📌 #የከተማ መሬትና ቤት ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር እንዴት ይፈፀማል ❓
በስመ ንብረት ዝውውር ወቅት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 33 ንዑስ አንቀፅ 2 አንፃር ሲታይ
🛑 1.1. የከተማ ቤትና ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር ስለመፈጸም የሚከተሉት ማስረጃዎች/ሰነዶች ሲሟሉ የስመ ንብረት ዝውውር የሚፈጸም ይሆናል፤ 👇
1) ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት/ካርታ፣
2) ጸድቆ የተሰጠ የግንባታ ፕላን፣ የስራ ዝርዝር ግምት ወይም የጸደቀ የነባር ግንባታ ፕላን፣
3) ጸድቆ በተሰጠው የግንባታ ፕላን መሰረት ስለመገንባቱ እና ግንባታው ያለበት ደረጃ የተረጋገጠበት ማስረጃ/50% እና በላይ/፤
4) ውዝፍ የሊዝ/ኪራይ ዕዳ የሌለበት ስለመሆኑ የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ወይም ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳውን ገዥው ለመክፈል በፊርማ ያረጋገጠበት የስምምነት ደብዳቤ ፣
5) በንብረቱ ላይ የባንክ እዳ/የፍ/ቤት ዕግድ የሌለበት ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሲቀርብ፣
6) የቤትና ይዞታ ስም ዝውውር ጥያቄው የቀረበው በህግ ባለመብት/በውርስ/በፍርድ አፈጻጸም ወይም በውክልና ከሆነ ይህንኑ የሚገልጽ ማስረጃ፤
7) በግለሰቦች ግዥና ሽያጭ ወይም ስጦታ ስምምነት ከሆነ በዉልና ማስረጃ በአካል ቀርቦ በእማኞች የተፈረመ የስምምነት የውል ማስረጃ ሲቀርብ፣
🛑 1.2. በሽያጭ/በስጦታ የሚተላለፍ ቤትና ይዞታ ስም-ዝውውር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፣ 👇
1) ግንባታው በዋስትና ያልተያዘ እንዲሁም እዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም እዳው በሚመለከተው አካል በደብዳቤ መነሳቱ ሲረጋገጥ፣
2) የቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋገጥና በፍትህ ወይም በመሪ ማዘጋጃ ቤት ፊት ቀርቦ ሲጸድቅ፣
3) ግንባታው ጸድቆ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት 50 በመቶና በላይ የተሰራ መሆኑ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲቀርብ፣
4) በይዞታው ላይ ውዝፍ የቦታ ኪራይ የሌለበት ስለመሆኑ ወይም ውዝፍ የቦታ ኪራይ ክፍያ አጠናቆ የከፈለ ስለመሆኑ የቀረበ ክፍያ ደረሰኝ ማረጃ ሲቀርብ፣
5) የአገልግሎትና የገቢዎች ክፍያ በቤቱ ግምት መሰረት ስለመከፈሉ ሲረጋገጥ፣
🛑 #ዝውውሩ የሚፈፀመው #በሊዝ በተገኘ ይዞታና ግንባታ ላይ ከሆነ
1) የሊዝ ይዞታ ባለቤትነት ኦሪጅናል ካርታና ውል ሲቀርብ፣
2) በሊዝ ውል መሰረት ክፍያው የተጠናቀቀና ሌሎች ግዴታዎቹን የተወጣ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም የሊዝ እዳው ያልተጠናቀቀ ከሆነ ስም የሚዞርለት ወገን እዳውን ለመክፈል እና ነባሩን የሊዝ ውል ግዴታዎች የተቀበለ ስለመሆኑ ከከተማው በጽሁፍና በፊርማ አረጋግጦ ሲያቀርብ፣
3) በሊዝ የተገዛን የመሬት ይዞታ ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በቅድሚያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የሚፈለገውን የግንባታ ደረጃ ያሟላ መሆኑ ወይም የግንባታ ፈቃድ የጊዜ ገደብ ያላለፈ ወይም የግንባታ ማራዘሚያ የተፈቀደለት መሆኑ ሲረጋጥ፣
4) የከተማ ቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋጥና በዉልና ማስረጃ ቀርቦ ሲጸድቅ ይሆናል፡፡
🛑 1.3. በውርስ የተገኘ ይዞታና ቤት የባለቤትነት ስመ-ንብረት ዝውውር አፈፃፀም፣
(ሀ) በውርስ የተላለፈ #ነባር_ይዞታ ዝውውር ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው፡-
1) የሚዛወረው የመሬት ይዞታ ወይም ቤት ህጋ የባለቤትነት ማስረጃ/ካርታ ሲኖረው፣
2) ወራሾች የውርስ ባለመብትነትን የሚያረጋግጥ የፍርድ ቤት ውሳኔ ማስረጃ ሲያቀርቡ፣
3) ወራሾች በውርስ ያገኙትን ይዞታ ወይም ቤት በየግላቸው የባለቤትነት ማስረጃ ለመያዝ ሲፈልጉ ለእያንዳንዳቸው ድርሻ መጠን በፍ/ቤት የፀደቀ ማስረጃ ሲያቀርቡ ወይም የሁሉም ወራሾች የጋራ ስምምነት በውል አፅዳቂ አካል ጸድቆ ሲቀርብ፣
4) የእያንዳንዱ ወራሽ የድርሻ መጠን በፍርድ ቤት ያልተረጋገጠ ከሆነ የስም ዝውውሩ በሁሉም ወራሾች ስም በጋራ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
የፍርድ ቤቱ የውርሱ ውሳኔ የይዞታ ክፍፍልን የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ የሚፈፀመው የወቅቱን አነስተኛ የይዞታ መጠን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ካልሆነም በተነፃፃሪ የመሬት ይዞታ ድርሻ ህግ ወይም በጋራ ሰነድ/ካርታ መሰረት ይስተናገዳል፡፡
ይዞታው በውሉ መሰረት ግንባታ ለመጀመር የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ያለፈበት እና ግንባታው ያልተጀመረ ከሆነ በውርስ ሊተላለፍ አይችልም፡፡
(ለ) #በሊዝ የተያዘ ይዞታ ለህጋዊ ወራሽ የሚተላለፈውና ዝውውር የሚፈፀመው፡-
1) አውራሹ በገባው የሊዝ ውል ግዴታ መሰረት አመታዊውን የሊዝ ክፍያ የፈፀመና ሌሎች የሊዝ ግዴታችን በተገቢው መንገድ የተወጣ ሲሆን፣
2) ወራሽ አውራሽ የገባቸውን የውል ስምምነቶች(የሊዝ መብት፣ክልከላና ኃላፊነት) ሙሉ በሙሉ የተቀበለ መሆኑን በፊርማው ሲያረጋግጥና ውዝፍ ክፍያ ካለ ከፍሎ ደረሰኝ ሲያቀርብ ይሆናል፡፡
3) በሊዝ ውሉ መሰረት አውራሹ በህይወት እያለ ለግንበታ መጀመሪያ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ካለፈና ግንባታ ካልጀመረ ውሉ ተቋርጦ ቦታው ለከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ተመላሽ ይሆናል፡፡
አውራሽ በይዞታው ላይ ግንባታ ያልጀመረው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑ ከተረጋጠ አውራሽ በህይወት ቢኖር ኖሮ በመመሪያው መሰረት ሊፈቀድለት የሚችለው የግንባታ መጀመሪያ የማራዘሚያ ጊዜ ለወራሽ ሊፈቀድለት ይችላል፡፡
🛑 1.4. በባንክ ሃራጅ የሚሸጥ እና የሚወረስ ቤት የባለቤትነት ስም ዝውውር
1) በባንክ የተሸጠ ቤት የባለቤትነት ስም ዝውውር ለመፈፀም በሐራጅ ጨረታው አሸናፊ የሆነው ሰው ያሸነፈበትን ዋጋና ለዝውውሩ በውል የገባቸው ግዴታዎች ተገልፀው ከባንኩ የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤና ውል ሲቀርብ፣
2) በባንክ ዋስትና ተይዞ የነበረው ይዞታ የባለቤትነት ማረጃ/ካርታ በማህደሩ ውስጥ ካለው ሰነድ ጋር ተገናዝቦ ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ፣
3) ይዞታው በሌላ ባንክ ብድርና ዋስትና ያልተያዘ ወይም እገዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ፣
4) በሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ዋስትና የተመዘገበ ዋስትና ያለው ባንክ መኖሩ ከተረጋገጠ ባንኩ ስለ ይዞታው መሸጥ ሲፈቅድ፣
5) በባንክ ሃራጅ ሽያጭ እንዲዞር የተጠየቀው ቤትና ይዞታ የተሟላ ሰነድ የሌለው/ሰነድ አልባ ከሆነ በቅድሚያ በሥራ ላይ ባለው የሰነድ አልባ መመሪያ መሰረት ሰነድ ተሰጥቶት ሲቀርብ፣
6) ባንኩ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ የሚረከብ ከሆነ የቤቱና ይዞታው ግምት እንደማንኛውም ቋሚ ንብረት ግምት ተሰልቶ ተገቢውን የአገልግሎትና የገቢ ክፍያ ሲፈጸም፣
7) ቤቱና ይዞታው ባንኩ በሚያወጣው ጨረታ የሚሸጥ ከሆነ ባንኩ ያቀረበው የጨረታ መነሻ ዋጋ በከተማው በኩል ተገቢ መሆኑ ተረጋግጦ በጨረታ ሲሸጥ እና የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችን ስለመፈጸሙ የክፍያ ደረሰኝ ማስረጃ ሲያቀርብ የሥመ-ንብረት ዝውውሩ የሚፈጸም ይሆናል፣
በሳሙኤል ግርማ
#ሼር #አለ #Share #ALE
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties