አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
Trade remedies.pptx
73.9 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade.pdf
272.5 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 42.docx
43.2 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
trade 4.pptx
118 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
Trade remedies.pptx
73.9 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️
813_2013-trade-competition-and-consumers-protection.pdf
26.8 MB
Forwarded from አለሕግAleHig ️
Law Of Traders & Bisness Organizations.pptx
408.1 KB
Forwarded from አለሕግAleHig ️
813_2013-trade-competition-and-consumers-protection.pdf
26.8 MB
እስከ መጋቢት 12/2014 ዓ.ም የማስገቢያ ጊዜው ተራዝሟል
አለሕግAleHig ️
የህግ የበላይነት ብዙ ምሁራን በየፊናቸው በምርምርና ጥናት ባገኙት እውቀት ተመርኩዘው የህግ የበላይነት መርህ ምንነት፤ ይዘትና ፋይዳውን አስመልክቶ አያሌ ንድፈ ሀሳባዊ ትንታኔዎችን አቅርበዋል፡፡ በአገራችን ደግሞ አባቶችና እናቶች በልባቸው ከተጻፈው እውነትና ከልምድ ከቀዱት ቱባ እውቀት በመነሳት የህግ የበላይነትን ጽንስ ሀሳብ በአንድ አባባል እንዲህ ይገልጹታል፡፡ “በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ያለፍርድ የሄደች…
የስልጣን ክፍፍል

የስልጣን ክፍፍል በአገራችን ህገ መንግስታዊ መርህ ሲሆን ህግ አውጭው፤ ህግ ተርጓሚውና ህግ አስፈፃሚው ያላቸውን ስልጣን ከፋፍሎ ያስቀምጣል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ መርህ በተቃራኒ የአስተዳደር ህግ ከተግባራዊ ምክንያቶች የተነሳ ስራ አስፈፃሚው አካል ሕግ ከማስፈፀም ስልጣኑ በተጨማሪ ህግ የማውጣትና ህግ የመተርጐም ተግባራትን እንዲያከናውን በልዩ ሁኔታ ይፈቅዳል፡፡ እነዚህ ተደራራቢ ስልጣናት የመንግስት አስተዳደርን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ሁኔታ የተሰጡ እንጂ በመርህ ደረጃ ከስልጣን ክፍፍል መሰረተ ሀሳብ ጋር ይጋጫሉ፡፡ ስለሆነም የህገ መንግስቱ የስልጣን ክፍፍል መርህ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ደንብና መመሪያ የማውጣት እና ዳኝነታዊ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን በአፈፃፀም ረገድ በጠባቡ እንዲተረጐም በማድረግ የዚህ ስልጣናቸው ገደብ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ይኸው መርህ ፍርድ ቤቶች ሚናቸው እስከየት ድረስ እንደሚዘልቅ ይወስናል፡፡ መደበኛ ፍ/ቤት በህግ ተለይተው በታወቁ የምርመራ ምክንያቶች ስልጣን ካልተሰጠው በስተቀር በስልጣን ውስጥ የተፈፀመ ድርጊት ከማረም መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ ፍ/ቤቶች በስልጣን ውስጥ የተፈፀመ ድርጊትን የሚያርሙ ከሆነ በስራ አስፈፃሚው ስልጣን ጣልቃ በመግባት የስልጣን ክፍፍል መርህን ይጥሳሉ፡፡
ደረጃ እና እርከን እንዴት ይወጣል .pdf
820.4 KB
በወንጀል ቅጣት ሂደት ደረጃ እና እርከን ያልወጣላቸውን ወንጀሎች ደረጃና እርከን ሲወጣ ስህተት መኖሩ፤ ተመጣጣኝና ወጥ ቅጣት አለመኖሩ፣ እና የቅጣት አነሰ በዛ ይግባኛኝ በፍ/ቤቶቻችን መስተዋሉ፣ እና በቴክኒካል ቅጣት አሰራር ችግር ምክኒያት የቅጣት አሰጣጥ እና አተገባበር ችግር መኖሩ እና በአንዳንድ ደኞች ቅጣትን በአግባቡ ማሰላት አለመቻል ስለሚስተዋል ዳኞች ቅጣትን ለመወሰን ደረጃ እና እርከን በማዉጣት የሚወስደዉን ጊዜ ለመቆጠብ ብሎም ይህንን ደረጃ እና እርከን ለማዉጣት የሚቸገሩ ዳኞችን በመረዳት በወንጀል ዉሳኔ አሰጣጥ ጊዜ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት ደረጃ ያልወጣላቸዉን የወንጀል ድንጋጌዎችን በተመለከት ደረጃ እና እርከን እንዴት ይወጣል? የሚለዉን የቀመር አወጣጥ ችግር ይቀርፋል ያሉትን መፍትሄ ለፍርድ ቤታችን በማስፈለጉ ይህ ፅሁፍ ተዘጋጅቷል፡፡
Etrade for Region Training 16-3-2022.pdf
1.7 MB
Vacancy at Ethiopian Human Rights Commission (EHRC)

♨️ Experience: 0 year

♨️SALARY: ETB 16,515.00- ETB 19,670.00 plus ETB 6,000.00 Housing allowance and ETB 1,500.00 Transport allowance

♨️ MA/BA Degree Law, Human Rights Law, International Law and Related field

📌 Deadline: Mar 29, 2022

📌ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇👇
👉Read Detail:- https://bit.ly/3FrxD6l
Apply via HRM@ehrc.org
🔰ከተለያዩ ድርጅት የሥራ ማስታወቂያዎች
በዚህ ሊንክ ዌብሳይቱ ላይ ይመልከቱት👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ
#አለ_ህግ
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
#Boston Partners PLC#10 - Position
🚩For Fresh & Exp

▪️1- Trainee Manager
▪️2 - Receptionist
▪️2 - Accountant
▪️3 - Bussiness Development Assistant
▪️4 - Architect
▪️5 - Office Secretary
▪️6 - Legal Officer
▪️7 - Event Coordinator
▪️8 - Admnistration Assistant
▪️9 - Marketing Representative
▪️10 - Graphics Designer
▪️Find More Details here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3MZgw06

▪️Deadline - March 31, 2022

🔰ከተለያዩ ድርጅት የሥራ ማስታወቂያዎች
በዚህ ላይ ይመልከቱት👇#አለ_ህግ
#አለ_ህግ
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
#UNHCR(For Fresh Graduate)#

▪️Position - Internship on Risk Management
▪️Experience - 0 year
▪️Education - Be a recent graduate or studies in current or Majoring in a Degree.
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3vGVNYH

▪️Deadline: March 17, 2022
One_person_private_limited_Company_vs_Limited_Liability_Partnership.pdf
174.7 KB
🔶One Person Private Limited Company Vs Limited Liability Partnership Under the New Commercial Code of Ethiopia

ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (One-person private limited Company) እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር (Limited Liability Partnership) በአዲሱ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013


ባሳለፍነው ዓመት ኢትዮጵያ ላለፉት ስድስት አስር አመታት ስትጠቀምበት የነበረውን የንግድ ሕግ በማሻሻል በአዲሱ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 ተክታለች፡፡ በቀድሞ የንግድ ህግ አንድ ነጋዴ ሊመሠርት የሚችለው የንግድ ማህበር ወይም ድርጅት ስድስት ዓይነት ሲሆን እነዚህም ተራ የሽርክና ማህበር (ordinary partnership) ፣ የህብረት ሽርክና ማህበር (general partnership) ፣ ሁለት ዓይነት ኃላፊነት ያለበት የሽርክና ማኅበር (limited Partnership)፣ የእሽሙር ሽርክና ማህበር (joint venture) ፣ የአክሲዮን ማህበር (share company) እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል (private limited company) ማህበር ናቸው፡፡

በአዲሱ የንግድ ሕግ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (One-person private limited Company) እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር (Limited Liability Partnership) አዲስ የተጨመሩ ማህበራት ሲሆኑ ተራ የሽርክና ማህበር ደግሞ ከአማራጭ ማህበርነት ተቀንሷል፡፡ የዚህ አጭር ፅሁፍ ዓላማ አዳዲስ የተጨመሩትን እንግዳ የንግድ ማህበራት በመመርመር ማስተዋወቅ ነው፡፡

መልካም ንባብ!

#AbyssiniaLaw
#AbejeKassahunAdamu
#አበጀካሣሁን
#የይርጋ መነሻ ጊዜና የሰበር የህግ ትርጉም፦

የይርጋ ቀን መቆጠር የሚጀምረው ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ወይም ውሉ የሚሰጠው መብት ከተሰራበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ የሥራ ውል የተቋረጠበትና የስንብት ደብዳቤ የተሰጠበት ቀን ከተለያየ ይርጋ መቆጠር የሚጀምረው ደብዳቤው ለሠራተኛው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 94931 ቅጽ 16፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1846

በፍትሐ ብሔር ስነ-ስርዓት ህጉ የሚገኙት የጊዜ ገደቦች አቆጣጠር የሚመራው በፍትሐ ብሔር ህግ ባሉት የጊዜ አቆጣጠር ደንቦች ነው፡፡ ጉዳዩ በሌለበት ታይቶ ውሳኔ የተሰጠበት ወገን ውሳኔው እንዲነሳለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 78/1/ መሰረት በአንድ ወር ውስጥ የሚያቀርበው ጥያቄ የአንድ ወር ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ውሳኔ መሰጠቱን ከተረዳበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ቀን ለይርጋው ጊዜ መቆጠር መነሻ አይሆንም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 76601 ቅጽ 13፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 78/1/

በወራሾች መካከል ውርስ እንዲጣራ አቤቱታ መቅረብ ያለበት በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሲሆን ይህም ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው አንደኛው ወራሽ የውርሱን ንብረት በእጁ ካደረገበት እንጂ ስመ ሀብቱን በስሙ ካዞረበት ጊዜ ጀምሮ አይደለም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 52407 ቅጽ 11፣ ፍ/ህ/ቁ. 1000/1/

ከውርስ ሃብት ጋር በተያያዘ ወራሽ የሆነና አካለ መጠን ያልደረሰ ሰው ላይ የይርጋ ጊዜ ሊቆጠር የሚገባው አካለ መጠን ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 57114 ቅጽ 11

ይዞታን አስመልክቶ ከሚነሳ የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ መቆጠር ያለበት አቤቱታ አቅራቢው የይዞታ መብቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ካገኘበት ቀን ጀምሮ እንጂ አቤቱታ የቀረበበት ድርጊት መፈፀም ከጀመረበት ዕለት አይደለም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 60392 ቅጽ 11፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1140፣ 1149፣ 1146/1/፣ 1144/2/(በሎው ሶሳይቲ)