አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በውላቸው ውሰጥ እነዚህ ዝርዝሮች ከሌሉበት ግን ክፍያው የሚፈፀምበት ቦታ በሻጩ አድረሻ እንደሆነ በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2309 ተደንግጓል፡፡ ሽያጩ የዱቤ በሆነ ጊዜ ደግሞ ዋጋው መከፈል ያለበት በውሉ ተገልፆ ከሆነ በውሉ መሰረት ካልተገለፀ ግን ገዢው የገዛውን ነገር ከተረከበ በኋላ ሻጩ እንደጠየቀ ወዲያውኑ መሆን እንዳለበት በህጉ አንቀፅ 2311 ተደንግጓል፡፡

#ማጠቃለያ

በአጠቃላይ የሽያጭ ውል መሰረታዊ ሀሳቦች ከላይ የተገለፁት ሲሆኑ የሸያጭ ውል በእለት ተእለት ኑሯችን የምንተገብረው ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል ድርጊት እንደመሆኑ በህጉ ዙሪያ ያለንን እውቀት በማዳበር እና ህጉ ተከትሎ በመንቀሳቀስ እራሳችንን ከአላስፈላጊ እንግልት መታደግ ይጠበቅብናል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
#Daily_Tips
Your personal data collected by messengers
#Ethiopianbusinessdaily
የውጭ ምንዛሬ
ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ተድርጓል።

ከዚህ ቀደም ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፎ በነበረው የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዕቃዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክና ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

ማሻሻያ የተደረገባቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች የሚከተሉት ናቸው ፦

1. በታሪፍ ቁጥር 9401. 9000 እና 9403. 9000 የሚመደቡ እቃዎች ክፍሎች ማምረቻ ግብአቶች፣

2. ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በውጭ ምንዛሬ የመሸጥ ፍቃድ ያላቸው ሬስቶራንቶችና ሱፐር ማርኬቶች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣

3. ባለ ኮከብ ሆቴሎች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስመጧቸው ዕቃዎችና

4. የቀረጥ ነጻ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች

የውጭ ምንዛሬ ክልከላው የማይመለከታቸው መሆኑ ተገልጽዋል፡፡

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ የ38 እቃዎች ዝርዝር በጥቅምት ወር   2015 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወሳል (ለማስታወሻ ከላይ ተያይዘዋል) ።

ምንጭ፦ ገንዘብ ሚኒስቴር
https://t.me/lawsocieties
ሰ-መ-ቁ 221716.pdf
824 KB
አሰሪና ሰራተኛ ህግ- ክፍያ ለዘገየበት የሚከፈል ቅጣት- አከራካሪ ክፍያ ሰ-መ-ቁ 221716
አብርሃም ዮሐንስ
የስራ ውል ከመቋረጡ በፊት ማስጠንቀቂያ በተለያየ መንገድ መስጠቱን የሚከራከር አሰሪ ፍርድ ቤት የማስጠንቀቂያ አሰጣጥ ስርዓቱ በህጉ አግባብ ባለመሆኑ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እንዲከፍል ሲወሰንበት ይህንኑ ክፍያ በማዘገየት በሚል ቅጣት ሊከፍል አይገባም።
ሰራተኛው የጠየቀው ክፍያ አከራካሪ ከሆነ አሰሪው ያመነውን ያህል በህጉ በተገለጸው ጊዜ ገድብ ውስጥ መክፈል እንዳለበት የአዋጁ በአንቀጽ 37 ያመለከታል። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው የክፍያው ዓይነትና መጠን እንደጉዳዩ ባህርይ የሚለያይ በመሆኑ አከራካሪ የሆነውን እና አከራካሪ ያልሆነውን በመለየት አሰሪው በህግ የተጣለበትን ግዴታ መፈጸም ይጠበቅበታል።
አብርሀም ዮሀንስ
Forwarded from Yehualashet Tamiru
It is to be recalled that the Ministry of Finance has banned 38 items from entering the country by restricting banks from opening L/C. Now, the Ministry of Finance amended this restriction on the following items:
• Inputs for production of items categorized under tariff classification No. 9401. 9000 (seats and others) and 9403. 9000 ( furniture and others)
• Those supermarkets and restaurants which have the license to receive payment in hard currency and import items by their own foreign currency
• Those ranked hotels imported items using their own hard currency
• Items imported by duty free shops
Source: Yehualashet Tamiru Tegegn
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁ 1234-2013 አንቀጽ 28

#ያስቀርባል /አያስቀርብም የሚወሰነው በአጣሪ ችሎት ሳይሆን ዋናውን ጉዳይ በሚያዩት አምስት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት ነው።

#ሶስት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት ስልጣኑ በሁለት ነገሮች ላይ ብቻ ነው

1- በአመልካቹ አቤቱታ ላይ የተጠቀሰው የህግ ስህተት በአዋጁ አንቀጽ ፪ ንዐስ አንቀጽ (፬) የሚወድቅ ስለመሆን ማጣራት። ለምሳሌ የምዘና ማስረጃን ጠቅሶ የሰበር አቤቱታ ካቀረበ አጣሪ ችሎቱ ውድቅ ያደርገዋል።

2- የሰበር አቤትታ የቀረበበት ውሳኔ በአዋጁ አንቀጽ ፲ አግባብ “የመጨረሻ ውሳኔ” መሆኑን ማጣራት

ሲጠቃለል በአዋጅ ቁጥር 1234 መሰረት ያስቀርባል/አያስቀርብም ስልጣኑ አምስት ዳኞች የሚገኙበት ዋናው ችሎት ነው።
መሠረታዊ የሕግ ስህተት እና የአጣሪ አጣሪ
(በአልማው ወሌ)
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 28 (3) ምን አስቦ ነው?
 ሁለት ጊዜ የማጣራት ስራ እንዲሰራ?፣
 ድሮውም ሆነ አሁን ያለው የሰበር አጣሪ ችሎትና የባለ 5/7 ዳኞች ሰበር ችሎት በተጨባጭ የሰሩት ወይም አሁን እየሰሩ ያሉት እንዴት ነው?፣
 የሰበር አቤቱታ ወደ 5 ዳኞች ሰበር ችሎት በሰበር አጣሪ ችሎት ከተመራለት በኋላ የሰበር ተጠሪን ሳይጠራ ባለ 5 ዳኞች ሰበር ችሎት ጉዳዩ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብሎ ሊዘጋ ይችላልን?፣
 አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩት ጭብጥ የሚለው በሰበር አጣሪ ነው ወይስ በባለአምስቱ ዳኞች ሰበር ሰሚ ችሎት?፣
 ባለ ሶስት ደኞች ሰበር አጣሪ ችሎቱ ለተጠሪ መጥሪያ መላክ አይችልም ማለት ነው?፣
 በዚህ ረገድ አሁን እየተሰራ ያለው አጣሪ ችሎቱ ጭብጥ መስርቶ ጉዳዩን ለባለአምስቱ ዳኞች እንዲቀርብ እና ተጠሪም በጭብጡ መሰረት መልስ በጽሁፍ እንዲሰጥበት ተገልጾ መጥሪያ ወጪ ማድረግ አይደለንም?...ከሆነስ ከሕግ ውጪ ነው የሚሰራው ማለት ነው?
 በአጠቃላይ የተጠቃሹ ንዑስ ድንጋጌ አቀራረጽ የሰበር አቤቱታ በሚታይበት ስርዓት ውስጥ የማጣራቱ ሂደት ሁለት ጊዜ (በባለ ሶስት እና በባለ አምስት ዳኞች ሰበር ችሎት) ሊታይ እንደሚገባ፣ ጭብጥ መስርቶ ተጠሪን መጥራት የሚችለው ባለአምስቱ ዳኞች ሰበር ሰሚ ችሎት መሆኑን በሚያስገነዝብ መልኩ የተደነገገ ሁኖ የሚታይ ሲሆን በተጨባጭ እየተሰራ ያለው ግን እንደ ንዑስ ድንጋጌው አገላለጽና አነጋገር አይደለም፡፡
 ስለሆነም ድንጋጌው ሕጉን በማርቀቅ ሂደት በተከሰተ ግድፈት (Poor Drafting) የተቀመጠ ነው? ወይስ ሆነ ተብሎ የማጣራቱን ሂደት ጥብቅ ለማድረግ የመጣ አዲስ አካሄድ ነው?፣ ባለ 5 ዳኞች ሰበር ሰሚ ችሎት ባለ 3 ዳኞች የሰበር አጣሪ ችሎት ዳኞች በአዋጁ አንቀጽ 2 (4) እና 10 መሰረት ጉዳዩ በሰበር ችሎቱ ሊታይ የሚገባው ነው ብለው ከወሰኑ በኋላ ይኼው ውሳኔያቸው በባለ 5 ዳኞች ታይቶ ውድቅ የሚሆን/ሌላ ጭብጥ ተመስርቶ ተጠሪ የሚጠራ ከሆነ የባለ 3 ዳኞች አጣሪ ችሎት አስፈላጊነትስ የቱ ላይ ነው?...... ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ይመስለኛል፡፡
ለማንኛውም የአዋጁ ድንጋጌ ይዘት የሚከተለውን ይመስላል፡፡
1234/2013
አንቀጽ 28 (1)፡-
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሰበር ችሎት የሚቀርቡ ጉዳዮችን ክርክር አመራር ሥነ ሥርዓትን በተመለከተ የሚያወጣው ደንብ እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲ መሠረት አቤቱታ በሰበር የሚሰማው አስቀድሞ ሶስት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት ውሳኔው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ንኡስ አንቀጽ (፬) እና አንቀጽ ፲ ላይ በተመለከቱት መሠረት በሰበር ችሎት መታየት አለበት ብሎ ሲወሰን ነው፡፡ ብሎ ይደነግጋል፡፡
ንዑስ ቁጥር ሶስት ደግሞ፡-
በአማርኛው ቅጅ፡-
-የሰበር ችሎቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሰረት የተመራለትን ጉዳይ መርምሮ አቤቱታ በቀረበበት ጉዳይ ላይ ያስቀርባል ብሎ ከተረዳ ጭብጥ በመያዝ በተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት በአመልካች ከቀረበው የሰበር ማመልከቻ እና መጥሪያ ጋር ይልካል፡፡ ይላል፡፡
በእንግሊዝኛው ቅጅ ደግሞ፡-
-When the Cassation Division to which the application is referred concludes upon examination of the application that the case has a merit, it shall frame issue and send the same with the Cassation application and summon to the respondent to reply in writing. ብሎ ያስቀምጣል፡፡
ሌላው የሠበር አጣሪ የሰበር አቤቱታውን በቃል ሲሰማ የሕግ ባለሙያ ያልሆነ አቤት ባይን እስኪ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አስረዳ ብሎ የሚጠይቅበት አሰራር የሕግ መሠረቱ ምንድን ነው?፣ ከሰበር ዓላማ ጋርስ ይሄዳል?
አጣሪ ችሎቱ አቤቱታውን ከሠማ በኋላ ውጤቱን በሬ/ጽ/ቤት ተከታታሉት !የሚለው አሰራር ምንጩ ሕግ ነውን? ፣ ለአቤቱታ አቅራቢ ጥሩ ያልሆነ የምርመራ ውጤቱ ወዲያውኑ ቢነገረው ሊደነግጥ/ሊጮህ ይችላል ብሎ አስቦ ይሆን? በግልጽ ችሎት የመሰማት መብትስ ውጤቱን መስማትንም አያካትትምን?
ለነገሩ አያስቀርብም የሚል ውጤት ወዲያው ሲነገራቸው መድኃኒት የጠጡና የወደቁ፣ ግቢውን በጩኸት የቀወጡ ....ተዝለፍልፈው የወደቁ ...ባለጉዳዮች ያጋጥሙ እንደነበር አስታውሳለሁ:: የሆነ ሁኖ ሕግ ገዥ መሆን የለበትም ወይ?
ባለ አምስት ዳኞች ችሎትስ የፍርድ አጻጻፍና አገላለጽ ሥርዓቱ በልማድ/ከመደበኛው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ) የመጣ ነው ወይስ ችሎቱ በአሰራር ያዳበረው?.....የልዩነት ሐሳብ አጻጻፍና አገላላጽስ ተገቢነት አለው?....ወዘተ
የዳኞች አመዳደብስ?.......
NB:_
የኢትዮጵያ የሠበር እና የአስገዳጅ ሕግ ትርጉም ስርዓት በሚለው መጸሐፌ(coming soon)
የእኔን አቋም በዝርዝር አስቀምጬአለሁ!
.......👇👇👇👇👇👇👇
በፍትህ ስርዓቱ ስላጋጠመው አደጋ የመፍትሄ አቅጣጫ እና
ለዳኞች እና አቃቤ ህጎች ፍልሰት  ምክንያቶቹ እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች‼️

👆👆👆👆👆👆👆👆👆

እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት
🔘 Live on Telegram 👈👈

#በአለ_ህግ ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን።

ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰሙ ወደ ወይይቱ ይጋብዙ👆👆👆

የእለቱ እንግዳችን
👇👇👇👇👇👇👇👇
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው
.......🙏

ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ.......

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig

Watch "Ale_Hig🔴አለ_ህግ" on YouTube
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw
201235.pdf
833.1 KB
በሁከት ይወገድልኝ ክርክር የማይስተናገዱ ጉዳዮች
Abrham Y
ውል እንዲፈርስ ሰ/መ/ቁ 201235
ሁከት እንዲወገድ በቀረበ ክስ ላይ ለይዞታው መነሻ የሆነ ሽያጭ ወይም ሌላ ውል እንዲፈርስ የተጠየቀ ዳኝነት በሌለበት ሁኔታ ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ፍርድ ሊሰጥ አይገባም።
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሊቀርብ የሚችለው በይዞታው በእውን በሚያዘው ሰው ሰላማዊ የይዞታ አጠቃቀም ላይ ችግር ወይም መሰናክል ሲፈጠር ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1140 እና 1149 ድንጋጌዎች ይዘት መረዳት ይቻላል። በዚህ መልኩ ለቀረበው ክስ የሚሰጠው ዳኝነትም የተነሳው ህውከት እንዲወገድ እንዲሁም ስለደረሰ ጉዳት ኪሳራ እንዲከፈል ሊሆን ይችላል። በተለይ ተከሳሽ አድራጎቱን የሚፈቅድ መብት እንዳለው በፍጥነትና በማይታበል ዓይነት ካላስረዳ በቀር ሁከቱ እንዲወገድ እንደሚታዘዝ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3) ሥር ተመልክቷል። በአንፃሩም ሁከቱን ፈጠረ ከተባለው ሰው ጋር የተደረገ በውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ካለ ግንኙነቱ የሚገዛበት የውልና የህግ አግባብ ተለይቶ ራሱን ችሎ ዳኝነት ሊሰጥበት ይገባል።
ፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3)፤ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2)
አዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አዲስ የስራ ማስታወቂያ በ0 አመት እና በልምድ በተለያዩ የስራ መደቦች
35 Positions
Deadline: Nov 25, 2022
ስለ ህግ ጉዳይ መረጃ እና ማብራሪያዎች ከፈለጉ
ይህንን የዩቱብ ቻናል ሰብስክራብ አድርጉ እንዲደረግ ለሌሎች አጋሩ።
please, Subscribe‼️🙏
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆
"Ale_Hig🔴አለ_ህግ" on YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
📌New Vacancy Abyssinia bank S.c .
Position 3: Administrative Assistant

Position 4: Foreclosure Officer
Position 5: Surveillance Officer
Position 6: Senior Attorney

📌For More Detail
https://lucyjob.com/job/abyssinia-bank-s-c-6-positions/
#ተከሳሽ_በሌለበት_የወንጀል_ክስን_ማየት
በመርህ ደረጃ ክስ መሠማት ያለበት ተከሳሽ ባለበት ነው፡፡ በወንጀል ተጠርጥሮ የተከሰሰ ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱ ደርሶትና ተረድቶት የመሰማት ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንሥግሥት አንቀጽ 2ዐ ደንግጓል፡፡ ይህ ማለት ግን የወንጀል ክስ ሁሉ ተከሳሽ ፍርድ ቤት ካልቀረበ ታይቶ አይወሰንም ማለት አይደለም፡፡

በሕግ ተለይተው በተመለከቱ ወንጀሎች ላይ ተከሳሽ በሌለበትም ክሱን መርምሮ መወሰን ይቻላል፡፡ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ አራተኛ መድሐፍ አንቀጽ 2 ልዩ ሥነ ሥርዓት በሚለው በምዕራፍ አንድ ቁጥር 160/2/ ሥር ነገሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ተከሳሽ ካልቀረበ ወይም ለመቅረቱ በቂ ምክንያት የሚሰጥለት እንደራሴ ካልቀረበ እንዲያዝ ትዕዛዝ ፍ/ቤት እንደሚሰጥ ይደነግጋል፡፡ በዚህ ትዕዛዝ መሠረት መፈፀም ካልተቻለ ተከሳሹ በሌለበት ነገሩን ለመስማት ፍ/ቤቱ እንደሚያስብበት የዚሁ ቁ. 160/3/ ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ መርህ ሁለት ነጥቦችን እናያለን፡፡ ተከሳሽ ሲቀር የመጀመሪያው የፍ/ቤቱ ተግባር እንዲያዝ ማዘዝ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሌለበት ጉዳዩን ለማየት ማሰብ ናቸው፡፡

አንድን የወንጀል ክስ ተከሳሽ በሌለበት መስማትና መወሰን የሚቻለው በቁ. 161/2/ መሠረት ከ12 ዓመት በማያንስ ጽኑ እሥራት የሚያሳስር ወንጀል የሠራ ወይም በቀድሞ ወ/መ/ሕግ ቁ. 354-365 በአዲሱ የወንጀል ሕግ ቁ. 343 እስከ 354 ድረስ ያሉ ወንጀሎች ፈጽሞ ጽኑ እሥራት ወይም ከ5ዐዐዐ ብር በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን እና እንዲሁም በውጭ ሀገር ጥገኛ ሆኖ ጥገኛ ያደረገው ሀገር አሳልፎ ያልሰጠው እንደሆነ ነው ቁ. (161/3/) ተከሳሹ በቁ. 160/2/ ካልቀረበ ወይም ለመቅረቱ በቂ ምክንያት ካልተሰጠና ወንጀሉ በቁ. 161/2/ እና /3/ የተመለከተው ከሆነ ክሱ በሌለበት እንዲሰማ ይታዘዛል፡፡ በቁ. 162 መሠረት ፍ/ቤት በጋዜጣ ማስታወቂያ ተከሳሽ እንዲጠራ የሚያዘው ነገሩ እንዲሰማ ቀጠሮ በተሰጠበት ቀን ባይቀርብ በሌለበት ጉዳይ እንዲታይ በታዘዘው መሠረት ቀጥሎ እንደሚታይ ለማስታወቅ ነው፡፡ ከጋዜጣ በተሻለ በሌላ መንገድ መጥሪያው ለተከሳሽ ሊደርስ ይችላል ከተባለም አማራጩ ለፍ/ቤት የተተወ ነው፡፡

በተግባር የሚታየው አሠራር የተለየ ሊመስል ይችላል በቁ. 161 የተመለከቱት ሁኔታዎች በተሟሉበትም ቢሆን ፍ/ቤት የተከሳሽን ጉዳይ በሌለበት ለማየት የሚወሰነው በጋዜጣ ማስታወቂያ ጥሪ ካደረገ በኋላ ነው ምናልባትም ይህ አሠራር የተከሳሹን መብት በተሻለ መንገድ ይጠብቅለታል ከሚል የመነጨ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ፍ/ቤቱ ተከሳሹ የቀረው ያለበቂ ምክንያት መሆኑን ካረጋገጠ በጋዜጣ ጥሪ የሚያደርግበት አግባብ የለም፡፡

በዚህ ሁኔታ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ የተፈረደበት ሰው ፍርዱ ውድቅ እንዲደረግለት ፍርዱን ባወቀ በ3ዐ ቀን ውስጥ ለፈረደው ፍ/ቤት ማመልከት ይችላል (ቁ. 164,197,198) ማመልከቻውም ተቀባይነት የሚያገኘው ተከሳሹ ፍ/ቤት ያልቀረበው መጥሪያው ስላልደረሰው ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የቀረ መሆኑን ማስረዳት ከቻለ ብቻ ነው፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ምንድነው የሚለውን የመወሰን ኃላፊነት የፍርድ ቤቱ ነው፡፡ ማመልከቻው ተቀባይነት አግኝቶ ፍ/ቤቱ በሌለበት የሰጠውን ውሣኔ ውድቅ ካደረገው ጉዳዩ/ ክሱ እንደገና በሌላ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት እንዲታይ ይታዘዛል ቁ. 202፡፡

በሌለበት የተፈረደበት ፍርድ እንዲነሳለት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ የተደረገበት ተከሳሽ ይግባኝ ማለት የሚችለው በቅጣቱ ላይ ብቻ ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
201235.pdf
833.1 KB
በሁከት ይወገድልኝ ክርክር የማይስተናገዱ ጉዳዮች

ውል እንዲፈርስ ሰ/መ/ቁ 201235
ሁከት እንዲወገድ በቀረበ ክስ ላይ ለይዞታው መነሻ የሆነ ሽያጭ ወይም ሌላ ውል እንዲፈርስ የተጠየቀ ዳኝነት በሌለበት ሁኔታ ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ፍርድ ሊሰጥ አይገባም።
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሊቀርብ የሚችለው በይዞታው በእውን በሚያዘው ሰው ሰላማዊ የይዞታ አጠቃቀም ላይ ችግር ወይም መሰናክል ሲፈጠር ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1140 እና 1149 ድንጋጌዎች ይዘት መረዳት ይቻላል። በዚህ መልኩ ለቀረበው ክስ የሚሰጠው ዳኝነትም የተነሳው ህውከት እንዲወገድ እንዲሁም ስለደረሰ ጉዳት ኪሳራ እንዲከፈል ሊሆን ይችላል። በተለይ ተከሳሽ አድራጎቱን የሚፈቅድ መብት እንዳለው በፍጥነትና በማይታበል ዓይነት ካላስረዳ በቀር ሁከቱ እንዲወገድ እንደሚታዘዝ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3) ሥር ተመልክቷል። በአንፃሩም ሁከቱን ፈጠረ ከተባለው ሰው ጋር የተደረገ በውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ካለ ግንኙነቱ የሚገዛበት የውልና የህግ አግባብ ተለይቶ ራሱን ችሎ ዳኝነት ሊሰጥበት ይገባል።
ፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3)፤ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2)
By Abrham Yohannes

https://t.me/lawsocieties
የአስተዳደር_ተቋም_ረቂቅ_መመሪያ_ለፍትሕ_ሚኒስቴር_ለአስተያየት_የሚላክበት_እና_የፀደቀ_መመሪያ_የሚመዘገብበት.pdf
283.4 KB
የአስተዳደር ተቋም ረቂቅ መመሪያ ለፍትሕ ሚኒስቴር ለአስተያየት የሚላክበት እና የፀደቀ መመሪያ የሚመዘገብበት የአሠራር ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 911.2014
የሥነምግባር ደንብ መርሆዎች Principles of Ethical Service

1. ቅንነት (Integrity)

2. ታማኝነት (Loyalty)

3. ግልፅነት (Transparency)

4. ሚስጢር ጠባቂነት (Confidentiality)

5. ሀቀኝነት (Honesty)

6. ተጠያቂነት (Accountability)

7. የሕዝብን ጥቅም ማስቀደም (Serving the public interest)

8. ሥልጣንን በአግባቡ መጠቀም (Exercising legitimate authority)

9. አለማዳላት (Impartiality)

10. ሕግ ማክበር (Respecting the law)

11. ለሕዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት (Responsiveness)

12. አርአያ መሆን (Exercising leadership)

https://www.youtube.com/@Lawsocieties
We need you on YouTube. Subscribe now.🙏🙏🙏‼️
https://t.me/lawsocieties