አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ሙስናን መታገል በፋሽን ወይስ በፓሺን?

የልቦና ውቅር ለውጥ‼️

The Fighting against corruption with fashion or passion?

Key Note Speaker;
Samuel Kassahun:
Director of Transparency International Ethiopia
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

የትራንስፓረንሲ ኢንተናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ካሳሁን

እሁድ ምሽት 2:30 ቀጥታ ስርጭት

🔘 Live on Telegram 👈👈
https://t.me/lawsocieties
#በአለ_ህግ ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን።

ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰሙ ወደ ወይይቱ ይጋብዙ👆👆👆
https://t.me/lawsocieties
ዛሬ እሁድ #ችሎት ከምሽቱ 2:30 በሙስና የልቦና ውቅር ለውጥ‼️

By #Samuel Kassahun:
Director of Transparency International Ethiopia

#የእለቱ_ችሎት

በትራንስፓረንሲ ኢንተናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ካሳሁን ይመራል

#የችሎቱ_ጭብጥ
ሙስናን መታገል በፋሽን ወይስ በፓሺን
የልቦና ውቅር ለውጥ‼️

The Fighting against corruption with fashion or passion

#ውሳኔ
ችሎቱ ቢያመልጥዎት በሌሉበት የሚሰማ ይሆናል።

ቀጠሮው እሁድ ማታ በስልክዎት በ @lawsocieties የቴሌግራም ቻናል በመዝገብ ስዓት ቁጥር 2:30 የመገኘት መብትዎ የተከበረ ነው።

#ትዕዛዝ
ለከሳሽ እና ተከሳሽ ሙስናን መታገል በፋሽን ወይስ በፓሺን መዝገቡ ክፍት ነው።
ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይመለሱ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
#የሚነበብ#አለ_ህግ ስም አለበት
https://t.me/lawsocieties
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
ስለማንዋል ደረሰኝ ህትመት ፈቃድ አሰጣጥ እና አጠቃቀም በጥቂቱ
1.ግለሰብ ታክስ ከፋይ የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅበታል

- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ወይም ከተማ አስተዳደሮች የሚነግድ ወይም ቤት የሚያከራይ ዋና ምዝገባ ባከናወነበት ቦታ ደረሰኝ አስፈቅዶ ማሳተም፣

- በእያንዳንዱ ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ለሚያከናውነው ግብይት (ሽያጭ) ይህንን ደረሰኝ እንዲሰጥ፣

- የታተመው ደረሰኝ ተከፋፍሎ ሲሰራጭ የደረሰኙን ጥራዝ ዝርዝር የደረሰኝ ህትመት ፈቃድ ለሰጠው የታክስ ባለስልጣን በጽሑፍ ማሳወቅ፣

- የህትመት ፈቃድ የሰጠው የታክስ ባለስልጣንም ለታክስ ከፋዩ የፈቀደውን የደረሰኝ አይነትና ብዛትና ስርጭቱን ለሚሰራበት ክልል/ከተማ መረጃ መላክ፣

2.ድርጅት

- በስሩ ቅርንጫፎች ያሉት የንግድ ድርጅት ለቅርንጫፎቹ የሚጠቀምበት የታክስ ደረሰኝ ዋና ምዝገባ ባደረገበት ያሳተመውን ይሆናል፣

- ከአንድ በላይ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ ያለው ታክስ ከፋይ አሳትሞ በሚጠቀምበት ደረሰኝ ላይ ሁሉም ዘርፎች እና አድራሻቸው ተጠቃሎ መታተም ይኖርበታል፡፡

- በተለያየ ቦታ የቅ/ጽ/ቤቶቹ የሚጠቀሙት ተፈቅዶ የታተመውን ደረሰኝ መሆኑን፣ የታተመውን ደረሰኝ ተከፋፍሎ ሲሰራጭ የደረሰኙን ጥራዝ ዝርዝር የደረሰኝ ህትመት ፈቃድ ለሰጠው የታክስ ባለስልጣን በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር
https://t.me/lawsocieties
★ አቢሲኒያ ባንክ አዲስ የስራ ማስታወቂያ

Deadline: December 16, 2022

Abyssinia bank invites qualified applicants for the following Positions.

Position 1: Foreclosure Officer
Position 2: Senior Attorney – Foreclosure
Position 3: Senior Attorney– Corporate

🔻Place of work: Addis Ababa ( Head Office )

How to Apply Online??
👇👇👇👇👇
https://effoysira.com/2022/12/12/abyssinia-bank-jobs-december-2022/
ባለሥልጣኑ ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሁን በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ አሳሰበ‼️
==========.........==========
ባለሥልጣኑ አሁን በግል የከፍተኛ ትምህርት ቋማት በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን አግባብ ማየት አስፈላጊ ሆኖ በማግኝቱ እውቅና በሰጣቸው የትምህርት መስኮች በትምህርት ላይ የሚገኙ የተማሪዎችን የስም ዝርዝር የያዘ መረጃ በሶፍትና በሀርድ ኮፒ በማጠናቀር በ30 ቀናት ውስጥ እንዲልኩ አሳስቧል፡፡
የሚላከው የተማሪዎች መረጃ በፕሬዝዳንት ወይም በበላይ ኃላፊ ተፈርሞ መውጣት እንዳለበት ከዚህ ውጪ ፈራሚ አካል ካለ ስምና ኃላፊነት የሚገልጽ ደብዳቤ በነዚሁ የበላይ ኃላፊዎች እንዲገለጽ እና የተማሪዎችን መረጃ በተናጥል በሚልኩ ተቋማት ላይ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ገልጿል፡፡
https://t.me/lawsocieties
ስለ ብርበራ
በዛሬው ‘ከነጋሪት ገፃች’ አምዳችን “ብርበራ”ን የሚመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችን ልንጠቁም ወደድን

 ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር ቤቶን መበርበር አይችልም።

 ከፍርድ ቤት በተለየ ካልታዘዘ በቀር ብርበራ የሚደረገው ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።

 ማንኛውም የብርበራ ማዘዣ የሚበረበረውን እና የሚያዘውን ዕቃ ማመልከት ያለበት ሲሆን መርማሪው ፖሊስ ወይም አብሮት ያለ የፖሊስ አባል በማዘዣው ላይ ከተመለከተው ውጭ ሌላው ዕቃ መያዝ አይችልም።

 መርማሪው ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በማዘዣ ትዕዛዙ የተመለከተውን ዕቃ በሚይዝበት ጊዜ የተያዘውን ዕቃ ዝርዝር መያዝ ያለበት ሲሆን ከተቻለ ገለልተኛ የሆነ ሰው ሊስቱ ላይ እንዲፈርምበት ይደረጋል።

ምንጭ፡- የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ
https://t.me/lawsocieties
ጁዌሪያ መሀመድን የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል በሞት ቅጣት እንዲቀጣ ተወሰነበት

የሶማሌ ክልል ምክር ቤትና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ጁዌሪያ መሀመድ ኢብራሂምን በጅግጅጋ አየር ማረፊያ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል በሞት ቅጣት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

ጥቅምት 15 ቀን 2015 በሶማሌ ክልል ገራል ዊልዋል አየር ማረፊያ የክልሉ ምክር ቤት እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆነችውን ጁዌሪያ መሀመድ በአየር ማረፊያው በሥራ ላይ ከነበረ የፌደራል ፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል።

በጅግጅጋ ከተማ የጅግጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትላንት በዋለው ችሎት፤ ጁዋሪያ መሐመድን በመግደል ተጠርጥሮ ክስ የተመሰረተበት የፌደራል ፖሊስ አባል በሞት እንዲቀጣ የወሰነ ሲሆን፤ ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብም የይግባኝ መብቱ የተጠበቀ ነው ተብሏል።

ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በተፈጠረው ክስተት ከጁዌሪያ መሀመድ ሞት በተጨማሪ ሌሎች አራት ሰዎች መቁሰላቸውን የክልሉ ፖሊስ ማስታወቁ ይታወሳል።
https://t.me/lawsocieties
የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብ

የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብ ደንብ ቁጥር 410/2009 በደንብ ቁጥር 485/2014 እና በደንብ ቁጥር 520/2014 ተሻሽሏል። ይህንን ማሻሻያዎች በአንድ በማካተት በነጋሪ መተግበሪያ አካትተናል። ደንቡን እና ማሻሻያዎቹን በአንድ ቦታ ከነጋሪ መተግበሪያ ያግኙ፤

ደንብ ቁጥር 410/2009 - ስለፌደራል የገቢ ግብር የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የገቢ ግብር ደንብ
http://negari.abyssinialaw.com/laws?id=162