አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት /Legal Immunity/

በዚህ አጭር ጽሁፍ የህግ ጥበቃ (ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት) ምንነት፣ ጥበቃ የተደረገላቸው መስኮች እና የህግ ጥበቃው ስለሚነሳበት እንዲሁም የህግ ጥበቃ ያላቸው ሰዎች በወንጀል ሲጠረጠሩ ስለሚያዙበት እና ስለሚከሰሱበት ህጋዊ ሁኔታ ምብራሪያ ይቀርባል

ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት /Legal Immunity/ ምንነት

ለህዝብ እና ሀገር ጥቅም ሲባል ለተወሰኑ ሰዎች የሚሰጥ በሁኔታ ላይ የተመረኮዘ የህግ ጥበቃ ሲሆን ይሄንን መብት የተጎናጸፉ ሰዎች በህግ የተደነገጉ ሁኔታዎችን እስካልተላለፉ ድረስ ወይም ከለላው እስካልተነሳ ድረስ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ ይህ ልዩ መብት ወይም (Privilege) ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን የሚሰጥበት አላማ ይህ መብት ወይም ጥበቃ የሚሰጣቸው ሰዎች ባላቸው ሀላፊነት እና ተግባር ምክንያት ስራቸውን በሚያደናቅፍ መልኩ በየምክንያቱ የማሰርና የመክሰስ ተግባር እንዳይኖር በማድረግ የሚያከናውኑትን ተግባር እና የሚወከሉትን ሀላፊነት መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ልዩ መብት ጥፋት ወይም ወንጀል ለመፈፀም ፈቃድ ለመስጠት ወይም ተጠያቂነትን ለማስቆም (impunity) እንዲኖር አይደለም፡፡ ልዩ መብቱ የሚሰጣቸው ሰዎች ይታመናሉ ህግንም ያከብራሉ ከሚል እምነት ነው፡፡ ይህ ልዩ መብት የሚሰጠው በልዩ ሁኔታ እንደመሆኑ በጠባቡ የሚተረጎምና አስፈላጊ መሆኑ በታመነ ጊዜ ብቻ በአዋጅ የሚሰጥ መሆኑ ሌላው ባህሪው ነው፡፡ ከለላው የተሰጣቸው ሰዎች ጥፋት ወይም ከባድ ወንጀል ፈፅመው ሲገኙ ግን ይህን ሁኔታ በምርመራ ክፍሉ በቂ ጥርጣሬ ብቻ ሳይሆን ከለላውን በሚከታተለው አካል የጥርጣሬው ትክክለኛነት ተረጋግጦ በህግ እንዲጠየቁ ይደረጋል፡፡

 ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ያላቸው አካላት

1. የምክር ቤት አባላት

ምክር ቤት ማለት የህግ አውጪው የመንግስት አካል ሲሆን አንዳንድ አገራት ባለ አንድ ምክር ቤት (unicameral) ያላቸው ሲሆን ሌሎች ደግሞ ባለ ሁለት ምክር ቤት (bicameral) የሆኑ አሉ፡፡ ስያሜውን ስናይ በኮመን ሎው የህግ ስርአት የሚከተሉ አገራት የላይኛው እና የታችኛው ምክር ቤት እያሉ የሚገልጹት ሲሆን በእንግሊዘኛ አጠራሩ house of lord and house of common ይባላል፡፡

ያለ መከሰስ መብት ብዙውን ጊዜ ለነዚሁ ለህዝብ እንደራሴዎች የተሰጠ መብት ሲሆን አባላቱ የወከላቸውን ህዝብ ሃሳብ እና ፍላጎት በነጻነት እንዲገልጹ እና በውጤታማነት መወከል እንዲችሉ ለማስቻል ያለመ መብት ነው፡፡ በአሜሪካ እና እንግሊዝ የምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ ለሚያደርጉት ንግግር በፍትሐብሄር ሃላፊነት የማይጠየቁ ሲሆን አይታሰሩም፡፡ ነገር ግን ወንጀል ከፈጸሙ የሚጠየቁበት (የሚከሰሱበት) አግባብ አለ፡፡ በሌላ በኩል በፈረንሳይ እና ሌሎች አውሮፓ አገራት ህግ አውጪ የሆነው ምክር ቤት ሳይፈቅድ አባላትን ማሰር የተከለከለ ነው፡፡

በአገራችን የስርአተ መንግስት አወቃቀር መሰረት በፌደራል እና በክልል ደረጃ የህግ አውጪ አካላት ያሉ ሲሆን በፌደራል ደረጃ ሁለት ምክር ቤቶች አሉ፡፡ እነሱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ሲሆኑ ክልሎችም የየራሳቸው ምክር ቤቶች አላቸው፡፡ እነዚህ የምክር ቤት አባላት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 54 ንኡስ አንቀጽ 4 እና በአንቀጽ 63 መሰረት የሁሉም ህዝብ ተወካይ ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረት ማንኛውም የምክር ቤት አባል በምክር ቤቱ ውስጥ በሚሰጠው አስተያየት ምክንያት አይከሰስም፣ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወሰድበትም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ማንኛውም የምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም በወ/መ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 19 እና 20 መሰረት እጅ ከፈንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም በወንጀልም አይከሰስም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ መረዳት እንደሚቻለው በአገራችን ያለመያዝ እና ያለ መከሰስ መብት ለሁሉም ሰው የተሰጠ ሳይሆን ለምክር ቤት አባለት የተሰጠ ልዩ ጥበቃ ነው፡፡ ሆኖም ፍጹም መብት ግን አይደለም ምክንቱም በሁኔታዎች ላይ የተመረኮዘ መብት ስለሆነ። ስለዚህ የምክር ቤት አባላት አባል የሆኑበት ምክር ቤት ሲፈቅድ ወይም የምክር ቤቱ ፈቃድ ሳያስፈልግ ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ የሚያዙበት እና የሚከሰሱበት የህግ አሰራር ያለ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በክልሎች ህገ-መንግስታት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995(እንደተሻሻለው) አንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ 3 እና 4 እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ቻርተር መሰረት የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮቹ ምክር ቤት አባላት ከላይ በተገለጸው መልኩ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሲሆን ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ ግን የሚያዙበት ሁኔታ በህግ ተደንግጓል፡፡ ለሌላ ወንጀል ጉዳይ ግን የምክር ቤቶቹ ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡ እዚህ ላይ ከባድ ወንጀል ምንድን ነው ለሚለው የአገራችንን የወንጀል ህግ ማየት የሚስፈልግ ሲሆን ህጉ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ያስቀመጠው ነገር የለም፡፡ ሆኖም የወንጀል ህጉ አንቀጽ 106 እና 108 ባስቀመጡት አግባብ ቀላል እስራት እና ጽኑ አስራት የሚያስቀጡ ወንጀሎችን እንደየሁኔታው ከባድ ወንጀልን ለመለየት በመስፈርትነት መጠቀም ይቻላል፡፡

2. የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ

በአለምአቀፍ ህግ መሰረት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የላካቸውን አገር እና አለምአቀፍ ድርጅት ወክለው ባሉበት አገር ፍርድ ቤት በወንጀልም ሆነ በፍትሐብሔር ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ ይህ ያለመከሰስ መብት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በመኖሪያቸው እና በቢሮዎቻቸው ለሚያደርጓቸው እንቅስቃሴም የሚሰጥ መብት/የህግ ጥበቃ ነው፡፡ ይህ ጥበቃ ሀገራችንም ፈርማ ባፀደቀችው የ1961 የቬና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነት መሰረት የሚሰጥ ሲሆን ለውጭ አገራት አምባሳደሮች፣ ቆንስላዎች እና የኢምባሲቸው ሰራተኞች የሚሰራ ነው፡፡ እንዲሁም ለአለምአቀፍ ድርጅት ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች ከስራቸው ጋር በተገናኘ ሀገራችን በፈረመችው የመቀመጫ ሀገር ስምምነት(host country agreement) የሚሰጥ የህግ ጥበቃ ሲሆን ሆኖም ይህ ያለመከሰስ መብት ፍጹም አይደለም፡፡ ወንጀል በሚፈጸምበት ጊዜ የላካቸውን አገር ወይም አለምአቀፍ ድርጅት የበላይ ሀላፊ ያለመከሰስ መብቱን እንዲያነሳ በመጠየቅ ሲነሳ መያዝ እና መጠየቅ የሚቻል ሲሆን ይሄንን ማድረግ ካልተቻለ ግን ተጠርጣሪውን ከአገር እንዲወጣ ማድረግ (persona non grata) የአንድ አገር ሉዓላዊ ስልጣን ነው፡፡

3. ዳኞች

በፌደራል የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 34 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት ማንኛውም ዳኛ ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፈንጅ ካልተያዘ ወይም በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያለመከሰስ መብቱ ካልተነሳ በስተቀር ሊያዝ፣ ሊታሰር እና ክስ ሊቀርብበት አይችልም፡፡ ይህ ህግ ዳኞች በህገመንግስቱ አንቀጽ 79 ንኡስ አንቀጽ 2 እና 3 ላይ የተደነገገውን ዳኞች ከማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ወይም ሌላ አካል ነጻ ሆነው በህግ ብቻ እየተመሩ የዳኝነት አገልግሎትን ማከናወን እንዳለባቸው የተደነገገውን ለማስፈጸም የወጣ ህግ ነው፡፡ በዚህም ዳኞች በሚወስኑት ውሳኔ ፍትህን ለማስፈን ከየትኛውም አካል መያዝ፣ እስር እና ክስ ሳይደርስባቸው ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ለማስቻል ሲሆን በዚህም ፍትህ ፈላጊው ማህበረሰብ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህ የህግ ጥበቃ ፍጹም እና ዳኞችም እንደፈለጉት
እንዲሰሩ የሚፈቅድ አይደለም፡፡ ዳኞች ከላይ ባነሳነው የወንጀል ህግ እና የወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህግ መሰረት ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ ቀጥታ የሚያዙበት፣ የሚታሰሩበት እና የሚከሰሱበት ሁኔታ ያለ ሲሆን ከባድ ወንጀል ባይሆንም ወንጀል ከፈጸሙ በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ተደርጎ ተይዘው ክስም የሚቀርብባቸው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

4. የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች

በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሰረት አገራዊ ምክክሩን እንዲያመቻች በኮሚሽን ደረጃ የተቋቋመ ህጋዊ ሰውነት ያለው አገራዊ ተቋም ሲሆን ይሄንኑ ኮሚሽን እንዲመሩ በኮሚሸነርነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰየሙ 11 ኮሚሽነሮች እንዳሉት ይታወቃል፡፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15(1(ሀ) መሰረት እነዚህ ኮሚሽነሮች ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሲሆን በዚሁ መሰረት ያለመከሰስ መብታቸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልተነሳ ወይም ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ በስተቀር በኮሚሽነርነት በሚያገለግሉበት ወቅት ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ እነዚህ ኮሚሽነሮች ከባድ ሀላፊነት ያለባቸው ሲሆን ስራቸውም ከማንም አካል ተጽእኖ ነጻ ሆኖ መከናወን እንዲችል የዚህ አይነቱ ጥበቃ በህግ ተድርጎላቸው ይገኛል፡፡

5. የምርጫ ስራ አመራር ቦርድ አባላት

በምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 4 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሙሉ ጊዜ የሚያገለግሉ 5 አባላት ያሉት ስራ አመራር ቦርድ ያለው ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 15 ንኡስ አንቀጽ 6 መሰረት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ሃላፊነት ላይ አስካሉ ድረስ ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ በስተቀር ያለ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ ያለመያዝ እና በወንጀል ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ ይህ መብት ስራ አመራሩ የተጣለበትን ከፍተኛ ሀላፊነት ያለ ተጽኖ በነጻነት አንዲወጣ ለማስቻል ታስቦ የተደነገገ ነው፡፡ ይሄም መብት ጊዜአዊ ሲሆን አባለቱ ሀላፊነታቸውን ሲለቁ ወይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ሲያነሳ የሚያበቃ ነው፡፡

6. ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች

በአትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 42 መሰረት የግልም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩ ተወዳዳሪ /እጩ ተመራጭ/ የሆኑ ሰዎች ከተመዘገቡበት ቀን አንስቶ ምርጫው አልቆ ውጤቱ እስኪገለጽ ድረስ በወንጀል ተጠርጥረው ያለመያዝ መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን ከባድ ወንጀል ፈጽመው እጅ ከፈንጅ ከተያዙ ተይዘው ሊከሰሱ ይችላሉ፡፡ የፈጸሙት ወንጀል እጅ ከፈንጅ ባይሆንም የህግ እርምጃ የሚወሰድባቸው ምርጫው አልቆ ውጤቱ ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡ ተጠርጣሪው በምርጫው ያሸነፈ ከሆነ በዚሁ ህግ መሰረት ሊያዝ እና ሊታሰር የሚችለው ያለመከሰስ መብቱ በተወከለበት ምክር ቤት ከተነሳ በኋላ ነው፡፡ የዚህ ከለላ ዋነኛ አለማ የምርጫ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግ እና ተወዳዳሪዎች ያለምንም እስር እና ክስ እና ሌሎች እንቅፋቶች የሚወክሉትን መራጭ የህብረተሰብ ክፍል ሀሳብ እና ፍላጎት እንዲገልጹ ወይም እንዲያራምዱ ለማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን ከለላውን ሽፋን በማድረግ ወንጀል ከፈጸሙ ከላይ በተገለጸው አግባብ ከተጠያቂነት አያመልጡም፡፡

7. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 210/2002 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) በአንቀጽ 35 መሰረት የኮሚሽኑ ከፍተኛ ሀላፊዎች እና መርማሪዎች ያለመከሰስ መብታቸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልተነሳ ወይም ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ በስተቀር አይከሰሱም፡፡ እነዚህ የስራ ሃላፊዎችም በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ዋና ኮሚሽነር፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነሮች እና የልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ የተሾሙ ኮሚሽነሮችን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም በአዋጅ ቁጥር 210/2002 አንቀጽ 2(10) እና አንቀት 35 መሰረት በዋና ኮሚሽነሩ የተሰየሙ የሰብአዊ መብት ጥሰት መርማሪዎችም የዚህ መብት ተጠቃሚ ናቸው፡፡

በጥቅሉ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስቀር ሳይሆን ከለላው የተሰጣቸው ሰዎች ካለባቸው የስራ ሀላፊነት ባህሪ አንጻር ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ታስቦ የተደነገገ ሲሆን ወንጀል ከፈጸሙ ግን ይህ ከለላ በህጋዊ ሂደት ተነስቶ የሚጠየቁ መሆኑን እና የህግ የበላይነት በማንኛውም ሰው በእኩልነት የሚረጋገጥ እና የሚፈጸም መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

በንቃት ህግ: ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
የድለላ ስራ
****
የድለላ ሥራ ሆነ ይህንን ሥራ የሚሠራዉ ሰዉ የሕግ ጥበቃ ሊያገኝ የሚችለዉ እንደማንኛዉም ሰዉ አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት በነጋዴነት ተመዝግቦና የንግድ ፈቃድ አዉጥቶ መሥራት ሲችል ነዉ። ሰ/መ/ቁ 204199፥ 119272
Position: Legal Aid (V. No: – 0663/22)

Qualification & Experience: Diploma in Law plus 2 years of experience as a Legal Aid.
The Job holder is responsible for representing the Bank before quasi-judicial tribunals and administrative bodies, assists attorneys in foreclosure process and conducts auction, follows up implementation of court decisions and orders, follows up criminal cases, searches for collateralized vehicles and searches for attachable.
Place of Work- Addis Ababa
Skills Requirement– Knowledge of computer operation is mandatory
Salary & Benefits -As per the Bank’s Salary Scale & Benefits Package
Term of Employment – Permanent
Salary & Benefits – As per the Bank’s Salary Scale & Benefits Package
 
How to Apply:
Interested applicants, who fulfill the above requirement, are invited to apply only via Online Job Application System; https://jobs.awasbank.com. within 7 consecutive days from the first date of this announcement.
For further information, please visit our website https://www.awashbank.com/vacancy/
N.B- Incomplete applications will not be considered
Awash Bank Deputy Chief – Human Capital Management Officer Office
216938.pdf
816.8 KB
ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ በሚል የሠራተኛዉ ወደ ስራ መመለስ ዉሳኔ ከፀና ከአንድ ዓመት ያልበለጠ ዉዝፍ ደሞዝ ሊወስን እንደሚገባ ሰበር ከአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 43(5) መሰረት ውሳኔ ሰጠ።
እንደሚታወቀዉ አንድ ሠራተኛ በህገ ወጥ መልኩ ከስራ ተሰናብቶ ጉዳዩን በተለያዩ የዉሳኔ ሰጪ አካላት ፊት በማቅረብ ሲከራከር የተወሰኑ ጊዜያትን ማሳለፉ አይቀርም፡፡ የክርክሩ ዉጤትም የአሠሪዉ ሕገ ወጥ ድርጊት መረጋገጥና ሠራተኛዉም ወደ ስራዉ እንዲመለስ የሚታዘዝበት ከሆነ ጉዳዩ ለወሰደበት ወራት ስራ ሳይሰራ በመቆየቱ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ወጪዎችንም በማዉጣት ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል አያጠያይቅም፡፡ ስለዚህ የዉዝፍ ደመወዝ እንዲህ ዓይነት ጉዳት ለመካስ የሚያገለግል ሲሆን አጠቃላይ ዓላማዉም አሠሪዉ ሠራተኛዉን በህገ ወጥ መልኩ ከስራዉ አሰናብቶት በመቆየቱና ስራ ባለመስራቱ ምክንያት የሚያጣዉን ደመወዝ ለመተካት እንደሆነ ይታመናል፡፡
https://t.me/lawsocieties
ሰ-መ-ቁ 214222.pdf
235.5 KB
አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ተከራይ ውሉ ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ቢሆንም ውሉን በማንኛውም ጊዜ ሊያቋርጥ የሚችል መሆኑ፤ ነገር ግን በዚህ አግባብ ውሉን ሲያቋርጥ ለደረሰው ኪሳራ እና በውሉ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መልሶ ለማካራየት የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ለዚህ ጊዜ ኪራይ ሊከፍል ይገባል።
216938.pdf
816.8 KB
ውዝፍ ደመወዝ በይግባኝ ሲጸና
ፍርድ ቤቶች በአስተዳደር ክፍል የተሰጠ የቤት ካርታ የተሠጠበትን ወይም የተሻረበትን ስነ
ስርዓት  እና አስተዳደራዊ ውሳኔ ህግ እና መመሪያን ያገናዘበ መሆን አለመሆኑን በማጣራት ውሳኔ የመስጠት ስልጣን አላቸው ።
የሰ/መ/ቁ,99071  ቅፅ   18
ዘወልድ ምክረ ህግ
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
#ጥንቃቄ❗️

በመዲናዋ ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም  ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች  በመኖራቸው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።

ግለሰቦቹ በተለያየ ስልክ በመደወል እንኳን ደስ አላችሁ ሎተሪ ደርሷችኋል ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው ፣ከሌሎች ባንኮች ጋር ኦንላይን ሲስተም እየጀመርን  ነው በሚሉ እና በሌሎች ማደናገሪያዎች በመጠቀም የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀል እንደሚፈጽሙ ታውቋል።

አንዳንዶቹ የማጭበርበሪያ ስልቶች  ግለሰቦች እንዲያምኑ በኤቲም ገንዘብ ያወጡበት ትክክለኛ ቀን ተነግሯቸው የወንጀሉ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙ ሲሆን የግለሰቦች የባንክ ሚስጥር የሚወጣበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ምርመራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል።

ወንጀሉ በልዩ ልዩ የአፈፃፀም ስልቶች እየተፈፀመ ከመሆኑም ባሻገር ስልክ በመንጠቅና ቴክኒካል የሆኑ ዘዴዎችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ አካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስተላለፍ ወንጀሉ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡

ህብረተሰቡ የማያውቋቸው የስልክ ጥሪዎች እና የጹሁፍ መልዕክቶች ሲደርሷቸው ተገቢውን ማጣራት ማድረግ እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
#tikvahethmagazine
https://t.me/lawsocieties
ቤቶች ኮርፖሬሽን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ሊያደርግ ነው‼️👇👇👇👇

የመንግሥት ኃላፊዎችና ተቋማት የሚጠቀሙባቸውን ቤቶች ኪራይ እንዲከፍሉ ተጠይቀስ

አቶ ኃዴስ በርህን ዜማ የቤቶች ኮርፖረሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በተያዘው በጀት ዓመት የነባር መኖሪያ ቤቶች የኪራይ ዋጋ ክለሳ በማድረግ፣ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑን የፌደራል ኮርፖሬሽን አስታውቀ

ቤቶች

የኪራይ ቤቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ ጥናት ማድረጉን የገለጹት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለ ብርሃን ዜና፣ ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ በተከስቱ _ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮች ምክንያት ዕቅዱ መቆየቱን ተናግረዋል::

ኮርፖሬሽኑ ከጥቂት ዓመታት በፊት በንግድ ቤቶች ላይ ጭማሪ ባደረገበት ወቅት፣ ከተከራዮች በገጠመው ተቃውሞ ሳቢያ የፓርላማው ዕገዛ ትልቅ እንደነበር ያወሱት ምክትል ዋና አስፈጻሚው በተያዘው ዓመት ዕቅዱን ለማሳካት የምክር ቤቱን ዕገዛ እንደሚፈልግ ተናግረዋል::

ከ1967 ዓ.ም. ጀምሮ በመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ የማስተካከያ ጭማሪ ባለመደረጉ፣ በቀጣይ በሚካሄደው ጥናት ላይ ገልጸዋል:: ከቤት ባለቤቶችና ከሚመለከታው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት በኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር ቦርድ ፀድቆ እንደሚተገበር ተነግሯል::............ይቀጥላል።👆👆👆https://t.me/lawsocieties
Forwarded from Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ
#እንድታውቁት

" ነገ እና እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት መታወቂያ ማሳደስ ትችላላችሁ "

#መታወቂያ_ለማሳደስ እየተጠባበቁ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነገ #ቅዳሜ እና #እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ማለትም ህዳር 3 እና 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስ በየአካባቢው ባሉ የወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ  ፅ/ቤቶች ይሰጣል።

ነዋሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየአቅራቢያቸው ባሉ ፅ/ቤቶች ተገኝተው መስተናገድ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አሳውቋል።
#tikvahethiopia
95338.pdf
123.4 KB
ሰ-መ-ቁ 95338 (ያልታተመ)
የባልና ሚስት ንብረት ፍቺ ተከትሎ ተጣርቶ ውሳኔ ካላረፈበት አንደኛው ተፋቺ የጋራ ንብረት በሽያጭ ለሶስተኛ ወገን ካስተላለፈ ውሉ እንዲፈርስ ክስ ማቅረቢያው የይርጋ ጊዜ 10 /አስር ዓመት/ ነው።
እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት 👈

የመወያያ እርዕስ፣
በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋ👇
የዳኞችና የአቃቤ ህጎች ፍልሰትና  ውጤቱ፨

ከዳኛ ወደ 🔜ጠበቃ
ከአቃቤ ህግ ወደ🔜 ጠበቃ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Topic of the discussion
.
https://t.me/lawsocieties
እሁድ 👇👇👇👇👇👇
በዚህ ቴሌግራም ይጠብቁ

ሼር በማደረግ ሰዎቸን ይጋብዙ👆👆👆
https://t.me/lawsocieties
Live 🔘 Live on Telegram 👈👈
#አለ_ህግ #Ale_Hig

የእለቱ እንግዳ
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው
.......🙏

Live🔴on Telegram                   

🔵 Ale_Hig / አለ ህግ


Starting Time: 8:30PM -
[Sunday evening]

Join us: https://t.me/lawsocieties

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties

Subscribe our YouTube👇👇👇
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋ ነው🔜
የወራሽነት ማረጋገጫ፣ መቃወሚያ እና ልጅነት፡- ክፍተተ ወሕግ ወአሰራር እና መፍትሔዎቻቸው

በዚህ ጽሑፍ ወራሽ ለመሆን ወይም ልጅ መሆንን ለማረጋገጥ ስለሚሰጡ ማረጋገጫዎች እንዲሁም እነዚህን ማረጋገጫዎች ስለመቃወም የሚቀርቡ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ጸሐፊው በጽሑፍ በወራሽነት ማረጋገጫ፥ ልጅነት እና መቃወሚያ ያሉ የሕግ እና የአሠራር ክፍተቶችን በማሳያት የመፍትሔ ሐሳቦችን ይሰነዝራል።
ፈቃዱ ዳመነ - ጠበቃ
መልካም ንባብ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.abyssinialaw.com/blog/2022-11-11-16-44-28
በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Join us for more‼️🙏
https://t.me/lawsocieties
የመወያያ ርዕስ

በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋየዳኞችና የአቃቤ ህጎች ፍልሰትና  ውጤቱ‼️


እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት
Live 🔘 Live on Telegram 👈👈
በዚህ ቴሌግራም ይጠብቁ
ሼር በማደረግ ሰዎቸን ይጋብዙ👆👆👆

የእለቱ እንግዳችን
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው
.......🙏

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig