አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የመሰየም ምንነትና ሕጋዊ ውጤቱ
====================
ቀድሞ ወንጀለኛ የነበረ ሰው ወደ ንፁህነት የሚመለስበት ወይም ስሙ እንደገና የሚታደስበት ሁኔታ መሰየም ተብሎ ይጠራል፡፡ አንድ ወንጀለኛ ቅጣቱን ከፈፀመና ወደ ሕበረተሰቡ ተመልሶ በሕጉ የተመለከተውን የፈተና ጊዜ በብቃት ካለፈ የወንጀል ሪኮርዱ ሊፋቅለት ይገባል እንጅ ወንጀሉ በሄደበት ቦታ ሁሉ እንደ ጥላ ሊከተለው አይገባም፡፡ ሕብረተሰቡ ውስጥ ገብቶ መልካም ኗሪነቱን በተግባር ያረጋገጠው የቀድሞ ወንጀለኛ እንደ ማንኛወም የሕብረተሰብ አባል መታየት የሚጀምርበት ሁኔታ መፈጠር አለበት፡፡ የፈፀመው ወንጀል አሉታዊ ውጤት እስከ ሕይወት ፍጻሜው እንዲከተለው መደረጉ ለሕብረተሰቡም ምንም ዓይነት ገንቢ አገልግሎት የለውም፡፡

ለመሰየም በጥፋተኛው ላይ የተጣለው ቅጣት በተለያዩ ምክንያቶች ቀሪ ከሆኑ በኋላ የተወሰነ ጊዜ ማለፍ አለበት፡፡ ቅጣቱ ቀሪ ከሆነ በኋላ ምን ያህል ጊዜ ቆይቶ ነው የቀድሞው ወንጀለኛ ለመሰየም ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው የሚለውን በተመለከተ ተወስኖበት በነበረው የቅጣት ዓይነት ይወሰናል፡፡ በወንጀለኛው ላይ ተወስኖበት የነበረው ቅጣት ፅኑ እስራት፣ ከአገር እንዲወጣ ወይም ንብረቱ እንዲወረስ ከሆነ ቅጣቱ ቀሪ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ አምስት ዓመት (የቀድሞው ሕግ አስር ዓመት ይል ነበር) ማለፍ ያለበት ሲሆን አጥፊው ተወስኖበት የነበረው ቅጣት ከነዚህ ዝርዝሮች ውጭ ከሆነ ግን ሁለት ዓመት (የቀድሞው ሕግ አምስት ዓመት ይል ነበር) ማለፍ አለበት፡፡ ይህ አጠቃላይ የጊዜ ወሰን በመርህ ደረጃ የተደነገገ ቢሆንም የመሰየም ጥያቄ የሚያቀርበው ተቀጪ በሕዝባዊ፣ በወታደራዊ ወይም በማህበራዊ አገልግሎት መስክ ተሰማርቶ በግልፅ የሚታይ የሚያስመሰግን ሥራ ለሕብረተሰቡ አበርክቶ ከተገኘ በሕግ የተወሰነው አነስተኛ የጊዜ ገደብ ከመድረሱ በፊት መሰየሙ ሊፈቀድለት ይችላል(አንቀጽ 234(2))፡፡ እንዲሁም ለመሠየም የሚያበቃው አነስተኛ ጊዜ ተፈፃሚነት የሚኖረው ስለደጋጋሚነት የተደነገገውን የጊዜ ገደብ እስካልነካ ድረስ ነው፡፡ ይህም ማለት አንድ ሰው ቅጣቱ ቀሪ ከሆነለት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት ካለፈ በፍርድ ቤት ውሳኔ ሊሰየም የሚችል ቢሆንም ስለ ደጋጋሚነት በተቀመጠው መስፈረት መሰረት ደግሞ ቅጣቱ ቀሪ ከሆነለት ጊዜ ጀምሮ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ወንጀል ከፈፀመ በደጋጋሚ ወንጀለኛት ሊፈረጅ የሚችል በመሆኑ መሰየሙ እንደ ደጋጋሚ ወንጀለኛ ከመቆጠር አያድነውም ማለት ነው፡፡ ይህ ልዩ ሁኔታ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ላይ ያልነበረ በወንጀል ሕጉ ውስጥ እንዲካተት የተደረገ አዲስ መመዘኛ ነው፡፡

ቅጣቱ ቀሪ ከሆነ በኋላ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው አነስተኛ የጊዜ ገደብ ማለፉ ብቻ ወድያውኑ መሰየምን አያስከትልም፡፡ እንዲሁም በወንጀል ሕጉ ላይ በግልፅ እንደሰፈረው “መሰየም የሚገኘው በመልካም ሥራ ነው እንጂ በይገባኛል አይደለም” (አንቀጽ 232(1))፡፡ ለመሰየም ቅጣቱ ቀሪ ከሆነ በኋላ በሕግ የተወሰነው ጊዜ ማለፍ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሌሎች ለመሰየም የሚያበቁ ቅድመ ሁኔታዎችም ተሟልተው መገኘት አለባቸው፡፡ እነርሱም፡-

1. ለመሰየም ብቁ እንዲሆን በሕግ በተወሰነው ከላይ በተጠቀሰው አነስተኛ የጊዜ ገደብ ወስጥ በመልካም ጠባይ ተመርቶ እንደሆነና በእስራት ቅጣት የሚያስቀጣ ወንጀል ፈጽሞ ጥፋተኛ ሳይሆን ቆይቶ ከሆነ፤ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ይህ ቅድመ ሁኔታ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በማናቸውም ጥፋት ሳይከሰስ እንዲሁም አቤቱታ ሳይቀርብበት ቆይቶ እንደሆነ በሚል ነበር ተመልክቶ የነበረው (ቁጥር 243(ለ))፡፡

2. ከዋናው ቅጣት ጋር ተጨማሪ ቅጣት በአጥፊው ላይ ተወስኖ የነበረ ከሆነ ይኸው ቅጣት ተፈጽሞ እንደሆነ፤ በዚህም መሰረት አጥፊው ለምሳሌ የወንጀሉን ተጎጂ ይቅርታ እንዲጠይቅ ተጨማሪ ቅጣት ተወስኖበት የነበረ ከሆነ ይህንኑ መፈፀሙ ካልተረጋገጠ በቀር ለፍርድ ቤት ያቀረበው የመሰየም ጥያቄ ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም፡፡
3. የተለቀቀው ተቀጪ አቅሙ በፈቀደ መጠንና ራሱም ሊፈፅመው ይገባዋል ብሎ በሚገመትበት ሁኔታ በፍርድ የተወሰነበትን ካሳ፣ የዳኝነትና ማናቸውንም ሌላ ኪሣራ በሚገባ አጠናቅቆ ከፍሎ እንደሆነ፣
የሚሉት ናቸው፡፡

በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ቁጥር 247 መሠረት አንድ ጥፋተኛ በተሰየመ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ማናቸውም ዓይነት ነፃነትን የሚያሳጣ ወይም የሞት ቅጣት የሚያስቀጣ አዲስ ወንጀል የፈፀመ እንደሆነ የመሰየም ውሳኔው ይሻራል፡፡ በዚህም መሰረት ተቀጪው የፈፀመው አዲስ ወንጀል ቀላል እስራትም ሆነ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣው ቢሆን የመሰየም ውሳኔውን የማሻር ውጤት ይኖረዋል፡፡ በአዲሱ የወንጀል ሕግ ላይ ግን በዚህ መመዘኛ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ ይኸውም ተቀጪው የፈፀመው አዲስ ወንጀል በፅኑ እስራት ወይም በሞት ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በቀር የመሰየም ውሳኔውን የማሻር ውጤት አይኖረውም፡፡ ስለሆነም በአዲሱ ሕግ መሰረት ተቀጪው እንዲሰየም ከረፈቀደለት በኋላ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አዲስ ወንጀል ፈፅሞ በሞት ወይም በፅኑ እስራት ከተቀጣ (ፅኑ እስራት ከተወሰነበት) የተፈቀደለት መሰየም ይሰረዛል፣እንዲሁም ዳግመኛ እንዲሰየም ሊፈቀድለት አይችልም (አንቀጽ 237)፡፡

በቀድሞው ሕግ ላይ ጥፋተኛው በገደብ የተለቀቀ በሚሆንበት ጊዜ ስለሚሰየምበት ሁኔታ አልተመለከተም ነበር፡፡ ከዚህ በፊት ለመግለፅ እንደተሞከረው አንድ ወንጀል አድራጊ በፍርድ ቤት ተከስሶ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ በኋላ የሚጣልበት ቅጣት የተወሰነ ፈተና ጊዜ ተሰጥቶት ሳይፈፀምበት ሊቀር የሚችልበት ያለ ሲሆን በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ አጥፊው በገደብ በሚለቀቅበት ጊዜ ለመሠየም የሚያበቃው አነስተኛ ጊዜ የሚሰላው ቅጣቱ ከታገደበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ በአዲሱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 233(ሀ) ላይ በግልፅ ሰፍሯል፡፡

የመሰየም ውሳኔ ቀደም ሲል በተቀጪው ላይ ተወስኖ የነበረውን ፍርድ ሙሉ በሙሉ የሚሰርዘው በመሆኑ የመሰየም ውሳኔውን የሚያሽር ወንጀል ካልተፈፀመ በስተቀር ተቀጥቶ የነበረው ሰው ከቅጣቱ የተነሳ እንዳይጠቀምባቸው ተከልክሎ የነበሩትን መብቶች ሁሉ እንደገና ይዞ የመስራት ችሎታ ይኖረዋል፡፡ ፍርዱ የሚሰረዝለት በመሆኑ ከወንጀለኞች መዝገብ ላይ ተፍቆለት ወደፊት እንዳልተፈረበት ይቆጠራል፡፡

የሕጉ ዓላማ የወንጀለኛው ወደ መልካም ሰውነት መመለስ ይቃና ዘንድ ለዚህ ብቁ የሆነን የቀድሞ ወንጀለኛ ምንም ዓይነት የወንጀለኛንነት ምልክት እንዳይኖር ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ጥፋተኛነቱና ቅጣቱ እንዳልነበሩ ሆነው ሊቆጠሩ ይገባል፡፡ በተግባር ቀደም ሲል መፈፀሙ በፍርድ ቤት ጭምር በማስረጃ ተረጋግጦ የነበረውን እውነታ (የወንጀል ድርጊት) ሕጉ ለግለሰቡና ለሕብረተሰቡ ጥቅም ሲል እንዳልነበረ (እንዳልተፈጠረ) የሚቆጥረው በመሆኑ ከመሰየሙ በፊት የነበረውን ጥፋት እያነሳ የተሰየመውን ሰው መውቀስ በስም ማጥፋት ወንጀል የሚያስጠይቅ አድርጎታል፡፡ ስለ ጥፋቱ የተነሳው ለመልካም ዓላማ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ ከተጠያቂነት መዳንም አይቻልም፡፡ በዚህ መሰረትም የመሰየም ውሳኔው ተሰያሚውን ከቀድሞ የወንጀለኛነት ሪከርዱ ፍፁም ንፁህ ያደርገዋል ማለት ነው፡፡
Via Legal consulting limited
#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
the person charged with crime.” በማለት ይገልፃሉ፡፡ በመሆኑም የወንጀል ምርመራ የወንጀል የምርመራ መዝገቡን እስከ ማጠናቀቅ ድረስ ያለውን ሂደት ብቻ የሚመለከት አድርገው የሚያስቡና ተከሣሹንና በምርመራ ሂደት የተሰበሰቡትን ማስረጃዎች ለፍርድ ቤት በማቅረቡ ሂደት ምንም አይነት እገዛ ማድረግ እንደሌለባቸው የሚያስቡ መርማሪ ፖሊሶች “ የወንጀል ምርመራን እንደ መሠረታዊ ግብ ማሣኪያ ሂደት ሣይሆን ምርመራ ማጣራቱ በራሱ ግብ አድርገው የሚመለከቱ በመሆናቸው የአመለካከት ለውጥ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. #የወንጀል ምርመራ ልዩ ባህሪ ያላቸውና የወንጃል ሰለባ የሆኑ ሰዎች በመያዣነት የታገቱባቸው ወንጀሎች ተፈፅመው በሆነ ጊዜ ከላይ ከተገለፁት ተግባራት በተጨማሪ የወንጀል ሰለባ የሆኑትን ሰዎች ከተጋረጠባቸው አደጋ ለመታደግና አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያገኙ የሚከናወነውን ተግባር ያጠቃልላል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ሰውን አስገድዶ መሰወር፣ ጠልፉ፣ ንፁሐን ዜጎችን ማገትና መደራደሪያ ማድረግ የመሳሰሉት በሆነ ጊዜ ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪ የወንጀሉን ሰለባ ለማስለቀቅ የሚከናወኑ ተግባራትን ያጠቃልላል፡፡
ከፀጋዬ ደመቀ ገፅ
#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties