6. ጌጣጌጥ የሚያመርቱ ድርጅቶች ያመረቱትን ጌጣጌጥ የሸጡበትን የማስረከቢያ እና የሽያጭ ሰነድ መያዝ አለባቸው፡፡

7. የጌጣጌጥ አምራቾች በተፈቀደለት አምራችነት የመመዝገብ እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡

ምንጭ፡- ገቢዎች ሚኒስቴር
#EthiopianBusinessDaily
ይህ መንግስታዊ ነውር ነገ በእያንዳንዳችን ላይ የሚደርስ ነው!

" ከደመወዝ የሚያግድ ደብዳቤው በተፃፈ በ13 ቀኑ ዛሬ ማገጃው ደርሶኛል"

"የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጥቁር ልብስ ለብሳችሁ ቢሮ አትገቡም ለምን ተባልን በሚል ድምፄን በማሰማቴ ከስራና ደመወዝ የሚያግድ ደብዳቤው በተፃፈ በ13 ቀኑ ዛሬ ማገጃው ደርሶኛል "
Beletu Zeleke Mersha
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ #አለ_Share #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
በቆዳ ስፋታቸው 10 ቀዳሚ የአፍሪካ ሀገራት እነማን ናቸው?

ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጀሪያ አልጀሪያ ቀዳ ስትሆን፤ ኢትዮጵያም በዝርዝሩ ተካታለች።

በአፍሪካ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ የሆነችው ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጀሪያ ስትሆን 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ስኩዬር ኪሎ ሜትር ስፋት አላት።

ከአልጀሪያ በመቀጠልም በመካከለኛው አፍሪካ የምትገኘው እና የበርካታ አምቅ ማዕድናት ባለቤት የሆነችው ዲሞክራቲክ ኮንጎ በ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ስኩዬር ኪሎ ሜትር ስፋት ሁለተኛዋ ሀገር ተብላለች።

ዝርዝሩን ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/africa-10largest-countries-by-area
የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ዲያቆን ጌታቸው ላይ የ1 ዓመት ከ8 ወር የእስራት ቅጣት ተወሰነበት ።
...
በምስራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ወጣት ላይ የ1ዓመት ከ8ወር የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን ፋስት መረጃ ከጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተከሳሽ ዲያቆን ጌታቸው አለልኝ አግባብ ባለው የቤተሰብ ህግ ከተፈቀደው ውጭ ለአካለ መጠን ያልደረሰች ልጅ ለማግባት በማሰብ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 11፡0ዐ ሲሆን በግ / ወይን ከተማ አስተዳደር ዐ1ቀበሌ ልዩ ቦታው አርሴማ ቤተክርስቲያን ውስጥ የግል ተበዳይ የ12 ዓመት ህፃንን በተክሊል ጋብቻ ወይም በሀማኖት ስርዓት ያገባት በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመው ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ልጅ ማግባት ወንጀል ዓ/ህግ የሰውና ጋብቻው ሲፈፀም የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃ በማያያዝ ክስ መስርቶ ተከሳሽም የዓ/ህግ ክስ በችሎት ተሰጥቶት የዓ /ህግ ክስ በችሎት ተነቦለት ክሱን እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ወንጀሉን መፈፀሙን አምኖ ነገር ግን ህፃናትን ማግባት በቤተክርስቲያ ህግ የተፈቀደ ነው ወንጀል አይደለም በማለት ተከራክሮ ፍ/ቤቱም የህግ ምስክሮችን ሰምቶ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ ቁ113/2 / መሠረት ፍ/ቤቱ ወደ ወንጀል ህግ አንቀጽ 648 /ሀ/በመቀየር እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ ግን የመከላከያ ምስክር አቅርቦ የአቃቢ ህግን ማስረጃዎች ባለማስተባበሉ በቀን 13/6/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ያስተምራል ተብሎ የታሰበውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ቅጣት ውሳኔ ተላልፎበታል ፡፡
#አለ_ህግ  #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ህግ #አለ_Share #lawsocieties