አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Vision Fund Micro Finance
በሚከተሉት የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position:-

1: Attorney I

2: Deputy Branch Manager

📚የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ
University degree/ diploma in economics/ accounting/ business administration/ banking/management/ marketing/ cooperative/ agricultural economics/ Rural development or related social sciences and business fields;

🇪🇹 የስራቦታ:-Gibe & Gibe, SNNPR.

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ መስከረም
1/2014 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ

https://jobs.amazonethiopia.com/job/vision-fund-micro-finance/
#VisionFund MFI#

▪️1 - Intermediate Teler
▪️2 - Attorney I
▪️3 - Deputy Branch Manager
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3Q8xOIc

▪️Deadline - September 06/22
Notice for Graduating Class of 2014 E.C

Pleasantly, this is to bethink you that your graduation date  is on Tuesday 01/13/2014 E.C.
We're so proud of you, and honored to celebrate graduation day with you!
MTU School of law
Fisical policy
Fisicla refers to the use of government spending and tax policies to influence economic conditions Macroeconomic especially conditions. These include aggregate demand for goods and services, employment, inflation, and economic growth.
 
During a recession, the government may lower tax rates or increase spending to encourage demand and spur economic activity. Conversely, to combat inflation, it may raise rates or cut spending to cool down the economy.

Fiscal policy is often contrasted with monitory policy which is enacted by central bankers and not elected government officials.
EII.
የውጭ አገር ሰዎች /ኩባንያ #የንግድ_ምልክት የተቃዉሞ አቤቱታ ሰ/መ/ቁ 193292

የሀገራችን የንግድ ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ሆነ ሌሎች የሀገሪቱ አዕምሯዊ ንብረት ህጎች ከአለማቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣሙ ሆነው የተቀረፁ በመሆኑ፤ ሀገሪቱ ለውጪ ሀገር ሰዎች ዜጎቿ ያላቸውን መብትና ግዴታ በተመሳሳይ በማወቅ የንግድ ምልክት ምዝገባና ተያያዥ ተግባራትን ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ስታካሂድ የኖረች መሆኑም የተረጋገጠ በመሆኑ የውጭ አገር ሰው /ኩባንያ/ ኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ምልክት በተመለከተ መቃወሚያው ማቅረብ ይችል።

የእንካ ለእንካ መርህ (principle of reciprocity) በሀገራት መካከል ግልፅ የሆነ ስምምነት ባይኖርም እንኳ አንድ ሀገር ለሀገሩ ዜጎች የሚያከብረውን መብት እና የሚጥለውን ግዴታ ለሌሎች ሀገሮች ዜጎችም በተመሳሳይ እንደሚያደርግ የሚያስገነዝብ ነው። በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 3 ሥር የተመለከተው የእንካ ለእንካ መርህ ሊተረጎም የሚገባውም ሌላው ሀገር ለዜጎቹ የሚያደርገውን የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ ለኢትዮጵያዊያን የማያደርግ ከሆነ የዚያ ሀገር ዜጎችም ሆነ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የንግድ ምልክታቸው እንዲመዘገብና ጥበቃ እንዲደረግላቸው ለመጠየቅ እንዲሁም የተያያዥ መብቶች ተጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም ተብሎ ነው።

https://chilot.me/2022/09/03/objection-to-trademark-registration-by-foreign-companies-c-f-n-193292/

የእንካ ለእንካ መርህ (principle of reciprocity) በሀገራት መካከል ግልፅ የሆነ ስምምነት ባይኖርም እንኳ የውጭ አገር ሰው /ኩባንያ/ ኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ምልክት በተመለከተ መቃወሚያው ማቅረብ ይችላል።

ከችሎቱ ሐተታ በከፊል

የእንካ ለእንካ መርህ (principle of reciprocity) በዘርፉ የሚታወቅ ሲሆን መርሁ የሚይዘው ትርጉም “አንተ ባደረክግልኝ መጠን እኔም አደርግልሃለሁ” እንዲሁም “እኔ ባደረኩልህ መጠን አንተም ታደርጋለህ” የሚል ይዘት ያለው ነው፡፡ ይህን መርህ ተጠቅመው ሃገራት ጥቅማቸውን ያስከብራሉ የሌሎችንም ጥቅም በዚያው መጠን ያከብራሉ፡፡ ይህ የእንካ ለእንካ መርህ የ”ናሽናል ትሪትመንት” (National Treatment) አካል ሲሆን የ”ናሽናል ትሪትመንት” መሰረተ ሃሳብ የአለማቀፍ ልማዳዊ ህግን መሰረት የሚያደርግ ሆኖ በሃገራቱ መካከል ግልፅ የሆነ ስምምነት ባይኖር እንኳ አንድ ሀገር ለሀገሩ ዜጎች የሚያከብረውን መብት እና የሚጥለውን ግዴታ ለሌሎች ሀገሮች ዜጎችም በተመሳሳይ እንደሚያደርግ የሚያስገነዝብ ነው።

ከአእምሯዊ ንብረት መብት እና በልዩ ሁኔታም ከንግድ ምልክት ጋር በተያያዘም የ WTO እና TRIPS ስምምነት፤ እንዲሁም የበርን ኮንቬንሽን (Berne Convention)፣ የፓሪስ ኮንቬንሽን (Paris Convention)፣ እና የማድሪድ ፕሮቶኮል (Madrid Protocol) የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህና መሰል የአለም አቀፍ ስምምነቶች የሚመሩበት መሰረታዊ መርህ ብሄራዊ ስምምነት ሲሆን ለአንድ ሀገር ዜጎች የሚጠበቀው መብት ወይም የሚጣለው ግዴታ በሌሎች ሀገሮች ዜጎችም ያለ አድሎ በእኩልነት ተፈጻሚነት እንዲኖረው የሚገባውን ግዴታ የሚመለከት ነው፡፡ ይህም ለአብነት በ TRIPS አለምአቀፍ ስምምነት አንቀጽ 3 ስር ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ሀገራት ለውጭ ሀገር ዜጎች ጨምሮ የአእምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ የሚያደርጉ ሲሆን የሚሰጠው ጥበቃ አይነትና ተፈጻሚነት ግን የአለም አቀፍ ስምምነቶች አባል በሆኑት እና የሁለትዬሽ እና አህጉራዊ ስምምነቶችን ባጸደቁ ሀገራት የተሻለ ሆኖ ይታያል፡፡ አንዳንድ ሀገራት ደግሞ አብዛኞችን አለም አቀፍ ስምምነቶች ሳያጸድቁ ነገር ግን የአእምሯዊ ንብረት መብቶችን የተመለከቱ አለማቀፋዊ መርሆችና አሰራሮችን በሀገራቸው ህጎች ደንግገው ይገኛሉ፡፡ በዚህ መልኩ ለመብቱ ጥበቃ ከሚያደርጉ ሀገራት መካከል ኢትዬጵያ አንዷ ስትሆን አዋጅ ቁጥር 501/98 እና ሌሎቹ የአእምሯዊ ንብረት አዋጅና ደንቦች ይህን የሚያሳዩ ናቸው፡፡
By #Abrham_Yohanes
የሚተላለፉ #የገንዘብ #ሰነዶች በኢትዮጵያ #የንግድ #ህግ

መግቢያ

በሀገራችን የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ንግድን ከማፋጠን እና የፋይናንስ ግብይትን ከማሳለጥ አንጻር የገንዘብነት ዋጋ ያላቻው የሚተላለፉ ሰነዶች የሚጫወቱት ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ እነዚህኑ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ምንነት እና የሀገራችን የሚተዳደሩበትን የህግ ማእቀፍ በአጭሩ እናያለን፡፡

የህግ ማእቀፍ
እስከቅርብ ጊዜ በስራ ላይ የነበረው የ1952ቱ የንግድ ህግ ስድስት መጽሐፍት የነበሩት ሲሆን የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችና የባንክ ስራዎች በተመለከተ የደነገገው የህጉ ክፍል በመጽሀፍ አራት ስር የተደራጁ ናቸው፡፡ አዲሱ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 በይዘቱ በሶስት መጽሐፍት የተከፋፈለ ሲሆን የበፊቱ ንግድ ህግ መጽሐፍት 3 እና 4 የአዲሱ የንግድ ሕግ አካል ሳይሆኑ ራሳቸዉን ችለዉ የፋይናንስ አገልግሎት መድብል ወይም ኮድ ሆነው እንዲወጡ በመተው መጽሐፍ አንድ፣ሁለት እና አምስት የንግድ ሕግ ተብሎ እንዲሻሻል ተደርጎ በአዲሱ የንግድ ሕግ ተካተው ወጥተዋል፡፡ በዚህም አዲሱ የፋይናንስ አገልግሎት ህግ እስኪወጣ ድረስ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ወይም የንግድ ወረቀቶች በነባሩ የንግድ ህግ ምእራፍ አራት ድንጋጌዎች መሰረት የሚታዩ መሆናቸው ይቀጥላል፡፡

የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ምንነት
በ1952ቱ የንግድ ህግ አንቀፅ 715 /1/ መሰረት የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ማለት መብቱ ከሰነዱ ተለይቶ ሊሰራበት ወይም ሊተላለፍ የማይችል የአገልግሎት መብት ያለበት ሰነድ ሁሉ ነው በማለት ይደነግጋል፡፡ ይህ ትርጉም የሚተላለፉ ሰነዶች የመብትና የግዴታ ማረጋገጫ ሰነዶች ናቸው ከማለት በተጨማሪ በሰነዶቹ ውስጥ የተመለከቱት መብቶች ከሰነዶች ተለይተው ሊተላለፉ /ሊሰራባቸው/ እንደማይችሉ የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም አባባል ጠቅለል ባለ መልኩ ሲገለፅ የሚተላለፍ ሰነድ ማለት በሠነድ ላይ የተመለከተው መብት ከሰነድ ላይ ለይቶ ሊሰራበት እና ሊተላለፍ የማይችል የመብትና የዕዳ ማረጋገጫ ሰነድ መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡

የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነድ አይነቶች
በ1952ቱ የንግድ ህግ አንቀፅ 732 መሰረት የንግድ ወረቀቶች ማለት በገንዘብ መክፈል የሚሆነውን ግዴታ የሚናገሩ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ናቸው፡፡

እነዚህ ሰነዶችም፡-
የሀዋላ ወረቀት /Bill of Exchange/

ለመክፈል ተስፋ ሰነድ /Promisory Note/፣

ቼክ /Cheques/፣
የመንገድ ቼክ/Travellers Cheques/፣

የእቃ መጋዘን ለተቀመጡ እቃዎች ምስክር ወረቀቶች/ደረሰኞች /warehouse goods deposit certificates/ ናቸው፡፡


የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ሊያሟሏቸው ስለሚገቡ መስፈርቶች እና የሚያስከትሉት ህጋዊ ውጤት

የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች የሚወጡት በህግ ችሎታ ባላቸው ሰዎች ብቻ ነው፡፡ በ1952 የንግድ ህግ አንቀጽ 733 መሰረት ማናቸውም በውል ለመገደድ ችሎታ ያለው ሰው በንግድ ወረቀትም መገደድ እንደሚችል ደንግጓል፡፡ ማንኛውም ሰው በውል የሚገደደው በህግ ችሎታውን ያላጣ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ህጋዊ ችሎታ የሌላቸው ሰዎች ማለት በፍትሐብሔር ህጉ መሰረት የጸና ህጋዊ ውጤት የሚያስከትሉ ክንውኖችን ለማካሄድ አቅም የሌላቸው ሰዎች ሲሆኑ እነሱም ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህጻናት፣ በህግ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ ከህጋዊ ውጤት ካላቸው ድርጊቶች ውስጥ ከመሳተፍ የተከለከሉ ሰዎች (ለምሳሌ የአእምሮ ህመምተኛ፣ በእርጅና ምክንያት የሚያደርጉትን ድርጊት ህጋዊ ውጤት የማያውቁ ሰዎች እና በወንጀል ቅጣት ከመብት በመሻር ውሳኔ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 123 መሰረት የተወሰነባቸው ሰዎች) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን ወይም የንግድ ወረቀቶች ማውጣት አይችሉም፡፡ ካወጡም አይገደዱባቸውም ማለት ነው፡፡

ሌላኛው መስፈርት ፊርማ ነው፡፡ የሚተላለፉ ሰነዶች ሲወጡ የግድ በአውጪው መፈረም አለባቸው፡፡ ይኸውም በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ባወጧቸው ሰዎች ወይም መግለጫውን በሰጡ ሰዎች የእጅ ፣ጽሁፍ ፊርማ ሊፈረሙ ይገባል፡፡ መፈረም ለማይችሉ ሰዎች በእጅ ምልክት ወይም ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በሁሉም ሁኔታ በንግድ ወረቀቶች ላይ መፈረም የማይሉ ሰዎች ሰነዱን ስለማውጣታቸው እና ይዘቱ በባለስልጣን ፊት ቀርቦ መረጋገጠ አለበት፡፡

በንግድ ህጉ አንቀጽ 719 መሰረት የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች በሁለት መደቦች ሊወጡ የሚችሉ ሲሆን እነሱም ለአምጪው ወይም ስሙ ለተጠቀሰው ወይም ለታዘዘለት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለትም ላምጪው ተብለው የወጡ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ሰነዶቹን ለባለ ግዴታው ያቀረበ ማንም ሰው በሰነዶቹ የተገለጸው ገንዘብ ተከፋይ ባለመብት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ባለእዳው የአምጪውን ማንነት ግምት ውስጥ ሳያስገባ ሰነዱን ያቀረበው ሰው በቀጥታ ባለመብት መሆኑን በመገንዘብ በሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን ክፍያ መፈጸም ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ በህጉ አንቀጽ 721 እንደተገለጸው ሰነዱን ያቀረበው ሰው በሰነዱ የተገለጸው ግዴታ ባለመብት ለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡

ሁለተኛው የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች የሚወጣበት ፎርም ስሙ ለተጠቀሰው ወይም ለታዘዘለት ሰው ተብለው ሊወጣ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት የተከፋይነት ወይም የአገልግሎት ተጠቃሚነት ባለመብትን የመብቱን ተጠቀሚ ማንነት ቀድሞ በመለየት ይሄንኑም በተላላፊ የገንዘብ ሰነዶቹ ላይ በመግለጽ የወጡ ሰነዶች ናቸው፡፡ በሰነዱ የተገለጹ ገንዘብ ወይም ግደታዎች ባለ እዳ የሆነው ሰው ወይም ድርጅት አገልግሎቱን ወይም ክፍያውን ሰነዱን ላቀረበለት ሰው ሁሉ ቀጥታ የሚፈጽመው ሳይሆን በሰነዱ ስሙ ወይም ማንነቱ ለተገለጸው ሰው ብቻ መፈጸም አለባት፡፡ ስሙ የተገለጸው ሰው እና ሰነዱን ያቀረበው ሰው አንድ መሆናቸውን በመታወቂያና መሰል ሰነድ ማረጋገጫ መንገዶች አጣርቶ መክፈል አለበት፡፡

የአክስዮን ማህበር አክስዮንን በተመለከተ የቀድሞው የንግድ ህግ አክስዮኖች በሁለቱም መንገዶች ማለትም ለአምጪ ወይም ስሙ በአክስዮኑ ለተመዘገበው ሰው በማለት የሚወጡ እና የሚተላለፉ ሲሆን በአዲሱ የንግድ ህግ አዋጅ 1243/2013 አንቀጽ 267 መሰረት ግን አክስዮኖች በባለአክስዮኖች ስም በመመዝገብ መውጣት እንዳለባቸው ህጉ ደንግጓል፡፡ ቀደም ሲልም ለአምጪው ተብለው የወጡ አክስዮኖች በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ወደ ተመዝጋቢ ባለአክስዮንነት እንዲቀየሩ ተደንግጓል፡፡ ስለዚህ ለአምጪው ተብሎ የሚጠቀስ እና የሚወጣ አክስዮን በአዲሱ ንግድ ህግ መሰረት አዲሱ የንግድ ህግ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከሶስት ዓመት በኋላ ህጋዊ ተቀባይነት የለውም ማለት ነው፡፡

በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ውስጥ የተገለጸ እዳ ባለእዳ የሆነ ሰው እዳውን መክፈል ያለበት ሰነዱን ከቀረበለት ብቻ ሲሆን ይህ ባለእዳ ክፍያውን ሲፈጽም ከባድ አታላይነት ወይም ቸልተኝነት ካልፈጸመ በስተቀር የገንዘብ ተከፋይ ትክክለኛው ሰው ባይሆን እንኳን ሰነዱ ባለገንዘብነት መብት ለሰጠው ሰው የክፍያ ጊዜው ሲደርስ ከከፈለ ከእዳው ነጻ መሆኑን ህጉ በአንቀጽ 716 ንኡስ አንቀጽ 3 ላይ ደንግጎ ይገኛል፡፡ ከዚህም የምንረዳው ይህ በሰነዶች የሚደረግ የገንዘብ ልውውጥ የፋየናንስ ግብይቱን እና አጠቃላይ የኢኮኖሚውን ፈጣን ግብይት ለማረጋገጥ ታስቦ የተቀረጸ ለግብይቱ የተደረገ የህግ ጥበቃ እና ዋስትና መሆኑን ነው፡፡
........ 👇ይቀጥላል👇👇👇👇
..........👆👆የቀጠለ 👆👆👆
ነገር ግን እዳ ከፋዩ ሰነዱን ከያዘው ሰው ጋር ባሉ የግል ግንኙነቶች በመመስረት በሰነዱ አጻጻፍ፣ ፎርም፣ ቃላት፣ የማስመሰል ፊርማ፣ ሰነዱን የማውጣት ችሎታ ወይም የውክልና ስልጣን አለመኖር እና ሌሎች ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች አለመሟላታቸውን በማንሳት እዳ ከፋዩ ሰነዱን የያዘውን ሰው እዳውን ላለመክፈል ሊቃወም ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ በቅን ልቦና የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን የያዘ ሰው መልስ ተብሎ ሊከሰስ አይችልም፡፡ በሌላ በኩል የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን የያዘ ሰው የሰነዶቹን ለአምጪው ከሚለው ወደ ስም የተጻፈበት ሰው እንዲቀይርለት ሰነዶቹን ላወጣው ሰው በራሱ ኪሳራ ሊጠይቅ እንደሚችል ህጉ ይፈቅዳል፡፡

ሌላው የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነድ በትእዛዝ በሚል የሚተላለፍ ሲሆን ይህም የሚፈጸመው በህጉ አንቀጽ 724 እና ቀጥሎ ባሉ ድንጋጌዎች መሰረት በሰነዱ ጀርባ በመፈረም እና ባለመብት ለሆነው ሰው በመስጠት ነው፡፡ በዚሁ ህግ መሰረት በሰነዱ ጀርባ ላይ በመፈረም በትእዛዝ በሚል የሚተላለፉ ሰነዶች በጀርባው መፈረሙ በሰነዱ ላይ መገለጽ ያለበት ሲሆን በጀርባውም በጻፈው ሰው በራሱ መፈረም አለበት፡፡ እዚህ ላይ በጀርባው የተፈረመ ሰነድ የተፈረመለት ሰው ስም ባይገለጽም ህጋዊ ዋጋ አለው፡፡ ለዚህ አላማ ሲባል ለአምጪው ተብሎ በጀርባ የተፈረመበት ገንዘብ አስተላላፊ ሰነድ ልክ ስም እንዳልተገለጸበት ይቆጠራል፡፡ በዚህም ሰነዱን ያቀረበው ሰው በሰነዱ የተገለጹ ግዴታዎች ባለመብት ይሆናል ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም በሰነዱ ጀርባ ሀተታ ማስገባትን ህጉ አይፈቅድም መፈረሙ ብቻ በቂ ነው፡፡ የገቡ ሀተታዎች ካሉም እንዳልገቡ ይቆጠራሉ፡፡

ከህጋዊ ውጤት አኳያ በጀርባው የተፈረመ ገንዘብ ማስተላለፊያ ሰነድ በሰነዱ ውስጥ የተገለጹትን መብቶች ሁሉ ያስተላልፋል፡፡ በዚህ መልክ የሚወጣ የገንዘብ ማስተላለፊያ ሰነድ በጀርባው ጽሁፍ ወይም ስም ያልተሞላበት ከሆነ አምጪው ባዶውን ቦታ በራሱ ወይም በሌላ ሰው ስም መሙላት፣ ሰነዱን እንደገና ስም ሳይጽፍ ወይም የሌላ ሰው ስም በማስገባት ማስተላለፍ የችላል፡፡ በተጨማሪም ይህ ሰነዱን የያዘው ሰው የሰነዱን ባዶ ቦታ ሳይሞላ በጀርባውም ሳይፈርም ለሶስተኛ ወገን ሰነዱን ማስተላለፍ ይችላል፡፡ በዚህ ሁኔታ በሰነዱ ጀርባ የሚፈርም ሰው ሰነዱን ያወጣው ሰው ስላልፈጸመው ግዴታ ተጠያቂነት የለበትም፡፡ ይህ ማለት በሰነዱ ጀርባ የሚፈርም ሰው ሰነዱን ያወጣው ሰው በሰነዱ ይዘት ውስጥ የገባው ግዴታ ሀላፊነት አለበት ማለት ነው፡፡ በሰነዱ በተገለጸው ልክ ሰነዱ የሚያስከትለውን ግዴታ በሰነዱ ጀርባ የፈርመው ሰው ልክ እንደ ሰነዱ አውጪ በመሆን በተገለጸው ግዴታ ሀላፊነት አለበት ማለት ነው፡፡ ሰነድ የተላለፈለት ሰው ሰነዱን ሲቀበል እዳ ከፋዩን ለመጉዳት እያወቀ ካላደረገው በስተቀር ሰነድ አውጪ ከሰነድ ፈራሚው ጋር ባለው የግል ግንኘነት ላይ ከተመሰረቱት መከራከሪያዎች በቀር በዋስትና ስም ሰነዱ የተላለፈለትን ሰው ሊቃወምባቸው አይችልም፡፡

ማጠቃለያ
ገንዘብ ማስተላለፊያ ሰነዶች ወይም የንግድ ወረቀቶች አገራዊ ኢኮኖሚውን በተፋጠነ የግብይት ስርአት እንዲመራ ማድረግ ወስጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ሲሆን የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ ፍሰት ፖሊሲንም ከማሳለጥ እና ለኢንቨስትመንት በብድር የሚሰጥ ወይም ለገንዘብ ጠያቂ ደንበኞቻቸው የሚከፈል የተከፋይ ገንዘብ እጥረት (liquidity problem) እንዳይገጠማቸው ያደርጋሉ፡፡ በዚህም አገራዊ እና ተቋማዊ እድገትን በከፍተኛ ሁኔታ ያግዛሉ፡፡ ከዚህ ባለፈ ያልተመዘገበ (የካሽ) የግብይት ስርአት እንደ አገር ከፋይናንስ ስርአቱ ውስጥ እንዲቀንስ ማድረግ ላይ ጉልህ ሚና አላቸው፡፡
https://t.me/lawsocieties
የውጭ ባንኮች የኢትዮጵያን ገበያ መቀላቀላቸውን አስመልክቶ የተለያዩ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሐሳቦች እየተንጸባረቁ ነው።

በዝርዝር ለመተቸትም ሆነ ለመደገፍ ፖሊሲዎች የአፈጻጸም መመሪያዎች እስኪወጡ መጠበቅ ተገቢ ስለሆነ፣ ለዛሬው ጥቅል ሐሳቦችንና ትኩረት የሚሹ ነጥቦች ብቻ በጨረፍታ አቀርባለሁ።

የዓለም አቀፍ ገበያ ድርጅትን (WTO) ለመቀላቀል አንዱ መስፈርት የሆነው ባንክና ቴሌን የመሳሰሉ ተቋማትን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ ነው። በዚህ ምክንያትም የውጭ ሀገር ባንኮች የሀገራችንን የባንኪንግ ኢንደስትሪ የመቀላቀላቸው ጉዳይ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀሬ እንደነበር የሚታወቅ ነው።

አሁን ሊያወያየን የሚችለው ጉዳይ ባንኮቹ ገበያውን እንዲቀላቀሉ የተፈቀደበት ወቅት ተገቢ ነበር ወይ? የመንግስት፣ የብሔራዊ ባንክና ሀገር በቀል ባንኮች አቅምና ቅደም ዝግጅታቸውስ ምን ይመስላል? የገበያችንን ስርዓት ( Market Structure ) ምን ያህል ሕጋዊነትን የተከተለና ለወንጀልና ወንጀለኞች ያልተጋለጠ ነው። የግብር አከፋፈል፣ የመረጃ አሰባሰብና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂያችን ምን ያህል ጥብቅና ለውንብድናና ለጠለፋ ( Hacking ) ያልተጋለጡ ናቸው የሚሉትና መሰል ጉዳዮች ይሆናሉ

የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ሀገራችን የሚመጡት ገበያ፣ ነባርና አዲስ ደንበኛና ትርፍ ፍለጋ ስለሆነ ስለ ሀገር እድገት በተለይ የሚጨነቁና የማይጠበቡ ልማታዊ እሳቤም የሌላቸው እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የሚቀላቀሉት ገበያ ያለበት ሀገርም ሀገራቸው ስላልሆነ ትርፍ እስካገኙ ድረስ በማንኛውም መንገድ ከማትረፍ ወደኃላ የማይሉና የሕግ አስገዳጅነት እንጂ የሞራል ጥያቄ እምብዛም የማይገዳቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ታሳቢ መሆን አለበት። በተቃራኒው ደግሞ ሀገር በቀል ባንኮች ከትርፍ ባሻገር የሀገራቸው፣ የመንግስትና የልማታቸው አጋር ስለሆኑ ከሕግ ባሻገር በርካታ የውዴታ ግዴታና የሞራል ፈተና ስላለባቸው ውድድሩ የተለየ ጫና  ሊያሳድርባቸው ይችላል።

የውጭ ሀገር ባንኮች  በርካታ የውጭ ምንዛሬ ያመጣሉ የሚለውም እሳቤ የተጋነና በአብዛኛው የተሳሳተ መረጃ ነው። የውጭ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በገፍ ይዘው መጥተው በብር የመለወጥ ፍላጎት አይኖራቸውም። በአብዛኛውም ያለችውን ገበያና የውጭ ምንዛሪ መቀራመት ላይ እንደሚያተኩሩ ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ይታወቃል።

ትርፋቸውንም በውጭ ምንዛሪ ከሀገር የማውጣት እድላቸው ጠባብ ስለሆነና ዋና መስርያ ቤታቸውን እንዲገነቡ ለሚሰበስቡት ብር ተመጣጣኝና ኃላፊነትና ግዴታ (Risk) እንዲወስዱ ካልተገደዱ በስተቀር ዘርፉ ቅርንጫፍ ተከራይቶ ቁሳቁስ በማሟላትና ገንዘብ በመሰብሰብ በትንሽ ኢንቨስትመንት የሚሰራ ስለሆነ ኢንቨስትመንታቸውንም ውስን በማድረግ ያለ በቂ ኃላፊነት፣ ስጋትና መተማመኛ ሊነግዱ ይችላሉ።

ሌላው ሀገር በቀል ባንኮች ከተደራሽነትና ሕዝብን ከማገልገል አኳያ ትርፍ ኖረም አልኖረ እንደ አቅማቸው ሁሉም ቦታ ቅርንጫፍ ይከፍታሉ። የውጭ ባንኮች ግን ሀብትና ኢኮኖሚያዊ አቅም በስፋት የሚታይባቸው አካባቢዎች ላይ ብቻ አትኩረው ሊሰሩ ስለሚችሉ አቅም ባለበት ቦታ ላይ ብቻ የሚኖረው ውድድሩ በሚፈጥረው ሽሚያ  በሚፈጠረው አቅም መዳከም ምክንያት ቀሪው አካባቢና ማህበረሰብ የባንክ አገልግሎት ላያገኝ ይችላል።

ሌላው ሀገራችን ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ አስቀማጭና ተበዳሪዎች በጥቂት መቶዎች የሚቆጠሩ ሰለሆኑ እነዚህን ደንበኞችና ገበያ (Niche Market) ላይ ብቻ በማተኮር ወይም ከፍተኛ እጥረት ያለበት የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን በማባበያነት በመጠቀም፣ የኢንዱስትሪውን አቅም ከ70 በመቶ በላይ በቀላሉ ለመቆጣጠር ይችላሉ። ይህ ደግሞ የተዛባና ወደ አንድ ጎን ያጋደለ (Economic imbalance) ፣ ኢ-ፍትሐዊ ወይም ሚዛናዊ ያልሆነ ውድድር (Unfair Competition) ሊፈጥሩ ይችላሉ።

በዚህ መንገድ ከሞላ ጎደል ገበያውን መሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ስለሚችሉም የፈለጉትን የአገልግሎት ዋጋ በመጣል፣ ወለድ በመተማንና ለፈቀዱለትና ለሚመስላቸው ዘርፍ ብቻ በማበደር ኢኮኖሚውን ወደ ፈለጉበት በመጠምዘዝ ልማታዊ እድሎችን እስከማደናቀፍ ሊደርሱ ይችላሉ። የውጭ ምንዛሪ ሲፈቅዱ የሀገራቸው ምርት ብቻ እንዲገባ በማድረግም ሀገሪቱን የሸቀጥ ማራገፊያ ( Damping ground) ሊያደርገት ይችላሉ። እንደዚህ ዓይነት አካሄዶች በማደግ ላይ ባሉ በርካታ ሀገራት ላይ ያጋጠመ ፈተናና ችግር ነው። በአንዳድ ሀገራትም አንዴ ባንኮቹ ጡንቻ ካፈረጠሙ በኃላ ለተለያዮ ኃይሎች የፖለቲካ መሳርያ በመሆን የመንግስትን እጅ እስከ መጠምዘዝ የደረሱበት ሁኔታም ታይቷል።

የውጭ ባንኮች ወድ ሀገር ውስጥ መግባታቸው በጠንካራ ጎንነት ሊወሳ የሚችለው የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዘመናዊ የባንክ ሙያና እውቀት ስርጸት፣ አዳዲስ የማኔጅመንትና የአመራር ጥበብ ሽግግር የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ከዚህም በላይ ለነባርና ብቃት ላላቸው የባንክ ሰራተኞችን ጨምሮ ለአዳዲስ ስራተኞችም የስራ እድል ይፈጥራል።

የውጭ ባንኮቹ ሀገር ውስጥ መኖራቸው በወጭና በገቢ ንግድ ላይ የነበረውን የተንዛዛ አሰራርና ተደራራቢ የክፍያ ስርዓት ሊቀንስ ይችላል። ኢንደስትሪው በስርዓትና በሕግ ከተመራም የዘመነና ጤናማ ውድድርን ሊያስከትል ይችላል። በአጠቃላይ ዘመናዊ አሰራር በማስተዋወቅ አዲስ ሃብት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ በማሸጋገርና በማበልጸግ የተቀማጭም ሆነ የውጭ ምንዛሪ ይበልጥ እንዲሳለጥና Economics of Scale ከፍ እንዲል ሊያግዝ ይችላል።
Mushe Semu
https://t.me/lawsocieties
Traffic Rules
Tsehay Insurance S.C በሚከተሉት የስራ መደቦች በርካታ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position:-
1: Underwriting Officer II
2: Auditor II
3: Claims Officer II
4: Legal Officer I

📚የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ
BA/BSc Degree in Management, Accounting, Economics, Computer Science or Law,related fields.


🇪🇹 የስራቦታ:- Addis Ababa

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ መስከረም
4/2015 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ

https://jobs.amazonethiopia.com/job/tsehay-insurance-s-c-5/
#United Insurance Company#

▪️1: Trainee Underwriting/Trainee Claims Officer
▪️2: Property Administration Officer
▪️3: Human Resource Officer/Personnel Officer
▪️4: Attorney
▪️5: Driver II/CEO Driver
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3KNs5qg

▪️Deadline - September 11/22
#Enat Bank SC#

▪️1: Business Development Officer
▪️2: Legal Aid
▪️3: Senior Business Research Management Officer
▪️4: Senior IS Auditor
▪️5: Branch Manager Grade B
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3TWvw2j

▪️Deadline - September 10/22
NBE Directive (1).pdf
1.8 MB
New directive Alert📍📍📍The National Bank of Ethiopia isused a directive that requires every person residing in Ethiopia (includes Ethiopians and foreigners having a permanent or temporary residence permit) to convert all of their foreign currency into Birr within 30 days of their entry in to Ethiopia. Those acquiring #forex through gift or donation before September 5 are also required to convert the same within 30 days as of today. The directive entered into force as of today.
Religious Radio and TV Licensing Directive_899.pdf
437.2 KB
የሃይማኖት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 899/2014
ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶች
***

* ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ በተወሰኑ የፍትሐ ብሔር እና የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።

* የመጀመሪያውን ማሻሻያ ያደረገው አዋጅ ቁጥር 65/89 ነው።
* ይህ አዋጅ በፍ/ሕ/ቁ 2851 እና 3ዐ6ዐ ላይ ማሻሻያ አድርጎባቸዋል።
* ማሻሻያው የሚመለከተው ባንክ በመያዣ የተያዙ ንብረቶች አሻሻጥ ሥርዓትን ነው።
* ባንክ በመያዣ የያዘውን ንብረት ወደ ፍ/ቤት መምጣት ሳያስፈልገው ራሱ እንዲሸጥ።
* የሚያደርገ ስምምነት ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው ተደርጓል።
* አዋጅ ቁጥር 97/9ዐ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን አዋጅ ሽሮታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለባንክ በመያዣ የተሰጠ የንግድ መደብርን በተመለከተ አዋጅ ቁጥር 98/98 በቀድሞው የንግድ ሕጉ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
* እነዚህ አዋጆች ባንክ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች ራሱ የውል ጊዜው ተጠናቆ ብድር ካልተመለሰ እንዲሸጥ የሚያደርገውን ስምምነት ህጋዊነት ይቀበላሉ።
* አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት እና በኋላ በመያዣ በተሰጡ ንብረቶች ላይ ልዩነት አድርገዋል።
* አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ባንኩ የተዋዋዮቹ ስምምነት ሳያስፈልገው ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ህጉ መብት ሰጥቶታል።
* አዋጆቹ ከወጡ በኋላ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ራሱ ለመሸጥ ግን ስምምነት ያስፈልገዋል።
* ባንኩ ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ስምምነት ካላደረገ የፍትሐብሔር ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።
* በአሻሻጥ ሥርዓቱ ላይ ከተደረገው ለውጥ በቀር የፍትሐብሔር ህጉ ሆነ የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል።
* በአዲሱ የንግድ ሕግ በአንቀጽ 654 ሥር የተቀመጡ ድንጋጌዎች ንግድ ባንኮች በአዋጁ የተሰጠንን መብት የሚሸረሽር ነው በሚል ቅሬታ እያቀረቡበት ነው ።
📌* በዚህ አንቀጽ ሥር የተቀመጠው መሠረታዊ ድንዳጌ፣ ‹‹…የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ፣ የንብረት ዋስትና ያላቸውን፣ የቅድሚያ መብት ያላቸውን፣ እንዲሁም ባለሀብትነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የተደረጉ የሽያጭ ውሎች ያሏቸው ገንዘብ ጠያቂዎችን ጨምሮ፣ በማናቸውም ገንዘብ ጠያቂዎች ክፍያ ለማስፈጸም በተናጠል የሚደረጉ ክርክሮች፣ በሙሉ ባለ ዕዳው ወይም በመልሶ የማደራጀት ኃላፊው በተናጠል ክፍያ ለማስፈጸም የሚደረጉ ክርክሮች እንዲቋረጡላቸው ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው በመጠባበቂያ ጊዜው ወቅት በሕግ ተቋርጠው ይቆያሉ፤›› የሚል ነው፡፡
📌* በዚህ የአዲሱ ህግ ድንጋጌ እና በጠቅላላው ምዕራፍ 3 ላይ የተካተቱ ድንጋጌዎች መሰረት አንድ ተበዳሪ ያለበት ብድር ተበላሽቷል ( bad debit) ሆኗል ከመባሉ አስቀድሞ ብድሩን ሊከፍል የሚችልበት አማራጭ እድል ይሰጠዋል።
📌* ይህም በብዙዎች ኢ- ህገመንግስታዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ነው ተብሎ ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ሲተች የነበረውን አዋጅ ቁ. 90/97 እና አዋጅ ቁጥር 98/98 የማሻሻል የህግ ውጤት ስላላቸው የንግድ ህጉ አካሄድ ይበል እሚባል ነው ።

💼#ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)
https://t.me/lawsocieties