አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ጥብቅና የተከበረ ሙያ ነው። የዛሬ ችሎት ውሎዬና ትዝብቴ:-

ጠበቃ - ውሉ ህገወጥ ነው

ዳኛ -ህገወጥነቱን ያስረዱ

ጠበቃ- ሁሉም ነገር ህገወጥ ነው

ዳኛ -ለምሳሌ

ጠበቃ - ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ መጨረሻው
ህገወጥ ነው።
ዳኛ - እስቲ አንዱን እንኳ ይጥቀሱ ? ክቡር ጠበቃ
ውሉ የህግ ጉድለት ነው ያለበት ወይስ ዋጋ
አልባ ውል ነው የሚሉት ?

ጠበቃ - ሁለቱም ። በህገመንግስቱ መሰረት
ህገፕወጥ ነው

(ችሎት ውስጥ ቁጭ ብለን እስክንጠራ የምንጠባበቅ ጠበቆች አጉረመረምን፣ ተንሾካሸክን)

ዳኛ - ፀጥታ አሉና ይቀጥሉ ክቡር ጠበቃ አሉ

ጠበቃ- ያው ቀደም ሲል እንዳልኩት ህገወጥ ነው
ውል ክፍል አልተፈረመም
ዳኛ - ውል ክፍል ባይፈረምስ? ለመሆኑ ምንድን
ነው ውል ክፍል ማለት ?

ጠበቃ - እኛ የምንለው ውሉ ህገወጥ ነው ብለን
ነው የምንፋለመው ?

ዳኛ - ክርክራችሁ መፋለም ነው ወይስ ውል
ይፍረስልኝ ነው ?
ጠበቃ - ሁለቱንም ። እንፋለማለንም ውልም
ይፍረስልን
ዳኛ - ክቡር ጠበቃ የይዞታው ባለቤት እኛ ነን ነው
የምትሉት ወይስ ውሉ ህገ ወጥ ነው
የሚሉት ?
ጠበቃ - (ከጀርባቸው ቁጭ ያከው የችሎት ታዳሚ
ጠበቆች ጉርምርምታና ሹክሽክታ
ያሳቀቃቸው ይመስላል ። ) እኛ እንግዲህ
በህገ መንግስቱ መሰረት ንብረት የማፍራት
መብት አለን።

ዳኛ - ታዲያ ማን ንብረት እንዳታፈሩ ከለከላችሁ ?
(ሙድ የያዙ ይመስላሉ)

ጠበቃ - ተከሳሽ ?
ዳኛ - እንዴት?
ጠበቃ - ህገወጥ ውል ይዘው ____ ብለው ዝም
አሉ።
ዳኛ - ጨረሱ ?

ጠበቃ - አዎ ጨርሻለሁ ክቡር ፍ/ቤት አሉ ። ወደ
ኃላ እኛን ዞር ብለው እየተመለከቱ

ዳኛ - ተከሳሽ ይቀጥሉ

የተከሳሽ ጠበቃ - ገልበው ገልበው ልክ አስገቡልኝ።

NB - *** ለካ
ሁሉም ሰው ጠበቃ መሆን ይችላል ።
By: Birhanu Assefa
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት
@LawsocietiesBot
Forwarded from Abrham Tadesse
With regard to Abrhama Deressa's suicide case, What kind of code is that ? As far as I know it was only 4digit code and also it was posted on each exam room no need to go back to home even there was nothing given to the examinee in hard copy code so what kind of code was that???
I was one of the examinee there
Forwarded from Deleted Account
በዐ/ሕግ ሙያ 13 ዓመት አገልግያለው በታናሽ ወንድማችን የሕግ ባለሙያ አብርሃም ዱሬሳ ምናልባትም ከኔ በተሻለ የለበስኩትን ጥቁር በቀይ ጋወን ተረክቦኝ ፍትሕ ሊያስከብር የሚችለውን ጀግናችንን በደረሰበት አሰቃቂ በደል አተነዋል...እጅግ..ያንገበግበኛል...ይህ አልበቃ ብሎ በሱ ዙሪያ የተሰ ምላሾችም እጅግ ደካማ መሆናቸው ደግሞ ይበልጥ ያስቆጫል...ግን ጥቁር በቀይ ጋዎን ለብሼ በምከራከርበት ችሎት በቆምኩበት ለጀግናው ወንድማችን የሕግ ባለሙያ አብርሃም ዱሬሳ ልዩ ክብር አለኝ......"ፍትሕ ለጀግናው ወንድማችን አብርሃም ዱሬሳ"......ዐ/ሕግ
አእምሮ አልባ ዳኛ

በክፉ ህሊና እድልህን ዘግቶ በጉዳት ያጠቃህ፣
ታታሪውን ወጣት የነገን ተስፈኛ ለህልፈት ያበቃህ፤
ማን ይሆን ያ ክፉ ርህራሄ ያጣ?
ለምን ፈቀድክለት ደንብን ተከልሎ በጉዳተኛ ላይ ቂሙን እንዲወጣ?
እንዴት ዘነጋሃው አብራሃም ወንድሜ ግብግብ መሆኑን የኔና ያንተ እጣ?
ልብህ እያወቀው በምቀኞች መንደር በክፎዎች አንባ ልንኖር ተወልደን፣
ኮረኮንቹን መንገድ የጉዞን ጋሬጣ እሾሁን ተራምደን፣
የህብረተሰብ ሸጋታ አስተሳሰብ የሚቆልለውን የመከራ ቋጥኝ በጀግንነ አልፈን፣
በየህይወት ዘርፉ በትምህርት በስራ የገፉንን ሁሉ በወኔ አሸንፈን፤
ለድል የምንበቃ የእድሜልክ ታጋዮች መሆናችንን ልብህ እያመነው፣
አብራሃም ወንድሜ በክፉዎች ወጥመድ በእኩያኑ ሴራ መውደቅህ ለምነው?
ዳገት ቁልቁለቱን ያን ሁሉ መከራ አልፈኸው በብርታት፣
በአንዲት እርጉም አፍታ በከፋ ሰው ድርጊት በድንገት መረታት?

እስቲ ይሁን በቃ፣
በእውቀት አቅምህ ሳይሰንፍ አእምሮህ ጎልብቶ ሙሉ ሆኖ ልብህ፣
ማየት ብቃት ሆኖ ህሊና አልባ ዳኛ ሞት አስፈረደብህ።
ግን አይዞህ አልሞትክም ቃል ገብተንልሃል ሞትክን ላለመርሳት፣
በልባችን ነዷል ያቃጠለህ እሳት።

አይን አእምሮ በሚመስላቸው የእውቀትና ህሊና ድሆች ፍርደገምድል ፍርድ ራሱን ላጠፋው አይነስውር ወንድሜ አብራሃም ዱሬሳ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ ብዬ የፃፍኩት።

የህግ ባለሙያ እና የቀድሞው የፍሪካ እንዲሁም የኢትዮጵያ የአይነ ስውራን ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት #አቶ ካሳሁን ይበልጣል።
ፍትህ የየሚመጣው በሁላችን ተሳትፎ ነው።
Ethical and corruption free society that upholds integrity and accountability
Contact Us via
@Transparency_Ethiopia_Bot
and
ethiopiatransparency@gmail.com
ከመድሎ የፀዳች አገርን እንፍጠር‼️‼️
ኢትዮጵያ ለ50 ዓመታት የተጠቀመችበትን የንግድ ሕግ ልትቀይር ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮጵያ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ስትጠቀምበት የነበረውን የንግድ ሕግ ከዘመነ ቴክኖሎጂ ጋር የተናበበና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ አዲስ ሕግ ልትቀይር መሆኑ ተገልጿል።
አገሪቷ ከምትጠቀምባቸው መድኃኒቶች ውስጥ 80 ከመቶ የሚሆነው በውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ መሆኑም ተጠቁሟል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድኤታ ምስጋኑ አረጋ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ስትጠቀምበት የነበረው የንግድ ሕግ ከዘመነ ቴክኖሎጂ ጋር የተናበበና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በአዲስ ሕግ ልትተካ ነው።
አገሪቷ እያካሄደች ያለው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ መርህ በዋናነት በማክሮ ኢኮኖሚ፣ መዋቅራዊ እና የዘርፍ ማሻሻያ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመው ፣ በዚህም በአሁኑ ወቅት ሁለንተናዊ ለውጦችን ለማምጣት ከመቼውም በላይ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አብራርተዋል።
እንደ ሚኒስትር ድኤታው ገለፃ፤ እየተደረጉ ካሉ ማሻሻያዎች መካከል 50 ዓመታትን በሥራ ላይ የነበረው የንግድ ሕግ ዘመኑ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ የማሻሻል እና ሕግ ሆኖ የማውጣት ሂደቱ ከጫፍ መድረሱን አብራርተዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Forwarded from Cozet
Selam Ale...pls share to me if u have cassation bench decisions regarding legality n sufficiency of modes of civil case summons through e-mail, telegram, fax, tv or in any electronic media
New vacancy
Legal Officer
Berhan Insurance S.C

Addis Ababa (+1 other)

Apply


Job Requirement • Educational Qualification: LLB Degree from a recognized University or College • Experience: Minimum 2 years of relevant work experience Place of work: Addis Ababa How to Apply NB: Only short listed candidates will be communicated. Interested and qualified applicants may submit their application letter, curriculum vitae and other credentials in person or through the following addresses within 7 (seven) working days from the date of this announcement. Address: Berhan Insurance S.C. at Beklo Bet Yeshitam Building 4th floor, around Global Hotel near Garad Mall. P.O.Box 9266, Addis Ababa. Email: hr@berhaninsurance.com

Join..........

❤️Via Telegram channel❤️ https://t.me/lawsocieties
የሕግ የበላይነት እንዲከበር ዜጎች ለሕግ ተገዥ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ
__________________

የሕግ የበላይነትና የሕግ ተገዥነት በሚል ርዕስ እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በሚመለከት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለክፍለ ከተማው የተለያዩ የህብረተስብ አባላት የንቃተ ህግ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ አቶ ሹመት ጌትነት ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት ሕግ የሰው ልጆችን መብትና ግዴታዎች ዘርዝሮ የሚያቀርብ ሁሉንም ዜጎች ያለ ልዩነት የሚመራና የሚዳኝ እንደሆነ እና ሕጎች ሲወጡ ለረዥም ጊዜ ተብለው ቢሆንም ከህብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታ ለውጦች ጋር ተያይዞ ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ገልጸው የፍትሀ-ብሄርና ወንጀል ህጎችን በዝርዝር ለሰልጣኞቹ አብራርተዋል፡፡

ዐቃቤ ሕጉ በገለጻቸው ሕጎች አለም አቀፍና ብሄራዊ በሚል ተፈጻሚነት እንዳላቸው እና ማንም ሰው ከህግ በታችና በህግ ፊት እኩል በመሆኑ የተቀመጡ የህግ ስርዓቶችን ለማስፈን ስልጣን በመገደብና የስልጣን ክፍፍል እንዲኖር በማድረግ የህግ የበላይነት እንደሚረጋገጥ ገልጸዋል፡፡

የሕግ ተገዥነት የሚፈጸመው በተግባራችን ሕጉ የሚፈቅደውን ስናደርግ፣ ሕግ አክብረን መብታችን ማስከበር ስንችል የሌሎችን መብት ሳንገፋ ሕግ አስከባሪዎችን ማክበር ስንችል ነው ያሉት ዐቃቤ ሕጉ የሰዎች ተግባር ከሕጉ ጋር አለመገናኘትና አለመፈጸም የሕግ ተገዥ አለመሆን የሚያስከትል ስለሆነ መብትና ግዴታዎችን የሚያውቅ ዜጋ ለመፍጠር ስልጠናው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ዐቃቤ ህግ አቶ ሳሙኤል ገዳሙ በአንድ ሀገር ላይ የዲሞክራሲ መገለጫ የሚሆነው ሰብዓዊ መብቶች ሲከበሩ በመሆኑ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ህገ-መንግስቱ እንዲቆም ያደረጉ መሰረታዊ መብቶች ናቸው ብለዋል፡፡

አቶ ሳሙኤል አክለውም ሰብዓዊ መብቶች ሰዎች ሰው በመሆናቸው ያለ ልዩነት የሚሰጣቸው መብቶች መሆናቸውን እና ዲሞክራያዊ መብቶች ደግሞ ህዝቦች ያላቸውን ተሳትፎ የሚያሳዩበት እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሀገራችን ያሉ ህጎች መልካም ቢሆኑም ህብረተሰቡ ህጉን አውቆ ተጠያቂ እዲሆን የህግ አካላት ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
Jan 03, 2021
Manager, Legal Division
Zemen Insurance SC Addis Ababa, Ethiopia
FULL_TIME Insurance Jobs in Ethiopia Legal Jobs in Ethiopia
Job Description
Job Requirement
Education Qualifications: LLB in Law
Work Experience: 8.5 years of relevant work Experience
Place of work: Addis Ababa

How to Apply
Dead line for Application: 6 working days from the date of this Vacancy Announcement

Place of application: Zemen Insurance Share Company Bole Road, Alem Building second Floor.

Interested Applicants should apply in person, post office and email Address along with non-returnable updated CV and copies of relevant credentials from the date of this vacancy announcement until January 9/2021. Post office

Address: Zemen Insurance S.C.

PO.Box 23029 Addis Ababa, Ethiopia
ምንም እንኳን በወንጀል ባያስጠይቅም, የፍትሀቤር ክስ ለማንሳት ግን ከበቂ በላይ ነው. በምንም አይነት ሁኔታ ቢፈጠር, damage should be made irrespective of intention or fault. ከዚህ በዘለለ እንኳን በወንጀል ለመጠየቅ እንደማይችል የወንጀለኛ መቅጫ ህጉን አንቀጽ 57-59 እና አንቀጽ 23-24 በአንድነት በማንበብ በወንጀል ለመጠየቅ መሟላት ያለባቸው elements አለመሟላታቸውን ማወቅ ይቻላል. ይሁንና እንደመብት ጥሰት ለዚያውም ሰብኣዊ መብት ጥሰት በመቁጠር, ቢያንስ ከዚህ አስቀያሚ ድርጊቱ እንዲታቀብና ሌላ አይነስውር በትምኅርት ላይም ሆነ በስራ ላይ መሰል አጋጣሚ እንዳይገጥመው/ማት መንግስትን ልንሞግት ይገባል እላለው. ለዚህም እኛ ማየት የተሳነን ራሳችንን ለትግልና ለስኬት ማነሣሳት አለብን. የተቀራችሁት የማህበረሰቡ አካላትም ድጋፋችሁን እንሻለን.
Forwarded from Deleted Account
እንደ አንድ የሕግ ባለሙያ የወንድማችንን አብርሃም ዱሬሳ ጀግንነት የማደንቅለት ማየት የተሳነው አካል ጉዳተኛ ሆኖ ሳለ ብዙ ውጣ ውረ ዶችን ተጋፍጦ ሕግን የሚያክል ውስብስብ ትምህርት ተምሮ እዚህ ደረጃ መድረሱ ሲሆን ግን ይህን የኛን ጋወን ተረክብ በሰለጠነ የሕግ ችሎታ ፍትሕን ሊያስቀጥል ቢሮአችን በር ላይ በክብር የመጣውን ውድ እግዳችንን ስብዕና በጎደላቸው ግለሰቦች አተነዋል እጅግ ያስቆጫል..አንድ ማየት የተሳነው አካል ጉዳተኛ.ተንበርክኮ አልቅሶ ለመናቸው ..ከ ዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላል ..?ሥንት ዘመን ሙሉ በዳበሳ ተምሮ እዚህ የደረሰው ወንድማችን ፍቅር ና ፍትሕን አንድ ላይ ሲነፈግ ብቻውን ሲቀር እጅግ ደከመው በፍቅር ቃል ወቅሶንር ድካሙን፣ተስፋውን፣ልጆቹን ጥሎልን ሄደ....ይህን ያክል መጨካከኑ..ምን ትርፍ ያስገኛል..... ብዙዎች የሕግ ትንታኔ የመስጠት ብቃት አላቸው...ትልቁ ችግር ግን ፍትሕ የመ ሥጠት ጉዳይ ነው...አብርሃም ብቻ አይደለም የሕግ ምሁራንን የሚያሳትፍ በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች አሉ..ግን መልስ የለውም..ለምሳሌ፦ እጅግ አሳዛኙ ብሔር ተኮር ጭፍጨፋዎች፤አባይ ወንዝ...በተመለከተ ችግኙን የተከለው የኢትዮጲያ ሕዝብ ውሃው ይገባናል የሚለው ግን ሌላው ክፍል...በተለይ ግብፅ..አንድ ችግኝ ተክላ የማታውቅ ሀገር ..ውሃው ህልውናችን ነው ሥትል ትንሽ አታፍርም...የሕግ ክፍሉ ምን ይላል ..እኛ ያስፈለገን አለም አቀፍ እውቅና ያለው በሀገር መብት ሽንጡን ገትሮ የሚከራከር የሕግ ማህበር አስፈልጎናል....የአብርሃም ጉዳይ ሀገራችንን ጭምር ሊያስተች እንደሚችል ማወቅ አለብን ...ጉዳዩ ኢትዮጲያን ለማስወቀስ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን እየተሰጠው ነው.ወገን አንተ.የምክንያትና..የውጤት ግንኙነት እያክ በሃገሪቱ ሕግ ስትሟገት.."ኢትዬጲያ ለአካል ጉዳትኞች ትኩረት አትስጥም..." ለማስባል ና በዓለም ለማስተቸት አደገኛ አካሄድ እየተኬደ ነው ..ጉዳዩ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ትኩረት ካገኘ ተጎጂዎች ነን....ልጁ ሶስት ቀን በጥሩ ዲሲፒሊን ተፈትኗል፤ አራተኛው ቀን የተፈጠረው ክፍተት ልጁ ማየት የተሳነው አካል ጉዳተኛ መሆኑ ከግምት አስገብቶ እንዲገባ ማድረግ ሲቻል ጥረት አልተደረገም፤ በዛ ላይ አንድ አካል ጉዳተኛ ተንበርክኮ ሲለምንህ ቆሞ ማየትና ምላሽ አለመስጠት.. ክብር እንደሌለን ያሳያል...የሟች ሁኔታ ሲታይ ደግሞ የሕግ ባለሙያ..በደሉን ያስተናገደው በሕግ ክፍል..የሞተበት ሁኔታ ደግሞ ራሱን በእሳት አቃጥሎ...የምንተችበት አንዱና ትልቁ በር የሀገሪቱ የሕግ ክፍል እንኲን ለአካል ጉዳተኞች መብት እውቀት የለውም...በየትኛውም የዓለም ሀገር ላይ ያሉት አካል ጉዳተኞች እኩል መብት ነው ያላቸው...በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ....ዓለም ዓቀፍ እውቅናን ከሚያሳጡ ጉዳዮች አንዱ የአካል ጉዳተኞች መብት ጉዳይ ነው..ሌላው ዓለም ላይ ቢሆን አብርሃም በእንክብካቤ ጭምር ነበር ፈተናውን የሚወስደው ፈተናቸውም ለብቻው ነው ሚታረመው ..ምክንያቱም የአካል ጉዳተኞች አይምሮ በተደረገባቸው ጥናት ከፍተኛ የሆነ እንክብካቤ ና ፍቅር ይፈልጋል...ትንሽ ከነካኸው አደገኛ ውሳኔ ይወስናል..ለዚህም ነው ሁል ጊዜ ሞራላቸው ይጠበቃል..የተለየ እንክብካቤ ነው ሚደረግላቸው..ሁሌም ሚጠብቁት ቃል..አይዞህ በርታ ጎበዝ..ስራቸውን በትተደጋጋሚ ማድነቅ.. አለብህ..ፍቅር ማብዛት ግድ ይልሃል..ትንሽ ከተበሳጩ ውሳኔያቸው የመጨረሻው ደርጃ ነው..የእነሱ የአይምሮ ክፍላቸው መኖር የሚችለው በብዙ እንክብካቤ ብቻ ነው...።አብርሃም አንተንም ሆነ ጉዳዮቹን ሚያየው በጆሮው በሚስማው ድምፅ ና በእጆቹ እየዳበሰነው...ሞራሉን ሚነካ ድምፅ ከሰማ አይምሮውን እጅግ ያስጨንቀዋል.. ታዲያ ጭንቀታቸውን ለማምለጥ የሚወስኑት ውሳኔ አደገኛ.ነው።እናም ሁላችንም ለአካል ጉዳተኞች ፍቅር፣ሞራል ና ክብር ከጎናቸው ልንሆን ይገባል..የአብርሃም ውሳኔ ብዙ የአካል ጉዳተኞችን ጭንቀት ውስጥ ይከታል...ጥንቃቄ ማድረግ አለብን...ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል እንክብካቤ ና ፍቅር ካገኙ የማይታመን ድንቅ ችሎታ አላቸው..አስገራሚ ነገር ያሳዩሃል...እኔ በግሌ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ፍቅር አለኝ ..የተለየ ሚመስጥ ነገር አላቸው..እንቅረባቸው...እናክብራቸው..እንውደዳቸው...
Forwarded from Ni ጋቱ
Hello ! Ale families I hope u r doing very fine,
Share me notes on how to prepare effective term paper !....
regardingly ...thanks .