አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ስለወጭና ስለኪሳራ /በክርክሩ ምክንያት የወጡ ወጪዎች የሚመለከተው ወገን/
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
#ስለ ፍርድ ቤቱ ሥልጣን
በሌላ አኳኋን እንዲፈጸም በግልጽ ካልተደነገገ በቀር በክስ ምክንያት ስለሚከፈለው ስለማናቸውም ወጭና ኪሳራ፣ የሚከፈለውን ወገን የወጭንና የኪሳራውን ልክ የሚከፈልበትን የሃብት ምንጭ የአከፋፈሉን ሁኔታ ሌላውንም ተገቢ መስሎ የታየውን ውሳኔ ወይም ትእዛዝ ፍርድ ቤቱ ትክክል በስሎ በሚገመተው ሁኔታ ሊሰጥ ይችላል፡፡
#ስለወጭና ስለኪሳራ ዝርዝር
ተረቺው ለረቺው ኪሳራና ማናቸውንም ወጭ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ሲያዝ፣ ወጭ ያደረገው ወገን የወጭውን ልክ የሚያሳይ ዝርዝር አዘጋጀቶ ማቅረብ አለበት፡፡
ዝርዝር የሚቀርበው ፍርዱን ለፈረደው ፍርድ ቤት ሲሆን አንዱ ግልባጭ ለከፋዩ ወገን ይሰጣል፡፡
#የወጭው ሂሳብ ስለሚመረመርበት ሁኔታ
የወጭው ሂሳብ ዝርዝር ለፍርድ ቤቱ ከቀረበ በኋላ ትክክለኛነቱ የሚመለመርበትን ቀን ቀጠሮ ወስኖ ባለጉዳዮቹ እንዲቀርቡ ያዛል፡፡
ሂሳቡን መርምሮና ተከራካሪዎቹ ወገኖች የሚያቀርቡትን ሃሳብ ተቀብሎ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ይፈጽማል፡፡
በቀረበው የሂሳብ ዝርዝር ውስጥ በቂ ባልሆነ ምክንያት ከፍ ብሎ የሚታየውን ገንዘብ ይቀንሳል፡፡ ወይም
በዝርዝሩ ውስጥ የክሱን ጉዳይ ለማስፈጽም ወይም አስፈላጊውን ዳኝነት ለመከታተል ተገቢ ያልሆነ ወጭ ተመልክቶበት የተገኘ እንደ ሆነ ፍርድ ቤቱ ሊቀንሰው ወይም ሊያስቀረው ይችላል፡፡
ወጭው ወይም ኪሳራው ሊከፍለው የሚገባው ወገን የሚጠይቀውን የወጭ ዝርዝር ያላቀረበ እንደ ሆነ ፍርድ ቤቱ ይህንኑ መዝግቦ ሌሎች ወገኖች ያደረጉትን ወጭ መርምሮ ያረጋግጥላቸዋል፡፡ ወይም የሂሳቡን ዝርዝር አንዱ ወገን ባለማቅረቡ ምክንያት ሌሎች ወገኖች እንዳይጎዱ ላላቀረበው ወገን ተገቢ ግምት ያለው ኪሳር ይወስንለታል፡፡
ማንኛውም የወጭ ወይም የኪሳራ ገንዘብ በፍርዱ መሰረት እስኪፈጸም ድረስ ዋናው ፍርድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሕግ የተወሰነ ወለድ ይታሰብበታል፡፡
ፍርድ ቤቱ በኪሳራና በወጭ አከፋፈል ምክንያት ለተነሳው ክርክር ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የፍርድ ቤቱ ሬዢስትራር ወይም የምግብ ቤቱ ሹም የቀረበውን ዝርዝር መርምሮና ተከራካሪዎቹ ወገኖች የሚያቀርቡትን አሳብ ተቀብሎ የተጣራውን ሂሳብ እንዲያቀርብለት ከማዘዝ የዚህ ቁጥር ድንጋጌ አያግደውም፡፡
#ካሳ ስለሚከፈልበት ምክንያት
በማንኛውም ክስ ወይም ክርከር ላይ በክስ ወይም በመከላከያ መልክ ከሳሹ ወይም ተከሳሹ ያቀረበው የመከራከሪያ ወይም የመከላከያ ማስረጃ ወይም ክርክሩ ራሱ ወይም ማስረጃው አሰተኛ ነው ወይም መከራከሪያውንና አሰተኛ ማስረጃ ያቀረበው ወገን በሐሰት የተከራካሪውና አሰተኛ ማስረጃ ያቀረበው ክርክሩን ለማሰናከል፣ ጊዜ ለመፍጀት ወይም አንደኛውን ወገን ለመበደል ወይም ለማጉላላተር ሆነ ብሎ ያደረገው ነው በማለት ወይም የክርክሩንና የማስረጃውን አሰተኛነት እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ሆን ብሎ ማቅረቡን ሲያመለክትና ፍርድ ቤቱም ተቃዋሚው ወገን ያቀረበውን ነገር እርግጠኛነት ሲረዳው ይህንኑ በመዝገቡ ላይ አስፍሮ አሰተኛ ማስረጃ ወይም ክስ ወይም መከላከያ ያቀረበው ወገን ላቀረበው ለእያንዳንዱ ሀሰተኛ ማስረጃአንዱን ወገን ለመበደል፣ ለማጉላላት ወይም ጊዜ ለመፍጀት ላቀረበው አሰተኛ ክርክር ከማናቸውም ኪሳራና ከሌላው ወጭ በቀር ከ500 ብር የማይበልጥ ካሳ ለተበዳዩ እንዲከፈል ሊወስንበት ይችላል፡፡
#ይህም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በቁጥር 446 በተመለከተው መሰረት ሃሰተኛ ማስረጃና ክርክር በማቅረቡ ከመከሰስና ከመቀጣት ነፃ ሊሆን ይችላል፡፡
ካሳ የተወሰነለት ወገን በሀሰት በመከሰሱ ወይም ሃሰተኛ መከላከያ ወይም ክስ የቀረበበት በመሆኑ ካሳና ኪሳራ ይገባኛል ሲል ሌላ ክስ አቅርቦ ካሳ ወይም ኪሳራ የተወሰነለት እንደሆነ በመጀመሪያው ክስ ላይ ከሚወስንለት ኪሳራና ካሳ ላይ ይቀነስበታል፡፡
#ስለ ይግባኝ
ማንኛውም ተከራካሪ ወገን በስረ ነገሩ ላይ ይግባኝ ባያቀርብም፣ በተወሰነበት የወጭ ወይም የኪሳራ አከፋፈል ብይን ላይ ይግባኝ ለማለት ይችላል፡፡ በዚህም ነገር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡
መረጃ!
Vsat LNB ይባላል፣ ይህ መሳሪያ ማንኛውም ዲሽ ላይ ከተገጠመ ከቴሌ እውቅና ውጭ ስልክ መደወል እና ኢንተርኔት ማስጠቀም ያስችላል። ይህን እና ይህን መሰል መሳሪያ ማንኛውም ዲሽ ላይ ከተመለከቱ ለፖሊስ ይጠቁሙ! ሐገር ያድኑ።

ብዙ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት በስፋት በአዲስ አበባ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ የተያዙም አሉ። ሐገራችንን በጋራ እንጠብቅ!

መረጃውን ሼር በማድረግ ለሌሎች አድርሱ! #በፍጥነት_ሼር
https://t.me/lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
Senior Attorney

Lucy Insurance S.C

Addis Ababa

Full–time

Job Title: Senior Attorney Company: Lucy Insurance S.C Salary: As per Company Scale Location: Addis Ababa Deadline: November 15, 2021 Job Requirement
• Qualifications and skills: LLB in Law
• Minimum Work Experience: 4 years’ experience as a legal expert (attorney)in addition, those who have minute taking experience (exposure as Board Secretary)are more advantages
• Other required skills:– Computer literate
• Year of experiences will be counted after graduation Duty Station: Addis Ababa
How to Apply
Interested and qualified candidates are invited to submit non-returnable application with copies of credentials in person to HR and Logistics Management Division located at Lucy Insurance S.C.
Head Office 3rd floor in front of Capital Hotel (Hayahulet, near Waryt Building) within SEVEN working days Please note that only short listed applicants will be contacted.
HR & Logistics Management Division
Tel: 011-470-33-61
Lucy Insurance S.C

https://t.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Mikias Melak)
https://t.me/casemanagers
ጉዳይዎን እናስፈፅምልዎ ከግል ተቋማት ሆነ ከግለሰብ፣ ከመንግስት መስሪያቤት ጋር በተያያዘ ያሰቡትን እንፈፅምልዎ።
@Casemanager_bot
#ጊዜያዊ_መታወቂያ !

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መመሪያ ፥ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መመሪያ አውጥቷል፡፡

* መመሪያው ከላይ ተያይዟል።
#tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ_ቤት_ለሚገዙ_ለሚሸጡ

በአሁን ግዜ ቤት የሚገዙ፣ የሚሸጡ ሁሉ ስራቸው ህገወጥ ስለሆነ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት አሳስቧል።
.
የቋሚ ንብረት ሽያጭ የቆመ ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎቱ ሳይጀመር ሽያጭ እና ማስተላልፈ በመንደር ውል እና በውክል እየተሰራ መሆኑ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ፤ በውክልናም ሆነ በመንደር ውል የቤት ሽያጭ ማከናወን ህጉ እንደማይፈቅድ ገልፀዋል።
.
አገልግሎቱ የሚጀምርበትን ጊዜ እናሳውቃለን ብለዋል።

" ቤት ሽያጭ ውል ሰነድ የማረጋገጥ አገልግሎት ነው " ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ " ይህ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል። ተቋሙ በተለይ ከአ/አ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ህገወጥ ይዞታዎችን የማረጋገጥ ስራ እየሰረ ስለሆነ ከዛ ጋር ተያይዞ ላልተገባ ሰዎች ያልተገባ ውል ውስጥ እንዳይገቡ ያን የማረጋገጥ ስራ እስኪጠናቀቅ በጊዜያዊነት አገልግሎቱን መስጥ ቆሟል " ሲሉ አስረድተዋል።

ይሄ ህገወጥ ይዞታዎችን የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙሉቀን ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ላልተወሰ ጊዜ የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም መኖሪያ ቤት ሽያጭ / በስጦታ የማስተላለፍ ውሉ አሁንም ለጊዜው እንደተቋረጠ ይቀጥላል ሲሉ አሳውቀዋል።

ተቋሙ የተቋረጠውን አገልግሎት በሚጀምርበት ሰዓት በግልፅ በተለያየ ሚዲያ መረጃውን የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።

በተለይ የተጠራቀመ አገልግሎት ካለ ተገልጋዮች በሰልፍ ብዙ ሳንይገላቱ ለመስራት አሰራር ተዘርግቶ ይኬዳል ሲሉ ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ ላልተገባ የመንደር ውል ሆነ ባልተገባ መረጀ ላይ ተመስርቶ ከሚደረጉ ውሎች እንዲቆጠብ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ለሸገር ራድዮ በሰጠው ቃል አሳስቧል።
በይርጋ የማይታገዱ የፍትሀብሄር ጉዳዬች
=======//////========

የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ማንኛውም በህግ በግልፅ የተደነገገ መብትና ግዴታ በህጉ በተወሰነው ወይም በተገደበው ጊዜ ውስጥ ስልጣን ላለው አካል እንዲቀርቡ ግዴታን በማስቀመጥ መብቴ ተጣሰብኝ የሚል ወገን ዳተኛ ሳይሆን በትጋት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል መሆኑ ይታወቃል።

ነገር ግን አንዳንድ ጉዳዬች ከንብረቶቹ ልዩ ባህሪና የመንግስት ፖሊሲ አንፃር ህግ አውጪው በይርጋ እንዳይታገዱ አድርጎ ያስቀመጣቸው የፍትሀብሄር ጉዳዬች አሉ። ከእነዚህ መካከል፦

#የመፋለም ክስ ( petitory action)
~~××××××~~~~~

ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡

ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡

ድንጋጌው የሚንቀሳቀስ ንብረትን የባለሀብትነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት በሌለው በፍ/ብ/ህግ አንቀፅ 1845 ስር የተመለከተው ተመሳሳይ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሆን ተፈልጎ ካለመሆኑ በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀስ ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት ባህሪ ያለው እና ከትውልው ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ የባለሀብትነቱ መብት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች( አንቀፅ 1168....) ይሆን ዘንድ ተፈልጎ የተቀመጠ ድንጋጌ መሆኑን እንገነዘባለን።

በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መዝ/ቁ 43600)

N.B= ይህ ሲባል ግን ከውርስ፣ ከሽያጭ፣ ከስጦታና ከሌሎች ውሎች በመነጨ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ማለት የሚቻል ሳይሆን ለጉዳዩ አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቀመጡ የይርጋ ጊዜዎች የሚስተናገዱ ይሆናል።

#ህገ ወጥ ውል (unlawful contrat)
~~~×××××~~~~~~

እንድ ውል የፀና ውል ለመሆን መሟላት ከሚገባው አንዱ ነጥብ ውሉ ህጋዊ በሆነ ጉዳይ ላይ የተመሰረተ መሆን የሚገባው እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ 1678 ይደነግጋል። አንድ ውል ህገ ወጥ ውል ነው የሚባለው ደግሞ ተዋዋዬቹ የተዋዋሉበት መሰረታዊ ጉዳይ ዓላማ በመሰረታዊና ሞራላዊ ይዘቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በማድረግ መብትና ግዴታ እንዲፈጥሩበት በህግ ያልተፈቀደ ወይም በህግ ክልከላ የተደረገበት ሆኖ ሲገኝ ነው።

አንድ ውል የተመሰረተበት መሰረታዊ ጉዳይ (object of contract) በህግ ክልከላ የተደረረበት በሆነ ጊዜ ውሉ በህግ ፊት እንደሌለና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል (null and void contrat) እንዲሁም ችግሩን በማስተካከል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ የማይቻል ነው። ለምሳሌ፦ የመሬት ሽያጭ ውል፣ በሰው ለመነገድ የተደረግ ውል፣ ወንጀል ለመፈፀም የተደረገ ውል......
ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ ደግሞ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊቀርብ የማይችልና ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በይርጋ የሚታገዱ አይደሉም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 43226)

N.B= ይህ ሲባል ግን የህጉን መስፈርት ያላሟሉ ውሎች (illegal contract) ከህገ ወጥ ውል በተለየ ሁኔታ ታይተው የይርጋ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆንባቸው መሆኑን መረዳት ይገባል።

#የመንግስትን መሬት የማስመለስ ክስ
~××××××~~~~~~

ግለሰቦች በፌደራሉ እና በክልሉ መንግስት በወጡ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር አዋጅ በሚደነግጉት መሰረት በህጋዊ መንገድ ሳይሰጣቸው ከህግ ውጪ የወል ወይም የመንግስትን መሬት ይዘው መቆየታቸው እና የመሬቱ ባለይዞታ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማግኘታቸው የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ ሊያደርጋቸው አይችልም። በወረራ የተያዘ የመንግስት መሬትም ይርጋ የሌለው መሆኑን የአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 በግልፅ ያስቀምጣል።

በመሆኑም ከህግ ውጭ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን መኖራቸውን ሲረዳ መሬት አስተዳደርም ሆነ የመንግስት ወኪል የሆነ አካል መሬቶቹን ለማስመለስ የሚያቀርበው ክስ በይርጋ የሚታገድ አይደለም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 93013 እና 96203 ያልታተሙ)

#በህገ ወጥ መንገድ የተያዘ የግለሰብ ይዞ መሬት
~~××××××~~~~~~

ከላይ እንደተመለከትነው ህገ ወጥ ውልን መሰረት አድርጎ የግለሰብን መሬት በያዘ ሰው ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የሌለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 መሰረት ህጉ በማይፈቅድበት መንገድ በሀይልም ሆነ በህገ ወጥ አግባብ የገጠር መሬትን ይዞ የተገኘ ግለሰብ ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የለውም።

N.B= በህገ ወጥ መንገድ የሚለው ሀሳብ በህግ ተቀባይነት በሌለው አኳኋን የያዘን በሚመለከት እንጂ የህጉን መስፈርት ባላሟላ ውል ወይም ተግባር (illegal contrat) አማካኝነት የተያዘን መሬት የሚመለከት አይደለም። ምክንያቱም መሬቱን የያዘው በህጉ በተፈቀደ የውል ተግባር ሆኖ የሚፈለገውን ፎርማሊቲ ወይም መስፈርት አለማለቱ ብቻ አያያዙ ህገ ወጥ ነው የሚያስብል ስላልሆነ ነው።

#የአደራ ውል
~×××

አደራ ተቀባይ በአደራ የሚጠብቀውን ዕቃ የሚመልስበት የጊዜ ገደብ በውል ተመልክቶ ከሆነ ይህ ጊዜ ሲያበቃ ዕቃውን መመለስ ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2781(1) የተመለከተ ሲሆን በውል ላይ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ከሌለ ግን አደራ ሰጪው እንደጠየቀ ወዲያውኑ እንደሚመለስ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2989(1) ስር ተመላክቷል።

ከእነዚህ ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻለው አደራ ተቀባይ ዕቃውን የሚመልስበት የጊዜ ገደብ ከሌለ በቀር አደራ ሰጪው በአደራ እንዲቀመጥ የሰጠው ዕቃ ያለምንም የጊዜ ገደብ በማንኛውም ጊዜ እንዲመለስለት መጠየቅ የሚችል መሆኑን ነው።

#የውርስ ሀብት ክፍፍል
~~~~××××~~~~

ወራሾች ተለይተው እና የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ነገር ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየን የውርስ ሀብት በማናቸውም ጊዜ መጠየቅ እንደሚችልና በይርጋ የሚታገድ እንዳልሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1060 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።

እንዲሁም ከውርስ ሀብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውርስ ሀብቱን በእጁ አድርጎ በመገልገል ላይ ያለ ተከራካሪ የሆነ ወራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የውርስ ንብረት በጋራ ይዞ ከቆየ ሰው ላይ የውርስ ድርሻዬን ልወቅ ወይም ይለይልኝ ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል የሚባልበት አግባብ የለም።

#የድምፅ ብክለት
~×××~~
የድምፅ ብክለት ክልከላ ባለቤቱ ስራውን የሚፈፅመው በራሱ ንብረት ወይም ቤት ውስጥ ቢሆንም ድርጊቱ ሌላውን ጎረቤት እንዳይረብሽ፣ እንዳያውክ፣ ወይም ችግር እንዳያስከትል በማድረግ መብቱን ይጠቀም ዘንድ ህጉ ያበጀው የባለቤትነት መብት አጠቃቀምን አድማስ የሚወስን ስርዓት መሆኑን ከአንቀፅ 1226 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።

ይህን ችግር ለማስወገድ የሚቀርበው አቤቱታ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 ስር ከተመለከተው በይዞታ ላይ ሁከት መፍጠር ተግባር የሚለይ ሲሆን አንዴ የተፈጠረ የድምፅ ብክለት እንዲቀጥል የሚደረግበት አግባብ ስለሌለ በይርጋ የሚታገድ አይደለም።
ከሄኖክ ታዬ በማንኛውም ፍ/ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ ገፅ ተወሰደ
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ሕገ-ወጥ ደረሰኝ መጠቀም የሚያስከትለው ቅጣት
💥💥💥💥💥💥💥💥
ደረሰኝ በዕቃ ወይም በአገልግሎት ግብይት ላይ ተመሥርቶ ከሻጩ/ አቅራቢው ለገዥው የሚሰጥና ግብይት ስለመፈፀሙ፣ ገንዘብ ስለመሰብሰቡ፣ ዋጋው ስለመከፈሉ ወይም ለወደፊት ለመክፈል ውል መግባቱን የሚያሳይ ሰነድ ነው፡፡
ደረሰኝ የሚሰጠው ጠቀሜታ ሰፋ ያለ ቢሆንም በዋነኛነት በተለያዩ አካላት መካከል የሚፈፀመውን ግብይት ግልጽና በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ለማድረግ የሚሰጠው ጠቀሜታ በጣም የጐላ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴውን ውጤት የሚያሳየው የሂሳብ መዝገብ ተቀባይነት ባላቸው የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች ላይ ተመሥርቶ ቢዘጋጅም እንኳ ለምዝገባው መሠረት የሚሆኑት ደረሰኞች አጥጋቢ ካልሆኑ በሂሳብ ውጤቱ ተጠቃሚ በሆነው አካል ላይ ሊያስከትል የሚችለው ኪሳራ ቀላል አይደለም፡፡
ይህን ኪሳራ ለመቀነስ እና የህግ ተገዢነትን ለማሳደግ የታክስ አስተዳደር ስርዓቱ የራሱ የሆነ ህግ እና ደንብ አለው በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው የተጭበረበሩ ደረሰኞችን ያዘጋጀ፣ ያተመ፣ የሸጠ ወይም ያሰራጨ ወይም የታክስ ዕዳውን ለመቀነስ ወይም ተመላሽ ለመጠየቅ የተጭበረበሩ ደረሰኞችን የተጠቀመ እንደሆነ ብር 100ሺ እና ከ7-10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
ሀሰተኛ ደረሰኞችን፣ ለማዘጋጀት/ለማተም የሚያገለግል ማሽን፣ መሳሪያ፣ ወይም ሶፍትዌር የያዘ፣ የሸጠ፣ ያከራየ ወይም በሌላ መንገድ ያቀረበ ማንኛውም ሰው ብር 200ሺ የገንዘብ ቅጣት እና ከ10-15 ዓመት ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
ሀሰተኛ ደረሰኞችን የያዘ፣ ያስቀመጠ፣ ለሽያጭ ያመቻቸ ወይም ሀሰተኛ ደረሰኞች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደረገ ሰው ከ3-5 ዓመት በሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ እስከ ብር 200ሺ ቅጣት እና ከ7-10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
#ለበለጠ መረጃ የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ይመልከቱ።
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties