አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፍርድ ቤቶች ስልጣን
የፍርድ ቤቶች አንድን ክርክር አይተዉ አከራክረዉ ለመወሰን ስልጣን አላቸዉ የሚባለዉ በህግ ተወስኖ ሲሰጣቸዉ ነዉ፡፡

የፍርድ ቤቶችን ስልጣን ለይተዉ ከቀረቡ ህጎች መካከልም የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013፣ የተሻሻለዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ቁጥር 361/1995፣ የኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ስነ-ስርአት ሕግ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

የፍርድ ቤቶች ስልጣንም ሲባል ከማህበራዊ ፍርድቤት ተነስቶ እስከ ፌደራል ፍርድ ቤቶች ያሉትን ያካትታል፡፡

የአንድ ፍርድ ቤት ስልጣንም ሊወሰን የሚችለዉ፡-
1. በሚከራከሩበት ንብረት የዋጋ መጠን
2. በተከራካሪ ወገኖች ማንነት 
3. የሚከራከሩበት ንብረት የሚገኝበት ቦታ
4. ተከራካሪ ወገኖች የሚገኙበት ቦታ
5. በዉል ጉዳይ ከሆነ ዉሉ የተፈረመበት ቦታ፣ ሊፈጸምበት የታሰበዉ ቦታ በመሳሰሉት
6. በሚከራከሩበት ጉዳይ የግዝፈት መጠን እንዲሁም በሌሎች ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ ይወሰናል፡፡
የከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ስልጣንን በተመለከተ
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ላይ ስንመለከት አንቀጽ 4(16) ላይ የወንጀል ጉዳዮችን የሚያይበት ስልጣኑ የተለየ ሲሆን በፍትሐብሔር ጉዳዮች ዙሪያ አንቀጽ 5(ደ) ስር ተዘርዝረዉ ይገኛሉ፡፡
የተሻሻለዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ቁጥር 361/1995 በሌላ መልኩ ደግሞ በአንቀጽ 41 ላይ የፍትሐብሔር እና ወንጀል ስልጣናቸዉን አስቀምጧል
ይህን ካልን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያሉት ፍርድ ቤቶች  የመጀመሪያ ደረጃ እና  ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ናቸዉ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ለከተማዉ የተሰጠዉን የፍትሐብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች አጠቃሎ የሚያይ ሲሆን የይግባኝ ሰሚ  ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን በይግባኝ ያያል።  ነገር ግን በይግባኝ ፍርድ ቤቱ በተሰጠዉ ዉሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን በአገሪቱ ባሉ  ፍርድ ቤቶች የተሰጠን የመጨረሻ ዉሳኔ የማየት ስልጣን ለተሰጠዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ማቅረብ ይቻላል። በመጨረሻም ህገ መንግስታዊ ዉሳኔ ለሚያስፈልጋቸዉ ጉዳዮች የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፍትህ ስርዓቱን የመጨረሻ ዉሳኔ ይሰጣል።
ወደ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስንመጣ  ከከተማ ፍርድ ቤቶች የሚለያቸዉ 3 እርከን ስላላቸዉ ነው። የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ፣ ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ናቸዉ። የፍርድ ስልጣናቸዉም በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ላይ ተለይቶ ተቀምጥዋል። አንድ ተከራካሪ ወገንም የመጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክሩን አቅርቦ ዳኝነት የጠየቀበት ጉዳይ ዉድቅ ቢደረግበት የይግባኝ ቅሬታዉን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚያቀርብ ሲሆን የመጀመሪያው ዉሳኔ ከጸና ጉዳዩን ለሰበር ችሎት አቅርቦ የህግ ስህተት ካለ ከማሳረም ዉጪ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን አቅርቦ ለሁለተኛ ግዜ ይግባኝ ማቅረብ አይችልም። ይህም ማለት አንድ ጉዳይ ከአንድ ግዜ በላይ ይግባኝ ሊባልበት አይችልም። የከፍተኛ ፍርድ ቤትም በመጀመሪያ ፍቅደ ስልጣኑ ያየዉን ክርክር ይግባኝ ሊባልበት የሚችለዉ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሆናል።
ዉበአለም መስፍን የቦ/ክ/ከ/ፍ/ጽ/ቤት/የህ/ስ/ም/መ ዳይሬክቶሬት ዐ/ህግ
https://t.me/lawsocieties
ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)

ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COUNCIL (EHRCO)
የግማሽ ቀን አውደ ጥናት ላይ ውይይት እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በበጎ አድራጎት ማህበራት አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ሐገር በቀል ድርጅት ሆኖ በ1984 ዓ.ም የተመሰረተና በምዝገባ ቁጥር 1146 ከ02/11/11 ዓ.ም ጀምሮ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዳግም ተመዝግቦ በህጋዊነት የሚንቀሳቀስ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል የሰበዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ነው። ኢሰመጉ ለትርፍ ያልተቋቋመ ነፃና ገለልተኛ ከማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሃይማኖት ተቋም፣ የብሄረሰብ ቡድን፣ ማህበራዊ መደብ ወዘተ የማይወግን የሰብዓዊ መብቶች ተሞጋች ተቋም ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
የምቹ የሥራ ሁኔታዎች እና ፍትህ የማግኘት ሂደት
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት (ኢሰመድህ) (ንዑስ አመልካች) ከአክሽን ኤድ ኢትዮጵያ (AAE) (ዋና አመልካች)፣ የህዝብ ጤና ኢትዮጵያ (HE)፣ የኢትዮጵያ ሴቶች እና ህጻናት ማህበራት ህብረት (UEWCA) እና አማኑኤል ልማት ድርጅት (EDA) (ንዑስ አመልካቾች) ጋር በመተባበር ከኖርዌይ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት ትብብር ኤጀንሲ (NORAD) በተገኘ ድጋፍ “በኢትዮጵያ ብዝዛን፣ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን፣ የግዳጅ ስራ እና ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን መግታት” የተሰኘ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረትም በስሩ ከያዛቸው ድርጅቶች መሃከል የኢትዮጵያ ሱብአዊ መብቶች ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ሰራተኞች መብቶች ተሟጋች ጋር በመሆን ይህን ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት ኢሰመጉ በግለሰቦች የምቹ የሥራ ሁኔታዎች እና ፍትህ የማግኘት ሂደት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የግማሽ ቀን የምክክር አውደ ጥናት ለተለያዪ የመንግስት ተቋማት፣ ለቀጣሪ ድርጅቶችና ለሰራተኛና አሰሪ አገናኝ ድረጅቶች አዘጋጅቶ የተለያዩ የድርጅት ተወካዮች  በተገኙበት ዛሬ ህዳር 30/2015 በካሶፒያ ሆቴል ከ 2፡30 ሰዓት ጀመሮ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
https://t.me/lawsocieties
አካልን ነፃ ስለ ማዉጣት (Habeas Corpus)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሰዉ ልጆች ሰዉ በመሆናቸዉና በተፈጥሮ ያገኟቸዉ ሰብአዊ መብቶችና ነፃነቶች የተከበሩ ናቸዉ፡፡ ከእነዚህ መብቶች አንዱ ህጋዊ ያልሆነ እስርን የመቃወም መብት (አካልን ነፃ ማዉጣት) አንዱ ነዉ፡፡ የሰዎች የነፃነት መብት የሚገደበዉ ሕጋዊ በሆነ ሥርዓት ብቻ ነዉ፡፡ ይህን ለመጠበቅ ሲባል የአያያዝ ሥርዓትም ሆነ እስር ላይ የሚቆይበት ሁኔታ በሕግ በግልጽ እንዲደነገግ ይደረጋል፡፡ የአያያዝ ሕጋዊነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል የያዘዉ ፖሊስ በ48 ስዓት ዉስጥ ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መደረጉ የነፃነት መብትን ማረጋገጫ አንዱ መንገድ ነዉ፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ አካልን ነፃ ስለ ማዉጣት እና ተያያዥ ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡

አካልን ነፃ ማዉጣት(Habeas Corpus) ምንነት

አካልን ነፃ ማዉጣት /Habeas Corpus/ ቃሉ የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም "that you have the body" ማለት ሲሆን ወደ አማረኛ ሲተረጎም አካል (ሰዉ) ይዘሃል የሚል ይሆናል፡፡ ሀብየስ ኮርፐስ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ተገድዶ እንዳይዘዋወር የተከለከለ ወይም የታሰረ ሰዉ ከዚህ ክልከላ ወይም እስራት እንዲለቀቅ የሚጠየቅበት ሥነ-ሥርዓት ነዉ፡፡ ከእስር እንዲፈታ የሚጠይቅ ሰዉ የታሰረዉ የወንጀል ድርጊት ፈጽመሀል በሚል ቢሆንም ሀብየስ ኮርፐስ የፍትሐብሔር ጉዳይ ነዉ፡፡ አካልን ነፃ ማዉጣት /Habeas Corpus/ ፅንሰ ሀሳብ በመጀመሪያ ተገልፆ የነበረዉ እ.ኤ.አ 1215 ለእንግሊዛዉያን ነዋሪዎች ልዩ ልዩ ነፃነቶችና መብቶችን ይዞ ብቅ ካለዉ ትልቅ ሰነድ /Magna Charta/ ማግና ካርታ ነዉ፡፡ መርሁም የንጉሶች ሳይሆን የህግ የበላይነት እንዲኖር ማድረግ ነዉ፡፡ ማንም ሰዉ ከሕግ ዉጪ በማንም ሊያዝ፣ ሊታሰር፣ ሊታገት እና እንቅስቃሴዉም ሊገደብ አይገባዉም የሚሉ ዓለም አቀፋዊ መርሆችን አቅፎ የያዘ ነዉ፡፡ ነፃነት ሊገደብ የሚችለው በህግ ሥርዓት (Due Process of law) ጠያቂና ተጠያቂነት በሰፈነበት መልኩ ሊሆን ይገባል በማለት የማግና ካርታ የዉስጥ ይዘት ያስረዳል፡፡

የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (International Convention on Civil and
Political Rights)

ሀገራችን ያፀደቀችው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን በአንቀጽ 9(1) ማንኛዉም ሰዉ የግል ነፃነቱና ደህንነቱ እንዲረጋገጥለት መብት እንዳለው አመልክቷል፡፡ ማንኛዉም ሰዉ በህግ ከተደነገገዉ ምክንያትና ሥርዓት ዉጭ የግል ነፃነቱ አይነፈግም፡፡ በስምምነቱ አንቀጽ 9(4) መሰረትም ማንኛዉም በመታሰሩ ወይም በመያዙ ምክንያት ነፃነቱን የተነፈገ ሰዉ የእስራቱን ሕጋዊነት ወዲያዉኑ መርምሮ ያለአግባብ መታሰሩን ካረጋገጠ በነፃ እንዲለቀቅ እንዲያዝለት ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አለዉ፡፡

የአካል ነፃነት አቤቱታ አቀራረብ እና አወሳሰን ሥነ-ሥርዓት

አካልን ነፃ ማዉጣት ከህግ አግባብ ዉጭ የታሰረ ሰዉ ከዚህ እስር እንዲፈታ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ የፍትሐብሔር ጉዳይ ነዉ፡፡ ነገሩ የሚታየዉ በፍትሐብሔር መዝገብ ቢሆንም በወንጀል ሰበብ የታሰረዉ ሰዉ ይጠቀምበታል፡፡ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 177 መሰረት በወንጀል ሕግ ወይም በዚህ ሕግ የተነገረዉን መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤት ሳይወስንበት ወይም ሳይፈርድበት ማናቸዉም ሌላ ትዕዛዝ ሳይሰጥ በማናቸዉም ሌላ ስልጣን ወይም በሌላ ሁኔታ ወይም በሌላ ሰዉ የተገደደ፣ እንዳይዘዋወር የተከለከለ፣ የተያዘ ወይም የታሰረዉ ሲኖር ይህ አድራጎት እንዲወገድለትና እራሱ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ሊያመለክት ይችላል፡፡ የመያዙ ወይም የመታሰሩ ትዕዛዝ የተሰጠዉ በሕግ ባለስልጣን ቢሆንም መያዙ ወይም መታሰሩ የተፈፀመበት ሁኔታ ሕግን ተቃራኒ በሆነ መንገድ ከሆነ አቤቱታ ማቅረብ ተገቢ ነዉ፡፡ በተገዳጅ የሚቀርበዉ ማመልከቻ በመሀላ-ቃል የተደገፈ ሆኖ የተያዘዉን ወይም የተገደደዉን ሰዉ ስም፣ የአስገዳጁን ሰዉ ስም፣ ተገዶ የተያዘበትን ስፍራ፣ ይህንኑ የሚያረጋግጡ ሰዎች እንዳሉ የምስክሮችን ስምና አድራሻ ዘርዝሮ የሚገለጽ ሊሆን ይገባል፡፡ የተያዘዉ ሰዉ ራሱ መቅረብና የመሀላ-ቃሉን መስጠት የማይችል ከሆነ ሌላ ሰዉ ሊያቀርብለት የሚችል ሲሆን በዚህ ሁኔታ አቤቱታውን የሚያቀርበው ሰው በሚሰጠዉ መሀላ ላይ ዋናዉ ባለጉዳይ ለመቅረብ ወይም ማመልከቻ ለመፃፍ ያልቻለ መሆኑን ጨምሮ ሊገለፅ ይገባል፡፡

በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 15(2)(ቀ) መሰረት የሚቀርበዉን አቤቱታ የመቀበል ስልጣን ሙሉ በሙሉ የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነዉ፡፡ በዚህ መሠረት ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ማመልከቻ ሲቀርብለት አስገዳጁ ወይም አሳሪዉ ተገዳጁን ወይም ታሳሪዉን ሰዉ ይዞ እንዲቀርብና ይህንንም ሰዉ የማይለቅበትን ምክንያት እንዲያስረዳ በመጥሪያዉ ላይ የመቅረቢያዉን ቀነ ቀጠሮ ወስኖ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ እንዲሁም ለፍርድ ቤቱ በቀረበዉ ማመልከቻ ላይ ነገሩን በምስክርነት ለማስረዳት ይችላሉ ተብለዉ የተጠቀሱት ምስክሮች እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል (የፍ/ /ሥ/ሥ/ህ/ቁ 178)፡፡

በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 179 መሰረት ጉዳዩ በሚሰማበት ቀን በቀረበዉ ማመልከቻ ላይ የተገለፀዉን አቤቱታ እዉነተኛነት ፍርድ ቤቱ ይመረምራል፡፡ ስለማስረጃዉም ተገቢ መስሎ የታየዉን ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ አመልካቹ የተያዘዉ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከተረዳዉ ወዲያዉኑ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ የዚህ ዓይነት ትዕዛዝ ከፍርድ ቤት ከተሰጠ በኋላ ማናቸዉም ሌላ ትዕዛዝ እንዲኖር ሳያስፈልግ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ብቻ በቂ ሆኖ መፈፀም አለበት፡፡ በሌላ በኩል ማመልከቻዉ ላይ የተገለፀዉ የአቤቱታ ቃል በማናቸዉም ሁኔታ ለፍርድ ቤቱ የሚያጠራጥር መስሎ የታየዉ እንደሆነ አቤት ባዩ ዋስ ጠርቶ እንዲለቀቅ ሊያዝ ይችላል፡፡ ይህ ዋስትና የገንዘብ ማስያዝ ወይም የሰዉ ዋስ ሊሆን ይችላል፡፡ በዋስትናዉም የሚገባዉ ግዴታ እንዲለቀቅ ያደረገዉ ፍርድ ቤት በፈለገዉ ጊዜ እንዲቀርብ ወይም ማንኛዉንም ፍርድ ቤቱ የሚሰጠዉን ትዕዛዝ አክብሮ እንዲፈፅም የሚያስገድድ ይሆናል ፡፡

ማጠቃለያ

አካልን ነፃ ማውጣት (Habeas Corpus) የሰዎች ሰብአዊ ነፃነት በህገወጥ መንገድ እንዳይጣስ ለመከላከል አስፈላጊ የሆነ ሥርዓት ሲሆን በሀገራችንም የህግ ጥበቃ ያለው መሆኑን በመረዳት ህብረተሰቡ ከህግ ውጪ የሆነ መያዝ ወይም መታሰር ሲያጋጥመው ይህን ህጋዊ መፍትሄ በመጠቀም መብቱን በማስከበር እና ህገወጥነትን በመካላከል የበኩሉን ሊወጣ ይገባል፡፡


በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም የቋሚ ንብረት ሥም ዝውውር አገልግሎት፤ ከትናንት ኀዳር 29 ቀን 2015 ጀምሮ በጊዜያዊነት መታገዱ ተገልጿል።

አገልግሎቱ የታገደው በከተማዋ ህገ ወጥነትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሒደት ውጤታማ ለማድረግ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

ለሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ለሚመለከታቸው አካላትም የተላለፋው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ትዕዛዝ መሰጠቱንም የከተማ አስተዳደሩን ዋቢ አድርጎ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
#tikvahethiopia
https://t.me/lawsocieties
የአመት ፈቃድ ህግ
https://t.me/lawsocieties
አንድ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ እና ማስረጃ በመመርመር ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ መልሱን አዘጋጅቶ እንዲቀርብ የታዘዘው እና ቀጠሮ የተሰጠው ከ 10 ቀን ባነሰ ጊዜ ውሰጥ ከሆነ የተከሳሹን የመከላከል አና የመስማት መብቱን የሚነፍግ በመሆኑ በቂ ጊዜ ተሰጥቶት የመከላከያ መልሱን እና ክርክሩን እንዲያቀርብ መደረግ አለበት።
የሰ/መ/ቁ154727 ቅፅ 23
የንግድ_ምዝገባ_ፈቃድ_እና_ድኅረ_ፈቃድ_ኢንስፔክሽን_መመሪያ_ቁጥር_935.pdf
946.7 KB
አዲስ መመሪያ
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፀደቀ አዲስ “የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና ድኅረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መመሪያ ቁጥር 935/2015 “፡፡
ስሞትን ያለፈቃድ መለወጥ ወይም በሌላ ስም መጠራት እንደማይችሉ ያውቃሉን?
https://t.me/lawsocieties
ሁለት መቶ ሃያ አንድ ባለአክሲዮኖች በአንድ መቶ ሚሊዮን ብር ካፒታል የንግድ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር መሰረቱ፤
****
ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም፡ በአዲሱ የመንገድ ትራንስርት አዋጅ ቁጥር 1274/2014 መሠረት ፈጣን ሎጂስቲክስ እና ትሬዲንግ ሼር ካምፓኒ በ25 ሚሊየን ብር የተከፈለና በ75 ሚሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል በ221 ባለአክሲዮኖች ከህዳር ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መመስረቱን ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ መርሻ ፀጋዬ ገለፁ፡፡

ዋና ስራ አስኪያጁ እንዳሉት ቀደም ሲል በማህበር ተደራጅተው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ኦፕሬተሮችን በማወያየት እና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ አክሲዮን ማህበሩ እውን ሆኗል፡፡ በግለሰቦች ላይ የተመሰረተና ተወዳዳሪነቱ ውስን የሆነውን የማህበራት አደረጃጀት በማስተካከል በንግድ ህግ መሠረት ለትውልድ የሚተላለፍ ተወዳዳሪ የንግድ ተቋም ለመመስረት ተችሏል ብለዋል፡፡ ከባለቤትነት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችና ሌሎች ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮችን ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በተደረጉ ውይይቶች እልባት መስጠት መቻሉን አክለው ለአክሲዮን ማህበሩ ምስረታ የተደረጉ ውይይቶች ጉልህ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል፡፡

የኦፕሬተሮች አደረጃጀት መመሪያ ቁጥር 35/2013ን ለማሻሻል እየተደረገ ባለው ሂደት ተጨማሪ ግብአቶች እንዲካተቱ አስተያየት በመስጠት በጋራ እየተንቀሳቀስን እንገኛለን ብለዋል፡፡ አቻ ማህበራት አዋጁ በሚፈቅደው ልክ ወደ አክሲዮን ማህበር አልያም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና በግል ጭምር እንዲደራጁ ለማገዝ ልምድ እያካፈሉ እንደሚገኙ አቶ መርሻ አክለው ገልፀዋል፡፡ አዋጅ ቁጥር 1274/2014 በሀገራችን ግዙፍ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች የሚፈጠሩበት እድል መኖሩን አመላክቷል ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ ህጋዊ ሂደቱን ተከትሎ ወደ ዘርፉ ቢገባ አዋጪ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ 22 ዓላማዎችን ይዞ የተመሰረተው ተቋሙ የአዋጪነት ጥናቶችን በማድረግ በሌሎች ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አብራርተዋል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ትዕግስት ጌታሁን በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት ማህበራትን ወደ ንግድ ድርጅት በማሸጋገር ተወዳዳሪ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀጠናዊ ትስስርን ሊያጠናክር በሚችል መልኩ እንዲደራጁ አዋጁ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

ቀደም ሲል የነበረው የማህበራት አደረጃጀት ግልፅነት የሚጎለው፣ ማህበራት የንግድ ስራ ቢሰሩም ህጋዊ ሰውነት ያልተሰጣቸው፣ ከተቋቋሙበት ዓለማ ውጪ የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን አስታውሰው አዋጅ ቁጥር 1274/2014 ለእነዚህ የአሰራር ክፍተቶች መፍትሔ ይዞ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
አዋጁ ቀጠናዊ የትራንስፖርት ትስስርን በማጠናከርና ቀልጣፋ ዓለም ዓቀፍ የሎጂስቲክስ አፈጻጸም ውጤታማነትን በማጎልበት ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ በሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የንግድ የመንገድ ማመላለሻ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች የሚያቋቁማቸውን የንግድ ተቋሞች የትራንስፖርት አሰራር የሚመለከት መመሪያ በማውጣት ለእነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች የሙያ ብቃት ደረጃ እና የኦፕሬተርናት ብቃት መስፈርት በመስጠት ውጤታማ ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
አዋጅ ቁጥር 1274/2014 በንግድ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ሥራ ላይ ለመሰማራት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በቅድሚ በሕግ ሥልጣን ከተሰጠው አካል የትራንስፖርት ንግድ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት፤ በንግድ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ለማከናወን ማንኛውም ሰው የኦፕሬተርነት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን መስፈርት ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሰረት እንደሚከናወን ይደነግጋል፡፡
በትራንስፖርት አዋጅ ቀጥር 468/1997 መሠረት ተመዝግበው የነበሩ የትራንስፖርት ማህበራት አዋጅ ቁጥር 1274/2014 ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ወደ ንግድ ማህበርነት የመለወጥና አስፈላገውን የኦፕሬተርነት የብቃት ማረጋገጫ መውሰድ እንዳለባቸው አዋጁ ይደነግጋል፡፡
**
ministryoftransportethiopia
ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ዜናና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ፤
የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ (preliminary objection)
ሲባል ምን ማለት ነው?

______________________............
የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ (preliminary objection)______________________............
ብዙውን ጊዜ በዜና አውታሮች ፍርድ ቤቱ በነ እገሌ የክስ ሂደት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ ሲባል እንሰማለን ለመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ሲባል ምን ማለት ነው? ለዛሬ በዚሁ አርዕሰት ላይ እናንተን ያስተምራል ያልነውን ጥንቅር ወደናንተ ልናደርስ ወደድን ተከታተሉን፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ተከሳሹ ስለ ክሱ ማመልከቻ ፎርም ወይም በክስ ማመልከቻ የተገለፀውን ነገር የሚቃወምበት ስርዓት ነው፡፡የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
አላማ ፍርድ ቤት እና ተከራካሪ ወገኖች ወደ ክርክሩ ፍሬ ነገር ሳይገቡ መነሳት ያለባቸውን ነጥቦች በማንሳት ውሳኔ በመስጠት ጊዜ መቆጠብ ነው፡፡ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ውስጥ
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊነሳባቸው የሚችሉ ነጥቦች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የክሱን ይዘት በተመለከተ ሊቀርብ ይችላል፡፡
ይህም ማንኛውም የክስ ማመልከቻ ቀንና ዓመተ ምህረት የተፃፈበት እና የተፈረመበት እንዲሁም
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እንዲገልፅ ያስፈልጋል፡፡እነዚህም ተከሳሽ የተከሰሰበት ወንጀል እንዲሁም የወንጀሉ መሰረታዊ ነገር እና ሁኔታዎች፤ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ስፍራ
ተገቢ በሆነ ጊዜም በደል የደረሰበት ሰው ስም ወይም ወንጀሉ የተፈፀመበት ንብረት፣ተከሳሽ ድርጊቱን በመፈፀም የተላለፈው የህግ አንቀጽ መያዝ አለበት፡፡
ክሱ ግልፅ እና የተከሳሽን የመከላከል መብት የማያጣብብ መሆን አለበት፡፡ በመሆኑም እነዚህ ነገሮች ግልፅ ባልሆኑ እና ባልተሟሉ ጊዜ ተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ ማንሳት ይችላል፡፡ በተጨማሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 130/2 ስር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚያስነሱ ነገሮች ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡
• ተከሳሽ በዚሁ ነገር ክስ በሌላ ፍርድ ቤት ተጀምሮ በቀጠሮ ያለ መሆኑ
• በዚሁ ክስ ከዚህ በፊት ተከሶ ነፃ የወጣ ወይም የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑ
• ክስ የቀረበበት ወንጀል በይርጋ ህግ የታገደ ወይም ምህረት ወይም ይቅርታ የተደረገለት
መሆኑ ከተረጋገጠ፡፡
ይርጋ ማለት አንድ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞ ክስ ለማቅረብ በ1996ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማለት ነው፡፡
በወንጀል ህግ አንቀጽ 219 ስር እንደተደነገገው የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማከበጃ ወይም ማቅለያ
ሁኔታዎች ግምት ውሰጥ ሳይገቡ በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል የተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀል ድርጊቱን
ከፈፀመበት አንስቶ ነው፡፡ለምሳሌ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ወንጀሉ በተፈፀመ በአስር አመት ውስጥ ክስ መቅረብ አለበት፡፡አስር አመት ካለፈ ግን ክስ ማቅረብ አይቻልም ማለት ነው፡፡
• ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር በተከሰሰ ጊዜ እና ለብቻው ተነጥሎ ክሱ ባይታይለት የሚጎደው መሆኑን፣
• ክሱን ለማቅረብ በህጉ መሰረት ፈቃድ ያልተሰጠ መሆኑ ለምሳሌ ተከሳሽ በአለም አቀፍ ህግ ዲፕሎማቲክ ኢሙኒቲ የማይከሰስ እንደሆነ፣
• በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም በዚህ የወንጀል ክስ ሊሰጥ የማይገባ መሆኑ፣
• ለፈፀማቸው ተግባሮች ኀላፊ አለመሆን ፤ለምሳሌ የተከሳሽ አድሜ ከዘጠኝ አመት በታች
ከሆነ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 48 ላይ እንደተመለከተው ማንም ሰው በእድሜ ፣ በህመም ፣ባልታሰበ የእድገት መዘግየት ወይም ጥልቅ በሆነ የአዕምሮ የመገንዘብ ችሎታ መቃወስ ወይም የወንጀል ድርጊት በሚፈፅምበት ጊዜ የድርጊቱን አይነት ወይም ውጤት ለመገንዘብ
ወይም በዚህ ግንዛቤ መሰረት ራሱን ለመቆጣጠር በፍፁም ያልቻለ ሲሆን ኢ-ኃላፊ ስለሚሆን አይቀጣም፡፡
ከላይ የተዘረሩት ነጥቦች ባጋጠሙ ጊዜ ተከሳሽ እራሱ ወይም ጠበቃ ካለው በጠበቃው አማካኝነት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሊያነሳ ይችላል፡፡
ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ሲጠይቀው ተከሳሹ የክሱን ማመልከቻ ወዲያውኑ ካልተቃወመ በቀር ቆይቶ እንዲህ ያለውን መቃወሚያ ነገሩ በሚሰማበት በሌላ ጊዜ ሊነሳ የሚችለው ፍርድ
ቤቱን የሚፀና ፍርድ ለመስጠት የሚያግደው ከሆነ ብቻ ነው (ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.130/3)፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ አንድ ጊዜ ተከሶ በተቀጣበት ወንጀል ድጋሚ ሊከሰስ እንደማይገባ ይህም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ እንደሚችል የሚያሳየንን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ72304 የሰጠውን ውሳኔ እንደ አብነት ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
ጉዳዩ ባጭሩ ተከሳሽ በስር ፍርድ ቤት በቀላል አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሶ ከተቀጣ በኃላ ተበዳይ በመሞታቸው ዐቃቤ ህግ ድጋሚ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ክስ ሲያቀርብ ተከሳሽ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሳያነሳ ቀርቶ በኃላ በተመሳሳይ ወንጀል ድጋሜ ያለመከሰስ መብት principle of double jeopardy ይነካል ማለቱ ተገቢ
አይደለም ብሎ የተከራከረበት ጉደይ ነው፡፡

ሰበር በውሳኔ ዝርዘሩ ላይ እንዳስቀመጠው “ አንድ ሰው በወንጀል ህግ እና ስነ ስርዓት ተከሶ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ተቀጥቷል ወይም ነፃ ተለቋል የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ የወንጀል ክስ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 130 የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበው የክስ መቃወሚያና ማስረጃ
በመመርመር ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 131 ተደንግጓል፡፡

ሆኖም አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተከሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሜ ያለመከሰስ ያለመጠየቅ መብት መሰረታዊ እና ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ ክርክሩ በሚካሄድበት በማናቸውም ደረጃ ሊነሳ የሚችልና በማስረጃ ተረጋግጦ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ መሆኑ በውሳኔው
አስፍሯል፡፡
ከመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጋር ሊምታታ የማይገባው መቃወሚያ በማለት ተከራካሪ ወገኖች እንደ አስፈላጊነቱ ዐቃቤ ሕግም ይሁን ተከሳሽ በክርክር ወይም ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ጣልቃ የሚገቡበት ስነ ሥርዓት ነው፡፡
ለምሳሌ ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ለምስክሩ በዋና ጥያቄ ላይ መሪ ጥያቄ ቢቀርብ ወይም ምስክሩ ከተመለከተው ወይም ከሚያውቀው ነገር ባሻገር ግላዊ አስተያየቱን ወይም ግምቱንእንዲሰጥ ቢጠየቅ ወይም ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ቢጠየቅ ተከራካሪ ወገኖች
መቃወሚያ አለኝ ብለው ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ ምስክሩ መልስ እንዳይመልስ ማድረግ
ይችላሉ፡፡
ለዛሬ ካዘጋጀንላችሁ ጥንቅር በጉዳዩ ዙሪያ ዕውቀት እንደጨበጣችሁ ተስፋ
እናደርጋለን በቀጣይ በሌላ ፕሮግራም እስክንገናኝ መልካሙን ሁሉ ተመኝን ሰላም::
ፌናን ተጊበሉ
https://t.me/lawsocieties