አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
July 24, 2021
the person charged with crime.” በማለት ይገልፃሉ፡፡ በመሆኑም የወንጀል ምርመራ የወንጀል የምርመራ መዝገቡን እስከ ማጠናቀቅ ድረስ ያለውን ሂደት ብቻ የሚመለከት አድርገው የሚያስቡና ተከሣሹንና በምርመራ ሂደት የተሰበሰቡትን ማስረጃዎች ለፍርድ ቤት በማቅረቡ ሂደት ምንም አይነት እገዛ ማድረግ እንደሌለባቸው የሚያስቡ መርማሪ ፖሊሶች “ የወንጀል ምርመራን እንደ መሠረታዊ ግብ ማሣኪያ ሂደት ሣይሆን ምርመራ ማጣራቱ በራሱ ግብ አድርገው የሚመለከቱ በመሆናቸው የአመለካከት ለውጥ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. #የወንጀል ምርመራ ልዩ ባህሪ ያላቸውና የወንጃል ሰለባ የሆኑ ሰዎች በመያዣነት የታገቱባቸው ወንጀሎች ተፈፅመው በሆነ ጊዜ ከላይ ከተገለፁት ተግባራት በተጨማሪ የወንጀል ሰለባ የሆኑትን ሰዎች ከተጋረጠባቸው አደጋ ለመታደግና አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያገኙ የሚከናወነውን ተግባር ያጠቃልላል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ሰውን አስገድዶ መሰወር፣ ጠልፉ፣ ንፁሐን ዜጎችን ማገትና መደራደሪያ ማድረግ የመሳሰሉት በሆነ ጊዜ ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪ የወንጀሉን ሰለባ ለማስለቀቅ የሚከናወኑ ተግባራትን ያጠቃልላል፡፡
ከፀጋዬ ደመቀ ገፅ
#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
July 24, 2021
#የወንጀል #ምስክሮችና ጠቋሚዎች #ጥበቃ
........
የወንጀል ድርጊትን ለመቆጣጥር እና ለመከላከል እንዲሁም ወንጀለኞች የወንጀል ድርጊት ከፈፀሙ በኋላ ተደብቀው እንዳይቀሩና ህግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ይህን ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በምስክርነታቸው ወይም በጠቋሚነታቸው ምክንያት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ከሚደርስባቸው አደጋና ጥቃት መከላከል አስፈላጊ ነው፡፡ ሀገራችንም ይህንኑ በመረዳት የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ህግ አውጥታ ሥራ ላይ ውሏል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የምስክር እና የጠቋሚዎች ምንነት፣ በአዋጁ የተካተቱ የጥበቃ እርምጃ ዓይነቶችን እና የጥበቃ ስምምነት እንዳስሳለን፡፡

የምስክር እና ጠቋሚዎች ምንነት

ጠቋሚ ወይም ምስክር ማለት በወንጀል ምርመራ፣ በወንጀል ክስ ወይም በወንጀል ማጣራት ሒደት መረጃ ወይም ምስክርነት የሰጠ ወይም ለመስጠት የተስማማ ሰው እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀፅ 2(1) ላይ ትርጓሜ ተሰጥቶታል፡፡

የጥበቃ ተጠቃሚነት እና ተፈፃሚነቱ

በአዋጁ አንቀፅ 2(2) የጥበቃ ተጠቃሚ ማለት ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር የጥበቃ ስምምነት የተፈራረመ ምስክር፣ ጠቋሚ ወይም የምስክር ወይም የጠቋሚ ቤተሰብ አባል ነው፡፡ በዚህ መልኩ ስምምነት የገባ ምስክር ወይም ጠቋሚ በአዋጅ ላይ የተቀመጡት የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ይደረጉለታል፡፡ ሆኖም እነዚህ የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ከፍተኛ የሰለጠነ የሰው ሀይል፣ ጊዜ፣ ገንዘብ እና ወጪን የሚጠይቁ በመሆኑ ከአገራችን እድገት እና የኢኮኖሚ አቅም አኳያ ለሁሉም ምስክሮች እና የወንጀል ጠቋሚዎች ከለላ እና ጥበቃ ማድረግ አይቻልም፡፡ በመሆኑም የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ማግኘት የሚቻለው በአዋጁ ላይ የተቀመጡት መስፈርቶች ተሟልተው ሲገኙ እንደሆነ በአዋጁ አንቀፅ 3 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚደረጉ የጥበቃ እና ጥንቃቄ እርምጃዎች ተፈፃሚ የሚሆኑት፡-

 በሕግ የተደነገገው የፅኑ እስራት መነሻ ከግምት ሳይገባ አስር ዓመትና ከዚያ በላይ በሆነ ፅኑ እስራት ወይም በሞት ሊያስቀጣ በሚችል የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪ ላይ የሚሰጥ ምስክርነትን ወይም ጥቆማን ወይም የሚካሄድ ምርመራን በሚመለከት ሆኖ:-

የወንጀል ድርጊቱ ያለምስክሩ ወይም ያለጠቋሚው ምስክርነት ወይም ጥቆማ በሌላ ማናቸውም መንገድ ሊረጋገጥ ወይም ሊደረስበት የማይችል ሲሆን እና

 በምስክሩ፣ በጠቋሚው ወይም በምስክሩ ወይም በጠቋሚው ቤተሰብ ህይወት፣ አካላዊ ደህንነት፣ ነጻነት ወይም ንብረት ላይ ከባድ አደጋ ይደርሳል ተብሎ ሲታመን ነው፡፡
ነገር ግን አዋጁ ይህንን መስፈርት ቢያስቀምጥም ፍትህ ሚኒስቴር እና የፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጥበቃ ተጠቃሚ ላልሆኑ ምስክሮችና ጠቋሚዎችም በአዋጁ አንቀፅ 4 ስር የተቀመጡ አንዳንድ ጥበቃዎችን እንደአስፈላጊነቱ ሊያደርግ እንደሚችል ይገልፃል፡፡

ይህም በሚስጥር መያዝ ያለበት ካልሆነ በስተቀር ለጠቋሚ ጥቆማ ባቀረበበት ጉዳይ ላይ ወቅታዊ መረጃና ምክር መስጠት እንዲመሰክር ለተጠራ ምስክር የጉዞና የውሎ አበል መስጠት
በበቀል የተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲታገድ ወይም እንዲሻር ማድረግ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የማካካሻ እርምጃ መውሰድ በበቀል እርምጃ ለደረሰ ጉዳት የህክምና አገልግሎት በመንግሥት ሆስፒታል በነፃ መስጠት ለምስክሩ ወይም ለጠቋሚው የምክር አገልግሎት መስጠት ወይም እንዲያገኝ ማድረግን የሚያካትት ነው፡፡

የጥበቃ እርምጃ ዓይነቶች

ለወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች የሚደረጉ የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች በአዋጁ አንቀፅ 4 ስር ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች እንደ ሁኔታው በተናጠል ወይም በጣምራ ለጥበቃ ተጠቃሚ ተፈጻሚ የሚደረጉ ሲሆን ይህም ፡-

 የአካልና ንብረት ደህንነት ጥበቃ

 የመኖሪያ ስፍራ መቀየርን ጨምሮ ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ ቦታ መስጠት

 ማንነትንና ባለንብረትነትን መደበቅ

 ማንነትን መቀየር

 ለራስ መጠበቂያ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ መስጠት

 መረጃ በተሰጠበት የወንጀል ድርጊት ያለመከሰስ

 መረጃ በሚሰጥበት የወንጀል ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊትም ሆነ በኋላ ተከሳሽ በጥበቃ ተጠቃሚው መኖሪያ ወይም የሥራ ቦታ ወይም ትምህርት ቤት አካባቢ እንዳይደርስ ማገድ

 የፍርድ ሂደት ተጀምሮ ምስክርነት እስከሚሰጥ ድረስ የምስክር ማንነት እንዳይገለጽ ማድረግ

 ምስክርነት በዝግ ችሎት እንዲሰጥ ማድረግ

 ምስክርነት በአካል ሳይታይ ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ ወይም ማንነትን በመሸፈን እንዲሰጥ ማድረግ

 ማስረጃ በኤሌክትሮኒክስ ወይም በሌላ የተለየ ዘዴ እንዲቀርብ ማድረግ

 በሚስጥር መያዝ ያለበት ካልሆነ በስተቀር ለጠቋሚ ጥቆማ ባቀረበበት ጉዳይ ላይ ወቅታዊ መረጃና ምክር መስጠት

 እንዲመሰክር ለተጠራ ምስክር የጉዞና የውሎ አበል መስጠት

 የጥበቃ እርምጃው የመኖሪያ ስፍራን ለውጥ ካስከተለ የጓዝ ማንሻ ወጪን መሸፈን

 በበቀል የተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲታገድ ወይም እንዲሻር ማድረግ ወይም
ተመጣጣኝ የሆነ የማካካሻ እርምጃ መውሰድ

 በበቀል እርምጃ ለደረሰ ጉዳት የህክምና አገልግሎት በመንግሥት ሆስፒታል በነጻ መስጠት

 በጥበቃ እርምጃው ምክንያት ለደረሰ የገቢ ማጣት ወይም በበቀል እርምጃ ለደረሰ የመሥራት ችሎታ ማጣት የመሠረታዊ ፍላጎት ማሟያ ወጪን መሸፈን

 በጥበቃ ሥር እያለ ለደረሰ ሞት የቀብር ማስፈጸሚያ ወጪ መሸፈንና ለቤተሰብ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ

 የጥበቃ ተጠቃሚው የሥራና የትምህርት ዕድል እንዲያገኝ መርዳት

 ለምስክሩ ወይም ለጠቋሚው የምክር አገልግሎት መስጠት ወይም እንዲያገኝ ማድረግን እንደሚያካትት በአዋጁ ላይ ተዘርዝሮ ይገኛል፡፡

የጥበቃ ስምምነት

በአዋጁ አንቀፅ 2(2) መሰረት የጥበቃ ተጠቃሚ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር የጥበቃ ስምምነት የተፈራረመ ምስክር፣ ጠቋሚ ወይም የምስክር ወይም የጠቋሚ ቤተሰብ አባል ሲሆን በአዋጁ አንቀፅ 8 መሰረት የአካልና ንብረት ደህንነት ጥበቃ፣ የመኖሪያ ስፍራ መቀየርን ጨምሮ ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ ቦታ መስጠት፣ ማንነትንና ባለንብረትነትን መደበቅ እና ማንነትን መቀየር ከተመለከቱት የጥበቃ ዓይነቶች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ ተግባራዊ ለማድረግ በሚኒስቴሩ እና በጥበቃ ተጠቃሚው መካከል የጥበቃ ስምምነት መፈረም አለበት፡፡ የጥበቃ ተጠቃሚው አካለ መጠን ያላደረሰ ወይም በፍርድ የተከለከለ ሰው ከሆነ የጥበቃ ስምምነቱ ከወላጆቹ ወይም ከአሳዳሪው ጋር የሚፈረም ሲሆን ጥበቃው የጥበቃ ተጠቃሚው አካለ መጠን ከደረሰ ወይም የህግ ችሎታውን መልሶ ካገኘ በኋላ የሚቀጥል ከሆነ ስምምነቱን የጥበቃ ተጠቃሚው ራሱ መፈረም እንዳለበት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

የጥበቃ ተጠቃሚ የሆነው አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ መረጃ ወይም ምስክርነት የሚሰጠው በወላጁ ወይም በአሳዳሪው ላይ ሲሆን፣ ወላጅ ወይም አሳዳሪ የሌለው ሲሆን፣ አስፈላጊው ጥረት ተደርጎ ወላጁን ወይም አሳዳሪውን ማግኘት ያልተቻለ እንደሆነ፣ ወላጁ ወይም አሳዳሪው በቂ ባልሆነ ምክንያት ፈቃዱን ሳይሰጥ ሲቀር ወይም በማናቸውም ምክንያት ፈቃዱን መስጠት ሳይችል ሲቀር ሚኒስቴሩ በአንቀፅ 9 መሰረት ከልጁ ጋር ልዩ የጥበቃ ስምምነት ሊፈራረም ይችላል፡፡.....................
January 4, 2023