አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በ internship እና
#በበጎ #ፈቃድ አገልግሎት ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ።
#ተመዝገቡ
ሁሌ አርብ አርብ በአካል እየተገናኘን የተለያዩ ስልጠና እና አቅጣጫ የሚሰጥበት ቀን ስለሆነ ከዚህ በታች በሚገኘው አድራሻ በአካል በመቅረብ መሳተፍ ትችላላችሁ።
ሳር ቤት ADAMS Pavilion ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር S14
በአካል ተገኙ እንላለን።
Transparency International Ethiopia

ስልክ +251118279746

@Transparency_Ethiopia_Bot

ethiopiatransparency@gmail.com

@TransparencyEthiopia

https://t.me/TransparencyEthiopia
Junior Associate

The Firm:

Aman Assefa and Associates Law Office is a full service law office engaged in providing legal advisory and representation in Ethiopia. It’s reputed as a pioneer in the corporate and transactional law practice in Ethiopia. At Aman Assefa & Associates, we provide commercial, investment, transaction advisory, labor relations, taxation, projects and project finance, energy, intellectual property, banking, construction, environment and related legal services for almost 20 years in Ethiopia. Our clients consist of both foreign and domestic investors and range from start-ups to prominent multi-nationals.

Aman Assefa & Associates is an alliance firm of Bowmans, an international legal practice based in South Africa.

Practice Area: Dispute Resolution | Due Diligence, Compliance & Investigation | Competition | Corporate Service | Company Law Advisory | Employment | Merger & Acquisitions | Intellectual Property |Private Equity and Financing | Privatization | Infrastructure and projects | Transportation and Logistics | Project Finance, PPP and Public Procurement | Regulatory and Government Affairs | Tax | Trade Practice & Anti-Trust

Industry: Manufacturing | Construction and Real Estate | Mining and Energy | Transportation and Logistics | Consumer Goods & Retail | Telecommunications | Healthcare | Hospitability | Media and Entertainment | Fintech | Banking and Insurance/Financial Services | Agriculture

 Position Summary:

A first-year associate is an entry level attorney. Entry-level and first-year associates perform a variety of tasks under heavy supervision and should be familiar with Ethiopia legal concepts and procedures. The role requires a general understanding of the law and transactional commercial advisory services rendered by the Office. The Junior Associate is required to work in the different practice and industry areas along with the other lawyers in the Office.

Specific Responsibilities and Deliverables:

Conduct extensive legal research on various legal practice areas and industries under the supervision of Senior Associates,

Represent Clients before various government and other entity engagement to undertake client tasks such as company establishment, renewal of licenses and registration, document authentications and other execution of tasks at such entities,

Assist in the preparation of client engagement documents such as proposal, response for proposals (RFPs), and engagement letters.

Maintain client files in an organized fashion to ensure up-to-date information is handy for other attorneys and support staff;

Engage in any project or work of any practice area and/or industry as assigned by the Office;

Working as part of a team and taking an active part in sharing knowledge and experience with the team, and

Attending internal and external meetings.

Job Requirements:

Experience and Qualification  

A qualified lawyer with excellent academics credentials with LLB.

0 - 3 years of relevant experience.

General understanding of legal trends, developments and changes and ability to adapt those changes. 

Excellent research, drafting, communication and writing skills.

Attention to detail, accuracy and strong time management skills.

Strong relationship management skills. 

How To Apply:

Applications are only accepted via email. Please send your applications on  career@aaclo.com

Application is open for 10 (ten days) consecutive days from the day it has been announced.

Email subject should have the ‘Job Title’ followed by ‘Full Name’

Applications received after the closing date will not be accepted.

Posted: 10.22.2021

Deadline: 11.01.2021

Job Category: Legal

Employment: Full time

Location: Addis Ababa
Aman Assefa & Associates Law Office
New_Ethiopian_Commercial_Code_Proclamation_No_1243_2021_English.pdf
2.7 MB
አዲሱ የንግድ ሕግ እንግሊዝኛ ቅጂ ከዚህ ያግኙ፤
New Ethiopian Commercial Code Proclamation No. 1243-2021 - English Version
ፓስፖርቶችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘጋጁ ነበር የተባሉ 10 የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ታሰሩ
October 26, 2021
ሰራተኞቹ መንግስትን ከ1 ሚሊዮን በላይ ብር አክስረዋል ተብሏል
ፖሊስ ፓስፖርቶችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘጋጁ ነበር ያላቸውን 10 የኢሚግሬሽን ሰራተኞች አሰረ፡፡
የኢሚግሬሽን፣ የዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ሰራተኞች ናቸው የተባለላቸው አስሩ ሰራተኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
የ5 አመት ህጻን አስገድዳ የደፈረችው ወጣት በእስር ተቀጣች
ተጠርጣሪዎቹ ህጋዊውን የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደት ወደ ጎን በመተው፣ የፓስፖርት ባለቤቶችን ሙሉ መረጃ በመቀየር እና በአንድ ማእከል መጠናቀቅ የነበረበትን አገልግሎት ወደ ተለያዩ ቅርንጫፎች በማዘዋወር ወንጀሉን በኔትወርክ መፈፀማቸውን በፌዴራል ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው ለኢቲቪ ገልፀዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ከደላሎች ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስር በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦች እና የውጭ ሀገር ዜጎችም ጭምር ፓስፖርት እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ መንግስት ሊያገኝ ይችል የነበረውን ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳሳጡም ነው ኮማንደር ታደሰ የተናገሩት።
የ5 አመት ህጻን አስገድዳ የደፈረችው ወጣት በእስር ተቀጣች
ተከሳሿ በፈጸመችው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የ33 ወራት እስር ተፈርዶባታል
እንደ ፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ተከሳሽ ጌጤ ባልቶሌ ትባላለች፤ የ20 ዓመት ወጣት ናት፡፡ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 627/4/ለ ስር የተመለከተዉን ተላልፋ በፈጸመችዉ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ተመስርቶባት ጉዳዩ በክርክር ላይ ቆይቷል፡፡
ተከሳሽ ከእርሷ ጋር ተቃራኒ ጾታ ካለዉ የ5 ዓመት ህጻን ልጅ ጋር ሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 10፡00 ሰዓት ሲሆን እንዲሁም ከተጠቀሰዉ ቀን በፊትም በተለያዩ ቀናት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታዉ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም በሚገኘዉ መኖሪያ ቤት ዉስጥ በሞግዚትነት የምታሳድገዉን የ5 ዓመት ህጻን አይኑን በማሰር እና ስሜቱን በማነሳሳት የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል መፈጸሟን በማስረጃ በማረጋገጥ ክስ የተመሰረተ ስለመሆኑ የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

ተከሳሽም ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት ቀርባ የእምነት ክህደት ቃሏን ስትጠየቅ ድርጊቱን ስለመፈጸሟ እንዲሁም ጥፋተኛ ስለመሆኗ በዝርዝር ያመነች በመሆኑ በተከሰሰችበት የወንጀል ድንጋጌ ስር የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባታል፡፡
በዚህም መሰረት ጥቅምት 02 ቀን 2014 ዓ.ም የዋለው ችሎት ተከሳሽ በ2 ዓመት ከ9 ወራት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል ተብሏል፡፡
Forwarded from ሕግ ቤት
ሰላም እንዴት ናችሁ
~~~~~
በመርህ ደረጃ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ማንኛውንም አካል መበርበርና መያዝ(መፈተሽ) ክልክል ነው።በልዩነት ግን እጅ ከፍንጅ ወንጀሉን ሰፈፅም፣ወንጀሉ በክስ ወይም በአቤቱታ መልክ ቀርቦ ከ3ት አመት በላይ ሊያስቀጣ እንደሚችል የታወቀ ከሆነ ግን ያለ ትእዛዝ እንደሚቻል ይገልፃል።
.
.
#ጥያቄ*1:--በመንገድ ላይ፣መንግታዊ በሆኑ ወይም ባልሆኑ ተቋማት በመግባት ጊዜ ያለ ፍ/ቤት ትእዛዝ ፍተሻ/ብርበራ ይካሄዳል።ግልፅ ከተቀመጠው የህግ አግባብ እንዴት ይታያል???
.
ጥያቄ 2:--ግለሰቡ በዚህ ጊዜ አልፈተሽም የማለት መብት አለው ወይ??? አልፈተሽም ብሎስ የመመለስ መብት ይኖረዋል ወይ??? እንድህ ከሆነስ የመንቀሳቀስ መብቱ መገደብ ጋር እንዴት ያዩታል????
.
.
.................መልካም ጊዜ ..............
#ሰበር_ዜና

የአፍሪካ ህብረት ሱዳንን ከአባልነት አገደ

የአፍሪካ ህብረት ሱዳን ሪፐብሊክ በየትኞቹም የድርጊት መርሃ ግብሮቹ እንዳትሳተፍ አገደ፡፡
ህብረቱ እገዳው የሽግግር ሂደቱን ይመራ የነበረው የሲቪል አስተዳደር ወደ ቦታው እስከሚመለስ የሚቀጥል ነው ብሏል፡፡
በጠ/ሚ ሃምዶክ የሚመራው የሱዳን የሲቪል መንግስት በሃገሪቱ ጦር ከስልጣን መወገዱ ይታወሳል፡፡

ከአፍሪካ ህብረት አባልነት የታገደችው ሱዳን በግድቡ የድርድር ሂደት አትሳተፍም ተባለ
ህብረቱ፤ ሱዳን የሽግግር ሂደቱን ይመራ የነበረው የሲቪል አስተዳደር ወደ ቦታው እስከሚመለስ ድረስ ከአባልነት ታግዳ እንደምትቆይ ማስታወቁ ይታወሳል።
አል ዐይን
የስያሜ ለውጥ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በመባል በ2008 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 943 በተለያዩ ተቋማት ስር ሲመሩ የነበሩ ዐቃቤ ህግ ስራዎችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ በአዲስ መልክ ተቋቁሞ የነበረው ተቋማችን በቅርቡ በጸደቀው በአዲሱ የፌዴራል አስፈጻሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረት የስያሜ ለውጥ በማድረግ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትህ ሚነስቴር ሆኗል፡፡

ተቋሙ ከተሰጠው ሃላፊነት እና ስልጣን አንጻር የሚመጥን ስም እንዲያገኝ ከመደረጉ ውጭ በአብዛኛው አሁን ስራ ባለው የተቋሙ ማቋቋሚያ አዋጅ እና በሌሎች አዋጆች ተሰጥተውት የነበሩት ስልጣን እና ተግባራት እንዳሉ የሚቀጥሉ ሲሆን የተወሰኑት የተጨመሩ ኃላፊነቶቹን የህጉን ታትሞ መውጣት ተከትለን ማብራሪያዎችን ይዘን የምንቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የተቋሙ አርማም መሰረታዊ ለውጥ ሳይደረግበት የቀጠለ ሲሆን በአርማው ላይ የነበረው የተቋሙ ስያሜ ብቻ ተለውጦ አገልግሎት ላይ መዋሉ እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡
ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ አሁንም የሱዳን ሕጋዊ መሪ መሆናቸውን የአውሮፓ ህብረት ገለፀ
October 27, 2021
የአውሮፓ ህብረት ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበደላ ሀምዶክ ጋር መገናኘት አፈልጋለሁ ብሏል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላ ሀምዶክ አሁንም የሱዳን ሕጋዊ መሪ መሆናቸውን የአውሮፓ ህብረት ገለጸ።
ባሳለፍነው ሰኞ በተደረገ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተነሱት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እና የካቢኔ አባሎች የሽግግር መንግስቱ ሕጋዊ መሪዎች መሆናቸውን ዕውቅና እንደሚሰጥ የአውሮፓ ሕብረት አስታውቋል።
በካርቱም የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ልዑክ በሱዳን የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ከሚያወግዙ ወገኖች ጋር ተመሳሳይ አቋም እንዳለው ገልጿል።
ህብረቱ ከፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዌይ፣ ስፔን፣ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድ፣ ብሪታኒያ እና አሜሪካ ኤምባሲዎች ጋር በመተባበር መግለጫ ሰጥቷል።
የሱዳን ሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትና በወታደሩ ከስልጣን የተነሱት ሃምዶክ ወደ መኖሪያ ቤታቸው መመለሳቸውን ብናውቅም፤ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም መዘግየት ከእስር እንዲፈቱ እንጠይቃለን ሲል ሕብረቱ አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ካቢኔያቸውን የሽግግር መንግሥቱ ሕገ መንግሥታዊ መሪዎች ስለመሆናቸው አሁንም ዕውቅና መስጠታችንን እንቀጥላለን ሲልም ነው የገለጸው።
መቀመጫቸውን በካርቱም ያደረጉ አምባሳደሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ ቢገናኙ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ያነሳው መግለጫው፤ ከአብደላ ሃምዶክ ጋር በአስቸኳይ እንዲንገናኝ እንጠይቃለን ብሏል።
.................................በተጨማሪም ህብረቱ ሁሉም የሱዳን ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መሰረታዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ እንዲሁም የጸጥታ እና ሌሎች የታጠቁ ሃይሎች ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች ላይ ጥቃቶችን እንዳያደርሱ ጠይቋል።
በመላ ሀገሪቱ የሰብአዊ አቅርቦትን ያለገደብ እንዲሰራጭ የጠየቀው የህብረቱ መግለጫ፤ በተለይም በእነዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዓለም አቀፉ የሰብአዊ ማህበረሰብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሱዳናውያን የሚያደርገውን የማድረስ ስራ ቀጣይነት እንዲሆን በሱዳን ውስጥ ያለ የማንኛውም ባለስልጣን ዋና ተግባር መሆን እንዳለበትም ሕብረቱ አሳስቧል።
በህገ መንግስታዊ ሰነዱ እና በጁባ የሰላም ስምምነት ላይ እንደተገለፀው የሱዳን የዴሞክራሲ ሽግግር ፍኖተ ካርታ በአስቸኳይ እንዲመለስም ሕብረቱ ጠይቋል።
በሱዳን ሽግግር ውስጥ በሁሉም ባለድርሻ አካላት መካከል ሁሉን አቀፍ፣ሰላማዊ እና ህገ-መንግስታዊ ውይይት መደረግ አለበትም ተብሏል።
አል ዓይን
ALE (Alternative Legal Education) All in one, for all.🔴አለ (አማራጭ የሕግ ትምህርት)ሁሉም በአንድ፣ ለሁሉም።🔴 @lawsocieties
Contact us: @LawsocietiesBot
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/lawsocieties/
መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው። ግዴታዎችንና መብቶችን ይወቁ።
ያለመከሰስ ከለላ እና የከለላው ተጠቃሚ ግዴታዎች
--------------------

ያለመከሰስ ከለላ ምንድ ነው?

ለወንጀልም ይሁን ለፍትሀ ብሄር ሀላፊት የተፈጥሮ ሰው ይሁን የህግ ሰውነት ያለው አካል መከሰስ መርህ ሆኖ ሳለ ያለመከሰስ ከለላ ደግሞ በልዩ ሁኔታ በህግ ለተወሰኑ አካላት የሚሰጥ መብት ነው፡፡ ያለመከሰስ ከለላ (immunity ) የአለም አቀፍ ህግ መርህ( a principle of international law) ሲሆን የውጪ ሀገር መንግስታት እና የአለም አቀፍ ድርጅቶች የተወሰኑ ሀላፊዎች (certain international organization officials) ለፈፀሙት የህግ መተላለፍ ከህግ ተጠያቂነት ነፃ የሚሆኑበት ስርዓት ነው፡፡ይሀም የአለም አቀፍ ህግን እና ከተቀባይ ሀገር ጋር የሚደረግ ስምምነትን ( host state treaty ) መሰረት ያደረገ ነው፡፡

በኢፌዴሪ የወንጀል ህግ በህግ ፊት እኩል ስለመሆን በሚደነግገው እንቀፅ 4 ስር እንዳተቀመጠው የወንጀል ህግ የሰውን፣ የማህበራዊ ኑሮ ደረጃ፣ የዘርን፣ የብሄርን፣ የብሄረሰብን፣ የቀለምን፣ የፆታን፣ የቋንቋን፣ የሃይማኖትን፣ የፖለቲካን ወይም የሌላ አስተሳሰብን፣ የሀብትን፣ የትውልድን ወይም የሌላ አቋምን ልዩነት ሳያደርግ በሁሉም ላይ በእኩልነት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ይሁንና በወንጀል አድራጊዎች መሐከል ልዩነት የሚደረገው ምንጩ የዓለም ዓቀፍ ህግ ወይም ህገ-መንግስት ሆኖ በወንጀል ህጉ የተደነገገ መሰረታዊ መብት ሲኖር የእንግሊዘኛው ቅጂ እንደሚያስቀምጠው(No difference in treatment of criminals may be made except as provided by this Code, which are derived from immunities sanctioned by public international and constitutional law)ሲኖር ነው፡፡

እንዲሁም በመደበኛ ሁኔታ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ለሚደረጉ ወንጀሎች አንድ ኢትዮጵያዊ ወይም የውጪ አገር ዜጋ በወንጀል ህጉ ከተመለከቱት ወንጀሎች ማናቸውንም ቢያደርግ ህጉ ተፈፃሚ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በዓለም አቀፍ ህግ የማይደፈር ህግ መብቶች ስላሏቸው ሰዎች የተደነገጉት የተጠበቁ ናቸው በማለት የወንጀል ህጉ አንቀፅ 11 ያስቀምጣል፡፡በተጨማሪ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ አንቀፅ 39/4 መሰረት ልዩ የአለም አቀፍ ህግ ከለላ ወይም ዲፕሎማቲክ ከለላ የወንጀል ምርመራ ከሚቋረጥባቸው ምክንያቶች አንዱ ነው፡

ያለመከሰስ ከለላ ለምን ይሰጣል?
ያለመከሰስ ከለላ የሚሰጥበት ምክንያት እንደ ከለላው አይነት ወይም ከለላው እንደሚሰጠው አካል ማንነት ማለትም ለሀገር፣ለመንግስታት ተወካዮች/ዲፕሎማቶች፣ልዩ መልክተኞች/ ወይም ለአለም ዓቀፍ ድርጅቶች እና ሀላፊዎቻቸው ቢለያይም በዋናነት ከለላው የተሰጠው አካል ከህግ ተጠያቂነት ስጋት ነፃ ሆኖ ስራውን በአግባቡ እንዲፈፅም/functionality/ለማስቻል ነው፡፡በተለይ ለድርጅቶች የሚሰጠው ከለላ ሉዓላዊነትን እና እንካ ለእንካን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ በዋናነት የድርጅቶችን ገለልተኝነት/independence/ እና የአባል ሀገራቱን እኩልነት /equality of member states/ ለመጠበቅና እና ከሚሰሩበት ሀገር ጫና ውጪ ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ማለትም የተቋቋሙበትን አላማ እንዲያሳኩ ለማስቻል ነው፡፡

ያለመከሰስ ከለላ አይነቶች
በአለም አቀፍ ህግ ያለመከሰስ ከለላን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ይህም የሀገር ወይም ሉዓላዊነት ከለላ(State or sovereign immunity)እና የዲፕሎማት ከለላ( diplomatic immunity) ናቸው፡፡

የሀገር ወይም ሉዓላዊነት ከለላ:- ለሀገራት የሚሰጥ ከለላ ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ይሀውም በአለም አቀፍ ግንኙነት ሁሉም ሀገሮች እኩል ስለሆኑ ማንም ሀገር የትኛውንም የውጪ ሀገር በሀገሩ ውስጥ መክሰስ እና መቅጣት የማይችል መሆን እና ሀገሮች ሉዓላዊ በመሆናቸው የማይደፈሩ በመሆናቸው ነው፡፡ለሀገራት የሚሰጥ ከለላ አንደ አውሮፕውያን አቆጣጠር 2004 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት በወጣው (UN Convention on Jurisdictional Immunities of States and Their Property) እውቅና ያገኘ ሲሆን በስምምነቱ አንቀፅ 5 መሰረት ሀገራት እራሳቸው እና ንብረታቸው ከሌሎች ሀገሮች ፍርድ ቤቶች ስልጣን ጥበቃ ወይም ከለላ እንዳላቸው ያስቀምጣል (A State enjoys immunity, in respect of itself and its property, from the jurisdiction of the courts of another)::

የሀገር ወይም ሉዓላዊነት ከለላ ሁለት ጉዳዮችን መሰረት ያደረገ ሲሆን እነሱም የሀገር ሀላፊዎችን ስራ (Immunity of State Officials Ratione Materiae(Immunity Attaching to Official Acts)) እና የሀገር ሀላፊዎች እራሳቸውን (Immunity of State Officials Ratione Personae (Immunity Attaching to an Office or Status) ናቸው፡፡የመጀመሪያው ከለላ ባለስልጣናት ወይም የሀገር ተወካዮች በሀገራቸው እንዲሰሩ በተሰጣቸው ስራ ምክንያት ተጠያቂ የማይሆኑበት ሲሆን ይህ ከለላ ስራን ወይም ተግባርን (functional ) ብቻ መሰረት ያደረገ ነው፡፡የሁለተኛው የከለላ አይነት ደግሞ ሀገራቸውን በመወከላቸው ምክንያት የሰዎቹ ማንነት (personality) ላይ የተመሰረተ ነው፡፡በዚህ የከለላ አይነት እርዕሰ ብሄሮች( Heads of State)፣እርዕሰ መንግስታት(Heads of Government) ፣የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች( ,Foreign Ministers)፣ዲፕሎማት እና የቆንፅላ ሀላፊዎች(Consular officers) ሀገራቸውን ወክለው በሄዱባቸው ሀገሮች ሙሉ ያለመከሰስ ከለላ / absolute immunity / አላቸው፡፡በተጨማሪም በ1969 ዓ.ም በወጣው የተባበሩት መንግስታት ልዩ መልዕክተኛ ኮንቬንሽን (UN Convention on Special Missions 1969) ላይ እንደ ተደነገገው በልዩ መልዕክተኝነት ሀገራቸውን ወክለው በሌላ ሀገር የተገኙ ሰዎች ያለመከሰስ ከለላ አላቸው፡፡
የዲፕሎማት ከለላ( diplomatic immunity):-በሀገር ተወክለው በሌሎች ሀገራት የሚኖሩ የመንግስት ሀላፊዎች ከስራችው ጋር በተያያዘ እንዲሁም ከስራቸው ውጪ ለሚፈፅሙት የህግ መተላለፍ ባሉበት ሀገር ፍርድ ቤቶች ወይም ሌሎች ባለስልጣናት ፊት ተጠያቂ የማይሆኑበት የአለም አቀፍ ህግ መርህ ነው፡፡ በሀገራት መካከል የሚደረግ የዲፖሎማቲክ ግንኙነት የሀገራቱ የጋራ ስምምነት ላይ የተንተራሰ ሲሆን የእንካ ለንካ መርህን(principle of reciprocity) ከግምት ያስገባ ነው፡፡ይህም አንዲት ሀገር በግዛቷ ውስጥ ለሚገኙ የውጪ ሀገር ተወካዮች ከለላ ስትሰጥ በተመሳሳይ መልኩ እሷ የወከለቻቸው ተወካዮች ባሉበት ሀገር ከለላ ያገኛሉ ማለት ነው፡፡የዲፕሎማት ከለላ በቬና የዲፒሎማቲክ ግንኙነት ኮንቬንሽን ( 1961 Vienna convection on diplomatic relation)ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በኮንቬንሽኑ አንቀፅ 3/1 ስር እንደ ተደነገገው የላኪ ሀገር(sending state) ዲፕሎማት ተወካይ ፣በተቀባይ ሀገር(host state) በወንጀል ያለመከሰስ ሙሉ ከለላ አለው፡፡ከዲፕሎማት ምድብ ውስጥ አምባሳደሮች እና ተወካዮች( envoys) ተጠቃሽ ናቸው::