Forwarded from ተስፍሽ አቢሢኒያ
ከህግ መውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የተከሰተውን
ችግር ትክክለኛ መረጃ የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲያደርጉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዘዘ
በምክር ቤቱ የሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሰሞኑ ከህግ መውጫ ፈተና ጋር በተገናኘ ህይወቱን ያጠፋውን አይነ ስውር የህግ ተማሪ አብርሃም ደሬሳ መነሻ ችግር ላይ የሚመለከታቸውን ጠርቶ ማብራሪያ ጠይቋል።
ችግሩ የፈተናዎች ኤጀንሲ የህግ መውጫ ፈተና ከሰጠባቸው አንዱ በሆነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ውስጥ የተከሰተ ነው።
አብርሃም ዱሬሳ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዲግሪውን እንዳገኘ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና
በመውሰድ ላይ እንደነበር ተነግሯል።
የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ፈተናውን በ2012 ዓ.ም ግንቦት ወር ላይ ለመስጠት ቢታቀድም በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው የጸጥታ ችግር ሳይሰጥ
መቅረቱን አውስተዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደፈተና ጣቢያ ማገልገሉን ጠቅሰው ፤ ለአይነ ስውራን አንባቢ ማዘጋጀንት ጨምሮ ፈተናውን መስጠት የሚያስች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጉን ጨምረው ገልጸዋል።
ለተማሪ አብርሃምም ኤጀንሲው በተመደበው አንባቢ አማካኝነት ከታህሳስ 13 እስከ 16 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጠውን ፈተና የመጀመሪያዎቹን 3 ቀናት በሰላም መውሰዱን አብራርተዋል።
ይሁን እንጂ በፈተናው የመጨረሻ ቀን ፈተናው የሚጀመረው 3 ሰአት ቢሆንም አንባቢው ፈተናው ከተጀመረበት እስከ 45 ደቂቃ ድረስ ሊያገኘው እንዳልቻለ አስረድተዋል።
ከ45 ደቂቃ በኋላ አንባቢውን ማግኘቱንና በፈተና መመሪያ መሰረት አንድ ተማሪ ማርፈድ የሚችለው 30 ደቂቃ በመሆኑ ፈተናውን መቀመጥ አለመቻሉን
ገልጸዋል።
ተማሪው በወቅቱ የፈተና ጣቢያ ሃላፊንና ፈታኙን አግኝቶ ከጊቢው እንደወጣና ህይወቱን ማጥፋቱን በመገናኛ ብዙሃን እንደማንኛውም ሰው መስማታቸውን ዋና ዳሬክተሩ በማብራሪያቸው አንስተዋል።
ዋና ዳሬክተሩ ይህን ይበሉ እንጂ የኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ወሰን አለሙ ተማሪ አብርሃም ዩኒቨርሲቲ ጊቢ የደረሰው 3 ሰዓት መሆኑን ማህበሩ መረጃ እንዳለው ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ የፈተና ኮድ ባለመያዙ ምክንያት ወደ ቤቱ መመለሱንና የፈተና ኮድ ይሁን ወይንም መታወቂያ ግን መረጃ እንዳሌላቸው አስረድተው በ40 ደቂቃ ውስጥ መመለሱን ጨምረዋል።
በዚህ ጊዜ የተማሪው አይነ ስውርነት ከግምት ውስጥ ገብቶ ፈተናውን እንዲወስድ ማድረግ ይቻል እንደነበር ጠቅሰው፤ መመሪያ ካልፈቀደም ክፍተቱ
የመመሪያ መሆኑን ገልጸዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በፍትህ ማሻሻያ መርሃ ግብር ውስጥ ከታዩ ጉዳዮች አንዱ የህግ መውጫ ፈተና መሆኑን በሰጡት ማብራሪያ ጠቅሰዋል።
ተማሪ አብርሃም ዱሬሳ ፈተናውን የወሰደው ለሶስተኛ ጊዜ እንደሆነና ፈተናው በዚህ አመት የተሰጠው በ2012 ዓ.ም መፈተን ለነበረባቸው መደበኛና ከዚህ በፊት ባሉት አመታት ፈተናውን ማለፍ ላልቻሉ እንደ ተጨማሪ እድል ተሰጥቶ
መሆኑን አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ ዩኒቨርሲቲው ያለአግባብ ስሙ ተነስቷል ሲሉ ቅሬታቸውን ተናግረዋል።
ፈተና በሚሰጥበት የዩኒቨርሲቲ ጥበቃዎች ተማሪውን እንዳይገባ አለመከልከላቸውን እንዳጣሩ ጠቅሰው፤ ይሁን እንጂ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን
ዩኒቨርሲቲው ጥፋተኛ እንደሆነ ተደርጎ መቅረቡ አግባብ አለመሆኑን ጨምረዋል።
ቋሚ ኮሚቴው የተሰጠውን ማብራሪያ መሰረት በማድረግ ትክክለኛውን መረጃ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ኮሚቴ በማቋቋም በአስቸኳይ አጣርተው እንዲያቀርቡ ቋሚ ኮሚቴው አዝዟል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ተወካይ አቶ ማዘንጊያ እያቶ "ለችግሩ አንዱን ከሳሽ አንዱ ተከሳሽ ማድረግን ትቶ" በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መሪነት ጉዳዩን በማጣራት ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አሳስበዋል።
በዚህም ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲና በአካል ጉዳተኞች ላይ ከሚሰሩ ማህበራት ኮሚቴ በማቋቋም በትክክል የተፈጠረውን ሪፖርት እንደሚያቀርቡ አስገንዝበዋል።
በማውቅም ይሁን ባለማወቅ ችግር የፈጠሩ አካላት ላይ አስተዳራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከዚህ በመነሳት ለቀጣይ ትምህርት እንዲሆን አሰራሮችና አዋጆች መፈተሽ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
#ዳጉ_ጆርናል