አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የ2013 ተመራቂ ተማሪወች‼️

ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በሁሉም ዩንቨርስቲወች ወጥ የሆነ አሰራር ለማስፈን አዳጋች በመሆኑ:ነገሮች ተስተካክለው ወደ ቀድሞው የአሰራር ሂደት እስከሚመለስ ድረስ Research እና Apparent በሚመለከት ዩንቨርቲወች ያላቸውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት በግል እንዲወስኑ የተተወ በመሆኑ ለዝርዝር ጉዳዬች ተማሪወች ከዩንቨርስቲያችሁ ጋር ተነጋገሩ:: አዲስ መረጃ ካለ የምናሳውቅ ይሆናል::

በኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳት አኒሳ

Ethiopian law school students Union (ELSSU) president Anisa

@lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
Forwarded from Deleted Account
ይህን ፔጅ መጠቀም ምፈልገው ለሕግ ና ለሕግ ዕውቀት ብቻ ነው..ብዙ ነገር ረድቶኛል...በጣም ጠቅሞኛል...አሁንም..ወደፊትም...የሕግ ጉዳዮችን በተሻለ መልክ ልንጠቀምበት የምንችልበት ትልቅ መድረክ ነው....አዘጋጅ ክፍሉን ሳላመሰግን አላልፍም... አዘጋጅ ክፍሉ ሰፋ ያሉ የሕግ ጉዳዮችን...ቢያቀርብልን..ይበልጥ ያምራል...ብዬ አምናለው....
Hello how are you doing every body currently there is on legal issue that becomes hot and some lawyers raise your stand here like wise as a lawyer i try to put my legal stand here first of all i wanna to say God put his soul in heaven next when i come to the legality of the act of supervisor i think the supervisor is not being liable under The FDRE criminal law b/c firstly there is no the direct casual relation ship b/n the acts of supervisor and Abriham death b/c the cause that makes Abriham suicide him self is his late from the exam mean if abriham arrive in the class exam on time he did not suicide him self there fore it is possible to say that the cause for the death of abriham is his lateness to arrive in the exam class then the supervisor is not criminally liable as long as there is no casual relation ship b/n the acts of the supervisor and Abriham secondly the supervisor is on the state of performing his duty according to the exam rule and regulation the examiner can not take the exam if they are not arrive in the exam class then Abriham did not arrive in the class exam that is decided by the pretiant body then the supervisor is not being liable under our criminal law thirdly ; to say a certian person is liable under criminal law the mental element of the criminal must be full filled mean the supervisor does not cause for the death of Abriham either intentionally or negligent illy Fourthly as i told before The supervisor is on the state of performing is state duty then according to art 68 of the criminal code he is not being liable fifthly all moral wrongs are not crime morally speaking it is shamfull prohibit Abriham to take the exam but legally speaking it is true prohibit him to take the exam as long as he did not arrive at the time which is decided by the pretiant body To sum up plc see all if you art 23,24,57-59,2,&68of the criminal code the thing what i wanna ask this group is some of you stands international law in which Ethiopia is signed there fore what international law make the supervisor being criminally liable. sorry plc enter the word not from being liable on the line 9
Thanks too
via Abebaw sisay Law🔴
የፌደራል_ዳኞች_የሥነ_ምግባርና_የዲስፕሊን_ክስ_ሥነ_ሥርዓት_ደንብ_ቁጥር_1_20013.pdf
1.8 MB
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የዳኝነት ተጠያቂነት ስርዓት ወጥ እና አለም አቀፍ መስፈርትን ባሟላ መልኩ ለመዘርጋት ያስችል ከዚህ በፊት ያለውን ደንብ በማሻሻል ዝርዝር ይዘት ያለው የፌደራል ዳኞች የሥነ-ምግባርና የዲስፕሊን ክስ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ቁጥር 1/20013 አጽድቆ ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡ ውድ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማህበረሰብ እና ተገልጋዮች ጉባዔው ያጸደቀውን ደንብ ለግንዘቤዎ በያሉበት ይድረሳችሁ ብለናል፡፡
https://t.me/lawsocieties
ከህግ መውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የተከሰተውን
ችግር ትክክለኛ መረጃ የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲያደርጉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዘዘ

በምክር ቤቱ የሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሰሞኑ ከህግ መውጫ ፈተና ጋር በተገናኘ ህይወቱን ያጠፋውን አይነ ስውር የህግ ተማሪ አብርሃም ደሬሳ መነሻ ችግር ላይ የሚመለከታቸውን ጠርቶ ማብራሪያ ጠይቋል።

ችግሩ የፈተናዎች ኤጀንሲ የህግ መውጫ ፈተና ከሰጠባቸው አንዱ በሆነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ውስጥ የተከሰተ ነው።

አብርሃም ዱሬሳ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዲግሪውን እንዳገኘ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና
በመውሰድ ላይ እንደነበር ተነግሯል።

የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ፈተናውን በ2012 ዓ.ም ግንቦት ወር ላይ ለመስጠት ቢታቀድም በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው የጸጥታ ችግር ሳይሰጥ
መቅረቱን አውስተዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደፈተና ጣቢያ ማገልገሉን ጠቅሰው ፤ ለአይነ ስውራን አንባቢ ማዘጋጀንት ጨምሮ ፈተናውን መስጠት የሚያስች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጉን ጨምረው ገልጸዋል።

ለተማሪ አብርሃምም ኤጀንሲው በተመደበው አንባቢ አማካኝነት ከታህሳስ 13 እስከ 16 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጠውን ፈተና የመጀመሪያዎቹን 3 ቀናት በሰላም መውሰዱን አብራርተዋል።

ይሁን እንጂ በፈተናው የመጨረሻ ቀን ፈተናው የሚጀመረው 3 ሰአት ቢሆንም አንባቢው ፈተናው ከተጀመረበት እስከ 45 ደቂቃ ድረስ ሊያገኘው እንዳልቻለ አስረድተዋል።

ከ45 ደቂቃ በኋላ አንባቢውን ማግኘቱንና በፈተና መመሪያ መሰረት አንድ ተማሪ ማርፈድ የሚችለው 30 ደቂቃ በመሆኑ ፈተናውን መቀመጥ አለመቻሉን
ገልጸዋል።

ተማሪው በወቅቱ የፈተና ጣቢያ ሃላፊንና ፈታኙን አግኝቶ ከጊቢው እንደወጣና ህይወቱን ማጥፋቱን በመገናኛ ብዙሃን እንደማንኛውም ሰው መስማታቸውን ዋና ዳሬክተሩ በማብራሪያቸው አንስተዋል።

ዋና ዳሬክተሩ ይህን ይበሉ እንጂ የኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ወሰን አለሙ ተማሪ አብርሃም ዩኒቨርሲቲ ጊቢ የደረሰው 3 ሰዓት መሆኑን ማህበሩ መረጃ እንዳለው ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ የፈተና ኮድ ባለመያዙ ምክንያት ወደ ቤቱ መመለሱንና የፈተና ኮድ ይሁን ወይንም መታወቂያ ግን መረጃ እንዳሌላቸው አስረድተው በ40 ደቂቃ ውስጥ መመለሱን ጨምረዋል።

በዚህ ጊዜ የተማሪው አይነ ስውርነት ከግምት ውስጥ ገብቶ ፈተናውን እንዲወስድ ማድረግ ይቻል እንደነበር ጠቅሰው፤ መመሪያ ካልፈቀደም ክፍተቱ
የመመሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በፍትህ ማሻሻያ መርሃ ግብር ውስጥ ከታዩ ጉዳዮች አንዱ የህግ መውጫ ፈተና መሆኑን በሰጡት ማብራሪያ ጠቅሰዋል።

ተማሪ አብርሃም ዱሬሳ ፈተናውን የወሰደው ለሶስተኛ ጊዜ እንደሆነና ፈተናው በዚህ አመት የተሰጠው በ2012 ዓ.ም መፈተን ለነበረባቸው መደበኛና ከዚህ በፊት ባሉት አመታት ፈተናውን ማለፍ ላልቻሉ እንደ ተጨማሪ እድል ተሰጥቶ
መሆኑን አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ ዩኒቨርሲቲው ያለአግባብ ስሙ ተነስቷል ሲሉ ቅሬታቸውን ተናግረዋል።

ፈተና በሚሰጥበት የዩኒቨርሲቲ ጥበቃዎች ተማሪውን እንዳይገባ አለመከልከላቸውን እንዳጣሩ ጠቅሰው፤ ይሁን እንጂ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን
ዩኒቨርሲቲው ጥፋተኛ እንደሆነ ተደርጎ መቅረቡ አግባብ አለመሆኑን ጨምረዋል።

ቋሚ ኮሚቴው የተሰጠውን ማብራሪያ መሰረት በማድረግ ትክክለኛውን መረጃ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ኮሚቴ በማቋቋም በአስቸኳይ አጣርተው እንዲያቀርቡ ቋሚ ኮሚቴው አዝዟል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ተወካይ አቶ ማዘንጊያ እያቶ "ለችግሩ አንዱን ከሳሽ አንዱ ተከሳሽ ማድረግን ትቶ" በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መሪነት ጉዳዩን በማጣራት ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አሳስበዋል።

በዚህም ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲና በአካል ጉዳተኞች ላይ ከሚሰሩ ማህበራት ኮሚቴ በማቋቋም በትክክል የተፈጠረውን ሪፖርት እንደሚያቀርቡ አስገንዝበዋል።

በማውቅም ይሁን ባለማወቅ ችግር የፈጠሩ አካላት ላይ አስተዳራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከዚህ በመነሳት ለቀጣይ ትምህርት እንዲሆን አሰራሮችና አዋጆች መፈተሽ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
"የሞባይል ሚስጥራዊ አገልግሎት''
================🔴🔴🔴
https://t.me/lawsocieties

1ኛ ሞባይሉ ውስጥ ያለውን ስልክ ቁጥር
ለማግኘት *111#
2ኛ ሞባይሉ የተሰራበት ዘመንና ባትሪ ለማወቅ
*#*#4636#*#*
3ኛ የሞባይል ሚስጥረ ቁጥር (Imel) serial no
*#06#
4ኛ የሞባይሉ ዋና መስገብ ሰርቨስ ለማግኘት
*#0*#
5ኛ የሞባይል ኮሜር መረጃ ለማግኘት፦
*#*#34971539#*#*
6ኛ ሞባይሉ ላይ ሙሉ ፋይል ለማግኘት፦
*#*#273282*255*663282*#*#*
7ኛ የሞባይሉ ዋይለስ LAN/ ለማየት *#*#232339#*#*
8ኛ ሞባይልን አገልግሎት ለማስጀመር፦
*#*#197328640#*#*
9ኛ የሞባይልን ግልፅ መብራት ለማየት
*#*#0842#*#*
10 የሞባይል የእስከር መያዣ ለማየት
*#*#2664#*#*
11ኛ የሞባይሉ ቫይቭሬሽን ለማየት፦
*#*#0842#*#*

12ኛ የሞባይሉን ኤፍት ሶፍትዌር ለማየት
*#*#1111#*#*ሠሁሦቡቡቡቡቡ
13ኛ የሞባይሉ ሶፍትዌር እና ሃርድዌር መረጃ ለማግኘት *#125080*369#
14ኛ የሞባይል ኮንፌግሬሽን ዲያጎሽቲክ ለማየት *#9090#
15ኛ የሞባይሉ ሴትአፕ ድሞድ (dump Model) *#9900#
16ኛ የሞባይል ሜኑ (HsDpa/Huspa ለማየት *#301279#
17ኛ የሞባይሉን ዩስፕ (USB) ለማየት፦ *#872564#
18ኛ የሞባይሉን ፅፈት ለማየት፦ *#7465625#
19ኛ የሞባይሉን ዳታ መረጃ ወደ መጀመሪያ ምሪት ለመመለስ፦ *#*#7780#*#*
20ኛ ሞባይሉን ወደ ፋብሪካ ምርት ለመመለስ፦ *2767*3855#
21ኛ የሞባይሉን motorola droids ለማግኘት፦ ##776426
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from Deleted Account
አንድ ሰው መኪና እየነዳ መኪናውም ሰውየውም ቢገጩ ተጎጅ ለአካል ጉዳቱ ክስ አቅርቦ ከተካሰ በኋላ በመኪናው ለደረሰው ጉዳት ክስ ቢያቀርብ ከፍ /ስ/ስ/ሕ/ቁ 5 አንፃር እንደት ይታያል???
Forwarded from Deleted Account
ይቅርታ ወገን..በእኔ እምነት የዚህን ፔጅ መሰረታዊ ዓላማ እየዘነጋነው ይመስለኛል..አንዱ የሌላውን ሃሳብ እየነቀፈ በ fb ላይ የሚታዩ ያልተገባ አካሄዶችን ልንጠቀም አይገባም...እዚህ ፔጅ ላይ የምንገኝ በጠቅላላ ቤተሰብ ነን..የሕግ ሰዎች ነን ...ማንኛውም የሕግ ጉዳይ ቢገጥመን ተከባብረን ለመወያየት ይህ መድረክ በቂ ነው...ይህን ፔጅ እኔ እንደ አንድ ትልቅ የሕግ ላይብረሪ ነው የማየው..ሁሌም በሰከነ መንፈስ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር ልንጠቀመው ይገባል...ነገ የዚችን ሀገር የሕግ ጉዳይ ኃላፊነት የተጣለው እናንተ ላይ ነው...ውድ የሕግ ቤተሰቦች ትልቅ ኃላፊነት አለብን...በተረፈ ፔጅ ላይ የማነባቸው የሕግ ጉዳዮች በጣም ጠቅመውኛል ሁላችሁንም...እጅግ አድርጌ አመሰግናለው።
Forwarded from ቀን ሳለ🏃‍♂️ (Me)
ሁላችንም ታሪካችን እንደ ተረት ከዕለታት አንድ ቀን ጀምሮ ከዕለታት አንድ ቀን ያበቃል ፤ ሕይወት ግን በበርካታ ግማሽ ቀናት የተሞላች መንገድ ናት .... መኖር ማለት ይኽችኑ ግማሽነት ለመሙላት የሚደረግ ትግል ነው!!

ከዕለታት ግማሽ ቀን ከሚለው መፃሀፍ የተወሰደ

@wise_generation

@wise_generation

@wise_generation
Join and share
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
https://t.me/lawsocieties
በሂወት ጉዞ እና አላማን ከግብ ለማድረስ በሚደረግ ጥረትና ሙከራ ወቅት ተስፋ አይቆረጥም‼️
https://t.me/lawsocieties
የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች በሕክምና ሥህተት ያለባቸው ተጠያቂነት
=======================
መግቢያ
በህክምና ተቋማት ወይም በጤና ባለሙያ እና በታካሚ መካከል ለሚኖረው ግንኙነት መሠረቱ የህክምና አገልግሎት ውል ነው፡፡ ሆኖም ግን የህክምና አገልግሎት በሚሰጡት ወቅት አንዳንድ ጊዜ የሙያ ስህተት በመፈፀሙ ምክንያት ታካሚው ላይ ጉዳት ሊደርስ ወይም የሚጠበቀውን መልካም ውጤት ላያመጣ ይችላል፡፡ በመሆኑም በመርህ ደረጃ ጉዳት የደረሰበት ታካሚ ከህክምና ተቋሙ ወይም ከጤና ባለሙያው ጋር ባለው የግንኙነት ዓይነት ተቋማትን ወይም ባለሙያው ካሣ እንዲከፍለው ሊጠይቅ ይችላል፡፡
የህክምና ተቋማትን ወይም የጤና ባለሙያን የህክምና ስህተት ተጠያቂነትን በተመለከተ የታሪክ መዛግብትን በምናይበት ወቅት የህክምና ተቋማት የሚሰጡት የጤና አገልግሎት ያለክፍያ የሚሰጥ የበጎ አድራጐት ተግባር ነበር፡፡ አገልግሎቱ ለትርፍ ዓላማነት የማይሰጥ በመሆኑ አብዛኛዎቹ የህግ ሥርዓቶች በሙያ ስህተት ለሚፈጠር ጉዳት አገልግሎት ሰጪው የጤና ተቋም ወይም ባለሙያ ያለመከሰስ መብት /Immunity/ እንዳለው በመግለፅ በሕጐቻቸው ደንግገው ነበር፡፡ ያለመከሰስ መብቱ መከበሩ ዋነኛ ዓላማው ያለ ክፍያ የጤና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋሙ ወይም ባለሙያው የሚመጣ ሰው አገልግሎቱን በሚያገኝበት ወቅት ለሚደርስበት ጉዳት ካሣ የመጠየቅ መብቱን መተው አለበት ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ ሆኖም በጊዜ ሂደት የሕክምና ተቋማት ለሚሰጡት የጤና አገልግሎት ክፍያ ማስከፈል ሲጀምሩ ኀብረተሰቡ ለጤና አገልግሎት እንዱስትሪው ከዚ ቀደም የነበረውን አመለካከት በመቀየር ከተቋሙ ወይም ከጤና ባለሙያው ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት የንግድ /consumerism/ መሆኑን በመገንዘብ አገልግሎቱን መክፍያ በሚያገኙበት ወቅት በሙያ ስህተት ወይም ደረጃውን ባልጠበቀ የጤና አገልግሎት ምክንያት ለሚደርሱበት ጉዳት ተቋሙ ወይም የጤና ባለሙያው ተጠያቂ መሆን አለበት የሚለውን ሃሣብ ማንፀባረቅ ጀመሩ፡፡ በዚህም ምክንያት የጤና ባለሙያዎች ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በሙያ ስህተት ለሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ መሆን አለባቸው የሚለው አስተምሮ የበላይነቱን በመያዙ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች በአስተዳደር፣ በፍትሐብሔር እና በወንጀል ተጠያቂ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
ወደሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ብንመለከት መንግሥት ደረጃውን ባልጠበቀ የጤና አገልግሎት እንዲሁም ብቃትና የሙያ ሥነ-ምግባር በጎደለው የጤና ባለሙያና ተቋም ምክንያት በዜጐች ላይ ሊደርስ የሚችለውን የጤና ችግር ለመከላከል ይቻል ዘንድ የጤና አገልግሎቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የተለያዩ ሕጐችን በማውጣትና ተግባር ላይ በማዋል የቁጥጥር ሥርዓት ዘርግቷል፡፡
በዚህ የግንዛቤ መፍጠሪያ ፅሑፍ የሕክምና ስህተት ምን ማለት እንደሆነ፣ በሕክምና ስህተት ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የጤና ችግር ለማስቀረት የሀገራችን ሕጐች መከላከልን እና ቅጣትን መሠረት ያደረረ የቁጥጥር ሥርዓት የሚደነግጉ በመሆኑ በነዚህ ሁለት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ የሚሰጥበት ይሆናል፡፡
2. የሕክምና የሙያ ስሕተት (medical malpractice)
የሕክምና የሙያ ስህተት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉም ከመስጠታችን በፊት የሙያ ስህተትን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ የሙያ ስህተት ማለት በአንድ የሙያ ዘርፍ የተሰማራ ባለሙያ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት ሊከተላቸው ወይም ሊመራባቸው የሚገባውን የሙያ ደንቦችና መመሪያዎች አውቆ ወይም በቸልተኝነት ሣያከብር መቅረት ወይም የሙያ ደንቦችን ባለማክበሩ በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ማድረስ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሕጋችን ከአንቀፅ 2031 እና 2035 መረዳት እንችላለን፡፡ ከዚህ ትርጉም የምንረዳው ቁምነገር አንድ ባለሙያ ምንም እንኳ የሙያ ደንቦችን እና መመሪያዎችን ባለማክበሩ ምክንያት በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ባያደርስም የሙያ ደንቦችን አለማክበሩ እራሱን ችሎ የሙያ ስህተት መሆኑን መረዳት ይኖርብናል፡፡
የጤና ሙያ አንድ የሙያ ዘርፍ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ የጤና ባለሙያዎች የሚፈፀሙትን የህክምና ስህተት ከላይ ከተመለከትነው የሙያ ስህተት ትርጉም አንፃር እና ደንብ ቁጥር 299/2007 በአንቀፅ 2 ንዑስ አንቀጽ 31 ሙያዊ ያልሆነ ተግባርን በተመለከተ ከሰጠው ትርጉም አንፃር እንደሚከተለው እናያለን፡፡ አንድ የጤና ባለሙያ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ በአስፈፃሚ አካሉ አንድን የተወሰነ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት በህግ ከተመለከተው የአገልግሎት ደረጃና የሙያ ወሰን ወይም ሥነ-ምግባርን በሚቃረን ሁኔታ የሕክምና አገልግሎት ከሰጠ የሕክምና ስህተት እንደፈፀመ ይቆጠራል፡፡ የጤና አገልግሎት ደረጃ /standard of health care/ ማለት አንድ የሕክምና ባለሙያ አንድን የተወሰነ የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ ሊያከብራቸው ወይም ሊፈፅማቸው ይገባል ተብለው በአስፈፃሚ አካሉ ወይም በልማድ የተቀመጡ ዝቅተኛ የሕክምና አገልግሎት ደረጃን /minimum standard of care/ የሚመለከት ነው፡፡ እዚህ ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ የሕክምና ባለሙያው አንድን የተወሰነ የሕክምና አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት የሕክምና ሙያ ደንቦችን በማክበር ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ሰጥቷል ወይስ አልሰጠም ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠቱ ላይ ነው፡፡ ሙያውን የሚመለከቱ ደንቦች በሕግ የታወጁ እና በሕግ ያልታወጁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ደንቦቹ በሕግ የታወጁ በሆነ ጊዜ የሕክምና ባለሙያው የሙያ ወሰኑ የሚፈቅድለትን አንድን የተወሰነ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ በሕጉ የተመለከተውን የጤና አገልግሎት ደረጃ ወይም ወሰን ማክበር ሲገባው በህጉ ከተመለከተው ውጭ አገልግሎቱን ከሰጠ የሙያ ስህተት እንደፈፀመ ይቆጠራል፡፡ ለምሣሌ የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና አገልግሎት አስተዳደር ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2002 በአንቀፅ 39 መድሃኒቶችን ማዘዝ የሚችለው አግባብ ላለው አካል የሙያ ሥራ ፈቃድ የተሰጠው የሕክምና ባለሙያ መሆኑን የሚገልፀውን ድንጋጌ በመተላለፍ መድሃኒት ያዘዘ እና የሸጠ የመድሃኒት ባሉሙያው (medicinal professional) መድሃኒቱ ለሚ.ያደርሰው ጉዳት በሙያ ስህተት ኃላፊነት ሊጠየቅ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የሕክምና ሙያ ደንቦች በሕግ የተደነገጉ ሳይሆኑ በሙያው የተሰማሩ ሰዎች አውቀው ከሚገለገሉባቸው ከተለመደ የመልካም አሠራር መመሪያዎች የሚመነጩ ሊሆኑ ይችላሉ(የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2030 ይመለከቷል)፡፡ አንድን ዓይነት አሠራር ተከትሎ እየደጋገሙ መስራት ልማድን የሚፈጥር ሲሆን (customary practice) ልማዱም የእነዚህ ደንቦች ምንጭ ይሆናል፡፡ እንዲህ ካሉት ልማዶች ዉጭ የሕክምና አገልግሎት በመሰጠቱ ጉዳት የደረሰበት ታካሚ ካሳ እንዲከፈለው ፍርድ ቤት በሚጠይቅበት ወቅት ዳኞች በቀረበው የህክምና ስህተት ውሳኔ ለመስጠት እውቀቱ ስለማይኖራቸው በሙያው የተሠማሩ ባለሙያዎችን በአዋቂ ምስክርነት /expert witness/ ሊጠይቁና የተባሉት ሰዎች ሞያቸውን የሚያስተዳድሩትን የተለመዱ የመልካም አሠራር መመሪያዎች ካስረዷቸው በኋላ የህክምና ሙያ ስህተት ተፈፅሟል ወይስ አልተፈፀመም የሚለውን ጭብጥ ላይ ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡