አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የአራጣ ወንጀል ምንድን ነዉ?
☑️☑️☑️☑️☑️☑️☑️☑️☑️☑️⤵️
ገንዘብን በወለድ ማበደር ቀድሞ በነበረዉ ማህበራዊና ሀይማኖታዊ ፍልስፍና ጀምሮ የተወገዙ ናቸዉ፡፡ የሀሳቡ መነሻ መገበያያ ገንዘብ እንደ ንብረት ስለማይቆጠር እና እራሱም ምንም ብክነት ሆነ ጉድለት ሳይደርስበት ለአበዳሪዉ ስለሚመለስ እና አበዳሪዉም ምንም አይነት አስተዋፅኦ ያላበረከተበት ስለሆነ በአበደረዉ ገንዘብ ላይ ወለድ መቀበል የለበትም የሚል ነዉ፡፡ ይህ አስተሳሰብ በእስልምናም ሆነ ክርስትና እምነት የሚያወገዝ ከመሆን አልፎ በማህበረሰቡም ዘንድ ተቀባይነት የነበረዉ ነበር፡፡ እዚህ ጋር ልብ ልንለዉ የሚገባ በብድሩ ላይ ምንም አይነት ወለድ ማሰብ የተከለከለ መሆኑን ነዉ፡፡

ነገር ግን መገበያያ ገንዘብ በኢኮኖሚ ዉስጥ ብቸኛ የሆነ የደም ስር እየሆነ ሲመጣ፤ ይህንን ገንዘብ በባንኮች አማካኝነት ማስቀመጥ፣ማዘዋወር እና ለኢንቨስትመንት ማበደር ሲጀመር በብድር በሚሰጥ ገንዘብ ላይ እንደ ፋይናንስ ገበያዉ ወይም ብሔራዊ ባንኮች በሚወስኑት መሰረት ተመጣጣኝ የሆነ ወለድ ማሰብ ተገቢ እና አስፈላጊ መሆኑ በዘመናዊዉ ኢኮኖሚ መዋቀር ታምኖበታል፡፡ ነገር ግን በዘመናዊዉ የኢኮኖሚ መዋቀርም ቢሆን ከፍተኛ የሆነ የወለድ መጠን ለኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ብሎም ፖለቲካዊ ጉዳቶች ምክንያት ስለሚሆን ሀገራት ከፍተኛዉን የወለድ ምጣኔ ይወስናሉ፡፡ ይህንን ጉዳት ለመከላከል በማሰብም ጉዳዩ በወንጀል የሚስቀጣ ሆኖአል፡፡ በህግ ከተወሰነዉ የወለድ ምጣኔ በላይ ገንዘብ ማበደር በብዙ ሀገሮች ዘንድ ወንጀል ተደርጎ ተደንግጓጓል፡፡ ወንጀሉም አራጣ በመባል ይታወቃል፡፡

በኢትዩጵያ ህግም በህግ ከተፈቀደዉ የወለድ ጣሪያ በላይ ብድር ማበደር እንደ ወንጀል ተቀምጧል፡፡ የአራጣ ወንጀልን አስመልክቶ የተደነገገዉ በ1996 ዓ.ም በወጣዉ የወንጀል ህግ ነዉ፡፡ ይህ የወንጀል ህግ በአንቀጽ 712 የአራጣ ወንጀልን እንደሚከተለዉ ይተረጉመዋል፡፡
ማንም ሰዉ የተበዳዩን ችግረኝነት፣ የበታችነቱን፣ ወይም የገንዘብ ችግሩን፣ ወይም መንፈሰ ደካማነቱን፣ ወይም ልምድ ወይም ችሎታ የሌለዉ መሆኑን መሰረት በማድረግ፡-
1. በህግ ከተፈቀደዉ ወለድ በላይ ገንዘብ ያበደረዉ እንደሆነ፤ ወይም
2. ካበደረዉ ገንዘብ ጋራ በግልፅ ተመጣጣኝነት የሌለዉ ንብረት በምትኩ እንዲሰጠዉ ያደረገዉ ወይም ቃል ያስገባዉ እንደሆነ፤
በቀላል እስራት፣ ወይም እንደነገሩ ሁኔታ ከአምስት አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት እና በመቀጮ እንደሚቀጣ ይነግረናል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ማንኛዉም ሰዉ ከላይ በተጠቀሰዉ ሀሳብ መነሻነት በአራጣ ላይ የተመሰረተ መብት የተቀበለ፣ በመከላከያነት የተጠቀመበት ወይም ለሌላ ሰዉ ያስተላለፈ እንደሆነ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጣል፡፡

የአራጣ ወንጀል መንስኤዎች
አስተማማኝ የፋይናንስ አገልገሎት በሌለበት እና ድህነት በሰፈነበት ኢኮኖሚ ዉስጥ የአራጣ ብድር የተለመደ ነዉ፡፡ ገንዘብ የተበደረዉ ሰዉ ገንዘቡን እንደ ነገሩ ሁኔታ ለፍጆታ ወይም ለኢንቨስትመንት ሊያዉለዉ ይችላል፡፡ ድህነት በሰፈነበት ኢኮኖሚ ዉስጥ ሰዎች እለታዊ ችግራቸዉን ለመቅረፍ ሲሉ ከፍተኛ ወለድ የሚታሰብባቸዉ ብድሮችን ለመዉሰድ ይገደዳሉ፡፡ በድህነት ከሚኖረዉ ማህበረሰብ ዉስጥ ጥቂትም ቢሆን ጥሪት ያላቸዉ ሰዎች የአበዳሪነት ሚና በመያዝ በዝባዦች ሁነዉ ይሰየማሉ፡፡ ከድህነት አስከሚወጣም ድርጊቱ ቀጣይ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
በሌላ ገፅ ድህነት መገለጫዉ ባልሆነ ማህበረሰብ ዉስጥም ሰዎች ለኢንቨስትመንት ሲሉ በአራጣ ይበደራሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ለአራጣ ብድር መንስዔዉ ቀልጣፋና በቂ የሆነ የፋይናንስ አገልግሎት አለመኖር ነዉ፡፡ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጭዎች ባንኮችን፣ ማይክሮ ባንኮችን አንዳንዴም የመንግስት ቀጥተኛ ፊሲካል ፖሊሲን ያጠቃልላል፡፡ መንግስት ከፍተኛዉን ግዥ ወይም ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ በሆነበት ኢኮኖሚ ዉስጥ የመንግስት የግዥ እና ክፍያ አፈፃፀም ቅልጥፍና እና ግልፅነት አለመኖር ለአራጣ ብድር መንስዔ ሊሆን ይችላል፡፡ አስተማማኝ የሆነ የፋይናንስ አገልግሎት አለመኖር ሰዎች የአራጣ ብድር መዉሰድን እንደ አማራጭ እንዲያዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች የፋይናንስ ክፍተታቸዉን ለመሙላት በሚያደርጉት ጥረት የፋይናንስ ተቋማት በግዜ ሊደርሱላቸዉ ካልቻሉ በአራጣ ለመበደር ስለሚገደዱ ነዉ፡፡

የአራጣ ወንጀል ጉዳቶች
የአራጣ ወንጀሎች መጠናቸዉና ግዝፈታቸዉ በጨመረ ቁጥር ከፍተኛ የሆነ ሀገራዊ ጉዳት ብሎም ሀገራዊ ህልዉና ላይ ፈተና የሚጋርጡ ናቸዉ፡፡ እነዚህ ወንጀሎች በፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳት ቢኖራቸዉም በጣም የከፋዉን ጉዳት የሚያደርሱት ግን በኢኮኖሚ ላይ ነዉ፡፡
ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች
በአሁኑ ሰዓት የአለም ኢኮኖሚ በአጠቃላይ በሚባል ሁኔታ የሚንቀሳቀሰዉ በወለድ መርህ ነዉ፡፡ በኢኮኖሚ ዉስጥ የሚንቀሳቀስ ማንኛዉም ንብረት ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ዋጋ እንዳለዉ ይታሰባል፡፡ ገንዘብም በኢኮኖሚ ዉስጥ ዕቃዎችን ለመግዛት፣ ኢንቨስት ለማድረግ፣ ምርቶችን ለመለዋወጥ እና ግዴታዎችን ለመወጣት አይነተኛ ካልተጋነነ ደግሞ ብቸኛዉ መሳሪያ ነዉ፡፡ ስለሆነም ይህንን ገንዘብ በኢኮኖሚ ዉስጥ ተዋናይ ለሆኑ አካላት በማቅረብ የማይተካ ሚና ያላቸዉ የፋይናንስ ተቋሞች ናቸዉ፡፡ ዋነኞች የፋይናንስ ተቋሞች ባንኮች ሲሆኑ ባንኮች ይህንን ስራ በሚሰሩበት ወቅት የሚመሩት ገንዘብ በሚበደሩት እና በአስቀማጮች ላይ በሚሰላ ወለድ ነዉ፡፡ ሆኖም ይህ የባንኮች የወለድ መጠን መሬት ላይ ያለዉን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ(ገበያ) መሰረት የሚያደርግ እንጅ በዘፈቀደ የሚወሰን ወይም የተጋነነ አይደለም፡፡ የወለድ መጠኑ የተጋነነ (አራጣ) ሲሆን የሚከተሉት ጉዳቶች አሉት፡፡

የመጀመሪያዉ ጉዳት፣ የአራጣ ወንጀል ከመነሻዉ በወንጀል ህጉ በተደነገጉ ምክንያቶች ያልተገባ የወለድ ስሌት ተበዳሪዎችን በማስከፈል የሚፈፀም ነዉ፡፡ እነዚህ ተበዳሪዎች እንዲከፍሉ የሚጠየቁት የወለድ መጠን በጣም የተጋነነ ስለሆነ ብድሩን መልሰዉ ሲጨርሱ ወይም በመካከል ተበዳሪዎች ያላቸዉን ሀብት ወይም በብድሩ ገንዘብ ሰርተዉ ያገኙትን ትርፍ አበዳሪዉ ስለሚወስድባቸዉ ለኪሳራ ይዳረጋሉ፡፡ በዚህም ቀድሞዉን እነዚህ በኢኮኖሚ ዉስጥ አምራች የሆኑ ሰዎች ጥሪታቸዉን ሁሉ ለአበዳሪያቸዉ አስረክበዉ ተሰብረዉ እንዲቀመጡ ያደርጋል፡፡ ምርትም ይቆማል ማለት ነዉ፡፡ ተበዳሪዎች ግዚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ብለዉ በተበደሩት ገንዘብ ድህነትን ሸምተዉ ድሀ ሆነዉ ሲቀሩ፤ አበዳሪዎችም ምንም እሴት በኢኮኖሚ ዉስጥ ሳይጨምሩ ሀብት የሚሰበስቡበት ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ ይህ ክስተት(ኢኮኖሚያዊ ጉዳት) በግብርናዉ፣ በኢንዱስትሪዉ እና በአገልግሎት ክፍለ ኢኮኖሚዎች ላይ ሁሉ የሚሆን ነዉ፡፡
ሁለተኛዉ ጉዳት የሚያያዘዉ ገንዘብ ያላቸዉ ሰዎች ገንዘባቸዉን ባንክ እንዳያስቀምጡ ከማድረጉ ጋር ተያያዘ ነዉ፡፡ ይህ ጉዳይ የሚከሰተዉ ጥቂትም ቢሆን ገንዘብ ያላቸዉ ሰዎች ገንዘባቸዉን ወደ ባንክ በማስቀመጥ ፋንታ አራጣ በማበደር እንዲሰማሩ በማድረጉ ነዉ፡፡ ይህም ገንዘቡ በባንክ ተቀመምጦ ለኢኮኖሚዉ ሊያበረክተዉ የሚችለዉን አስተዋጽኦ ያስቀረዋል፡፡ ወደ ባንኮች የሚሄደዉ ተቀማጭ እየቀነሰ መሄዱ በመጨራሻም ባንኮች አቅም እያጠራቸዉ እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል፡፡ ባንኮች ለብድር የሚዉል ተቀማጭ ገንዘብ እያጠራቸዉ ሲሄድ በተዘዋዋሪ አራጣ አበዳሪዎች የብድር አማራጭ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ በተመጣጣኝ ወለድ መጠን ገንዘብ ተበድረዉ ስራ ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎች ብድር ሳያገኙ እንዲቀሩ በአራጣ ቢወስዱም እንኳ ዉጤታማ ሳይሆኑ እንዲቀሩ ያደርጋል፡፡
ሶስተኛዉ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት፣ በጣም አቅም ያላቸዉ ሰዎች ወደዚህ ወንጀል ሲሰማሩ የሚከሰተዉ አይነት ነዉ፡፡ ከፍተኛ ገንዘብ ያላቸዉ ሰዎች አራጣ ማበደር ሲጀምሩ ተጽዕኖዉ እየከፋ በመሄድ ባንኮች የብሄራዊ ባንክ መመሪያዎችን በመከተል ስራቸዉን መስራት በማይችሉበት ደረጃ ያደርሳቸዋል፡፡ አራጣ የሚያበድሩ ሰዎች ምንም አይነት መመሪያ የማይከተሉና ከወለዱ መብዛት በቀር ላላ ያለ ዉጣ ዉረድን የማይጠይቁ ስለሆነ ተበዳሪዎችን በመሳብ የባንኮችን ስራ ወደ መጋራት ደርሰዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም አበዳሪዎች ተበዳሪዎችን በመምረጥ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ዉድድር እንዲፈጠር ያደርጋሉ፤ ተበዳሪዎች የተበደሩትን ገንዘብ የሚያዉሉበትን የስራ መስክ በመምረጥ ገንዘባቸዉ የሚመለስበትን ሁኔታ ብቻ በማመቻቸት ዘላቂ ልማት እና እሴት በማይጨምር መልኩ የሀገር ሀብት እንዲባክን ደደርጋሉ፡፡ ይህ ተፅዕኖ በጣም ሲከፋም በዚህ ወንጀል ዉስጥ ባንኮች እስከመሳተፍ የሚደርሱበት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡

የመጨረሻዉ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በመንግስት ላይ በቀጥታ የሚደርሰዉን የሚመለከት ነዉ፡፡ በአራጣ የሚዘዋወረዉ ገንዘብ ላይ መንግስት እዉቅና የሌለዉ ስለሆነ ከትርፉ ላይ ግብር ስለማይከፈል መንግስት ገቢ ሳይሰበስብ ይቀራል፡፡ ከፋይናንስ አገልግሎት ገቢ ሳይሰበሰብ መቅረቱ መንግስትን ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስበት ይሆናል፡፡

ማህበረሰባዊ ጉዳቶች
ማህበራዊ ጉዳቶች ከሞላ ጎደል ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች የሚመዙት ችግር ነዉ፡፡ የኢኮኖሚ እድገቱ በመጎተቱ ምክንያት ወይም በየደረጃዉ ያሉ የግል ተበዳዩች በቀጥታ ለማህበራዊ ዝቅጠት ይዳረጋሉ፡፡ ማህበራዊ ቀዉስ የመጨረሻዉ ዉጤት ይሆናል፡፡

ፖለቲካዊ ጉዳቶች

ፖለቲካዊ ጉዳቶች የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀዉሶች በሚያመጡት ዉጤት ወይም ከፍተኛ አቅም ያላቸዉ አራጣ አበዳሪዎች ፖለቲካዉን ማለትም የመንግስትን ስልጣንና ፖሊሲዎችን በመዘወራቸዉ የሚገለፁ ናቸዉ፡፡
via Legal counseled limited
@lawsocieties @AleHig
• Ethiopia 🇪🇹 has the highest number of cattle in Africa with 70 million as of 2020.

• Tanzania 🇹🇿 comes in second place with 33.9 million cattle according to the 2019/2020 National Bureau of Statistics (NBS) of Tanzania.

• Chad comes third with 32.2 million cattle.

#አለ_ህግ #Alehig

@lawsocieties @AleHig

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
በህግ አምላክ
ግራ እጅ የሌለው ጎበዝ ተማሪ ዶ/ር መሆን አይችልም ወይ?
ቢኒያም ኢሳያስ 3.8 ግሬድ ያለው 5ኛ ዓመት የህክምና ተማሪ ነበር። አሁን ግን መቀጠል አትችልም ተብሎ ተወስኖበታል።
አባቱ አቶ ኢሳያስ ልባቸው ተሰብሮ እያለቀሱ ነው።
ቢያንስ ሁለት እጅን ብዙ የማይፈልጉ የህክምና ስፔሻሊቲዎች ላይ መሥራት፣ አልያም ማስተማር አይችልም ወይ? በሌሎች ሀገራት የህክምና ት/ቤቶች ይህንን መሰል ውሳኔ ይቃወማሉ>

ለምስት ሰው ሼር በማድረግና በማጋራት ፍትህን በፍለጋ በህግ አምላክ በሉ።

please, share for justice. https://www.healthcareers.nhs.uk/explore-roles/doctors/career-opportunities-doctors/doctors-disabilities#:~:text=A%20disability%20or%20mental%20health,can%20offer%20patients%20genuine%20empathy

#አለ_ህግ #Alehig

@lawsocieties @AleHig

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በነዳጅ መጨመር ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በሲሪላንካ ዋና ከተማ ኮሎምቦ የሚገኘውን የፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤት ጥሰው ገብተዋል።

ገብተውም በፕሬዜዳንቱ የመዋኛ ገንዳ ሲዋኙ፣ በመኖሪያ ቤቱ በመግባትም ሲበሉ ፣ ሲጠጡ ፣ አልጋቸው ላይ ሲተኙ፣ መሳቢያዎቸውን እየከፈቱ እቃዎቻቸውን ሲበታትኑ ውለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ለጊዜው ደኅንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ መወሰዳቸውንና ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን አንድ ከፍተኛ የጦር ሹም ለኤኤፍፒ ገልጸዋል።

ፖሊስ፣ ወታደር ሀገሪቱ አለኝ የምትለው የፀጥታ ኃይል የዛሬውን ህዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠርም ሆነ መቋቋም አልቻሉም።

ለወራት በዘለቀውና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር በአግባቡ ባለመቆጣጠር በተነሳ ነው ፕሬዚዳንቱ ህዝባዊ ተቃውሞ የገጠማቸው።

ከዚህ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኒል ዊክሬሜሲንጌ ስልጣኔ ይቅርብኝ እውርዳለሁ ማለታቸውን ፅ/ቤታቸው አሳውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉንም ያሳተፈ መንግሥት እንዲመሰረት ለማድረግ ስልጣን ለመልቀቅ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነው የገለፁት።

ሲሪላንካ በአሁኑ ወቅት ላይ ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ውስጥ ናት። ሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ያጋጠማት ሲሆን፤ መድኃኒት፣ ነዳጅ እና ምግብ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት እንደተሳናት ቢቢሲ ፅፏል።

መረጃው ከሲሪላንካ ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ ከቢቢሲ፣ ኤኤፍፒ የተሰባሰበ ነው።

Video Credit : Anoyme Citoyen, SLTweet, Jamila Husain
via tikvahethiopia
#አለ_ህግ #Alehig

@lawsocieties @AleHig

https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
በአ.አ ከተማ አስተዳደር ከሥራ ባህሪያቸው አንፃር ከመንግሥት የሥራ ሰዓት ውጩ ገብተው እንዲሠሩ በሚያስፈልጉ የሥራ መደቦች ላይ የፐብሊክ ሰርቪስ የሰ/ኃ/ል/ቢሮ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስሌት አጥንቷል። በአንድ ወር ውስጥ የሚሠራው የትርፍ ሰዓት ጠቅላላ ተደምሮ ከ80 ሰዓት መብለጥ እንደሌለበት ሰፍሯል።
Vacancy at Ministry of Education

🔰Number of Positions: , 42 - positions with EXP

Professions: accounting,management,purchasing , social-work, sociology, statistics anthropology, applied-biology, communication, curriculum-studies, development-economics, development-studies, economics, education, education-leadership-and-management, education-planning-management, english-teacher, environmental-engineering, gender,geogr aphy, law, public-relation ,social-anthropology

📌 Deadline: July 22, 2022

📌ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇👇
👉Read Detail:-https://bit.ly/3RntFCk
Protection Officer Legal Job at DRC

Danish Refugee
Council (DRC)

Jijiga

Full–time

The DRC has published a job vacancy announcement on 9th July 2022 for qualified Ethiopians to fill in the vacant post of Protection Officer Legal to be based in Jijiga, Ethiopia. Recruiter Danish Refugee Council Position Protection Officer Legal Location Jijiga, Ethiopia Country Ethiopia Total Vacant Post N/A Qualification University Degree Experience Required Minimum Two years Application Deadline 20th July 2022 DRC Job Vacancy 2022 Overall Purpose Of The Role: The Legal officer under the supervision of Protection Team leader will undertake protection and legal activities within the project framework. The legal officer will be engaged in the provision of legal aid service including legal information dissemination, counselling, assistance, and facilitation of representation to the target population. In addition, the officer will take on any additional protection activity as required by the Protection Team Leader to meet the project objective.
Position in Organization: Title: Protection Officer- Legal
Location: Jigjiga, Dolo Ado and Dire Dawa Employment Category: H2 Reporting To: Protection Team leader Direct Reports: N/A Start of Contract & Duration: Six Months (6 Months) Application due: 7/20/2022 Workplace: Jigjiga , Dolo Ado and Dire Dawa Department/Country: Ethiopia Contract type: National contract Homepage: drc.ngo

Qualification: University degree in Law/ LL. B Experience: Minimum 2 years work experience in the legal sector, preferably in a humanitarian context; Prior Experience working with persons of concern including refugees, internally displaced and/ or returnees; Experience and familiarity with Ethiopia’s judicial system;

How to Apply DRC Protection Officer Legal Jobs 2022 Note: Before you apply, please download (link is given below) the full advertisement and read it carefully. Then to apply, go to https://candidate.hr-manager.net/ApplicationInit.aspx?cid=1036&ProjectId=165092&DepartmentId=19012&MediaId=5 The Closing Date: 20th July 2022. Only shortlisted candidates will be contacted for interviews
☀️Job Opportunity for law graduates☀️
The Armauer Hansen research Institute (AHRI) a Norwegian and Swedish based organization is searching for fresh graduate lawyers. So, if you have an LLB check out the requirements and submit your application.
👉🏾Click here to apply; https://bit.ly/3NSngvH
👉🏾Application deadline; July 19, 2022
#dereja #findyournextstep #youngafricaworks #lawgraduates #opportunities
The Law in Ethiopia: Where it is Now and Where it is Headed
Please, comment on it❗️
👇👇👇👇ዋስትና👇👇👇

የተጠርጣሪን የኋላ ታሪክ እስክናውቅ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይፈቀድልን
ተከሳሹ ደጋጋሚ ወንጀለኛ ስለሆነ ዋስትና ሊፈቀድ አይገባም በሚል የምትከራከሩ ዐ/ህግ እና መርማሪ ፖሊሶች እንዲሁም ይህን በምክንየትነት የምትቀበሉ ዳኞች ተከታዩን ግንዛቤ እንድትወስዱ "የተጠቃለሉ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች ከቅፅ1-23" መፅሃፍ መሀል ይህን የሰበር መዝገብ እንደ ማሳያ እነሆ።

👇👇👇
የሰ/መ/ቁ.132055፡-በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 67 (ለ) ስር የተደነገገው የዋስትና መብት ገደብ በተከሳሹ ያለፈ የወንጀል ታሪክ ላይ የሚመሠረት አይደለም፡፡

ይልቁንም የድንጋጌው ዓላማ በእጅ ላይ ያለውን የክሱ ሂደት ሊያደናቅፍ ይችላል ተብሎ በሚገመትበት ጊዜ በዋስ የመለቀቅ መብቱን ለመገደብ ነው፡፡ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 67 (ለ) ከንዑስ ቁጥር (ሀ) እና (ሐ) ጋር በአንድነት ሊነበብ ይገባል፡፡

ህጉ የተከሳሹን በዋስ የመለቀቅ መብት እየገደበ ያለው በዋስትና ወረቀት ላይ የሰፈሩትን ግዴታዎች አይፈጽምም ተብሎ ሲገመት ወይም ምስክሮችን ሊያባብል ወይም ሊያስፈራራ ይችላል ወይም ማስረጃዎችን ሊያጠፋ ይችላል ተብሎ ሲገመት ነው፡፡

የቁጥር 67 (ለ) ድንጋጌም ከንዑስ ቁጥሮች (ሀ) እና (ለ) ጋር በጣምራ ሲነበብ “ሌላ ወንጀል ሊሠራ ይችላል ተብሎ ሲገመት” የሚለው ድንጋጌ ከተያዘው ክስና ከተጀመረው የፍርድ ሂደት ጋር በተያያዘ ጠባብ የህግ ትርጉም በተጣጣመ መልኩ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡

ፍ/ቤቶቹ የተከሳሽችን ያለፈ የቅጣት ውሳኔ አሁን ከተከሰሰበት ጉዳይ ጋር በማያያዝ በዋስ ቢለቀቅ ተመሳሳይ ወንጀል ሊፈጽም ይችላል የሚል ግምት በመውሰድ የዋስትና ጥያቄውን አለመቀበል አግባብ አይደለም፡፡

በተጨማሪም በሌላ በኩል የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 138 (1) ህጉ በግልጽ ካልተደነገገ በቀር ተከሳሹ በፍርድ ዳኝነት በግልጽ እስካልታወቀ ድረስ የቀድሞ ጥፋተኝነቱ አይገለጽም ሲል ደንግጓል፡፡
ድንጋጌው የተከሳሽን ንጹህ ሆኖ የመገመት ህገ-መንግሥታዊ መብት የሚያመለክት ሲሆን በተጨማሪም ዳኞች የወንጀል ጉዳይ በሚመረምሩበት ጊዜ በተከሳሹ የጥፋተኝነት ሪከሪድ ጫና አድሮባቸው የተሳሳተ ውሳኔ እንዳይሰጡ ለማድረግ የሰፈረ ነው፡፡

በመሆኑም የተጠርጣሪዉ የቀድሞ የጥፋተኝነት መዝገብ በጊዜ ቀጠሮ ጊዜ ሲቀርብ ፍ/ቤቶች ከላይ በተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ መሠረት እንዳልቀረበ በመቁጠር ሊወሰን ይገባል እንጂ ህጉን በመጣስ በተጠርጣሪዉ የቀድሞ የጥፋተኝነት መዝገብ ላይ በመመሥረት ማከራከር እና መወሰን መሠረታዊ የህግ ስህተት ነዉ፡፡

በአጠቃላይ የአንድ ተከሳሽ ያለፈ የቅጣት ውሳኔን አሁን ከተከሰሰበት ጉዳይ ጋር በማያያዝ በዋስ ቢለቀቅ ተመሳሳይ ወንጀል ሊፈጽም ይችላል የሚል ግምት በመውሰድ የዋስትና ጥያቄን አለመቀበል አግባብነት የለዉም፡፡እንዲሁም በህግ በግልጽ ካልተደነገገ በቀር አንድ ተከሳሽ በፍርድ ዳኝነት በግልጽ እስካልታወቀ ድረስ የቀድሞ ጥፋተኝነቱ ሊገለጽ አይገባም፡፡ቅጽ/23

via #henoktaye law office

#አለ_ህግ #Alehig

@lawsocieties @AleHig

https://t.me/lawsocieties

https://t.me/AleHig